Red-8
Статистика- Последний пост
- 12 авг.
- Последнее чтение
- 15 авг.
- Постов за неделю
- 3
- Всего постов
- 20
- Тип
- открытый
- Язык
- und
- Категория
- Книги (по похожим)
- В каталоге с
- 14 авг.
- 1/24сутки в ленте
- 487
- 1/48двое суток
- 558
- 1/72трое суток
- 601
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
⁹ Sketch by A.I
⁸
⁷
⁶ ከጠላቶቹ ጋር ሊፋለም ጠመንጃውን ወልውሎ፣ መላ ፍለጋ ዐዋቂ ዘንድ ጎራ አለ። “ምን ፈለክ?” ቢለው፣ “ጥይት የማያስመታ ክታብ ስራልኝ” “ምን ትከፍላለህ?” “አሁን ምንም የለኝ፤ በህይወት ስመለስ ያልከኝን እከፍላለሁ” “አይ አይ...” አለ ዐዋቂው “ይህማ ጥርጣሬን ለልብ ማስተማር ነው። አሁኑኑ ክፈል”። “ምን ልክፈል?” “ጠመንጃህን ክፈለኝ” ተፋላሚው እያቅማማ ተስማማ። ጠመንጃውን አስረከበ፤ በምትኩ በአንገቱ ጥይት የማያስመታው ክታብ ታሰረለት። ባዶ እጁን ጠላቶቹ ፊት ሄዶ ተገተረ። እንደዶፍ ከዘነበበት ጥይት ዘጠኙ ሰውነቱን በሳስተው መሬት ጣሉት። እንደእድል ሆኖ ሁነኛ ቦታ አልተመታ ኖሮ ከሞት ተንጠልጥሎ ተረፈ። ጠላቶቹ የሞተ መስሏቸው ጥለውት ቢሄዱ፣ ለነፍሱ ያደረ መነኩሴ አግኝቶ ደጋግፎ ወደማደሪያው ወስዶ አስታመመው። ተጣጥሮ ተረፈ። ሻል ሲለው የማይላወሱ እጆቹን አንከርፍፎ፣ የደረቁ እግሮቹን እያንፏቀቀ...የግዱን አዋቂው ዘንድ ሄደ። እንደደረሰ አዋቂውን ወቀሰ። “ምነዋ? ምነዋ ጥይት አይመታህም አልከኝ?” ምነው አታለልከኝ?” ዐዋቂው መለሰ “አትተርፍም ብዬ...፣ ካንተ ቀድሞ እንዳሰርኩላቸው ሰዎች አንተም ተርፈህ አትወቅሰኝም ብዬ... ” አዬዬ... ከነፍሱ በልጦበት፡ ለድል መጓጓቱ ውሃ ነው ስላሉት ፡ የሚዘል ከእሳቱ ይሄ ሁሉ ምስኪን ፡ ሲጣደፍ ለሞቱ ተርፎ የሚጠይቅ ፡ የለም እያለ ነው፡ ነብዩ መብዛቱ። - red-8 -
⁵
⁴
³
²
¹
red-8
አያቴ አደራ ሰጥታኝ የሚያልፍ ዝናብ እንዳይመታኝ፤ ለሚቀር አውርቼ እንዳልቀር ፣ ለሚሞት ህይወት እንዳልሰጥ ፣ ፀጥ! የሚያልፈው አፌን ሳይከፍተው ዝግ ዝም እንድል እንድተው፤ አያቴ አደራ ብላኝ ተባይ ቃል አፌን ቢበላኝ ፣ መተንፈስ ሁሉ እስኪያቅተኝ ምላሴ ሲተናነቀኝ ምላሼ ሲተናንቀኝ ፣ ታግዬ ስንቱን ዝም አልኩት አይቼ ስንቱን አለፍኩት። ዙሪያዬ የነገር እቁብ ቆጥረዋት ምላሴን ከቁብ ፣ ጣል ቢሉኝ ቃል ካንደበቴ አደራ ይዞኝ ያ'ያቴ ፣ አቋም አቅሜን ደብቄ ስንቱን ያለፍኩት ታምቄ ፣ ምስኪን... ራሴን ባለማወቄ! የሚያልፈው ዝናብ ሳይመታኝ ለማለፍ ዙሪያዬን ስቃኝ ፣ ባየሁት ቃሌ እየቃጣ ስውጠው ፈርቼ ጣጣ ፣ ሳምቀው ኖሬ ሳፍነው ምስኪን... ለካስ እኔው ነኝ የማልፈው!
«...ደሞም የኢጣልያን ፋሽሽት አምስት አመት ኢትዮጵያን ይዘውት በነበረው ጊዜ ውስጥ በያንዳንድ ኢትዮጵያን ሰዎች ላይ የዘሩት አሳባቸውንም መዘንጋት አይገባም፡፡ ዛሬ ለኛ በጣም የሚጐለንና የሚጐዳን... የሚጠቅመው ነገር ሁሉ ባገራችን እያለ፣ ዕውቀትና የመተባበር የሥራ ትጋት በማነሱ ጠቃሚው የሆነው ሁሉ ሊጠቅመን ሊረዳን ባለመቻሉ፤ በኢትዮጵያ ሕዝብ ላይ ድህነትና ችግር ሰልጥኖ በመታየቱ ነው፡፡ አንዳንድ ያሜሪክ ሰዎች እዚያ ሄደው ተመልሰው የመጡ በሲኔማና በፎተግራፍም ላይ እያነሱ የሕዝቡን ድህነት፤ የንጽህናን አለመኖር፣ የበሽታውን ብዛት ያሳያሉ፡፡ ይኸውም ሥራን ቸል የማለታችን ሁናቴን ሁሉ የሚያመለክት ነው፡፡ እጅግ የሚያሳፍርና የሚያስደንቀን ሆኖአል፡፡ አንዳንድም እንኳን አቅድ ያለው ሥራ የሚታየው የውጭ አገር ሰዎች የያዙትና ያሉበት ነው፡፡ ዋና ነገር በጣም የሚያሳስብ ዛሬ በመተባበር ዕውቀትና ሥራ እየበዛ ባቋራጭ ላንድነት ሕዝብን ጠቃሚ የሆነው ነገር ሁሉ እየተደራጀ ቶሎ ቶሎ እየተሠራ እንዲጨበጥ፣ እንዲገኝ ማድረግ ብቻ ነው፡፡እንደዚህ ያለውም የንቃት፣ የትጋት የዕውቀት ሥራ የራስን ወገንም ጠቅሞ፣ የውጭንም ጠላት የሚያሳፍር ይሆናል፡፡ ... » ራስ እምሩ ኃ/ስላሴ ካየሁት ከማስታውሰው (ከራስ እምሩ ኃይለ ሥላሴ ለአፄ ኃይለ ሥላሴ የተላኩ ደብዳቤዎች ገ. 309 ) ክብር ለዲፕሎማሲ አርበኞቻችን ♥ #የድልበዓል #ሚያዚያ28
«....በዚህ ጊዜ ጃንሆይ ጄኔቭ ነበሩ። ኢትዮጵያ አለች? የለችም? ተብሎ ታላቅ ክርክር ተደርጐ፣ ለጊዜው አለች ተብሎ ለኛ ተፈርዶልን ነበር፡፡ ጃንሆይን በስልክ አግኝቼ ጉዳዩን ተገለጥኩላቸው በኋላ... ጃንሆይ፤ “እሁን ያቀረብንህ ደስታችንን ልንገልጥልህ ነው፡፡ ኢትዮጵያ አለች ተብሎ ተፈረደልን አሏቸው... » የአክሊሉ ማስታወሻ (ገ.15) ጸሀፌ ትዕዛዝ አክሊሉ ኃ/ወልድ ክብር ለዲፕሎማሲ አርበኞቻችን ♥ #የድልበዓል #ሚያዚያ28
አዚም...
ሕማማት #5
ሕማማት #4
ሕማማት #3
ሕማማት #2
ሕማማት #1
"መሀረቤን?" ስትባሉ? “አላየንም!” የምትሉ ፡ ባትሆኑም፡ ልክ ናችሁ ¡ ያ'ይኑን እንባ ፡ መች አያችሁ ? ሰው ፊት ቆሞ ፡ ሆደ ቡቡ ከፍቶት ዓይኑ ፡ በመርጠቡ ጋርዶት ሊስቅ፡ በማሰቡ "የታል?" ብሎ፡ መሀረቡን በጨዋታ ፡ ሥም የልቡን የጠየቀው ፡ እንደ ወረት አጥቶስ ቢሆን ፡ እንባው ትኩረት? መሀረቤን? " ሲል ሲቃትት "ምን ሆኖ ነው?" እንደማለት የጣሩን ጥግ ፡ ለመፈለግ ካ'ይኖቹ ሥር ፡እዥ ለመጥረግ ከመሀረብ እንደመቅደም ለ"አላየንም " መሽቀዳደም!? ናፍቆስ ቢሆን ፡ ያይን ምንጩን? ጥፍጥሬውን፡ ጥቁር ነጩን ፈልቅቆ አይቶ ፡ ለቅሞ ስቃይ የሚያዳውር ፡ ሙሾ ፈታይ የሚያጣፋ ፡ ጥለት ከላይ ናፍቆስ ቢሆን አስተዛዛኝ እኔን የሚል፡ አደግዳጊ ? "መሀረቤን !"፡ ባይ ፈላጊ መስሎስ እንደሁ፡ ያስተጋባው? እንጂማ ሰው፡ ለጥል ከእንባው መች ያንሰዋል ፡አይበሉባው!? እጅግ አይቶ ሆዱ ባብቶ ጭልም ቀኑ በርጥብ ዓይኑ እንዳይታይ ፡ በማሰቡ ቢያስፈልገው ፡መሀረቡ "ያያችሁ" ሲል ፡ ሲያስተጋባ ባታዝኑለት ፡ባትጠርጉ እምባ “አላየንም!” በጭብጨባ? #red-8