tgindex
INFO HEALTH CENTER

INFO HEALTH CENTER

Статистика

👉 Consultancy Service 👉 Health and Related Training 👉 National and International training 0921785903 0932338485 https://t.me/jossiale2022

Последний пост
13 авг.
Последнее чтение
14:34
Постов за неделю
8
Всего постов
51
Тип
открытый
Язык
английский
Категория
Новости и СМИ (по похожим)
В каталоге с
13 авг.
Подписчики
8 177
−1 за 3 дн.
Сутки
+4
+0,05%
Неделя
 
Месяц
 
Просмотров на пост
1 228
40 постов
Вовлечённость
15,0%
к подписчикам
Постов в день
1,1
всего 51
Упоминаний
1
каналов
Охват размещения
оценка
1/24сутки в ленте
656
1/48двое суток
751
1/72трое суток
810

Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.

Посты

  • ✍ #የኩላለት# ህመም #ምልክቶች 🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹 ♥♥#በቅንነት #ሼር #ያድርጉልን♥♥ ⏩  #የሽንት ስርዓት መዛባት/መቀየር የመጀመሪያው የኩላሊት በሽታ ምልክት የሽንት ሥርዓት መለወጥ ነው፡፡ መለወጥ ስንል የሽንት መጠን እና ሽንትዎን የሚሸኑበት የጊዜ ልዩነት ነው፡፡እንዲሁም ሌሎች ለውጦች የሚከተሉትን ያጠቃልላል፦ 🔹 ሌሊት ሽንት ለመሽናት ደጋግመው መነሳት 🔹 ለመሽናት መቸኮል 🔹 ከተለመደው ጠቆር ያለ ሽንት 🔹 አረፋ ያለው ሽንት 🔹 ደም የተቀላቀለበት ሽንት 🔹 ሲሸኑ መቸገር/በጣም መግፋት ለመሽናት 🔹 በሚሸኑበት ጊዜ ህመም ወይም የማቃጠል ስሜት ⏩  #የሰውነት #እብጠት 🔹 የስውነት ተረፈ ምርቶችንና ትርፍ ፈሳሾችን ከሰውነታችን ማስወገድ የኩላሊት ስራ ነው፡፡ ይህን ማድረግ ሲሳነው ግን የትርፍ ፈሳሽና ውሃ መከማቸት እብጠት እንዲፈጠር ያደርጋል፡፡ እነዚህ እብጠቶች በእጅ፣ እግር፣ ቁርጭምጭሚት መገጣጠሚያ፣ ፊት እና አይን አካባቢ ይፈጠራሉ፡፡ ⏩ #ከፍተኛ #የሆነ #የመዛልና #የድካም #ስሜት 🔹 ኩላሊት ተግባሯን በትክክል መወጣት በሚያቅታት ወቅት አብዛኛውን ጊዜ የመዛል ስሜት ይሰማናል፡፡ ይደክምዎታል ወይም በአጠቃላይ ባላወቁት ምክንያት ሃይል/ጉልበት ያጥርዎታል፡፡ የዚህ ምልክት ሁለት ዋና ዋና ምክንያቶች የደም ማነስና በሰውነት ውስጥ የተረፈ ምርቶች/ቆሻሻዎች መከማቸት ነው፡፡ ⏩ # የማዞር #ስሜት 🔹 በኩላሊት በሽታ ምክንያት የደም ማነስ የሚከሰት ከሆነ በተደጋጋሚ ያዞርዎታል የዚህም ችግር የራስ መቅለል፣ ሚዛን ማጣት ዓይነት ስሜቶች/ምልክቶች ይታይብዎታል፡፡ ይህ የሚሆንበት ምክንያት የደም ማነስ በሽታው ወደ አእምሮ በቂ የሆነ ኦክስጂን እንዳይደርስ ስለሚያደርግ ነው፡፡ ⏩ #የጀርባ #ህመም 🔹 ይህ ነው የማይባል የህመም ስሜት በጀርባዎና በሆድዎ ጎንና ጎን መሰማት የኩላሊት በሽታ ወይም የኩላሊት ኢንፌክሽን ምልክት ሊሆን ይችላል፡፡ ኩላሊት በትክክል ስራውን መስራት ካልቻለች የመገጣጠሚያ ህመም፣ መገተር/ለማጠፍ መቸገርና ፈሳሽ ይስተዋላል፡፡ ⏩ #የቆዳ #መሰነጣጠቅና #ማሳከክ 🔹ድንገተኛ የሆነ የቆዳ መሰነጣጠቅ፣ ሽፍታ፣ ማቃጠል/መለብለብ እና ከፍተኛ የማሳከክ ስሜት ተጨማሪ የኩላሊት ችግር ምልክቶች ናቸው፡፡ ኩላሊት ተግባሩን በትክክል አለመወጣት ቆሻሻዎችና መርዛማ ነገሮች በሰውነት ውስጥ እንዲከማቹ አስተዋጽዎ ስለሚያደርግ በርከት ላሉ የቆዳ ችግሮች ያጋልጣል፡፡ ⏩ #የአፍ #ሽታ 🔹የኩላሊት በሽታ የአፋችን ጣዕም ብረት ብረት እንዲለን ወይም አፋችን የአሞኒያ(የሽንት) ሽታ እንዲኖረው ያደርጋል፡፡ ይህ የሚሆነው ደካማ የሆነ የኩላሊት ተግባር በደም ውስጥ ያለው የዩሪያ መጠን እንዲጨምር ያደርጋል፡፡ ዩሪያ በምራቅ በመሰባበር ወደ አሞኒያ ይቀየራል ይህም አፋችን መጥፎ የሆነ ሽንት የሚመስል ሽታ እንዲኖረው አስተዋጽኦ ያደርጋል፡፡ ⏩ #ማቅለሽለሽ #ወይም #ማስመለስ 🔹በኩላሊት በሽታ የሚሰቃዩ ሰዎች ማቅለሽለሽ፣ ማስመለስ እና የምግብ ፍላጎት መቀነስ በጣም የተለመዱ ምልክቶች ናቸው፡፡ የማቅለሽለሽ እና ማስታወክ ስሜት በአብዛኛው የሚኖረው ጠዋት ከእንቅልፍዎ በሚነሱበት ወቅት ነው፡፡ ⏩ #አብዛኛውን #ጊዜ #ይበርድዎታል? 🔹ይህ በኩላሊት በሽታ ምክንያት በተፈጠረ ደም ማነስ ምልክት ነው፡፡ በማያውቁት ምክንያት የብርድ ስሜት ሊሰማዎት ይችላል ምንም አየሩ ሙቀት ቢሆንም እንኳን፡፡ አብዛኛውን ጊዜ ከማዞርና ድካም በተጨማሪ የሚበርድዎት ከሆነ በፍጥነት ህክምና ያግኙ፡፡ ⏩ #የትንፋሽ #ማጠር 🔹የትንፋሽ እጥረት የኩላሊት በሽታ ምልክት ሊሆን ይችላል፡፡ ኩላሊት ተግባሯን በትክክል አለመወጣቷ በሳንባ ውስጥ በዛ ያለ ፈሳሽ እንዲከማች ያደርጋል፡፡ ይህ የትንፋሽ ማጠር በኩላሊት ችግር ምክንያት በተፈጠረ የደም ማነስ ሊሆን ይችላል፡፡ ⏩https://t.me/jossiale2022

  • 🧠 #ስሜትና_ውሳኔ “ጊዜያዊ ስሜት ላይ ዘላቂ ውሳኔ አትውሰድ።” ስሜት እንደ ደመና ነው—ይመጣል፣ ያጨልማል፣ ከዚያም ያልፋል። ቁጣም፣ ሀዘንም፣ ብስጭትም ዘላቂ አይደሉም። ነገር ግን በጊዜያዊ ስሜት የተወሰነ ውሳኔ ዘላቂ ውጤት ሊያስከትል ይችላል። ሰዎች ሁልጊዜ ለምን እንደተናደድክ አያስታውሱም፤ የሚያስታውሱት ግን በዚያ ቁጣ የተናገርከውን ቃል እና የወሰንከውን ውሳኔ ነው። ስለዚህ ስሜትህ በከፍተኛ ደረጃ ላይ ሲሆን፣ አትመልስ፣ አትወስን፣ አትቁረጥ። ቆም በል፣ ተረጋጋ፣ አስብ—ከዚያ ወስን። ጥበብ ስሜትን ማጥፋት አይደለም፤ ስሜት በሚነሳበት ጊዜ ውሳኔህን እንዳይመራ መቆጣጠር ነው። “ስሜት ይለወጣል፤ ውሳኔ ግን ውጤት ይተዋል። ስለዚህ ዛሬ የሚያልፍ ስሜት ለነገ የማይለወጥ ውሳኔ እንዲወስንልህ አትፍቀድ።” https://t.me/jossiale2022

  • ለሁሉም የጤና ባለሙያዎች! 🎓 CPD Training በETHIO MEDICAL CPD CENTER በሚከተሉት ክልሎች እና ከተሞች የCPD ስልጠናዎችን እየሰጠን ነው፦ ✅ አዲስ አበባ ✅ ኦሮሚያ ክልል ✅ አማራ ክልል ✅ ሲዳማ ክልል ✅ ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ✅ አፋር ክልል ✅ ሶማሌ ክልል 👨‍⚕️ ለዶክተሮች፣ ለነርሶች፣ ለፋርማሲስቶች፣ ለላቦራቶሪ ባለሙያዎች፣ ለሚድዋይፎች እና ለሁሉም የጤና ባለሙያዎች። 📞 ለምዝገባና ለተጨማሪ መረጃ 📱 0921 785 903 📱 0932 338 485 ETHIO MEDICAL CPD CENTER "Learning Today, Saving Lives Tomorrow." https://t.me/jossiale2022

  • የCPD ስልጠና ETHIO MEDICAL CPD CENTER 🦠Antimicrobial Prevention & Control Training 📅 ቅዳሜ ነሐሴ 9/2018 ዓ.ም የሚጀምር 🎓 15 CEU Points 👩‍⚕️👨‍⚕️ ለሁሉም የጤና ባለሙያዎች 🏆 ይደውሉ ይመዝገቡ!!! ETHIO MEDICAL TRAINING AND CONSULTANCY PLC📞 0921785903 | 0932338485 https://t.me/jossiale2022

  • #የደረት_ላይ_ህመም • የደረት ላይ ህመም ወይም መጥፎ ስሜት በጣም የተለመደ እና ብዙዎች የጤና ባለሙያ እይታን የሚሹበት ጉዳይ ነው። • የደረት ላይ ህመም ወይም መጥፎ ስሜት ከሰው ሰው በደረጃ፣ በጊዜ ቆይታ፣ ህመሙ በሚሰማበት ቦታ፣ በስፋትና እና ጥልቀቱ ይለያያል። • በአንዳንዶች ላይ ጠቅ የሚያደርግ፣ በሌሎች ላይ በጩቤ የመወጋት፣ ወጥሮ የመያዝ፣ ድክም የማለት፣ የማቃጠልና የመሳሰሉት ስሜቶች ይከሰታሉ። • መታወቅ ያለበት ጉዳይ ግን የደረት ላይ መጥፎ ስሜት ሁሉ ለህይዎት አስጊ ነው ማለት እንዳልሆነ ነው። • ብዙ ሰዎች የደረት ህመም ወይም ድካም ካላቸው ችግሩን ቀጥታ ከልብ ችግር ጋር ያያይዙታል። ትኩረት መስጠቱ ተገቢ ቢሆንም አብዛኸኛው የደረት ህመም ግን ከልብ ጋር አይገናኝም። ብዙ ጥናቶች እንደሚያሳዩት ከሆነ የደረት ላይ ህመም ወይም መጥፎ ስሜት ኑሮባቸው ሲመረመሩ ከልብ ችግር ጋር የተያያዘ ሆኖ የተገኘው ከ10-15% የሚሆኑት ላይ ብቻ ነው። • ይህ ማለት 85-90% የሚሆነው የደረት ላይ ህመም ከልብ ጋር የተያያዘ አይደለም። አሁንም ይህን ስንል ግን የደረት ላይ ህመምን አቅለን እንይ እያልን አይደለም። #የደረት #ህመም #ምክናየቶች #የሚከተሉት #ናቸው። 1. ከልብ ጋር የተያያዙ ምክናየቶች 2. ከመተንፈሻ አካል ጋር የተያያዙ ምክናየቶች 3. ከስርአት-ምግብ ልመት አካል ጋር የተያያዘ 4. በደረት አካባቢ ከሚገኙ ጡንቻ(ስጋ) እና አጥንት ችግር ጋር የተያያዘ እና 5. ከአንዳንድ ነርቭን ከሚያጠቁ ኢንፌክሽንና በጭንቀትና ሽብር የሚመጣ ናቸው። #ከልብ #ጋር #የተያያዙ #የደረት #ላይ #ህመሞች #ምክናየት • ወደልብ የሚሄድ ደም መቋረጥ • በሰውነት ውስጥ የኦክስጅን ፍላጎት ወደ ውስጣችን ከገባው አየር በላይ መሆን ወይም አለመመጣጠን • ወደ ልብ ደም የሚወስደው የደም ቱቦ መዘጋት • የልብ ክፍል ወይም ዙሪያ ላይ ጠባሳ ወይም ኢንፌክሽን መፈጠር እና • የተለያዩ የልብ ህመሞች ናቸው። #አስታውሱ1፡ የደረት ላይ ህመም ከልብ ችግር ጋር ተያያጅ ከሆነ የሚከተሉትን ምልክቶች በከፊል እናያለን። • ደረትን የመወጠርና በፍቶ የመያዝ ስሜት • የድካምና ጭንቅ የማለት ስሜት • የጀርባ፣ የመንጋጭላ እና የትከሻ አካባቢ ህመም • ቀለል ያለ እራስ ምታት • የትንፋሽ ማጠር • ማቅለሽለሽ • የሆድ ህመም • አየር ወደ ውጭ ሲወጣ የህመም ስሜት መኖርና • የመፍዘዝ ባህሪ በከፊል ይታያል። #አስታውሱ2: ያለው የደረት ህመም መገለጫ ደግሞ የሚከተሉት ከሆኑ ችግሩ ከልብ ችግር ጋር አይገናኝም ማለት ነው። • ከጀርባ ጀምሮ ወደፊት ለፊት የሚዛመት ህመም ካለ • ከበሉ ወይም ከዋጡ በሗላ የደረት ህመሙ ከጀመረ • የጨጒራ ችግር ካለ እና አፍ ላይ አሲድክ ጣዕም ካለ • የመዋጥ ችግር ያለበት ሰው ከሆነ • ቶሎ ቶሎ መተንፈስ ካለ • ሲስሉ ወይም በጥልቅ ሲተነፍሱ ህመሙ የሚባባስ ከሆነ • አቀማመጥ ወይም አተኛኘትን ሲቀይሩ ህመሙ ከተባባሰ ወይም ከቀነሰ • ቁርጥማት፣ ትኩሳት፣ ብርድ ብርድ ማለት፣ ሳል፣ በአፍንጫ የሚወጣ ፈሳሽ አብሮ ካለ ችግሩ የልብ አይደለም ማለት ነው። #የደረት_ላይ_ህመም_ከምግብ_እንሽርሽሪት_ አካል_ጋር_ሊያያዝ_ይችላል። ለምሳል • የሀሞት ጠጠር ካለ • የሀሞት ከረጢትና የቆሽት መቆጣት • ጨጒራ ቁስለት መኖር • አሲድ በጋዝ ወይም ትነት መልክ ወደ ጉሮሮ መመለስ • የመዋጥ ችግር መኖርና ሌሎችም ናቸው። #የደረት ላይ ችግር ካሳንባና የመተንፈሻ አካል ጋር የተያያዘ ከሆነ የሚከተሉት ሊሆኑ ይችላሉ። • የሳንባ ምች • ሳንባ ውስጥ ፈሳሽ ወይም ከመጠን በላም አየር መኖር • የአየር ቱቦ በቫይረስ መጠቃት • ብሮንከስ የሚባለው የአየር ቱቦ በቫይረስ ሲጠቃና ሲጨማደድ • ለረጅም ጊዜ የቆዩ የመተንፈሻ ላይ ችግር መኖርና ሌሎችም ናቸው። #የደረት ላይ ህመም በአካባቢው ወይም በደረት ላይ ከሚገኙ አጥንትና ጡንቻ ችግር የተነሳ ሊሆን ይችላል። ለምሳሌ፡ • የተሰበረ ወይም የተቀጠቀጠ የጎን አጥንት መኖር • በደረት አካባቢ በሚገኝ ወይም በሚያልፍ ነርቭ ላይ ጫና ካለ ወይም ጉዳት የደረሰበት አጥንት ነርቭ ተጭኖ ከሆነ • የቆሰለ ወይም የተሸነቆረ ጡንቻ ወይም ስጋ መኖር ዋና ዋናዎቹ ናቸው። #መፍትሔው #ምንድን #ነው? • ውድ የኢንፎ ሄልዝ ሴንተር ቤተሰቦች ከላይ እንዳያችሁት የደረት ላይ ህመም ምክናየት ዘርፈ-ብዙ ናቸው። መፍትሔውን ለማግኘት መጀመሪያ የችግሩን ምክናየት ላይቶ መዋቅ ያስፈልጋል። • ስለዚህ መፍትሔው በጤና ባለሙያ ታይቶ ችግሩን ለይቶ ማወቅና እንደ አስፈላጊነቱ ህክምና ማግኘት ነው። ስለሚከታተሉን እናመሰግናለን። በቅንነት ሸር እያደረጉ ለብዙዎች ቢያደርሱት መልካም ነው። #ቴሌግራም #ቻናላችን #ይሄ #ነው። ሊንኩን ተጭነው ቤተሰብ ይሁኑ። #ለጥያቄም ሆነ #ለበለጠ መረጃ ይጠቅመወታል። https://t.me/jossiale2022

  • አባት ወንድ ልጁን እንዴት ማሳደግ አለበት? ወንድ ልጅን ማሳደግ ገንዘብ መስጠት፣ ጥሩ ትምህርት ቤት ማስተማር፣ ስጦታዎችን መግዛት ወይም “ጠንካራ ሁን!” ማለት ብቻ አይደለም። አባት ልጁ ወደፊት ጥሩ ባል፣ ጥሩ አባት፣ ታማኝ ሰው እና ኃላፊነት የሚሰማው ዜጋ እንዲሆን ዛሬ ላይ ያስተምረዋል። ❤️ “እወድሃለሁ” በለው። ወንድ ልጅም የአባቱን ፍቅር መስማት ያስፈልገዋልና። 👂 አዳምጠው። ችግሩን ሲነግርህ ችላ አትበልበት፤ የሚሰማው እንዳለው አሳየው። 💪 ጠንካራ እንዲሆን አስተምረው፣ ግን ስሜቱን እንዲደብቅ አታስገድደው። ማልቀስ ድክመት አይደለም። 🤝 ሴቶችን ማክበርን ከአንተ ይማር። እናቱን እንዴት እንደምታከብር ልጅህ ያያል። በቃልህ እና በተግባርህ ምሳሌ ሁን። ልጅህ የምትነግረውን ብቻ ሳይሆን የምታደርገውንም ይማራል። ሥራን፣ ትምህርትን፣ ትህትናን፣ ታማኝነትን እና ኃላፊነትን አስተምረው። ከልጅህ ጋር ጊዜ አሳልፍ። ልጅ ከአባቱ የሚፈልገው አዲስ ስጦታ ብቻ አይደለም፤ አባቱን ነው የሚፈልገው። አባት ሆይ፣ ዛሬ የምታሳድገው ልጅ ነገ የራሱን ቤተሰብ ይመራል። ስለዚህ አንተ የምታሳየው ምሳሌ የእሱ የወደፊት ሕይወት ነው። ❤️

  • 12 авг.1 29314

    የCPD ስልጠና ETHIO MEDICAL CPD CENTER 🦠Antimicrobial Prevention & Control Training 📅 ቅዳሜ ነሐሴ 9/2018 ዓ.ም የሚጀምር 🎓 15 CEU Points 👩‍⚕️👨‍⚕️ ለሁሉም የጤና ባለሙያዎች 🏆 ይደውሉ ይመዝገቡ!!! ETHIO MEDICAL TRAINING AND CONSULTANCY PLC📞 0921785903 | 0932338485 https://t.me/jossiale2022

  • 10 авг.1 22131

    CPD TRAINING ANNOUNCEMENT ANTIMICROBIAL RESISTANCE PREVENTION AND CONTROL (AMR) TRAINING Starting Date Saturday August 15/2026 🎓 15 CEU Points Antimicrobial resistance is one of the most serious challenges facing modern healthcare. This training will help health professionals strengthen their knowledge and practical skills in appropriate antimicrobial use, prevention and control of resistance, antimicrobial stewardship, and patient safety. What You Will Gain ✅ Updated knowledge on AMR ✅ Understanding the causes and consequences of antimicrobial resistance ✅ Practical approaches to Antimicrobial Stewardship ✅ Strategies for preventing and controlling AMR ✅ Improved antimicrobial prescribing and patient safety ✅ 15 CEU points toward your professional development 👩‍⚕️👨‍⚕️ Who Should Attend? • Doctors • Pharmacists • Nurses • Health Officers • Laboratory Professionals • Midwives • Public Health Professionals & Other Healthcare Workers 🏆 Don't collect CEUs only — build clinical excellence. ETHIO MEDICAL TRAINING AND CONSULTANCY PLC Beyond Certificate, Building Clinical Excellence. 📍 Gotera, Rami Building, 2nd Floor, Addis Ababa 📞 Register now and secure your place 0921785903 0932338485 https://t.me/jossiale2022

  • 6 авг.1 84598

    ስኳር በሽታ (Diabetes Mellitus) "ቀድሞ ማወቅ ሕይወትን ያድናል!" ስኳር በሽታ በዓለም ላይ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ሰዎችን የሚያጠቃ ሥር የሰደደ በሽታ ነው። ብዙ ሰዎች ምንም ምልክት ሳይታይባቸው ለብዙ ዓመታት ከዚህ በሽታ ጋር ሊኖሩ ይችላሉ። በዚህ ጊዜ ግን በልብ፣ በኩላሊት፣ በዓይን እና በነርቮች ላይ ቀስ በቀስ ጉዳት ሊያደርስ ይችላል። ስለዚህ ስኳር በሽታ ብዙ ጊዜ "ዝምተኛው ገዳይ" ተብሎ ይጠራል። ስኳር በሽታ ምንድን ነው? ሰውነታችን ከምግብ የሚገኘውን ስኳር (ግሉኮስ) ለኃይል ይጠቀማል። ይህን ስኳር ወደ ሴሎች ለማስገባት ኢንሱሊን የተባለ ሆርሞን ያስፈልጋል። ኢንሱሊን በበቂ ካልተመረተ ወይም ሰውነት በአግባቡ ካልተጠቀመበት፣ ስኳር በደም ውስጥ ይከማቻል፤ ይህም ስኳር በሽታ ይባላል። የስኳር በሽታ ምልክቶች - ብዙ መጠማት - ብዙ ሽንት መሽናት - ሁልጊዜ ድካም ካለ - የዓይን ብዥታ መኖር - ያለምክንያት ክብደት መቀነስ - ቁስል ዘግይቶ መዳን - ተደጋጋሚ ኢንፌክሽኖች ነገር ግን ምልክት ባይኖርም ስኳር በሽታ ሊኖር ይችላል። ስለዚህ መደበኛ ምርመራ በጣም አስፈላጊ ነው። እነማን ይበልጥ ተጋላጭ ናቸው? 👉 በቤተሰብ ውስጥ የስኳር በሽታ ካለ 👉 ከመጠን በላይ ክብደት ካለ 👉 ብየአካል እንቅስቃሴ የማያደርግ 👉 ከፍተኛ የደም ግፊት ያለው 👉 ጤናማ ያልሆነ አመጋገብ የሚከተል 👉 እድሜው 40 ዓመት በላይ የሆነ (በተለይ ከሌሎች የአደጋ ምክንያቶች ጋር) ስኳር በሽታ ምን ችግር ያመጣል? መቆጣጠር ካልተቻለ የልብ ድካም፣ ስትሮክ፣ የኩላሊት ሥራ መበላሸት፣ የዓይን እይታ መቀነስ ወይም ዓይነ ስውርነት፣ የነርቭ ጉዳት እና የእግር ቁስል ሊያስከትል ይችላል። ስኳር በሽታን እንዴት እንከላከል? 👉 ጤናማ ምግብ ይመገቡ። 👉 አትክልትና ፍራፍሬ ያብዙ። 👉 በየቀኑ ቢያንስ 30 ደቂቃ እንቅስቃሴ ያድርጉ። 👉 መደበኛ ክብደትዎን ይጠብቁ👉 ሲጋራን ያቁሙ። 👉 በየጊዜው የደም ስኳርዎን ይመርምሩ። የተሳሳቱ እምነቶች ❌ "ብዙ ስኳር ብቻ የሚበላ ሰው ነው የሚያዘው።" — አይደለም። የቤተሰብ ታሪክ፣ ውፍረት፣ የእንቅስቃሴ እጥረት እና ሌሎች ምክንያቶችም አስተዋጽኦ አላቸው። ❌ "መድኃኒት ከጀመርኩ ለዘላለም አልተውም።" — የሕክምና ዕቅድዎን የሚወስነው የጤና ባለሙያዎ ነው፤ መድኃኒት በራስዎ አያቁሙ። ጠቃሚ መልእክት የስኳር በሽታን ቀድሞ ማወቅ እና በትክክል መቆጣጠር ጤናማና ረጅም ሕይወትን ለመኖር ያስችላል። ዛሬ ነገ ሳይሉ የደም ስኳርዎን ይመርምሩ፣ ጤናዎን ይጠብቁ፣ ቤተሰብዎንም ያስተምሩ። "ቀድሞ መመርመር ሕይወትን ያድናል!" https://t.me/jossiale2022 📢 Ethio Medical Training & Consultancy PLC – ትክክለኛ የጤና መረጃ ለሁሉም! https://t.me/jossiale2022

  • 6 авг.1 77013

    የሥራ ቦታዎን ደህንነቱ የተጠበቀ፣ የጤና አገልግሎትዎን ጥራቱን የጠበቀ ያድርጉ! Infection Prevention and Control (IPC) እና Occupational Health and Safety (OHS) ሥልጠና በመውሰድ፦ ✅ የኢንፌክሽን ስርጭትን ይከላከሉ። ✅ የሥራ ቦታ ደህንነትን ያጠንክሩ። ✅ የታካሚዎችንና የሰራተኞችን ደህንነት ያረጋግጡ። ✅ በእውቀትና በተግባራዊ ክህሎት የጎለበቱ ባለሙያዎች ያፍሩ። CPD Accredited 👉15 CEU 📞 0921 785 903 📞 0932 338 485 Ethio Medical Training and Consultancy PLC Beyond Certificates… Building Clinical Excellence. አሰልጣኞቻችን ሀገር አቀፍ እውቅና ያላቸው የማሰልጠኛ ሞጁል አዘጋጆች ናቸው። 👇👇👇👇👇 https://t.me/jossiale2022 ሁልጌዜ ምዝገባ አለ።

  • 5 авг.1 560710

    ራስ ምታት (Headache) ሁሉም ሰው ሊያውቀው የሚገባ መረጃ ራስ ምታት ብዙ ሰዎች በሕይወታቸው ቢያንስ አንድ ጊዜ የሚያጋጥማቸው የጤና ችግር ነው። በአብዛኛው ከባድ ችግርን አያመለክትም፤ ነገር ግን አንዳንድ ጊዜ አስቸኳይ ሕክምና የሚፈልግ ምልክት ሊሆን ይችላል። የራስ ምታት የተለመዱ ምክንያቶች • ጭንቀት (Stress) • እንቅልፍ እጥረት • ድርቀት (ውሃ አለመጠጣት) • ረሃብ ወይም ምግብ መዝለል • የዓይን ችግር • ሳይነስ ኢንፌክሽን • ከፍተኛ የደም ግፊት (በአንዳንድ ሰዎች) የሚከተሉትን ልምዶች ማዳበር ራስ ምታትን ይቀንሳል። ✅ በቂ ውሃ ይጠጡ። ✅ በቂ እንቅልፍ ይተኙ። ✅ ምግብ አይዝለሉ። ✅ ጭንቀትን ይቀንሱ። ✅ አስፈላጊ ከሆነ በባለሙያ ምክር ቀላል የህመም ማስታገሻ ይውሰዱ። 🚨 ከተች ያሉት ምልክቶች ከታዩ ወዲያውኑ ወደ ህክም ይሂዱ 🔴 በድንገት እጅግ ከባድ የሆነ ራስ ምታት 🔴 ከንግግር መታወክ፣ የእጅ ወይም የእግር ድካም ጋር ከተያያዘ 🔴 ከከፍተኛ ትኩሳትና አንገት መደንደን ጋር ከመጣ 🔴 ከጭንቅላት ጉዳት በኋላ የተጀመረ 🔴 ተደጋጋሚ ወይም ቀን ከቀን እየባሰ የሚሄድ ጤናዎን አይዘንጉ፤ ራስ ምታት ቀላል ሊሆን ይችላል፣ ነገር ግን አንዳንድ ጊዜ ከባድ በሽታን የሚያመለክት ሊሆን ይችላል። ምልክቶቹ ከተባባሱ ወደ ጤና ተቋም ይሂዱ። 📢 Ethio Medical Training & Consultancy PLC – ትክክለኛ የጤና መረጃ ለሁሉም! https://t.me/jossiale2022

  • 3 авг.1 7411

    видео или голосовое, без подписи

  • 3 авг.1 69921

    ETHIO MEDICAL CPD CENTER EMERGENCY MEDICINE TRAINING 📅 ነገ 27/11/2018 ዓ.ም. ይጀምራል! CPD Accredited Training ✅ 15 CEU 📍 ቦታዎን አሁኑኑ ያስይዙ! 📞 0921 785 903 📞 0932 338 485 https://t.me/jossiale2022

  • 3 авг.1 58179

    " #ልጄን_ብርድ_መታት" .... ብርድ የሚባል በሽታ አለ ወይስ የለም? - ዶ/ር መሐመድ በሽር የህፃናት ሐኪም . ብዙውን ጊዜ በስራ ገበታ ጨቅላ ሕፃናት ለህክምና ሲመጡ ተሸፋፍነው ሲሆን ለምርመራም እናት ልብስን ገልጣ ማሳየት ይከብዳታል ምክንያት ብርድ እንዳይመታት ወይም እንዳይመታው ይባላል። . ልጆችም ከረጅም የቤት ውስጥ ቆይታ ወደ ትምሀርት ገበታቸው እየተመለሱ እንደመሆኑ ብዙ የሚያስሉ ሕፃናት መመልከት የተለመደ እንደመሆኑ ይህን እንደ መነሻ አሳብ ለዚህ ፅሁፍ በመውሰድ እስኪ ስለ ልጆች የሳምባ ምች (ኒሞኒያ) ትንሽ ጀባ ልበላችሁ . - እናቶች ልጄን  ብርድ  መታው የሚሉት ነገር እሳ? . ሳምባ ምች (ኒሞኒያ) ማለት የሳንምባችን የታችኛው እና የመጨረሻው ክፍል በኢንፌክሽን ወይም በኬሚካል ሲጠቃ ሳንባችን ሲቆጣ እና ሲታመም የሚከሰት በሽታ ነው። . ሳምባችን ለሰውነታችን ኦክስጅን የሚባለውን ጠቃሚ አየር የምናስገባበት እና ካርቦንዳይ ኦክሳይድ የሚባለውን የተቃጠለ አየር የሚናስወግድበት አካላችን እንደመሆኑ ይህ የሰውነታችን አካል በተለያዩ ነገሮች የመጎዳት እድል ሲገጥመው ይህ ተግባር ይስተጓጉላል። ከነዚ ውስጥ ዋነኛው ደሞ ኒሞኒያ የሚባለው በሽታ ነው። . ይህ የማይታይ ጀርም ወደ  ሳምባችን በሚገቡ ጊዜ ሳንባችን ዉስጥ ያሉ ህዋሳት በከፍተኛ መጠን ስለሚቆጡ አየር የሚቀያየርበት የሳምባ ቅንጣት አካላት (Alveolus) በፈሳሽ ነገር ይሞላሉ በዚህም ምክንያት ጠቃሚውን ኦክስጅን የማስገባት እና ጠቃሚ ያልሆነውን ካርበን ኦክሳይድ የማስወጣት ኢደትን ስለሚገታ ሰውነታችን በቂ የሆነ ኦክስጅን እንዳያገኝ ያደርገዋል። ይህም የኦክስጅን እጥረት በወቅቱ ካልታከመ እስከ ህይወት ህልፈት ሊያስከትል ይችላሉ ። . እንደ ዓለም የጤና ድርጅት (WHO) መረጃ መሰረት በ2017 ብቻ በዓለም ላይ 808,694 እድሜያቸው ከ 5 ዓመት በታች ያሉ ህፃናት በሳምባ ምች ምክንያት ህይወታቸውን አተዋል:: ይህም ከአጠቃላይ የልጆች ሞት 15% ይይዛል:: እንዲሁም በአገራችን እድሜያቸው ከ 5 ዓመት በታች ካሉ ህፃናት ገዳይ በሽታዎች የሳምባ ምች ዋነኛው ገዳይ በሽታ እንደሆነ ያውቃሉን 😱👌። . - የሳምባ ምች መንስኤው ምንድነው? . ይህ በሽታ ብዙ ጊዜ በአይን በማይታዩ የበሽታ አምጭ ጀርሞች ማለትም በቫይረስ ፣ በባክቴርያ ፣ በፕሮቶዝዋ አልፎ አልፎም በፓራሳይት አማካኝነት ሊመጣ ይቻላል:: ከነዝህም ዉስጥ በአብዛኞቹ ጀርሞች በሳል ወይም በንጥሻ ወቅት በትንፋሽ የሚተላለፉ ናቸው :: ከነዚህ በሽታ አምጭ ጀርሞች በተጨማሪም ኒሞኒያ በተለያዩ ኬሚካሎችም ሊመጣ ይቻላል:: ለምሳሌ የጨጓራ አሲድ በድንገት ወደ ሳምባ ሲገባ ልጆች በድንገት ኬሚካሊ ሲጠጡ ለምሳሌ ኬሮሲን ወዘተ ሳንባ ውስጥ የመግባት እድል ሲያገኙ ኒሞኒያ ሊያስከትሉ  ይችላል:: ከ5 ዓመት በታች ያሉ ልጆች ላይ የሳምባ ምች ብዙ ጊዜ መንስኤው ቫይረሶች ሲሆኑ የሚጀምረውም በጉንፋን  መሰል ምልክቶች ነው። . - የትኞቹ ልጆች ናቸው በዋነኛነት ለሳንባ ምች የሚጠቁት? . 1. የላይኛው የትንፋሽ አካላት ኢንፌክሽን ለምሳሌ ጉፋን፤ የቶንሲል ኢንፌክሽን እና የመሳሰሉት ሲይዛቸው . 2. ቤት ዉስጥ የሚጨሱ ማንኛዉም የጭስ አይነቶች ለምሳሌ የሲጋራ እጣን ሺሻ  የከሰል እና የእንጨት ጭሶች ዋነኛዎቹ ናቸው። በሀገራችን በከፍተኛ መጠን ብዙ ህፃናትን ለሳምባ ምች እያጋለጣቸው ይገኛል:: . 3. ዝቅተኛ የበሽታ መከላከል አቅም ያላቸው (በምግብ እጥረት ወይም በተለያዩ በሽታዎች ምክንያት ለምሳሌ HIV, Cancer etc) . 4. በጣም ተጠጋግቶ መኖር እና በቂ የሆነ የአየር ዝውውር በሌለበት ቤት እና አካባቢ መኖር . 5. የሳምባ የተፈጥሮ ችግሮች . 6. የቫይታሚን ዲ እጥረት (ሪኬትስ)፦ በተለይ ፀሐይ በደምብ ያልሞቁ ህፃናት ለሳምባ ምች ተጋላጭ ናቸው:: . - በሳንባ ምች የተጠቃ ልጅ ምን አይነት ምልክቶቹች ያሳያል? ★ ቶሎ ቶሎ መተንፈስ ★ ትንፋሽ ማጠር እና ለመተፈስ መቸገረ ★ ትኩሳት ★ ማቃሰት ★ ትውከት ★ ማስመለስ ★ የምግብ ፍላጎት መቀነስ ★ የደረት ውጋት ወይም ህመም ★ ሲተነፍሱ የታችኛው ደረት ክፍል ወደ ዉስጥ ግብት ግብት ማለት ዋና ዋናዎቹ  ናቸው:: . ልብ ይበሉ ልጆት ላይ እነዚህ የተጠቀሱት ምልክቶችን ከተመለከቱ ባፋጣኝ ወደ ጤና ተቋም በመውሰድ ማሳከም ይኖርቦታል :: . - የሳምባ ምች መከላከያ መንገዶች ምንድናቸው? ★ ክትባት በወቅቱ ማስከተብ ★ ቤት ዉስጥ ማንኛዉም ጭስ አለማጨስ ★ ቤት ዉስጥ በቂ የአየር ዝውውር እንዲሮር ያድርጉ . ★ ልጅዎን የተመጣጠነ ምግብ ይመግቡ ★ እስከ 6 ወር  የእናት ጡት ወተት ብቻ መስጠት ★ ልጆች የፀሀይ ብርሃን በበቂ ሁኔታ እንዲያገኙ ያድርጉ . ★ ልጆችን ጉንፋን ከያዛቸዉ ሰዎች ወይም ልጆች በተቻለ መጠን ያርቁ . በመጨረሻም ብርድ የሚባል በሽታ አለ ወይስ የለም? ለሚለው ጥያቄ በአጭሩ በዘመናዊ ሕክምና ዉስጥ ብርድ የሚባል ነገር በልምድ ይህንኑ ነው ! አንዳንድ ሰዎች ብርድ የሚለውን ቃል ከሳምባ ምች (ኒሞኒያ) ጋር ሲያምታቱ ይታያል ይሄ ትክክል አይደለም ቀዝቃዛ አየር የሳምባ ምች አያመጣም ! በርግጥ ቀዝቃዛ አየር ሊያነሳሳቸው የሚችሉ በሽታዎች ይኖራሉ ለምሳሌ የአፍንጫ ወይም የሳይነስ አለርጂ አስም  ወዘተ የመሳሰሉት :: ለማንኛዉም ማህበረሰቡ ብርድ የሚለውን ቃል ምን ለማለት ፈልጎ እንደሆነ ማወቁ አይከፋም ። . #አንብበው #ሲጨርሱ #ጠቃሚ #ነው #ብለው #ካሰቡ #በቀናነት #ለወዳጅ #ዘመድዎ #ሼር #ያድርጉት ። . መልካሙን ሁሉ ተመኘው ❤❤🙏 https://t.me/jossiale2022

  • 27 июл.57321из jossiale2022

    ለሁሉም የጤና ባለሙያዎች! 🎓 CPD Training በETHIO MEDICAL CPD CENTER በሚከተሉት ክልሎች እና ከተሞች የCPD ስልጠናዎችን እየሰጠን ነው፦ ✅ አዲስ አበባ ✅ ኦሮሚያ ክልል ✅ አማራ ክልል ✅ ሲዳማ ክልል ✅ ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ✅ አፋር ክልል ✅ ሶማሌ ክልል 👨‍⚕️ ለዶክተሮች፣ ለነርሶች፣ ለፋርማሲስቶች፣ ለላቦራቶሪ ባለሙያዎች፣ ለሚድዋይፎች እና ለሁሉም የጤና ባለሙያዎች። 📞 ለምዝገባና ለተጨማሪ መረጃ 📱 0921 785 903 📱 0932 338 485 ETHIO MEDICAL CPD CENTER "Learning Today, Saving Lives Tomorrow." https://t.me/jossiale2022

  • 25 июл.68952из jossiale2022

    ለሁሉም የጤና ባለሙያዎች! 🎓 CPD Training በETHIO MEDICAL CPD CENTER በሚከተሉት ክልሎች እና ከተሞች የCPD ስልጠናዎችን እየሰጠን ነው፦ ✅ አዲስ አበባ ✅ ኦሮሚያ ክልል ✅ አማራ ክልል ✅ ሲዳማ ክልል ✅ ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ✅ አፋር ክልል ✅ ሶማሌ ክልል 👨‍⚕️ ለዶክተሮች፣ ለነርሶች፣ ለፋርማሲስቶች፣ ለላቦራቶሪ ባለሙያዎች፣ ለሚድዋይፎች እና ለሁሉም የጤና ባለሙያዎች። 📞 ለምዝገባና ለተጨማሪ መረጃ 📱 0921 785 903 📱 0932 338 485 ETHIO MEDICAL CPD CENTER "Learning Today, Saving Lives Tomorrow." https://t.me/jossiale2022

  • 22 июл.2 78522

    🦠 ETHIO MEDICAL CPD TRAINING CENTER Powered by ETHIO MEDICAL TRAINING AND CONSULTANCY PLC 🦠 INFECTION PREVENTION AND CONTROL (IPC) TRAINING Starting Date: Saturday, 25/07/2026 CPD Credit: 15 CEU ለሁሉም የጤና ባለሙያዎች በስልጠናው የሚካተቱ፦ ✅ Standard Precautions ✅ Hand Hygiene Best Practices ✅ Personal Protective Equipment (PPE) ✅ Healthcare-Associated Infection Prevention ✅ Patient Safety and Quality of Care 📞 ለምዝገባ: 0921 785 903 0932 338 485 በEthio Medical CPD Training Center የምንሰጠው ስልጠና የCEU ማሟያ ብቻ አይደለም፤ የጤና ባለሙያዎችን እውቀት፣ ተግባራዊ ክህሎት እና የታካሚ እንክብካቤ ጥራት ለማሻሻል የተዘጋጀ ነው። ETHIO MEDICAL CPD TRAINING CENTER Professional Training • Practical Skills • Better Patient Care Beyond Certificate, Building Clinical Excellence ከሰርተፍኬት በላይ፣ የስራ ላይ ብቃትን እንገነባለን። https://t.me/jossiale2022

  • 17 июл.84932из jossiale2022

    ለሁሉም የጤና ባለሙያዎች! 🎓 CPD Training በETHIO MEDICAL CPD CENTER በሚከተሉት ክልሎች እና ከተሞች የCPD ስልጠናዎችን እየሰጠን ነው፦ ✅ አዲስ አበባ ✅ ኦሮሚያ ክልል ✅ አማራ ክልል ✅ ሲዳማ ክልል ✅ ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ✅ አፋር ክልል ✅ ሶማሌ ክልል 👨‍⚕️ ለዶክተሮች፣ ለነርሶች፣ ለፋርማሲስቶች፣ ለላቦራቶሪ ባለሙያዎች፣ ለሚድዋይፎች እና ለሁሉም የጤና ባለሙያዎች። 📞 ለምዝገባና ለተጨማሪ መረጃ 📱 0921 785 903 📱 0932 338 485 ETHIO MEDICAL CPD CENTER "Learning Today, Saving Lives Tomorrow." https://t.me/jossiale2022

  • 15 июл.2 117103

    🌹 ሙሉ በሙሉ እየራሰ በ1 ወይም 2 ሰአት ውስጥ አንድ ሞዴስ የቀየሩ እንደሆነ 🌹 ከፍተኛ መጠን ያለው ደም (የረጋ ደም) የፈሰሰ እንደሆነ ሲሆን #የወር_አበባ_ደም_መብዛት_አደገኛ_ሊሆን_የሚችለው 🦚 በ 2 ሰዓታት ውስጥ 4 ወይም ከዚያ በላይ ሙሉ በሙሉ የራሰ ሞዴስ ከቀየሩ ሃኪምዎን ያማክሩ ወይም ወደ ድንገተኛ ክፍል ይሂዱ። 🦚ነፍሰ ጡር ከሆኑና ደም ከፈሰሰም ድንገተኛ ነው። #ወደ_ህክምና_ተቋም_መሄድ_ያሸለብኝ_መቸ_ነው? 📌 ነፍሰጡር ነኝ ወይም ልሆን እችላለሁ ብለው ካሰቡ 📌የወር አበባዎ ከ 8 ቀናት በላይ የሚቆይ ከሆነ 📌 ሙሉ በሙሉ እየራሰ በ1 ወይም 2 ሰአት ውስጥ አንድ ሞዴስ የቀየሩ እንደሆነ 📌 ብዙ ደም እየፈሰሰዎት ስለሆነ ሁለት ሞዴሶች ደራርበው መጠቀም ካስፈለግዎት 📌 ለሊት ተነስተው ሞዴስ መቀየር ካስፈለግዎት 📌 ከ 1 ኢንች የበለጠ የረጋ ደም የፈሰሰ እንደሆነ 📌 የወር አበባ ከጨረሱ በኋላ በድጋሚ ያለጊዜው የወር አበባ ካዩ 📌 መጸነስ እየፈለጉ ካልቻሉ 📌 ቢያንስ ለአንድ አመት የወር አበባ ሳያዩ ከቆዩ በኋላ ደም ከፈሰሰ ፤ ማለትም ካረጡ በኋላ ደም ካዩ 📌 ከላይ የተጠቀሱትን ምልክቶች ከታዩ እና የደም ማነስ ካስከተለብዎት #የወር_አበባ_ደም_መብዛት_ህክምናው_ምንድን_ነው? ህክምናው እንደ መንስኤው ይለያያል። አብዛኛውን ጊዜ ሕክምና ላያስፈልግ ይችላል።ካስፈለገ ግን ህክምናዎቹ የሚከተሉትን ሊያካትቱ ይችላሉ። 📌 ሆርሞኖች ያላቸው የወሊድ መቆጣጠሪያ ዘዴዎች 📌 የደም መቅጠን የሚቀንሱ መድሃኒቶች 📌 እብጠት የሚቀንሱ መድሃኒቶች 📌 ፕሮጄስቲን የተባለ ሆርሞን ያላቸው መድሃኒቶች 📌 ኦቫሪዎችን ለአጭር ጊዜ ሥራቸውን እንዲያቆሙ የሚያደርጉ መድሃኒቶች 📌 በቀዶ-ህክምና ፋይብሮይዶች ወይም ሌሎች እባጮችን ማስወገድ ናቸው። ሸር ቢያደርጉ ሌሎች ይጠቀሙበታል። ቻናሉን join ያድርጉ። https://t.me/jossiale2022

  • 15 июл.1 0222из jossiale2022

    #በወር_አበባ_ጊዜ_ብዙ_ደም_እንድፈስ_የሚያደርጉ_ምክንያቶች 💃ከኦቫሪዎቹ አንዱ ለአንድ ወር ወይም ከዚያም በላይ እንቁላል ማዘጋጀት ካቆመ 💃የማህጸን እጢ (fibroids) 💃 በደም መርጋት ችግር 💃 አንዳንድ የወሊድ መቆጣጠሪያዎች ወይም ደም ለማቅጠን የሚወሰዱ መድሃኒቶች የጎን ተፅዕኖዎች 💃 ከየታይሮይድ ዕጢ ጋር (ሆርሞኖችን የሚያመነጭ ዕጢ) ጋር የተያያዙ ችግሮች 💃 የማሕጸን ካንሰር 🦋🦋🦋🦋🦋🦋🦋🦋🦋🦋🦋🦋🦋 ትክክለኛው የወር አበባ ከ3 - 7 ቀናት ይቆያል። #በወር_አበባ_ጊዜ_የበዛ_ደም_እንደሚፈስ_የሚጠቁሙን_ምልክቶች_ደግሞ ከታች👇👇👇

INFO HEALTH CENTER — tgindex