ትምህርት ሚኒስቴር
Статистикаተጨማሪ መረጃዎችን በዌብሳይት - www.moe.gov.et በሊንክዲን - https://www.linkedin.com/company/ministry-of-education-ethiopia በትዊተር - http://twitter.com/fdremoe በፌስቡክ -https://www.facebook.com/fdremoe/ በቴሌግራም-https://t.me/timihert_minister ይከታተሉ።
- Последний пост
- 11 янв. 2025 г.
- Последнее чтение
- 14 авг.
- Постов за неделю
- 0
- Всего постов
- 27
- Тип
- открытый
- Язык
- английский
- Категория
- Образование (по похожим)
- В каталоге с
- 14 авг.
- 1/24сутки в ленте
- —
- 1/48двое суток
- —
- 1/72трое суток
- —
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
ማስታወቂያ የድህረምረቃ ፕሮግራሞች (NGAT) የመግቢያ ፈተና ለመውሰድ የተመዘጋባችሁ በሙሉ ይህንን ሊንክ ( https://ngat.ethernet.edu.et) በመጫን መረጃ ማግኘት ትችላላችሁ።
በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የሚካሄዱ የማህበረሰብ ጉድኝት ሥራዎች የህብረተሰቡን ፍላጎት መሠረት ያደረጉና ችግር ፈቺ ሊሆኑ እንደሚገባ ተጠቆመ፡። (ታህሳስ 26/04/2017 ዓ.ም) ከ47 ዩኒቨርስቲዎች ለተውጣጡ የማህበረሰብ ጉድኝት ዳይሬክተሮች ስልጠና ተሰጥቷል። በትምህርት ሚኒስቴር የምርምርና ማህበረሰብ ጉድኝት ጉዳዮች ተወካይ መሪ ስራ አስፈጻሚ ዶ/ር ሠራዊት ሃንዲሶ በስልጠናው ወቅት እንደገለጹት የማህበረሰብ ጉድኝት ስራዎች የህብረተሰቡን ፍላጎት መሠረት ያደረጉ ፣ ሙያዊ ፣ ሳይንሳዊና ችግሮችንም በአግባቡ የሚፈቱ ሊሆን ይገባል። ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በአካባቢያቸው ሰፊ የግንዛቤ ማስጨበጫና የንቅናቄ ስራዎችን በማከናወን በማህበረሰብ ጉድኝት ስራዎች የተቆጠረ ተከታታይነትና ወጥነት ያለው ውጤት እንዲመዘገብ በትጋት መስራት እንደሚጠበቅባቸውም ዶ/ር ሠራዊት ተናግረዋል፡፡ የማህበረሰብ ጉድኝት እና አገር በቀል እዉቀት ዴስክ ሃላፊ ወ/ሮ ሰላም አለሙ በበኩላቸው በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ከሚከናወኑ ቁልፍ ተልዕኮዎች መካከል የማህበረሰብ ጉድኝት ሥራ አንደኛው መሆኑን አመልክተው ተቋማቱ የአካባቢያቸውን ማህበረሰብ በማሳተፍ ችግሮች እንዲቀረፉ በትጋት መስራትና የማህበራዊ ሀላፊነታውን መወጣት እንደሚገባቸው ተናግረዋል። የስልጠናው ዓላማም አሳሳቢ እየሆኑ በመጡና ተለይተው በተቀመጡ ማህበራዊ ጉዳዮች ማለትም የአእምሮ ጤናና አደንዛዥ እጽ፣ የመንገድ ትራፊክ ደህንነት፣ ህገወጥ ስደትና የሰዎች ዝውውር ላይ የምርምርና ግብዛቤ ፈጠራ ስራ እንዲሰሩ ለማስቻል መሆኑን አመልክተዋል።። ተቋማቱ የትምህርት ጥራትን ለማሳደግ በአካባቢያቸው ያሉ ትምህርት ቤቶችን እንዲደግፉ ፣ የማህበረሰቡ ዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀም ግንዛቤ እንዲያሳዳድጉ እና እንዲያግዙ ማስቻልም ሌላኛው አላማ መሆኑን ጠቅሰዋል። በስልጠናው ላይ ሁሉም የመንግስት ዩኒቨርስቲዎች የማህበረሰብ ጉድኝት ዳይሬክተሮች የተሳተፉ ሲሆን ከትምህርት ሚኒስቴር ፤ ከጤና ሚኒስቴር ፣ከመንገድ ደህንትና መድህን ፈንድ ፣ ከስደተኖች ጉዳይ አስተዳደር እና ከጅማ ዩኒቨርስቲ በመጡ ባለሙያዎች ስልጠና ተሰጥቷቸዋል።
без подписи
без подписи
без подписи
без подписи
без подписи
без подписи
የትምህርት ሚኒስቴር ከICDL Africa እና kepler ጋር በጋራ ለመስራት የሚያስችለውን የመግባቢያ ስምምነት ሰነድ ተፈራረመ፡፡ -------------------------- // ---------------------------- (ታህሳስ 04/2017 ዓ.ም) ስምምነቱ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችና ምሩቃንን የዲጂታልና ሶፍት ሰኪል በማጎልበት ብቁና ተወዳዳሪ እንዲሆኑ ድጋፍ ለማድረግ ያለመ መሆኑ ተገልጿል። በሂደትም የዩኒቨርሲቲ እና ኢንዱስትሪ ትብብርን በማሳደግ ምሩቃን የተሻለ ክህሎት እና የስራ እድል የሚያገኙበትን ሁኔታዎች ለማመቻቸት እንደሚያስችል ተገልጿል፡፡ በትምህርት ሚኒስቴር የከፍተኛ ትምህርት ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ኮራ ጡሹኔ በፊርማ ስነ-ስርዓቱ ላይ ባደረጉት ንግግር የተፈረመው የመግባቢያ ስምምነት የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችና ምሩቃን ያለባቸውን የዲጂታልና ሶፍት ስኪል ክህሎት ክፍተቶች በመለየት ድጋፍ ለማድረግ የሚያስችል መሆኑን አብራርተዋል። ሚኒስተር ድኤታው አክለው እንደገለጹት የተፈረመው የመግባቢያ ስምምነት ሰነድ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ከኢንዱስትሪ ዘርፉ ጋር ያላቸውን ትስስርና ትብብር በተለየ መልኩ ለመደገፍ እገዛ እንደሚኖረውም አብራርተዋል። የአይሲዲኤል አፍሪካ ዋና ስራ አስፈጻሚ ሶሎንዥ ኢሚዩሊሳ በበኩላቸው ድርጅታቸው አፍሪካውያን ተገቢውን የዲጂታል ክህሎት የተላበሱ እንዲሆኑ ለማድረግ የሚሰራ ደርጅት መሆኑን በመጥቀስ ባለው አቅም ድጋፍ ለማድረግና አብሮ ለመስራት ፍላጎት ያለው መሆኑን ገልጸዋል። በኢትዮጵያ የኪፕለር ዳይሬክትር በበኩላቸው የተፈረመው የመግባቢያ ስምምነት ሰነድ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችና ምሩቃንን በመደገፍና በማሰልጠን ብቁና ተወዳዳሪ ዜጋ እንዲሆኑ ለማስቻል ያለመ መሆኑን ገልጸዋል።
без подписи
без подписи
የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ የጀኔራል ዋቁ ጉቱ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤትን ጎበኙ። ----------------------//-------------- (ታህሳስ 03 / 2017 ዓ.ም) የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ በኦሮሚያ ክልል ባሌ ዞን ሮቤ ከተማ የሚገኘውን ጀኔራል ዋቆ ጉቱ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤትን ጎብኝተዋል። በጉብኝታቸው ወቅትም ለተማሪዎች ባስተላለፉት መልዕክት ትምህርት የሚፈልገው ጥረት መሆኑን በመገንዘብ ሁሉም ተማሪዎች ጠንክረው መማርና ማጥናት ይኖርባቸዋል ብለዋል። በትምህርት ሥርዓቱ የፈተና አስተዳደር ስርዓቱን ማስተካከል ያስፈለገው የትምህርት ጥራት እንዲሻሻልና ሀገር የሚረከቡ እውነተኛ ዜጎችን ለማፍራት መሆኑን መገንዘብ ያስፈልጋል ብለዋል። ኩረጃ ለጊዜው የሚጠቅም ሊመስል ይችላል ነገር ግን ሄዶ ሄዶ ራስንም ሀገርንም ይጎዳል ያሉት ሚኒስትሩ ኩረጃን የሚጸየፉ በራሳቸው የሚሰሩና የሚተማመኑ ተማሪዎች መሆን እንዳለበቸውም አሳስበዋል። የትምህርት ጥራት እንዲሻሻልና ትውልዱ ይህችን ሀገር የመገንባት የወደፊት ሀላፊነቱን በታማኝነት እንዲወጣ የሚያስችሉ በርካታ ተግባራት በትምህርት ሴክተሩ እየተከናወኑ መሆኑንም አብራርዋል ። አክለውም ነገ ብቁ ሀገር ተረካቢ ብሎም በአለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ ሆኖ ለመገኘት ተማሪዎች ትምህርታቸው ላይ ብቻ አተኩረው እንዲማሩ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።
без подписи
በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የምግብ ሜኑ ተመሳሳይ እንዲሆን ተወሰነ። ------------------- // ------------------- ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የተውጣጡ ባለሙያዎች የዩኒቨርስቲ ተማሪዎችን የምግብ ሜኑ ተቀራራቢ እንዲሆን እየሰሩ ነው። ወቅታዊውን የምግብ ዋጋ መጨመር መነሻ በማድረግ ትምህርት ሚኒስቴር ጥናት ያደረገ ሲሆን በጥናቱ ውጤት መነሻነትም የከፍትኛ ትምህርት ተቋማት የምግብ በጀት በቀን ወደ 100 ብር ከፍ እንዲል ተደርጓል። በተደረገው የበጀት ማሻሻያ መሰረት በተቋማቱ የምግብ ሜኑ ተመሳሳይ እንዲሆን በባለሙያዎች ስራዎች እየተሰሩ እንደሚገኙ ተገልጿል። በትምህርት ሚኒስቴር የአስተዳደርና መሰረተ ልማት መሪ ስራ አስፈጻሚ ዶ/ር ሰለሞን አብርሃ ወቅታዊ የምግብ ዋጋ ንረትን ግምት ውስጥ በማስገባት የምግብ በጀት ማሰተካከያ መደረጉን ገልጸዋል። ዶ/ር ሰለሞን አክለውም በሀገራችን ባሉ ዩኒቨርስቲዎች ያለው የምግብ ሜኑ ተቀራራቢ እንዲሆን እየተሰራ መሆኑን ጠቅሰው በአዲሱ የበጀት ተመን መሰረት ለዩኒቨርስቲዎቹ ባላቸው ተማሪ ቁጥር ልክ ገንዘቡ እንደሚለቀቅላቸው ጠቁመዋል።
#የእንግሊዝኛ ቋንቋ ክህሎትን ለማሳደግ በትኩረት መስራት እንደሚገባ ተጠቆመ። (ሕዳር 28/ 2017 ዓ.ም) በትምህርት ሥርዓቱ የሚስተዋለውን የእንግሊዝኛ ቋንቋ ክህሎት ችግር ለመቅረፍ በሚቻልበ ጉዳይ ላይ ያተኮረ የምክክር መድረክ ተካሂዷል። በምክክር መድረኩ የተገኙት የአጠቃላይ ትምህርት ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክብርት ወ/ሮ አየለች እሸቴ በእንግሊዝኛ ቋንቋ ክህሎት ላይ የሚስተዋለውን ችግር መቅረፍ ካልተቻለ የሚፈለገውን የትምህርት ጥራት ማረጋገጥና አለም አቀፍ ተወዳደሪ የሆኑ ተማሪዎችን ማፍራት እንደማይቻል ጠቅሰው ሁሉም ባለድርሻ አካላት በትኩርት ሊሰሩ እንደሚገባ ጠቁመዋል። በተለይም ተማሪዎች የሚማሩትን ትምህርት በአግባቡ እንዲረዱና ውጤታማ እንዲሆኑ እንግሊዝኛ ቋንቋን የማንበብ፣ የመጻፍ፣ የመናገርና የማዳመጥ ክህሎታቸውን በሚገባ ማሳደግ ይገባል ብለዋል። የቀጣዩ ትውልድ እጣ ፈንታ የሚወሰነው አሁን በሚሰራው ሥራ መሆኑን በመገንዘብ የመማር ማስተማር ሥነ - ዘዴውን ማስተካከል እንዲሁም ተማሪዎች የእንግሊዝኛ ቋንቋ ክህሎታቸውን የሚያዳብሩበትን ምቹ ሁኔታ በትምህርት ቤቶች መፍጠር ይገባልም ብለዋል። በትምህርት ሚኒስቴር የመምህራንና የትምህርት ቤት አመራር ልማት መሪ ሥራ አስፈጻሚ ሙሉቀን ንጋቱ (ዶ/ር) በበኩላቸው የእንግሊዝኛ ቋንቋ በትምህርት ዓይነትና በማስተማሪያ ቋንቋነት በትምህርት ሥርዓቱ እየተሰጠ እንደሚገኝ ጠቅሰው ነገር ግን ከፍተኛ የእንግሊዝኛ ቋንቋ ክህሎት ችግር መኖሩን የሚያመላክቱ ጥናቶችን አቅርበዋል። በዚህም የእንግሊዝኛ ቋንቋ ክህሎት ችግር በተማሪዎችና በመምህራን ዘንድ እንደሚስተዋል አንስተው ይህንን ችግር ለመቅረፍ የሚያስችል ትምህርት ቤትን መሰረት ያደረገ ሥልት ቀይሶ መስራት እንደሚገባ ተናግረዋል። ትምህርት ሚኒስቴርም https://learn-english.moe. gov.et የተሰኘ ያለ ምንም የኢንተርኔት ክፍያ የሚሰራ የእንግሊዝኛ ቋንቋ ማሻሻያ ፓርታል አልምቶ ወደ ሥራ ማስገባቱን የጠቀሱት መሪ ሥራ አስፈጻሚው ይህንን ፖርታል ተማሪዎች፣ መምህራን እንዲሁም የእንግሊዝኛ ቋንቋ ክህሎታቸውን ማሳደግ የሚፈልጉ ዜጎች እንዲጠቀሙበት በሚገባ በማስተዋወቅ ረገድ ሚድያዎችን ጨምሮ ባለድርሻ አካላት ሃላፊነታቸውን እንዲወጡ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል። በመድረኩም የተለያዩ ጽሁፎች ቀረበው በተሳታፊዎች ውይይት የተደረገባቸው ሲሆን ተሳታፊዎችም ተማሪዎች በክፍል ውስጥና ከክፍል ውጪ ቋንቋውን እንዲጠቀሙበት እና ክህሎታቸውን እንዲያሳድጉ የሚያበረታታ ሁኔታ አለማኖሩ ችግሩን የጎላ እንዳደረገው ገልጸው ይህንን ለመፍታት መምህራንና ተማሪዎች በድፍረት ቋንቋውን እንዲጠቅሙና ክህሎታቸውን እንዲያሳድጉ የሚያደርጉ ስልቶችን መቀየስ እንደሚገባም ተናግረዋል። በመጨረሻም የቋንቋ ክህሎትን በማሳደግ ረገድ የተሰሩ ሥራዎችና ሥልቶችን መሰረት በማድረግ ተሞክሮዎች መቀመርና ማስፋት በተለይም ክልል ከክልል፣ ትምህርት ቤት ከትምህርት ቤት ልምድ የሚለዋውጡበት ሥርዓት መዘርጋት እንደሚገባም ተመላክቷል። በምክክር መድርኩ ከሁሉም ክልልና ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የመጡ አመራሮችና ባለሙያዎች እንዲሁም ጉዳዩ የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ተሳትፈዋል። https://t.me/timihert_minister
без подписи
без подписи
без подписи
без подписи
без подписи