Ustaz Muhammad Ferej
Статистикаقال الله تعالى ( وَمَنْ أَحْسَنُ قَوْلًا مِمَّنْ دَعَا إِلَى اللَّهِ وَعَمِلَ صَالِحًا وَقَالَ إِنَّنِي مِنَ الْمُسْلِمِينَ )
- Последний пост
- 14 авг.
- Последнее чтение
- 13 авг.
- Постов за неделю
- 3
- Всего постов
- 22
- Тип
- открытый
- Язык
- арабский
- В каталоге с
- 13 авг.
- 1/24сутки в ленте
- 334
- 1/48двое суток
- 382
- 1/72трое суток
- 412
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
без подписи
የስራ ማጣት ወቅት የህይወት ማብቂያ ሳይሆን የትዕግስት፣ የጥረትና የኢማን ፈተና ነው። አንድ ሙስሊም በችግር ጊዜ ተስፋ ሳይቆርጥ፣ አላህ ላይ ሙሉ ተወኩል በማድረግና ምክንያቶችን በማድረስ ከተንቀሳቀሰ፣ አላህ ከማያሰበው በኩል መውጫ መንገድ እንደሚያዘጋጅለት ጥርጥር የለውም። ከእያንዳንዱ ጨለማ በኋላ ብርሃን አለና በጽናትና በሰብር ሰበቡን በማድረስ መቀጠል የመፍትሄው ዋና ቁልፍ ነው። ያ አላህ ሐላል ሪዝቃችን ሰፊ አድርግልን 🤲 ያ አላህ ስራ ላጡ ስራ ለተበላሸባቸው ወገኖቻችን ሰፊ የስራ የሪዝቅ በርህን ክፈትላቸው 🤲 ያ አላህ የኑሮ ውድነትን አንሳልን በሰጠህን ሪዝቅ መብቃቃትን ለግሰን 🤲
بسم الله الرحمن الرحيم ስራ ጠፋ ?(አየሩ ተመቷል ?) አብሽር :- በተለያዩ ምክንያቶች የስራ ፈትነት፣ የንግድ ኪሰራ ወይም የኢኮኖሚ ፈተና ሲያጋጥም የሰው ልጅ መንፈስ ሊደክምና ተስፋ ሊቆርጥ ይችላል። ሆኖም በእስልምና አስተምህሮ ውስጥ ማንኛውም ፈተና ጊዜያዊና ከአላህ አቅም በላይ ያልሆነ፣ ከጀርባውም በርካታ ሂክማዎችን (ጥበቦችን) የያዘ ነው ። ቸሩ አላህ የፍጥረታቱን ሲሳይ (ርዝቅ) ሙሉ በሙሉ የወሰነና የመደበ በመሆኑ፣ የስራ ማጣት ወቅት ተስፋ መቁረጫ ሳይሆን ወደ አላህ የመመለሻ፣ ራስን የመፈተሻና አዳዲስ የሪዝቅ በሮችን የመፈለጊያ አጋጣሚ ነው። እነሆ ከቁርኣንና ከሐዲስ የተወጣጡ አስር ወሳኝ ኢስላማዊ ምክሮች፦ 1. ተስፋ አለመቁረጥና አላህ ላይ መጠጋት (ተወኩል) አላህ የሰው ልጅን ሲሳይ (ርዝቅ) ሰጪ ነው። ችግሮች ሁሉ ጊዜያዊ መሆናቸውን ማመን ያስፈልጋል። - ከቁርኣን፦ አዛኙ ጌታችን አላህ እንዲሀ ይላል :- «وَمَن يَتَوَكَّلْ عَلَى اللَّهِ فَهُوَ حَسْبُهُ» «በአላህ ላይ የሚመካ ሰው እርሱ በቂው ነው።» (ሱረቱ አጥ-ጠላቅ፡ 3) 2. እስቲግፋርን (ከአላህ ምህረት መጠየቅን) ማብዛት እስቲግፋር የሲሳይ በሮችን እንደሚከፍትና ጭንቀትን እንደሚያስወግድ ከአላህ ቃል ተገብቷል። - ከቁርኣን፦ ቸሩ ጌታችን አላህ እንዲሀ ይላል :- «فَقُلْتُ اسْتَغْفِرُوا رَبَّكُمْ إِنَّهُ كَانَ غَفَّارًا يُرْسِلِ السَّمَاءَ عَلَيْكُم مِّدْرَارًا وَيُمْدِدْكُم بِأَمْوَالٍ وَبَنِينَ» «ጌታችሁን ምህረት ጠይቁ፤ እርሱ መሀሪ ነውና አልኳቸው። በእናንተ ላይ ዝናብን በብዛት ይልካል፤ በገንዘቦችና በልጆችም ይረዳችኋል።» (ሱረቱ ኑህ፡ 10-12) 3. ምክንያቶችን ማድረስና ጥረት ማድረግ (አስባብ) በቤት ተቀዝቅዞ ከመቀመጥ ይልቅ ወጥቶ መፈለግና ጥረት ማድረግ የእስልምና ትእዛዝ ነው። - ከሐዲስ፦ ነብያችን ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም እንዲህ ይላሉ «احْرِصْ عَلَى مَا يَنْفَعُكَ، وَاسْتَعِنْ بِاللَّهِ وَلَا تَعْجَزْ» «ለአንተ ጠቃሚ በሆነው ነገር ላይ ሁሉ ጉጉ ሁን፤ በአላህም ተረዳ፤ አትድከም (ተስፋ አትቁረጥ)።» (ሶሂህ ሙስሊም) 4. ማንኛውንም ሃላል ስራ አለመናቅ ስራ መምረጥ ወይም ትንሽ ነው ብሎ መተው አይገባም። በገዛ እጅ ሰርቶ መብላት ከማንም ዘንድ ከመለመን ይበልጣል። - ከሐዲስ፦ነብያችን ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም እንዲህ ይላሉ «مَا أَكَلَ أَحَدٌ طَعَامًا قَطُّ خَيْرًا مِنْ أَنْ يَأْكُلَ مِنْ عَمَلِ يَدِهِ» «ማንም ሰው ከእጁ ስራ የሚበላውን ያህል የተሻለ ምግብ በልቶ አያውቅም።» (ሶሂህ ቡኻሪ) 5. ከእያንዳንዱ ችግር ጋር እፎይታ እንዳለ ማመን የስራ ማጣት ፈተና አልፎ የተሻለ እድል እንደሚመጣ በፅኑ ማመን። - ከቁርኣን፦ ለጋሹ ጌታችን አላህ እንዲሀ ይላል :- «فَإِنَّ مَعَ الْعُسْرِ يُسْرًا إِنَّ مَعَ الْعُسْرِ يُسْرًا» «ከችግር ጋር በእርግጥ እፎይታ አለ። ከችግር ጋር በእርግጥ እፎይታ አለ።» (ሱረቱ አል-ኢንሺራህ፡ 5-6) 6. አላህን መፍራትና ህጋዊ (ሃላል) መንገድን ብቻ መከተል በችግር ጊዜ እንኳን ቢሆን ወደ ጥፋትና ወደ ሃራም መንገድ አለመሄድ። - ከቁርኣን፦ ሁሉን አስተዳዳሪ የሆነው ጌታችን አላህ እንዲሀ ይላል :- «وَمَن يَتَّقِ اللَّهَ يَجْعَل لَّهُ مَخْرَجًا وَيَرْزُقْهُ مِنْ حَيْثُ لَا يَحْتَسِبُ» «አላህንም የሚፈራ ሰው ለእርሱ መውጫን ያደርግለታል። ካላሰበበትም በኩል ይረዝቀዋል።» (ሱረቱ አጥ-ጠላቅ፡ 2-3) 7. ቋሚ ዱዓ (ጸሎት) አዘውትሮ ማድረግ ከድህነት፣ ከዕዳና ከጭንቀት አላህ እንዲጠብቀን አዘውትሮ አላህን መለመን። - ከሐዲስ፦ ነቢዩ صلى الله عليه وسلم እንዲህ ብለው ይለምኑ ነበር፦ «اللَّهُمَّ إِنِّي أَعُوذُ بِكَ مِنَ الْهَمِّ وَالْحَزَنِ، وَالْعَجْزِ وَالْكَسَلِ، وَالْبُخْلِ وَالْجُبْنِ، وَضَلَعِ الدَّيْنِ، وَغَلَبَةِ الرِّجَالِ» «አላህ ሆይ! ከጭንቀትና ከሀዘን፣ ከድካምና ከስንፍና፣ ከስስታምነትና ከፍርሃት፣ ከዕዳ መከማቸትና በሰዎች ከመሸነፍ በአንተ እጠበቃለሁ።» (ሶሂህ ቡኻሪ) 8. የዝምድና ግንኙነትን መቀጠል (ሲለቱ አረሂም) ከቤተሰብና ከዘመድ ጋር መልካም ግንኙነት ማድረግ መዘያየር የሲሳይ የሪዝቅ በሮችን ይከፍታል። - ከሐዲስ፦ነብያችን ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም እንዲህ ይላሉ «مَنْ سَرَّهُ أَنْ يُبْسَطَ لَهُ فِي رِزْقِهِ، وَأَنْ يُنْسَأَ لَهُ فِي أَثَرِهِ، فَلْيَصِلْ رَحِمَهُ» «ሲሳዩ ሪዝቁ እንዲሰፋለትና እድሜው እንዲረዝምለት የሚወድ ሰው የዝምድና ግንኙነቱን ይቀጥል።» (ሶሂህ ቡኻሪ) 9. ምስጋናን (ሹክር) ማብዛት ባለን ትንንሽ ፀጋዎች ላይ አላህን ማመስገን የተሻለና ተጨማሪ ነገር እንዲሰጠን ያደርጋል። - ከቁርኣን፦ አዛኙ ጌታችን አላህ እንዲሀ ይላል :- «لَئِن شَكَرْتُمْ لَأَزِيدَنَّكُمْ» «ብታመሰግኑ በእርግጥ እጨምርላችኋለሁ።» (ሱረቱ ኢብራሂም፡ 7) 10. በሶላትና በትዕግስት መታገዝ በችግር ጊዜ ሶላትን በወቅቱ መስገድና በትዕግስት አላህን መጠበቅ መንፈሳዊ ጥንካሬን ይሰጣል። - ከቁርኣን፦ አዛኙ ጌታችን አላህ እንዲሀ ይላል :- «يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا اسْتَعِينُوا بِالصَّبْرِ وَالصَّلَاةِ» «እናንተ ያመናችሁ ሆይ! በትዕግስትና በሶላት ተረዱ።» (ሱረቱ አል-በቀራህ፡ 153) ______ በስራ ማጣትና በችግር ጊዜ የሚደረጉ አጭርና ተስፋ ሰጪ ዱዓዎች፦ - ሀላል ርዝቅ የመጠየቂያ ዱዓ፦ «اللَّهُمَّ اكْفِنِي بِحَلَالِكَ عَنْ حَرَامِكَ، وَأَغْنِنِي بِفَضْلِكَ عَمَّنْ سِوَاكَ» «አላህ ሆይ! ከሃራም ይልቅ በሃላልህ አብቃቃኝ፤ ከአንተ ሌላ ካለ ማንኛውም አካልም በችሮታህ አብቃቃኝ (ጥቅመኝ)።» (ቲርሚዚ) - አዲስና ጠቃሚ ስራ የመጠየቂያ ዱዓ፦ «اللَّهُمَّ إِنِّي أَسْأَلُكَ عِلْمًا نَافِعًا، وَرِزْقًا طَيِّبًا، وَعَمَلًا مُتَقَبَّلًا» «አላህ ሆይ! ጠቃሚ እውቀትን፣ መልካም (ሃላል) ሲሳይንና ተቀባይነት ያለው ስራን እጠይቅሃለሁ።» (ኢብኑ ማጃህ) - ከጭንቀትና ከችግር የመገላገያ ዱዓ፦ «اللَّهُمَّ لَا سَهْلَ إِلَّا مَا جَعَلْتَهُ سَهْلًا، وَأَنْتَ تَجْعَلُ الْحَزْنَ إِذَا شِئْتَ سَهْلًا» «አላህ ሆይ! አንተ ገራም (ቀላል) ያደረግከው እንጂ ምንም ቀላል ነገር የለም፤ አንተ የፈለግከውን አስቸጋሪ ነገር ብትፈልግ ቀላል ታደርገዋለህ።» (ኢብኑ ሂባን) ባጠቃላይ፣-
አሰላሙ አለይኩም ወራህመቱላሂ ወበረካቱሁ ተቋርጦ የነበረው ደርስ በአላህ ፍፈቃድ ዛሬ ይጀመራል።
*ከሀራም ለመላቀቅ ይፈልጋሉን ?* *هل تريد الإقلاع من الذنوب ?* ከሀራም (ከአላህ ክልከላዎች) መራቅና ወደ ሐላል ወደ ኢማን ማዘንበል የጠንካራ እምነት (ኢማን) ምልክት ነው። በዚህ መልካም መንገድ ላይ ለመጽናትና መንፈስዎን ለማጠናከር የሚረዱ ዋና ዋና ነጥቦች፦ 1- ሶላትን በወቅቱ በጀመዓ መስገድ፦ ሶላት ከእኩይና ከሀራም ነገሮች ሁሉ የሚከለክል ትልቁ መከላከያ ነው። 2- መጥፎ አጋጣሚዎችንና ቦታዎችን መሸሽ፦ ወደ ሀራም የሚወስዱ መንገዶችን (ማህበራዊ ሚዲያ፣ መጥፎ ጓደኞች፣ ወይም አላስፈላጊ ቦታዎች) መራቅ። 3- ጥሩ ጓደኞችን መያዝ፦ ወደ መልካም ነገር የሚያስታውሱዎትና ወደ አላህ መንገድ የሚወስዶትን መልካም ጓደኞችን መርጦ መያዝ ። 4- ዱዓ ማብዛት፦ አላህ ከሀራም ነገሮች እንዲያርቆትና በሐላሉ እንዲያብቃቃዎት በቋሚነት እሱን ይለምኑት ። 5- ጊዜን በጠቃሚ ነገር ማሳለፍ፦ ትርፍ ጊዜዎን መስጅዱ ውስጥ በመሆን : በቁርዓን፣ በትምህርት ፣ በዚክር : በኢስቲግፉር : በስራ ወይም በስፖርት በማሳለፍ አእምሮዎ ወደ ሀራም እንዳያስብ ማድረግ። 6- ተውበት ኢስቲግፋር ማድረግን ማብዛት ፦ በሆነ አጋጣሚ ስህተት ቢሰሩ እንኳ ተስፋ ሳይቆርጡ ወዲያውኑ ወደ አላህ ተመልሰው ምህረትን መጠየቅ። 7- መልካም ስራዎችን አቅሞ በፈቀደው መጠን ማዘውተር ለምሳሌ:- ሰላት : ጾም : ሰደቃ : የቀብር ዚያራ : የታመመን መጠየቅ ... ወዘተ 8- በዚህ መንገድ ላይ መጽናት ትዕግስት ማድረግ ዋናው ቁልፍ ነው። *ያ አላህ በሀቅ መንገድ ላይ አጽናን*🤲 *ያ አላህ ከሀራም መንገድ አርቀን*🤲 *ያ አላህ ዱንያ አኼራችንን አሳምርልን*🤲 https://t.me/ustazmuhammadferej
የሙስሊምን ደካማ ጎን የመከታተል መዘዝ :- عَوَاقِبُ تَتَبُّعِ عَوْرَاتِ المًسْلِمِينَ አላህ (ሱብሃነሁ ወተዓላ) ባሪያዎቹን በምህረቱ የሚያቅፍ፣ ነውራቸውን በመሸፈን የሚታወቅ እጅግ በጣም ነውር ሸፋኝ (አስ-ሲቲር) የሆነ አምላክ ነው። «إنَّ اللَّهَ حَيِيٌّ سِتِّيرٌ يُحِبُّ الحَيَاءَ وَالسَّتْرَ» (رواه أبو داود) «አላህ እጅግ አፍሪ (እፍረተ-መልካም) እና ነውርን ሸፋኝ ነው፤ እፍረትንና ነውርን መሸፈንን ይወዳል» (አቡ ዳዉድ ዘግበውታል) ነገር ግን የሰዎችን ነውርና ጉድለት ለመፈለግና ለማጋለጥ የሚሮጥን ሰው፤ አላህ ከእርሱ ጋር ይጣላል፣ ነውሩንም ያጋልጥበታል። ቀጥሎ የቀረበው ሐዲስ ታላቅ የነቢዩ (ሶልለላሁ ዓለይሂ ወሰልለም) ንግግር ልባችን አላህን እንዲፈራና ምላሳችንን ሊገስጸው የሚገባ ከባድ ማስጠንቀቂያ ነው! عَنْ أَبِي بَرْزَةَ الأَسْلَمِيِّ رَضِيَ اللَّهُ عَنْهُ قَالَ: قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صَلَّى اللَّهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ: «يَا مَعْشَرَ مَنْ آمَنَ بِلِسَانِهِ، وَلَمْ يَدْخُلِ الإِيمَانُ قَلْبَهُ، لاَ تَغْتَابُوا الْمُسْلِمِينَ، وَلاَ تَتَّبِعُوا عَوْرَاتِهِمْ، فَإِنَّهُ مَنْ تَتَّبَعَ عَوْرَةَ أَخِيهِ الْمُسْلِمِ تَتَّبَعَ اللَّهُ عَوْرَتَهُ، وَمَنْ تَتَّبَعَ اللَّهُ عَوْرَتَهُ يَفْضَحْهُ وَلَوْ فِي جَوْفِ بَيْتِهِ» (رواه أبو داود) አቡ በርዛ አል-አስለሚ (ረዲየላሁ ዓንሁ) እንዳስተላለፉት፤ የአላህ መልእክተኛ (ሶልለላሁ ዓለይሂ ወሰልለም) እንዲህ ብለዋል፡ «በአንደበቱ አምኖ እምነት ወደ ልቡ ያልገባችሁ የሰዎች ስብስብ ሆይ! ሙስሊሞችን አታማ (ሐሜት አትሥሩባቸው)፤ ነውራቸውንም (ሕደታቸውንም) አትከታተሉ፤ የሙስሊም ወንድሙን ነውር የተከታተለን ሰው አላህ ነውሩን ይከታተልበታል፤ አላህ ነውሩን የተከታተለበትን ሰው ደግሞ በገዛ ቤቱ ውስጣዊ ክፍል ውስጥ እንኳ ቢሆን ያጋልጠዋል (ያዋርደዋል)።» (አቡ ዳውድ ዘግበውታል) ያ አላህ የሰውን አይብ ከመከታተል ጠብቀን ያ አላህ የእኛን አይብ ከሰው ሰትርልን ለእኛ አሳየን እንድናርምም ወፍቀን ።
የሀገራዊ ምክክር ሂደቱ ውጤታማ እና ስኬታማ እንዲሆን የሁሉም ዜጋ ንቁ ተሳትፎና መልካም ፍላጎት ወሳኝ ነው። በምን አስተዋጽዖ እናድርግ ካላችሁኝ የሚከተሉትን ነጥቦች በመተግበር በያለንበት እንሳተፍ፡ 1. ዱዓ — አላህ ለሀገራችን ሰላም፣ አንድነት እና መልካም ውጤት ለህዝቦችዋ በመልካም ነገር መተጋገዝንና ብልጽግናን እንዲያጎናጽፍልን ሁሉም በያለበት ዱዓ ላይ መበርታት አለበት ። 2. ሰብር (ትዕግስት) — የተለያዩ ሀሳቦችን ለማዳመጥ እና ሂደቱ ጊዜ እንደሚወስድ ተረድቶ ውጤቱን በትዕግስትና በጥሩ ተስፋ መጠበቅ። 3. በልበ ሰፊነት — ልዩነቶችን አክብሮ አዳዲስ እና የተለዩ ሀሳቦችን ለመቀበል ዝግጁ መሆን ። 4. በእርጋታ በጥሩ ስሜት ማዳመጥ — የእኛን ጥያቄ ሰለመመለሱ ብቻ ሳይሆን የሌላውን ወገን ስሜት፣ ስጋት እና ፍላጎት በትክክል ለመረዳት ማዳመጥ ። 5. ቅንነትና ግልጽነት — በውይይቶች ላይ ያለ ምንም ስውር አጀንዳ፣ ሀገራዊ ጥቅምንና እውነትን መሰረት አድርጎ መሳተፍ። 6. የጋራ መፍትሄ ላይ ማተኮር — በታሪክና በባለፈው ቅሬታ ላይ ብቻ ሳይታጠሩ፣ ለወደፊቱ ሰላምና እድገት እንዲሁም መግባባትና አንድነት የሚያበጁ መፍትሄዎችን በማስቀደም ላይ መስራት። 7. ይቅር ባይነትና እርቅ — ያለፉ በደሎችንና ቁስሎችን በመፈወስ ለሀገር ሰላምና ለትውልድ ብሩህ ተስፋ ሲባል በይቅርታ ለመራመድ መዘጋጀት። *ያ አላህ ለተመካካሪዎች ያንተ ውዴታ እዝነት በረከት ያለበትን ሀሳብ አመላክታቸው ።*🤲 *ያ አላህ ተመካካሪዎችን ከሸይጧናዊና : ሀገርንና ህዝብን ከሚጎዳ ሀሳብ ጠብቃቸው ።*🤲 *ያ አላህ ኢትዮጵያንና ህዝቦችዋን አንተ ወደምትወደው መንገድ ምራልን ። አሚን*🤲
без подписи
без подписи
без подписи
*فضل إكرام ذي الشيبة* *ሸበቶን የማክበር ትሩፋት* عن أبي موسى الأشعري رضي الله عنه قال: قال رسول الله صلى الله عليه وسلم: «إِنَّ مِنْ إِجْلَالِ اللَّهِ إِكْرَامَ ذِي الشَّيْبَةِ الْمُسْلِمِ، وَحَامِلِ الْقُرْآنِ غَيْرِ الْغَالِي فِيهِ وَالْجَافِي عَنْهُ، وَإِكْرَامَ ذِي السُّلْطَانِ الْمُقْسِطِ»(رواه أبو داود، وحسّنه الألباني). አቡ ሙሳ አል-አሽዐሪይ (ረዲየል ዐንሁ) እንዳስላለፋት፡ የአላህ መልእክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) እንዲህ ብለዋል፡ «አላህን ከማክበርና ከማላቅ መካከል፡ ሙስሊም የሆነን ሽማግሌ (የሸበተን) ማክበር፣ በቁርኣን ድንበር የማያልፍና (ያልተገባ ማጋነን የማያደርግበት) ከእሱም የማይርቅን (የቁርኣን) ሀፊዝ ማክበር፣ እንዲሁም ፍትሃዊ የሆነን መሪ ማክበር ይገኙበታል።» *(አቡ ዳውድ ዘግበውታል)*
без подписи
አሰላሙ አለይኩም ወራህመቱላሂ ወበረካቱሁ በግል ሀጃ ምክንያት ለዛሬ ደርስ የለም።
አሰላሙ አለይኩም ወራህመቱላሂ ወበረካቱሁ በአላህ ፈቃድ ዛሬ ደርስ ይኖረናል
без подписи
без подписи
без подписи
ሲጨንቅህ ወደ አላህ ሽሽ። አላህ አንተ ያላሰብካቸው እጅግ ብዙ መፍትሄዎች አሉትና ! {فَلَمَّا تَرَاءَى الْجَمْعَانِ قَالَ أَصْحَابُ مُوسَى إِنَّا لَمُدْرَكُونَ (61) قَالَ كَلَّا إِنَّ مَعِيَ رَبِّي سَيَهْدِينِ (62) فَأَوْحَيْنَا إِلَى مُوسَى أَنِ اضْرِبْ بِعَصَاكَ الْبَحْرَ فَانْفَلَقَ فَكَانَ كُلُّ فِرْقٍ كَالطَّوْدِ الْعَظِيمِ (63)} [الشعراء: 61-63] (( ሁለቱ ጭፍሮች (የፈርዖንና የሙሴ ሕዝቦች) በተያዩ ጊዜ፣ የሙሴ ሰዎች «አሁንማ ተያዝንብን!» አሉ፤ ሙሴም «በፍጹም አይሆንም! ጌታዬ ከእኔ ጋር ነው፣ እርሱ መንገድ ያሳየኛል» አለ፤ እኛም ወደ ሙሴ «ባሕሩን በበትርህ ምታው» ብለን አዘዝነው፤ (ባሕሩም) ተሰነጠቀ፤ እያንዳንዱም የተሰነጠቀው የውኃ ክፍል እንደ ትልቅ ተራራ ሆነ።))
без подписи
без подписи