Havan Academy
Статистика╱◥██████◣ │∩│🪟▤│🪟│ The First and Leading Freshman Tutoring Platform in Ethiopia❕ Mark this phrase #Your GPA Matters❗️ Ask: @havanstudentsupport Testimony: https://t.me/havanacademyinfo/44 Register: @havanacademybot Website: www.havanacademy.com
- Последний пост
- 16 авг.
- Последнее чтение
- 16 авг.
- Постов за неделю
- 11
- Всего постов
- 162
- Тип
- открытый
- Язык
- английский
- Категория
- Образование (по похожим)
- В каталоге с
- 13 авг.
- 1/24сутки в ленте
- 2 588
- 1/48двое суток
- 2 965
- 1/72трое суток
- 3 198
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
📌 ስለ Biomedical Engineering 📍 Biomedical Engineering ተምሮ ለመመረቅ ስንት አመት ይፈጃል?? ✅ በኢትዮጵያ ዩኒቨርሲቲዎች ካሪኩለም መሰረት ተምሮ ለመመረቅ በአጠቃላይ 5 አመት ይፈጃል። ❓ Biomedical Engineering ለመግባት የራሱ መግቢያ ፈተና አለው ወይ? ✅ እንደ ዩኒቨርሲቲው ይለያያል። በአብዛኞቹ ግቢዎች የ Freshman ውጤታችሁን እና የምርጫ ደረጃችሁን አይተው በቀጥታ የሚመድቧችሁ ሲሆን፣ እንደ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ (AAiT) ባሉ ቦታዎች ግን ከ Freshman ውጤት በተጨማሪ የራሳቸው መግቢያ ፈተና ወይም ኢንተርቪው ሊኖራቸው ይችላል። ✅ Department ውስጥ ገብታችሁ ለመማር መጀመሪያ የ Freshman ኮርሶችን አልፋችሁ መመደብ አለባችሁ፤ ከዛም የ Basic Engineering (እንደ Electronics, Circuits, Programming) እና የ Basic Medical Science (Anatomy & Physiology) ኮርሶችን አዋህዳችሁ ትማራላችሁ። 📍 Biomedical Engineer የሆነ ሰው ህመምተኛ ያክማል ወይስ የቀዶ ህክምና (Surgery) ይሰራል?? ✅ ይሄ ብዙ ተማሪዎች የሚሸወዱበት ነጥብ ነው! መልሱ አያክምም ነው። Biomedical Engineer ማለት በህክምናው መስክ ውስጥ የሚገኙ የቴክኖሎጂ እና የመሳሪያ ባለሙያ (Tech Expert) እንጂ ዶክተር አይደለም። ስራችሁ የህክምና መሳሪያዎችን (X-ray, MRI, Patient Monitors) መጠገን፣ ማስተዳደር፣ መገጣጠም እና አዳዲስ የህክምና ቴክኖሎጂዎችን መፍጠር ነው። ይሄን የምንነግራችሁ በስህተት "ዶክተር እሆናለሁ" ብላችሁ እንዳትገቡ ነው፤ ሆኖም በራሱ እጅግ ዘመናዊ እና ድንቅ ሙያ ነው። 📍 ትምህርቱ ከባድ ነው ወይስ ቀላል?? ✅ ከባድ የሚያደርገው ሁለት ሙሉ ለሙሉ የተለያዩ ዘርፎችን — Engineering (ሂሳብ፣ ኤሌክትሮኒክስ፣ ሶፍትዌር) እና Medicine (የሰው ልጅ የሰውነት መዋቅር/Anatomy) አዋህዶ መያዝ ስላለበት ነው። ነገር ግን ከደረቅ theory ይልቅ ከተግባራዊ የመሳሪያዎች ጥገና እና ፈጠራ ጋር ስለሚገናኝ፣ ለቴክኖሎጂ እና ለፈጠራ ቅርብ ለሆነ ሰው በጣም አስደሳች እና ቀላል ይሆንለታል። 📍 Biomedical Engineering ከተመረቃችሁ በኋላ ያሉት Opportunities ምንድን ናቸው? ✅ በሆስፒታሎችና ክሊኒኮች፦ የህክምና መሳሪያዎች አስተዳደር፣ ተከል እና ጥገና (Maintenance & Installation) ላይ መስራት። ✅ በህክምና መሳሪያ አስገቢ ድርጅቶች በ Import/Export ኩባንያዎች ውስጥ በቴክኒክ ድጋፍ እና በከስተመር ሰፖርት መስራት። ✅ በመንግስት ተቋማት በኢፌዴሪ የፌደራል መድኃኒት ቁጥጥር ባለስልጣን (EFDA) እና ጤና ሚኒስቴር ውስጥ የህክምና መሳሪያዎች ጥራት ቁጥጥር ላይ መስራት። ✅ የግል ስራ (Business) የህክምና መሳሪያዎች ጥገና፣ ተለዋዋጭ እቃዎች አቅርቦት እና አማካሪነት ድርጅት መክፈት። ✅ Scholarships በውጭ ሀገራት ለ Master's እና Ph.D. የትምህርትና ምርምር እድሎችን በቀላሉ ማግኘት። 👉ለጓደኞቻችሁ share በማድረግ መረጃውን ኣድርሱላቸው! _ _ _ _ _ _ _ _ _ _ _ _ _ _ _ _ _ _ _ _ _ _ 📚 join us: @HavanAcademyOfficial _ _ _ _ _ _ _ _ _ _ _ _ _ _ _ _ _ _ _ _ _ _
Havan COC Preparation program For 👇 Medicine Dental Medicine Pharmacy Other heath departments Law https://vt.tiktok.com/ZSVL3aLY8/
AS we told you before... 🇪🇹 ለዘንድሮው UAT ፈተና አዲሱን የBootcamp ፕሮግራማችንን ከፍተናል! 🎓🔥 ለፈተናው ዝግጅትዎን ከእኛ ጋር በነፃ ማድረግ ይችላሉ። 📚💯 👇 ነፃ የUAT Bootcamp ትምህርታችንን ለመቀላቀል ከታች ያለውን Telegram Channel ይቀላቀሉ፦ 🚀 JOIN US At @uatbootcamp @uatbootcamp @uatbootcamp 🎯 በትክክለኛ ዝግጅት ለስኬት ይዘጋጁ! #uattutorialofficial #uatexam #uat #addisababauniversity #etstudy
без подписи
⚖️ AAU ላይ Law መማር ለምን ይለያል? በኢትዮጵያ ውስጥ ከሚገኙ የህግ ትምህርት ቤቶች መካከል የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ (AAU School of Law) ቀዳሚው እና ትልቁ እንደሆነ ይታወቃል! የ AAU Lawን ልዩ የሚያደርገው ጥራት ያለው ትምህርት መስጠቱ ብቻ አይደለም፤ ከተመረቃችሁ በኋላ ከአገር ውስጥ እስከ ዓለም አቀፍ ደረጃ ባሉ ታዋቂ ተቋማት ውስጥ የሥራ እና የትምህርት ዕድሎችን (Scholarships & Career Opportunities) በቀላሉ እንድታገኙ ከበርካታ ትልልቅ አጋሮች ጋር አብሮ ስለሚሰራ ነው! በምስሉ ላይ እንደምትመለከቱት AAU School of Law ከበርካታ የዓለም አቀፍ ዩኒቨርሲቲዎች፣ ከየተባበሩት መንግስታት ድርጅት (UN) ኤጀንሲዎች፣ ከሀገር ውስጥ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቶች እና ከፍተኛ የፍትህ ተቋማት ጋር የጠበቀ ትስስር አለው። በ AAU Law መማር ማለት • በትምህርት ቆይታችሁ እነዚህ ተቋማት ውስጥ የ Internship (የተግባር ልምድ) ዕድል ማግኘት • ከምረቃ በኋላ በቀጥታ በሀገር ውስጥ እና በዓለም አቀፍ ደረጃ የስራ ዕድሎችን ማስፋፋት • በውጭ ሀገራት የ Scholarship እድሎችን በቀላሉ ማግኘት የሚያስችል ትልቅ መደላደል ነው! _ _ _ _ _ _ _ _ _ _ _ _ _ _ _ _ _ _ _ _ _ _ 📚 Join & Share: @HavanAcademyOfficial _ _ _ _ _ _ _ _ _ _ _ _ _ _ _ _ _ _ _ _ _ _
የ UAT BOOTCAMP ሊጀምር ነው!🔥 14 ቀናት። አንድ ግብ። ለUAT በተሻለ ሁኔታ መዘጋጀት! AAU ለመግባት እየተዘጋጃችሁ ነው? ለUAT ዝግጅታችሁን በተደራጀ መንገድ መጀመር ትፈልጋላችሁ? Havan Academy የUAT Bootcampን ይዞ መጥቷል! ለ14 ቀናት አብረን እንማራለን፣ እንለማመዳለን፣ እንፈተናለን እና ለUAT በተሻለ ዝግጅት እንዘጋጃለን። 🔥 በUAT Bootcamp የሚጠብቃችሁ 1️⃣ UAT Preparation Guidance 2️⃣ Daily Challenges 3️⃣ Previous year UAT Questions 4️⃣ Live Learning Sessions 5️⃣ Q&A Sessions 6️⃣ Free Study Resources 7️⃣ Mock & Diagnostic Activities 8️⃣ Expert & Student Guidance 9️⃣ Social Proof & Preparation Stories 🔟 Supportive Preparation Community 14 ቀናት የተደራጀ ዝግጅት፣ ልምምድ፣ መመሪያ እና አብሮ የመዘጋጀት ጉዞ ነው። 🎓 🎯 AAU ለመግባት የሚዘጋጁ ሁሉ መሳተፍ ይችላሉ! ✅ ምዝገባው በቅርቡ ይከፈታል! የምዝገባ መረጃውን ለማግኘት ከHavan Academy ይከታተሉ 📢 ለUAT ለሚዘጋጁ ጓደኞቻችሁም ሼር አድርጉ! #UATBootcamp #HavanAcademy #UATPreparation #AAU #UAT2026 @havanacademyofficial
በዛሬው የዲፓርትመንት ዳሰሳችን የብዙዎቻችንን የልጅነት ህልም MEDICINE እናያለን! የህክምና ትምህርትን በሀገራችን በብዙ ዩኒቨርሲቲዎች ማግኘት ይቻላል፤ ሆኖም በጠንካራ የትምህርት አሰጣጣቸውና በተሻለ የልምድ ልውውጥ ቀዳሚዎቹ የትኞቹ ናቸው? ✅ ጥቁር አንበሳ (AAU)፣ ቅዱስ ጳውሎስ፣ ጎንደር፣ ጅማ ፣ሐረማያ፣ አርባ ምንጭ፣መቀለ ፣ባሕር ዳር እና ሃዋሳ ዩኒቨርሲቲዎች በዋናነት ይጠቀሳሉ። ለመሆኑ ከተቀላቀሉበት ቀን ጀምሮ እስከ ምረቃ ከ 7 እስከ 8 ዓመታትን መውሰዱ የሚታወቅ ነው😱 ለመሆኑ ትምህርቱ እውን አስፈሪ ነው? ✅ እውነታው ያለው እዚህ ጋር ነው የሜዲስን ትምህርት አዲስ ፈጠራ ወይም ሂሳብ የመስራት ውጥረት የለውም፤ ዋናው ስራ ቁጭ ብሎ በደንብ ማንበብ ነው። ስለዚህ የማንበብ ልምድ ላለው ተማሪ ነገሩ ቀላል ነው! ነገር ግን ከባድ የሚያደርገው የመረጃው መጠን (Volume) እጅግ በጣም ሰፊ መሆኑ ነው። በተለይ በ Pre-Clinical 1 (PC1) እና Pre-Clinical 2 (PC2) ጊዜያችሁ አብዛኛውን ሰዓት ላይብረሪ ውስጥ ለማሳለፍ ትገደዳላችሁ🤯፤ ከሁሉም በላይ ደግሞ በቀጥታ ከሰው ህይወት ጋር ስለምትሰሩ ኃላፊነቱ ከፍተኛ ነው። ሌላው ብዙዎችን የሚያስጨንቀው፦ ከምረቃ በኋላስ ያበላል?💰💰 ✅ በየቦታው እንደሚወራው "ተስፋ የሌለው" ዘርፍ አይደለም። በርካታ አማራጮች አሉት፤ ነገር ግን ውጤቱን ለማየት ረጅም ጊዜና ትዕግስት ይጠይቃል። በአንድ ጀምበር ለውጥ ለሚፈልግ ሳይሆን በትዕግስት ላሰበ ተማሪ የሚሆን ነው😁 አንድ ተማሪ በሜዲስን ለመግፋት ምን ምን ነገሮች ያስፈልጉታል? ✅ ዋናው ነገር Discipline (ስነ-ስርዓት)፣ Commitment (ቁርጠኝነት) እና ለሙያው ያለው እውነተኛ ፍቅር ነው! ትምህርቱ ሰፊ ነው፣ የረጅም ሰዓት ጥናት ይጠይቃል፣ አመታቱም ረጅም ነው። ስለዚህ ለሙያው ፍቅር ሳይኖራችሁ ወይም በቤተሰብ ግፊት ብቻ አደራ እንዳትገቡ! ከምረቃ በኋላ የሚጠብቋችሁ ዕድሎች ✅ USMLE ፈተናን አልፎ ወደ አሜሪካ ማቅናት፣ ወደ አውሮፓ ሀገራት በ Scholarship መሄድ፣ በፈለጉት ዘርፍ Specialization መስራት፣ ወይም MPH (Public Health) በመማር በጤና ሚኒስቴር፣ WHO እና በተለያዩ ዓለም አቀፍ NGOs ውስጥ የማገልገል ሰፊ ዕድል አለ😎 👉ይህ ማለት ግን ሁሉም በ medicine የተማረ እነዚን opportunity ያገኛል ማለት ኣይደለም በስተመጨረሻም ይሄን የተከበረና ታላቅ ሙያ ለመቀላቀል ላሰባችሁ በሙሉ መልካም እድል ይሁንላችሁ!😊😊 _ _ _ _ _ _ _ _ _ _ _ _ _ _ _ _ _ _ _ _ _ _ Join & Share: @HavanAcademyOfficial _ _ _ _ _ _ _ _ _ _ _ _ _ _ _ _ _ _ _ _ _ _
Electrical & Computer Engineering (ECE) መግባት ላሰባችሁ... እውነታው ይኸው! ስለ ECE ብዙ የሚወራ ነገር አለ—አንዱ በጣም ከባድ ነው ይላል፣ ሌላው ደግሞ በጣም አሪፍ ነው ይላችኋል። ለመሆኑ ECE በትክክል ምንድነው? የትኛው ተማሪ ነው የሚሆነው? እውነታውን አብረን እንየው👇 ECE በትክክል ምንድነው? በአጭሩ ኤሌክትሪሲቲን፣ ኤሌክትሮኒክስን እና የኮምፒውተር ሲስተምን አዋህዶ የሚይዝ ትልቅ ዘርፍ ነው። ተምራችሁ ለመጨረስ 5 ዓመት ይወስዳል። በመጨረሻው ዓመት Internship (የተግባር ልምድ) እና ትልቅ Graduation Project አለው። ትምህርቱ ምን ያህል ይከብዳል? እውነቱን ለመናገር—ቀላል አይደለም! የትምህርቱ 80%–85% የሚሆነው Maths እና Physics ነው። ሒሳብና ፊዚክስ የምትጠሉ ከሆነ 👉 እዚህ በጣም ትቸገራላችሁ። ነገር ግን ነገሮችን የመተንተንና የመፍታት (Problem Solving) ፍላጎት ካላችሁ 👉 በጥረት ይቻላል። ኮርሶቹ ምን ይመስላሉ? 2ኛ ዓመት: Applied Maths II & III፣ Physics (Mechanics)፣ Engineering Drawing እና Computational Methods ይኖሩታል። 3ኛ ዓመት (ትልቁ ፈተና 😅): Electronics፣ Electromagnetic Fields፣ Signals & Systems፣ Control Systems እና Digital Logic Design ይገባሉ። አብዛኛው ተማሪ የሚፈተነው እዚሁ 3ኛ ዓመት ላይ ነው። Specialization (Stream) መቼ ይመረጣል? 4ኛ ዓመት ስትደርሱ ከእነዚህ አንዱን ትመርጣላችሁ፦ 📍Power ⚡ — የኃይል ማመንጨትና ማሰራጨት 📍Communication 📡 — የቴሌኮም እና የመረጃ ልውውጥ 📍Control — ኦቶሜሽን፣ ሮቦቲክስ እና ሚካትሮኒክስ 📍Computer 💻 — Embedded Systems፣ IoT እና Software Development 📌ከመወሰናችሁ በፊት ይህንን አስቡ! ECE ለማን ይሆናል? Math የሚወድ፣ አዳዲስ ነገሮችን የመማር እና ችግር የመፍታት ፍላጎት ያለው። ለማን አይሆንም? "ቀለል ያለ ትምህርት ተምሬ ልመረቅ" ለሚል እና Math/Physics ለሚጠላ። 📌 ትልቁ እውነት ECE ላይ የወረቀት ዲግሪ ብቻውን ቦታ የለውም። Skill ካላችሁ ገቢያችሁም ቦታችሁም ከፍተኛ ነው፤ Skill ካሌለ ግን ከባድ ነው። ዲግሪው ብቻውን ወደፊታችሁን አይወስነውም—ወደፊታችሁን የሚወስነው እናንተ የምታሳዩት ጥረትና የምታዳብሩት ክህሎት ነው! 👉ለጓደኞቻችሁ share በማድረግ መረጃውን ኣድርሱላቸው! _ _ _ _ _ _ _ _ _ _ _ _ _ _ _ _ _ _ _ _ _ _ 📚 join us: @HavanAcademyOfficial _ _ _ _ _ _ _ _ _ _ _ _ _ _ _ _ _ _ _ _ _ _
📌 ሀረማያ ዩኒቨርሲቲ 📍 መገኛ እና ጉዞ ሀረማያ ከተማ ከሀረር 17 ኪሎ ሜትር ያህል ርቀት ላይ ነው የምትገኘው። ❄️ የአየር ሁኔታ ሀረማያ ሞቃት ነው የሚለውን ወሬ አትስሙ! አንዳንዴ ሞቅ የሚሉ ወራት ቢኖሩም፣ አብዛኛውን ጊዜ ግን አየሩ ቀዝቃዛ ነው፤ በተለይ ምሽት ላይ ይበርዳል። • ወፍራም ልብስ ይዛችሁ ብትመጡ ይመረጣል • ከባድ ብርድ ልብስና ዕቃ ተሸክሞ ከመምጣት፣ ሀረማያ ልብስና አልባሳት ርካሽ ስለሆኑ ግቢ ከገባችሁ በኋላ መግዛት ትችላላችሁ 🏫 Sub-Campuses ዩኒቨርሲቲው አንድ ትልቅ ዋና ግቢ ሆኖ በውስጡ 3 ንዑሳን ግቢዎች አሉት። በተጨማሪም ሀረር ከተማ ላይ ሌላ ግቢ አለው 📍Main Campus (ዋናው ግቢ) • All Social Science departments • Computer Science • Business & Economics • Natural & Computational Sciences • Law, Teaching, Agriculture... 📍Gandajay (Techno Campus) • ከ2ኛ ዓመት በላይ ያሉ Engineering ተማሪዎች • Food Science Station Campus • Freshman Engineering ተማሪዎች • Veterinary Medicine 📍Harar Campus • Medicine, Health Sciences & Pharmacy ይህ ግቢ በተለይ በ Agriculture, Law እና Computer Science ትምህርት ክፍሎቹ በጣም ይታወቃል። 🍽️ የካፌና የምግብ ሁኔታ ምግብ ላይ ሀረማያ በሀገራችን ከሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች መካከል ከቀዳሚዎቹ ተመዳቢ ነው ማለት ይቻላል! • ምሳ፦ በሳምንት 5 ቀን Therefore (የተለያዩ ወጦች) ይቀርባል፤ 1 ቀን ፓስታ እንዲሁም 1 ቀን መኮረኒ ይሰራል። • ቁርስ፦ ሳንድዊች፣ ማርማላታ፣ በሳምንት 2 ቀን ዳቦ በስጋ ፍርፍር፣ ሩዝ እና ዳቦ ይቀርባል። ⚠️ ጠቃሚ ማሳሰቢያዎች • ስለ ጫት፦ በከተማው የጫት አጠቃቀም ቢኖርም፣ በህግ ደረጃ ግቢ ውስጥ ጫት መቃም በጥብቅ የተከለከለ ነው። ለአላስፈላጊ የዲሲፕሊን ውዝግብ እንዳትዳረጉ፣ በተለይ አዲስ የሆናችሁ ተማሪዎች ከጫትና መሰል ልማዶች ሙሉ በሙሉ እንድትረቁ እንመክራለን። • የውሃ አቅርቦት፦ የውሃ ችግር የለብንም፤ አልፎ አልፎ ቢቋረጥ እንኳ በካፌና በሴቶች ብሎኮች አካባቢ አቅርቦቱ አይቋረጥም። • አብሮነት፦ በብሄር ላይ የተመሰረቱ ቀልዶችና አላስፈላጊ እፎይታን የሚነሱ ነገሮች በጥብቅ የተከለከሉ ናቸው። ማንኛውንም ተማሪ አክብሮ አብሮ መኖር ሰላማዊ የግቢ ቆይታ እንዲኖራችሁ ይረዳል። 🚌 ደህንነትና አቀባበል ግቢው ሰላማዊና አስተማማኝ ደህንነት ያለው ሲሆን፣ ለፍሬሽ ተማሪዎችም የትራንስፖርት አገልግሎት (Service) ተዘጋጅቶ ይጠብቃችኋል። _ _ _ _ _ _ _ _ _ _ _ _ _ _ _ _ _ _ _ _ _ Join us:@HavanAcademyOfficial _ _ _ _ _ _ _ _ _ _ _ _ _ _ _ _ _ _ _ _ _
ከግቢ የምያስባርሩ ድርግቶች👇 https://vt.tiktok.com/ZS431AVdf/
🛑 በ 2019 የ Freshman ተማሪዎች ለሆናችሁ የግቢ መረጃዎችን፣ የዲፓርትመንት መረጣ መመሪያዎችን እና የተለያዩ የዩኒቨርሲቲ የትምህርት አጋዥ ቁሳቁሶችን ከፈለጋችሁ እንደ 📍Department Choice Guides 📍 Teacher's guides 📍Freshman courses 📍 Worksheets 📍Mid exams 📍Final exams 📍COC exams 📍Lecturer powerpoints 🤝ለሌሎች ጓደኞቻችሁም Share በማድረግ አድርሱላቸው! 📌እነዚህን እና ሌሎች ጠቃሚ የትምህርት መረጃዎችን የሚያቀርበውን ቻናል Join በማድረግ ተከታተሉ👇 _ _ _ _ _ _ _ _ _ _ _ _ _ _ _ _ _ _ _ 📚 Join us:@HavanAcademyOfficial _ _ _ _ _ _ _ _ _ _ _ _ _ _ _ _ _ _ _
🚨 FRESHMAN AWARENESS CHECK! 🎓 🎯 Are you ready for university life? Or are you still wondering what your first semester, courses, exams, and campus life will actually be like? 👀 Don’t let the unknown freshman year catch you off guard. 📚 👇 Be honest with yourself: 🟢 I’M READY ✅ 🔵 I NEED GUIDANCE 🤔 Comment your answer below 👇 Don’t just wait for university to start. Prepare for it. Start Smart. Study Smart. Succeed. #HavanAcademy #Freshman2019 #FreshmanPreparation #UniversityLife
📌Civil Engineering ምን ዓይነት Department ነው? መሠረተ ልማቶችን ማለትም መንገዶችን፣ ድልድዮችን፣ ህንፃዎችን፣ የውሃ መስመሮችንና መሰል ትልልቅ ፕሮጀክቶችን የመነደፍ (Design)፣ የመገንባት (Construction) እና Project Management ጥበብ የሚጠናበት የኢንጂነሪንግ ዘርፍ ነው። 📍ለመመረቅ ስንት ዓመት ይፈጃል? ከአዲሱ የትምህርት ስርዓት ጋር ፍሬሽማንን ጨምሮ በአጠቃላይ 5 ዓመት ይወስዳል። ❓ የሚሰጡ ዋና ዋና ኮርሶች ምንድን ናቸው? • Structural Analysis & Design • Engineering Mechanics • Construction Materials • Geotechnical Engineering (Soil Mechanics) • Hydraulics & Water Resources • Transportation Engineering • Surveying • Construction Management • Internship (የተግባር ልምምድ) እና Final Year Senior Project ❓ ትምህርቱ ከባድ ነው? አዎ፣ ቀላል ነው አይባልም። በተለይ በ Maths እና Physics ላይ ጠንካራ መሠረት ይፈልጋል። ከ Theory ባለፈ የሜዳ ስራዎች እና ዲዛይኖች ስለሚበዙበት ትጋትንና ተግባራዊ ክህሎትን ይጠይቃል። 📍ከተመረቁ በኋላ የሚሰሩ የስራ ዘርፎች ምንድን ናቸው? • የህንፃ ግንባታ ፕሮጀክቶች • የመንገድ እና የድልድይ ስራዎች • የውሃ እና የመስኖ ፕሮጀክቶች (Water & Irrigation) • የአማካሪ (Consultancy) ድርጅቶች • የመንግስት የመሠረተ ልማት መስሪያ ቤቶች ❓ በሀገራችን ኢትዮጵያ ውስጥ የስራ እድሉ እንዴት ነው? ኢትዮጵያ ውስጥ የመሠረተ ልማት እና የህንፃ ግንባታ ስራዎች ሁልጊዜም ስላሉ የሙያው ፈላጊ ከፍተኛ ነው። በግል Contractors፣ በአማካሪ ድርጅቶች (Consultants) ሰፊ እድል አለ። ❓ ይህ ዲፓርትመንት ለማን ይመረጣል? • የሂሳብ እና የንድፍ (Design) ስራ የሚስበው • በቢሮ ስራ ብቻ ሳይወሰን Field Work የሚወድ • በትልልቅ ፕሮጀክቶች ላይ ተሳታፊ መሆን የሚፈልግ 👉ለጓደኞቻችሁ Share በማድረግ መረጃውን አድርሱ! _ _ _ _ _ _ _ _ _ _ _ _ _ _ _ _ _ _ _ _ Join us :@HavanAcademyOfficial _ _ _ _ _ _ _ _ _ _ _ _ _ _ _ _ _ _ _ _ _
በዚህ ዓመት ስንት ፐርሰንት ተማሪ የኢንትራንስ ፈተና የሚያልፍ ይመስላችኋል? በትክክል በመገመት የ 5000 ብር እና የአንድ ዓመት የሃቫን አካዳም ነፃ ኮርስ ፓከጅ ይሸለሙ!! https://vt.tiktok.com/ZS4swQvsK/ ሌሎች ተማሪዎችም በትትክክል በመገመት የሽልማቱ ተካፋይ እንዲሆን ሼር አድርጉላቸው🙏 @havanacademyofficial
📌Software Engineering ወይስ Computer Science? የትኛው ልምረጥ ? ብዙ ተማሪዎች የትኛውን ዘርፍ መምረጥ እንዳለባቸው ግራ በመጋባት ይጨነቃሉ! ሁለቱም ከቴክኖሎጂ ጋር የተያያዙ ቢሆኑም፣ ትኩረታቸው እና የሚሄዱበት መንገድ ግን የተለያየ ነው። 👉 Computer Science (CS) የሚያተኩረው ኮምፒውተር «እንዴት ይሠራል?» በሚለው መሠረታዊ እና ቲዮሪቲካል እውቀት ላይ ነው። 👉 Software Engineering (SE) ደግሞ «ሶፍትዌርን በጥራት እንዴት እንገንባ?» በሚለው ተግባራዊ ስራ ላይ ያተኩራል። ብዙ ተማሪዎች ሁለቱን አንድ አድርገው ያስባሉ፤ ነገር ግን በትምህርት አቀራረባቸውም ሆነ በስራ ዘርፋቸው ላይ ግልጽ ልዩነት አላቸው። 📚 Computer Science ምን ያስተምራል? ይህ ዘርፍ የኮምፒውተርን አስተሳሰብ፣ አልጎሪዝም እና የ logic መሠረቶችን በጥልቀት ያስጨብጣል። ተማሪዎች በጥልቀት የሚማሯቸው ዋና ዋና ርዕሶች • Data Structures • Algorithms • Artificial Intelligence (AI) • Data Science • Computer Architecture • Operating Systems 📚 Software Engineering ምን ያስተምራል? ይህ ዘርፍ ደግሞ የነባር አሰራሮችን መመሪያ በመከተል ሶፍትዌርን ከባዶ ተነስተው እስከ ማጠናቀቅ ባለው ሂደት ላይ ያተኩራል። ተማሪዎች በጥልቀት የሚማሯቸው ዋና ዋና ርዕሶች • Software Development • Web & Mobile App Development • Software Design & Testing • Database Systems • Software Project Management • SDLC (Software Development Life Cycle) ❓ የብዙ ተማሪዎች የተለመዱ ጥያቄዎች • ሁለቱም ተመሳሳይ ናቸው? አይደሉም፤ CS መሠረቱን ሲሰጥ፣ SE ደግሞ ያንን መሠረት ተጠቅሞ መገንባትን ያስተምራል። • የተሻለው የትኛው ነው? የተሻለ የሚባል የለም፤ ከፍላጎትህ እና ከግል ዝንባሌህ ጋር የሚሄደው ነው ትክክለኛው። • ትኩረቴ ኮዲንግ እና አፕሊኬሽን መስራት ላይ ብቻ ከሆነ? Software Engineering ይበልጥ ይመችሃል። • AI፣ Machine Learning እና Data Science የሚስቡኝ ከሆነስ? Computer Science ይበልጥ የተሻለ ምርጫ ይሆናል። • በሀገራችን ኢትዮጵያ የስራ እድላቸው እንዴት ነው? በሁለቱም ዘርፍ ለወጡ ተመራቂዎች በባንኮች፣ ቴሌኮም፣ ስታርታፖች እና በሪሞት (Freelancing) ሰፊ የስራ እድል አለ። 📌የትኛው ዘርፍ ወደ ምን ስራ ይመራል? Computer Science ተመራቂዎች • AI / Machine Learning Engineer • Data Scientist • Systems Analyst • Researcher Software Engineering ተመራቂዎች • Software Developer • Mobile App Developer • Web Developer • DevOps Engineer ✔️ወሳኝ ምክር ለተማሪዎች በ theory CS ፤ SE ደግሞ ተግባር ተብለው ቢከፋፈሉም፤ በኢትዮጵያ ዩኒቨርሲቲዎች የሚሰጠው ትምህርት ለሁለቱም ዘርፍ በአብዛኛው ቲዮሪ ላይ ያዘነበለ ነው። 👉 ስለዚህ የትኛውንም ክፍል ብትማሩ፣ በዩኒቨርሲቲ ትምህርት ላይ ብቻ ሳትወሰኑ በግላችሁ በተግባር (Practice) መስራት፣ ፕሮጀክቶችን መገንባት እና ክህሎታችሁን ማሳደግ ግዴታ ይሆንባችኋል! _ _ _ _ _ _ _ _ _ _ _ _ _ _ _ _ Join & share👇👇 @HavanAcademyOfficial _ _ _ _ _ _ _ _ _ _ _ _ _ _ _ _
የኢንትራንስ ውጤት ሲለቀቅ ትምህርት ሚኒስቴር ዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተና ውጤታችሁን ለማየት 3 የተለያዩ አማራጮችን ያቀርባል፦ 📱 Telegram bot 🌐 Website 💬 SMS ነገር ግን በአንድ ጊዜ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ተማሪዎች ውጤታቸውን ለማየት ሲሞክሩ፣ የኢንተርኔት መጨናነቅና የግንኙነት ችግሮች ውጤታችሁን ለማየት አስቸጋሪ ያደርጋሉ። 😩 አሁን ግን ቀላል አማራጭ አለ! በ @ESSLCEResultBot ከዛሬ ጀምሮ በመመዝገብ፣ ውጤት ሲለቀቅ በቀላሉ ለማየት አስቀድማቸእሁ ዝግጁ መሆን ትችላላችሁ። ✅ ፈጣን ✅ ቀላል ✅ ደህንነቱ የተጠበቀ ✅ አስተማማኝ ✅ ለተማሪዎች የተዘጋጀ ከዛሬው ጀምረህ ተመዝገብ! 👉 @ESSLCEResultBot ለሌሎች ተማሪዎች ሼር ማድረግ እንዳትረሱ @havanacademyofficial
😨 5 ዓመት ተምረህ በመጨረሻ ስራህ በAI ቢተካስ? አስበው… 5 ወይም 6 ዓመታት ዩኒቨርሲቲ ገብተህ፣ ጊዜህን፣ ገንዘብህን እና ጉልበትህን አውጥተህ ተምረሃል። ተመርቀሃል።🎓 ዲግሪህን ይዘሃል።📄 ስራ ለመጀመር ተዘጋጅተሃል።💼 ከዚያ ግን አንድ ነገር ትሰማለህ፦ “ይህን ስራ AI በቀላሉ ማከናወን ይችላል።” 😶 ያኔስ? AI ብዙ የስራ ዓይነቶችን እየቀየረ ነው። በተለይ ተደጋጋሚ እና በቀላሉ ሊደረጉ የሚችሉ ስራዎች በአደጋ ላይ ናቸው። ስለዚህ ዛሬ በዩኒቨርሲቲ የት/ት ዘርፍ ስትመርጡ፣ “ይህ ስራ ዛሬ ተፈላጊ ነው?” ብቻ አትጠይቅ። “ከ5–10 ዓመት በኋላስ?” “AI ይህን ሙያ እንዴት ይቀይረዋል?” “AI በዚህ ሙያ ውስጥ ሲገባ እኔ ምን አዲስ ነገር መስራት እችላለሁ?” የወደፊቱን ስራ በርግጠኝነት መተንበይ ባትችሉም። ግን ለወደፊቱ ለመላመድ ራሳችሁን ማዘጋጀት ትችላላችሁ። 🎯 ዲግሪ ብቻ አትምረጡ። የወደፊት ክህሎት ምረጡ። ከAI ጋር የሚሰራ ተማሪ ሁን፤ AI የሚተካው ተማሪ አትሁን። Share : @havanAcademyOfficial Your Future Matters !
💥It's happening now!! 🎉The Grand UAT Live session!! ስለ UAT ምን ማወቅ፣ መጠየቅ ትፈልጋላችሁ ? Join and share this Link 👇🏽👇🏽 https://t.me/UATtutorialofficial?livestream=e0652897f167501108
በ2019 ዓ.ም ፍሬሽማን የምትገቡ ተማሪዎች፣ ሲኒዬሮች እንዳይስቁባችሁ እነዚህን ነገሮች ባታደርጉ ይሻላል! 😅 1. 5 ኮርሶችን በአንድ ደብተር የሚለውን የፍሬሽማን ደብተር አትግዙ። እኛም ገዝተን ነበር... ከዛ በኋላ እውነቱን ተረዳን። 😂 2. ዩኒቨርሲቲ ውስጥ ያለ እያንዳንዱ አረንጓዴ ሣር ላይ ፎቶ አትነሱ። ካምፓሱ ቆንጆ ነው... ግን እያንዳንዱ ሣር የፎቶ ስቱዲዮ አይደለም። 🤣 3. 10 ወይም 15 ሰው ሆናችሁ በአንድ ላይ አትጓዙ። ወደ Library፣ Cafeteria ወይም ክፍል ስትገቡ 2 ወይም 3 ሰው ሆናችሁ መሄድ ይሻላል። 😄 4. Havan Academyን ማወቅ አይርሱ። እንዴ... Havan Academy አታውቁም?" የሚለውን ጥያቄ ላለመስማት አሁኑኑ ይቀላቀሉ። 😎 5. ሲኒየሮችን ሁሉንም ትንሽ ነገር አትጠይቁ። አንዳንዶቹ በጣም ያግዛሉ፤ አንዳንዶቹ ግን ክፍል ፈልጋችሁ ሄዳችሁ መጸዳጃ ቤት ልልኳችሁ ይችላሉ! 😂 ❤️ ቀልድ ነው! ሁሉም ሲኒየሮች አንድ ቀን ፍሬሽማን ነበሩ። Havan Academy ግን ከመጀመሪያ ቀን ጀምሮ ከጎናችሁ ይሆናል። ❤️ 📌 ስለ ምዝገባ 📌 ስለ ዩኒቨርሲቲ ሕይወት 📌 ስለ ትምህርት 📌 ስለ Dept, GPA እና ሌሎች 📌 እና የሚያሳስባችሁን ሁሉ... ጉዞአችሁ ቀላል እና ስኬታማ እንዲሆን ከእናንተ ጋር ይሆናል! —————————————— Share : @HavanAcademyofficial ——————————————--
ፍሬሽማን ላይ እነዚህ 5 ነገሮችን ካደረጋችሁ የሲኒየር መሳቂያ ትሆናላችሁ😂 https://vt.tiktok.com/ZS44qGC84/