ጦቢያ የግጥም መድብል
Статистика- Последний пост
- 10 авг.
- Последнее чтение
- 15 авг.
- Постов за неделю
- 0
- Всего постов
- 20
- Тип
- открытый
- Язык
- und
- Категория
- Новости и СМИ (по похожим)
- В каталоге с
- 13 авг.
- 1/24сутки в ленте
- 1 196
- 1/48двое суток
- 1 370
- 1/72трое суток
- 1 478
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
ከራሴ የማልወደው አንድ ነገር ቢኖር አስራ ስድስት አመት ዘግይቼ መፈጠሬን ነው። በቻልኩት አቅም ላስተካክለው እሞክራለሁ። ጂንስ አልለብስም። ካኪ ሱሪ በወፍራም ሹራብ ለብሼ ጥግ ላይ እቀመጣለሁ። የዘወትር ፀሎቴ ሌላ አይደለም። "እባክህ ጌታዬ እኩያዋ አርገኝና አግብቻት ከዚህ መርዛማ ህዝብ ነጥቄ ወደ ሸዋ ልውሰዳት!!" ነው። በዚህ አመት ነው ከባለቤቷ እና ከሁለት ልጆቿ ጋር እኛ ወደምንኖርበት አከባቢ የመጡት። መልኳ፣ ፀባዩዋ እና አለባበሷ አንድ አይነት የሆነላት ሴት የማውቀው እሷን ነው። እንዲሁ ቀልብን የሚሰልብ ርግት ያለ ድባብ አላት። መንገድ ላይ ስታልፍ አባውራው ሁላ ምናምኑን በጋቢው እየሸፈነ ነው የሚያያት። ራሷን ልታጠፋ ሞክራ ከተረፈች ቡኃላ ግን ሁሉም አገለላት። እነማዬም እሷን ቡና መጥራት አቆሙ። ባሏም "ራሷን ብታጠፋ የለሁበትም" ለማለት ነው መሰል እየዞረ ስላለባት ችግር ሲያወራ ነው የሚውለው። «ምንድን ነው እንዲህ አይነት ቅብጠት? ማንም ሴት ትዳሯ በምትፈልገው መንገድ ላይሔድላት ይችላል! ራስን ለማጥፋት መሞከር ግን ትኩረት ፈላጊነት ነው።» ትላለች እማዬ ስለሷ ሲነሳ። እንዳለ ቡና ጠጭው በስምምነት ራሱን ይነቀንቃል። እኔጋ ስለምንቀራረብ እንድታብራራልኝ የማላደርገው ጥረት የለም። «ለምንድን ነው ግን ሁሉም የሚጠሉሽ?» «ምንድን ነው እንዲህ ያስከፋሽ?» እላታለሁ። የሷ መልስ ሁሌም አንድ ነው። «ወፍ ረግማኝ!» ትለኛለች እየሳቀች። መመለስ እንዳልፈለገች ይገባኝና እተወዋለሁ። የመጣች ሰሞን ከሷ የያዘኝ የአይን ፍቅር በሽተኛ አድርጎኝ ነበር። አልበላም፣ አልጠጣም፣ አልተኛም። ትክክለኛ የዘፈን ግጥሞች ላይ ያለው ፍቅር ነበር የያዘኝ። ፍቅር አያስበላ አያስጠጣ የሚለው ያፈቀርከውን ሰው ማግኘት እንደማትችል እያወቅክ ስታፈቅረው ሳይሆን አይቀርም። በመጨረሻ ግን ተሸነፍኩ። ቀጥ ብዬ ቤቷ ገባሁ። በረንዳ ላይ ቁጭ ብላ ለወፎች ጥሬ እየመገበች ነበር። ደንግጣ ዙራ አየችኝ። ተጠግቼ ሰላም እንኳን ሳልላት «ዘርዬ እወድሻለሁ» አልኳት። ቀልዴን መስሏት ነበር። እንባዬን ስታይ ከሳቋ ላይ ግርምት ጨመረችበት። «ና እስኪ ተቀመጥ የኔ ቆንጆ!» አለችኝ! እንባዬን እየጠረግኩ ተቀመጥኩ። «ስንት አመትህ ነው?» «አስራ ስድስት» «ታውቃለሀ? እኔ ራሱኮ በጣም ነው የምወድህ!» «እውነት?» «የምሬን ነው። ይሔ ልጅ ልጄ በሆነ ብዬ እመኝ ነበር።» ኧረ ቅስሜን! «ትምህርት እንደወጣህ የቤት ስራ ምናምን ካለብህ እኔጋ እየመጣህ ስራ እሺ! ጓደኛ ትሆነኛለህ።» ከዛ ጊዜ ጀምሮ ጓደኞቼን ዞር ብዬ አይቻቸው አላውቅም። የነሱ ጭንቀት "የምወዳት ልጅ እንደወንድሜ ነው የማይህ" አለችኝ ነው። የኔ ጭንቀት "የምወዳት ልጅ እንደልጄ ነው የማይህ" አለችኝ...እኩያቸውን ይፈልጉ። ትምህርት ቤት ራሱ የምሔደው የቤት ስራ ለመቀበል ነው። እንደመጣሁ እነማዬ ሳያዩኝ ተደብቄ ዘሪቱጋ እሔዳለሁ። ስራ ጨርሳ ወደ በረንዳው ስትመጣ ከአጠገቧ ሂጄ እቀመጣለሁ። ባሏ እንደልጅ ነው የሚያዬኝ መሰለኝ ሲያዘኝ ራሱ ሰላም ሳይለኝ ነው። እኔም ለነገሩ ለሱ ሰላምታ ግድ ኑሮኝ አያውቅም። «እንዴት ግን ይሔን ሰው አገባሽው?» አልኳት የሆነ ቀን። ምንም ብጠይቃት አትደነግጥም። ርጋታዋ ሳይናድ ትመልስልኛለች። «የህልም ሽንት ታውቃለህ?» አለችኝ። በቃ እኔ ለሷ ሁሌም ህፃን ነኝ። «ኧረ አላውቅም» አልኩ አልጋ ላይ ሸንቼ ማወቄን እንዳታውቅብኝ። «ሽንት ቤት ሂደህ በስነስርዓት ልብስህን አውልቀህ ትሸናለህ...ስትነቃ ግን አልጋህ ላይ ነው የሸናኸው።» «እእእእ» አልኩ! «እንደዛ ነው የኔ ፍቅር። በኔ ቤት ሁሉን ነገር በጥንቃቄ መርጨ ጨርሻለሁ። ስባንን ያልሆነ ቦታ ላይ ነው ልቤን የጣልኩት» አሁን አሁን በአጠገቤ ሲያልፍ በሆዴ "አንተ የህልም ሽንት" እለውና ለራሴ እስቃለሁ። ዘርዬ እንደነገረችኝ ከሆነ አዲሳባ እያሉ ለመፅሔቶች አንዳንድ ፅሁፎችን ትሰራ ነበር። ሰው መስሏት ይሔን የባንክ ሰራተኛ አገባችው። ከተራ የደንበኛ አስተናጋጅነት አንስተው ማናጀር አደረጉትና ወደዚህ አዛወሩት። የሱ ኑሮ ቀጠለ። የሷ እንደነገሩ ሁኖ ቀረ። እናት መሆን አቃታት። ሚስት መሆን አጎበጣት። እነማዬ ሌላ ህልም ኑሯቸው አያውቅምና ፍላጎቷን እንደቅንጦት ቢያዩት አይገርመኝም። አንድ ቀን ማታ ዘርዬ ባልተዘጋጀሁበት ስለዛች ወፍ ታወራኝ ጀመር። «ከአስራ ስድስት አመት በፊት ባንተ እድሜ እያለሁ ይመስለኛል።» አለች በድንገት። ነቃ አልኩ። «እንዲሁ በጨዋታ ዲንጋይ ስወረውር ያንደኛዋን ወፍ ክንፍ ሰበርኩት። በኢላማዬ ደስ ብሎኝ የወደቀችውን ሒጄ ሳያት መብረር አትችልም። አሳዘነችኝ። ቤት ወሰድኳት። ዶሮዎቼ ጋር ቀላቅዬ ጥሬ እያበላሁ እስክትሞት ድረስ አኖርኳት።» «ታዲያ ምን አጠፋሽና ትረግምሻለች? የተሳሳትሽውን አስተካክለሻልኮ!» አልኩ በጭንቀት። «ሁለት ጊዜ ነው የገደልኳት። ክንፏን መስበሬ ሳያንስ የክንፏን መሰበር እንደ ችግር በማያዩ ዶሮዎች መሀል እንድትኖር አደረኳት። ሲመስለኝ እሷ ወፍ ረግማኛለች።» ከጃኬቷ ኪስ ወረቀት አውጥታ ሰጠችኝ። ላነበው ስል «ነገ ማታ እንድታነበው ነው የምፈልገው» አለችኝ። ነገ ተነስታ ልትሰወር ነው ብዬ አልጠረጠርኩም። እኔ በተኛሁበት የኔ ወፍ ዘርዬ ሰባራ ክንፏን እየጎተተች ርቃ ሔደች። ጧት ወደ ትምህርት ቤት ስሔድ የግቢያቸው በር ተከፍቶ ፊትለፊት ባዶ ቤታቸው ከመንገድ ላይ ይታያል። ተንደርድሬ ስገባ ሁለት ሰዎች እየዞሩ እያዩ ነው። ለቀው መሔዳቸውን አረዱኝ። መከዳት ተሰማኝ። ትምህርት ቀርቼ ሳለቅስ ዋልኩ። በሶስት ቀን ውስጥ አንድ ሰሞን ወደነበርኩበት በሽታ ተመለስኩ። አልበላም፣ አልጠጣም፣ አልተኛም። ከመሔዷ በፊት ወረቀት ሰጥታኝ እንደነበር ያስታወስኩት ራሱ መምሬ ሶስት ቀን በፀበል ካጠመቁኝ ቡኃላ ነው። መሔዷን እያሰብኩ ያልረሳሁት ምን አለ? አልጠበኩም ነበር! ገልጨ ሳነበው ከህመሜ ተፈወስኩ። መምሬ በመዳኔ እማዬ ስታመሰግናቸው «ሶስት ቀን መቆዬቱ ራሱ ገርሞኛል» ሲሉ ጉራቸውን ነፉ። ዛሬ በዘሪቱ እድሜ ሁኜም ያ ደብዳቤ ከኪሴ አይጠፋም። የስሜት መዋዠቅ ሲገጥመኝ አውጥቼ አነበዋለሁ። «ቻው ያላልኩህ አንተን ቻው ማለት ስለከበደኝ ነው። ደስ ትለኛለህኮ። በአንተ ውስጥ ራሴን አያለሁ። አስራ አምስት አመት ፈጥኜ ባልወለድ የማገባው አንተን ነበር። አምላኬን የምጠይቀው አንድ ነገር እኔ ያጣሁትን ሁሉ ላንተ እንዲሰጥህ ነው። ያልኖርኩትን ኑርልኝ። ስለሁሉም አመሰግንሀለሁ። ያላንተ አላልፈውም ነበር ይሔን ጊዜ።» ይላል። ዛሬ ላይ የመፅሔት አዘጋጅ ነኝ። ደስተኛ ሰው ነኝ። ጓደኞቼ «ለምንድን ነው ሰው ሁሉ ያለ ምክኒያት የሚወድህ?» «ለምንድን ነው የነካኸው ሁሉ የሚሳካልህ?» ይሉኛል። የኔ መልስ ሁሌም አንድ ነው። «ወፍ መርቃኝ!» እላቸዋለሁ እየሳቅኩ። ማብራራት እንዳልፈለኩ ይሰማቸውና ይተውኛል። ፨፨፨ (March 2022) ✍ Mackel Azmeraw @WAS143 @WAS143
ሰሞንኛ (በእውቀቱ ስዩም) በአገራችን በተለያዩ ቦታዎች የሚኖሩ ወጣቶች የአካል ብቃት ፉክክር ሲያደርጉ በቲክቶክ ሳይ ደስ ይለኛል ፤ የሆነ ቦታ ጡንቻቸውን በስሚንቶ በተበጀ ዳምቤል ያጠጠሩ፣ ከወገባቸው በላይ የተራቆቱ ጎረምሶች ወደ ካሜራው አየሾፉ እንዲህ ይላሉ፤ ‘ ኢስቲ ወንድ ናን የሚል ካሌ ኢሂንን ቻሌንጂ ይሞኪር፤ የኛ ጀማ! ማኒንም አይሰማ ! “ ስክሮል ሳደርግ ሌላው ቡድን ከሆነ አካባቢ ብቅ ይላል፤ የቡድኑ መሪ በዳጉሳ ቂጣ ዳጎስ ያለውን ደረቱን እየመታ ‘’ እስቲ ይህንን ደረት አጣብረው፤ ሰባ አመት ብትማስን ምታመጣው ይመስልሀል፤ የልምጥ ልይ ! የኛ ዠማ ! ማንንም አያምጥ፤ ደሞ ሸር ኮቢሊንክ ማረግ እንዳይዘነጋ” የሚል መልክት ያስተላልፋል፤ ይህ በአንዲህ እያለ፣ የሚመለከተው አካል ቁጭ ብሎ ‘ያኛው ለአየር ወለድ፤ ይሄኛው ለኮማንዶ” እያለ ይመዘግባል፤ እኔ ጎረምሳ እያለሁ በሰፈራችን ልጆች መካከል የነበረው ብቸኛ ቻሌንጅ ብይ ጨዋታ ነበር፤ በቀለጠ የስኪብርቶ ቀፎ በተሰራ ብይ፣ የውሀ ብይ ለመብላት ስንንፉዋቀቅ ያለ እድሚያችን የጉልበታችንን ሎሚ አሙዋሙዋነው፤ ከዚያ አንድ ቀን መንግስት አዘናግቶ የሰፈራችንን ጎበዝ ብይ ተጫዋቾችን አፈሳቸው፤ በብይ አንዲህ ካንከረባበቱ በክላሽማ የሚችላቸው የለም ብሎ ይመስለኛል፤ በነገራችን ላይ ጦርነትን የምጠላውን ያክል የድብድብ ስፖርት ገዳፊ ነኝ፤ ቀጣዩ የርግጫና የቡጢ ግጥምያን በጉጉት እየጠበቅሁ ነው፤ ወንድ ልጅ በመን ፈቅ አንዴ አንኩዋ ክንዱን በእኩያው ላይ አንስቶ መፈተን አለበት ባይ ነኝ፤ አንዱ፤ የመግቢያ ዋጋቸው መቶሺ ብር ነው ብሎ ተቀድዶልኝ ደንግጨ ነበር፤ በነካ እጃቸውና እግራቸው በልጀነቴ ቡሊ ያደረገኝን ሙሉጌታ ቡሊን ቢደበድቡልኝ ራሱ ያንን ያክል አልከፍልም ብየ አመረርሁ፤ በቪቪአይፒ መግብያው አምሳሺ ሆኖ ለታዳሚው መጠጥ ይቀርባል የሚል መረጃ ስሰማ ግን ተጥናናሁ'; ይሄ ሸጋ ነው፤ ችግሩ ምንድነው- ትንሽ ከቀማመስኩ የአንዱ ተደባዳቢ ተቀያሪ ቤንች ልሁን ማለቴ አይቀርም፤ እኔ ከግጥሚያው በላይ ደስ የሚለኝ የተጋጣሚወች የዛቻ መርሀግብር ነው፤ ህዝብና ጋዜጠኛ ግጥግጥ ብሎ በታደመበት መድረክ ላይ አንዱ ሌላውን ምንሲለው ሰማሁ፤ “ እግርህን ሰብሬ አካለ ስንኩል አደርግሀለሁ”😟 ምነው ጎበዝ! ስፖርት ላይ ህግ፤ ፖሊስ ፤ ፍታብሄር ምናምን የሚባል ነገር የለም አንዴ ? ለማንኛውም የአጥንት ህክምና ክሊኒክ ያላችሁ ፣ ወይም የዊልቸር አስመጭ የሆናችሁ፤ ተሸናፊውን ተጋጣሚ የብራንድ አምባሳደር ለማድረግ ተሰናዱ! @WAS143 @WAS143
የመጻተኛው አገር አገር ድንኴን ት'ኹን ጠቅልዬ የማዝላት ስገፋ እንድነቅላት ስረጋ እንድተክላት ✍️በውቄ @WAS143 @WAS143
«የምር? የምርህን ነው?!» «ምን ልበልሽ?» «መልስልኝ የጠዬቅኩህን!» «አዎ የምሬን ነው። እስከሞት ድረስ ነው የምወድሽ!» «ቆይ...መቼ ነው የወደድከኝ?...ማለቴ ኤግዛክትሊ ምን ሳደርግ አይተኸኝ ነው ልሙትላት ያልከው? የትኛው ጨዋታዬ ነው በሌላ ነገር እንድታስበኝ ያደረገህ? የትኛው ቀሚሴ ነው ምኞት የቀሰቀሰብህ?» «ኧረ እኔ የመጀመሪያ ቀን እንዳዬሁሽ ነው የወደድኩሽ።» «ስለዚህ በመልኬ ነው ማለት ነው?» «አላዬሁትም ነበር ፊትሽን።» «ሰውነቴን አይተህ ነዋ? በአቋሜ?!» «የለም። ተቀምጠሽ ነበር።» «እና ምኔን ነው የወደድከው?» «ፀጉርሽን! ፀጉርሽ ነው ጠልፎ የጣለኝ።» እጇ የቻለላትን ያህል ዘግና እየተመለከተች...«ያን ያህል ራሱ'ኮ አልንከባከበውም።» «ተሰምቶኛል እንደዛ። ሃሃ! ሳይንከባከቡት እንዲህ ያማረ ቢንከባከቡት እንዴት ያምር ይሆን? አስባለኝ። ቀርቤ ባይሽ...ነፍስሽም እንደፀጉርሽ ያማረ ሁኖ አገኘሁት። እሱንም ግን የሚንከባከበው ስላላዬሁ ራሴን እጩ አድርጌ አቀረብኩ።» «ይገርማል!!!» ሌላ ተጨማሪ ነገር ትላለች ብዬ ስጠብቅ በዝምታ ከቆዬች ቡኃላ አሁንም በድጋሜ «ይገርማል!!» አለች። ፈራሁ። ከዛ ራሷን እያወዛወዘች ለሶስተኛ ጊዜ «ይገርማል!» አለችና በቆምኩበት ጥላኝ ሔደች። ሳምንቱን ሙሉ አላዬኋትም። ደወልኩ አታነሳም። ፃፍኩ አትመልስም። ሚስት ለማግኘት ስሞክር ምርጥ ጓደኛዬን በማጣቴ ስንገበገብ ሰነበትኩ። ከሳምንት ቡኃላ ስንገናኝ ሌላ ሰው መስላኝ አልፌያት ነበር ለጥቂት። ለዚህ ነገር ሊያዘጋጀኝ የሚችል አለም ላይ አንዳች ሀይል አልነበረም'ና እሷ መሆኗን ሳውቅ በረገግኩ። ቆ.ር.ጣ.ዋ.ለ.ች!!! ዞማ ፀጉሯን...ጥቁሩ ክንፏን...አንድም ሳታስቀር ሁሉንም ተቆርጠዋለች...! እኔ መተንፈስ አቅቶኝ ስቃትት እሷ የወትሮው ፈገግታዋ ሳይቀዬር ቀርባ ሰላም አለችኝ። እየሳቀች አወራችኝ። እየሳቀች ምሳ ጋበዘችኝ። በጉልበቷ ጓደኝነታችንን ልታስቀጥለው ሞከረች። በጉልበቷ ጓደኝነታችንን ልታስቀጥለው ተቻላት። ላለፉት አራት አመታት ይሔንን ክስተት በጨዋታ መሐል እንኳን አንስተነው አናውቅም። ያልተፈጠረ ያህል ከድተነው ነው ወዳጅነታችንን የቀጠልነው። እኔ ደህና ነኝ?...ይመስለኛል...እኔ'ጃ! ሰዎች «ጨዋታ ይችላል!» እያሉ ያሙኝ ጀምረዋል። አንድም፣ ሁለትም፣ ሶስትም ሁነው ከተሰባሰቡ ይጠሩኛል። «ከባድ የመሰለኝን ነገር ሁሉ እየቀለድክ ተራ ስለምታደርገው የጨነቀኝ ቀን አንተ ጋ መዋልን እመርጣለሁ!» ይሉኛል። ኧረ ወዲያ!...ደህናማ አይደለሁም! በፀጉሯ መቆረጥ እንድስቅ ከተገደድኩባት ቀን ጀምሮ ለምንም ነገር አዝኜ አላውቅም። ለምንም ነገር ግድ የለኝም። «ንባብ፣ ፍልስፍና፣ ኒቼ፣ የአለም አፈጣጠሯ!» ምናምን በሚሉ ሰበቦች እከለላለሁ። እቀባጥራለሁ። የሆነ ነገሬን ከፀጉሯ ጋራ ቆርጣ እንደጣለችው የማምንበት ወኔ አላገኘሁም። እሷም ብትሆን አየሆንኩ ያለሁት ነገር የገባት አትመስልም። ፍቅሯን ለማምለጥ ስል የፈጠርኩትን የውሸት ማንነት ክፉኛ ለምዳዋለች። ያኔ እንድትወደኝ በምፈልገው መንገድ እየወደደችኝ ነው። ያኔ እንድትስቅልኝ በምፈልገው መንገድ እየሳቀችልኝ ነው። ያኔ እንድታቅፈኝ በምፈልገው መንገድ እያቀፈችኝ ነው። ቤቴ ውላ ታድራለች። ምንም ሳልሞክር እሰናበታታለሁ። የሚያስቁ ካፕሎችን ቪዲዮ ትልክልኛለች። አይቼ ዝም እላታለሁ። ስንገናኝም ጨዋታዋ አንድ አይነት ሁኗል። «...'ፍቅረኛሞች ነው የምትመስሉት' አለኝ ባለሱቁ!» ትለኛለች። «ማርቲ'ኮ 'እንዴት ነው የምታፈጭበት?' አለችኝ!...ያን ያኽል አፈጥብሀለሁ እንዴ?» «...'ስሙን ሳታነሺ አስር ደቂቃ ማውራት አትችይም' አለችኝ እህቴ...አንተንም እንደዛ ያለህ አለ ወይስ እኔን ብቻ ነው?!» «እወድሀለሁ!» ከማለት በስተቀር የማትለኝ የለም። የሚሰማትን እንደኔ አፍረጥርጣ ብትናገር...እንደሷ የምጨክንባት እየመሰላት ይሆን? አላውቅም! አንዳንዴ የመኖር ጉጉቴ ፍቅሯን እየጠጣ፤ እንደ ፀጉሯ ሁሉ በዝግታ ሲያቆጠቁጥ ይሰማኛል። «የቀረበችህን ያህል ቅረባት!» ይለኛል። ግን አላሳድገውም። ብቅ ብቅ ያለ ምኞቴን ሳታዬኝ እላጨውና ልፋቷን ሁሉ ከንቱ አደርገዋለሁ። የሚቀርቡን ሰዎች መሳቃቸውን ትተው ወቀሳ ጀምረዋል። «ምናለ ከዚህ በላይ ባታስጨንቃት?» እያሉኝ ነው። ህይወት አልባ በመሆኔ የወደደችኝ ሴት ጋር እንዴት ብዬ ህይወት እጀምራለሁ? ፍቅሯ ነፍስ ሲዘራብኝ መልሳ እንደማትጠላኝ በምን አውቃለሁ? እኔ እንደሁ ስወድ አያምርብኝም። መጥኜ ማፍቀር አልችልበትም። እሷን ደግሞ መጎተት ሳቆም ነው የምስባት። ቀለል ስል ነው የምከብዳት። በድን ስሆን ነው ስሜት የምሰጣት። ስኖር አልጥማትም። ስሞት ነው የምትወደኝ። እኖራለሁ ብዬ ፍቅሯን ማጣት አልሻም! እስከሞት ድረስ ነው የምወዳት!! Mackel Azmeraw @WAS143 @WAS143
እኔ እንደሁ ስወድ አያምርብኝም። መጥኜ ማፍቀር አልችልበትም። እሷን ደግሞ መጎተት ሳቆም ነው የምስባት። ቀለል ስል ነው የምከብዳት። በድን ስሆን ነው ስሜት የምሰጣት። ስኖር አልጥማትም። ስሞት ነው የምትወደኝ። እኖራለሁ ብዬ ፍቅሯን ማጣት አልሻም! እስከሞት ድረስ ነው የምወዳት!! @WAS143 @WAS143
«ናፈቅሽኝ አቦ !» ብዬ የፃፍኩት ኩራት ሲሰማኝ - ቀድጄ ጣልኩት ። «ናፈቅከኝ በጣም» ብለሽ የፃፍሽው ልምምጥ መስሎሽ ወርውረሽ ጣልሽው ። የፍቅር ብርሃን እንዳልተሰማን ቅር እንዳላለን እንዳልናፈቅን በአዲስ ወረቀት - ፀብ ተላላክን ። እንበልና ... እኒያ ወረቀቶች ... ቀደን የጣልናቸው የክረምት ጎርፍ አገናኛቸው ። እስኪ አስቢያቸው ... ደራሽ ተሳፍረው ሆነው ጎን ለጎን እርስ በርሳቸው ተያይተው ቢሆን ? ምን ይሉን ይሆን ? ሀብታሙ✍️ @WAS143 @WAS143
ሁሌም የሴቶች ዶርም ድረስ መጥቶ ሸኝቶኝ ሲመለስ ባለማመን ያዩታል። «ሔለን ግን ሙድ እየያዝሽብን ነዋ! ያን ሁሉ ወንድ ያባረርሽው ይሔ ፉንጋ ጋር ለመሆን ነው?» ትላለች አንደኛዋ። «እስኪ ተያት ምን ታውቂያለሽ? ራቁቱን ያዬችው እሷ!» ብላ ሌላኛዋ ታሽካካለች። እኔም አስከፋናት ብለው እንዳይደብራቸው እስቅላቸዋለሁ። ዋና ምክኒያቴን ከሚያውቁብኝ የጠረጠሩት እውነት እንደሆነ እንዲሰማቸው ባደርግ ይሻለኛል። ለሰው ባይመስልም ፉንጋው የፀሎቴ መልስ ብቻ ሳይሆን ጨለማ ክፍል ውስጥ ያገኘሁት ሻማዬ ነው። «ሔሉዬ ሌላ ቅፅል ስም ጠፍቶ ነው 'ሻማዬ' የምትይኝ?» ይለኛል። «ሻማዬ ካላልኩህ ችቦዬ ነው የምልህ...የቱ ይሻልሀል?» «አይ ሻማው ይሁን በቃ!» ይላል እየተቅለሰለሰ። አንዲት ፀበል ለፀበል የምትመላለስ ታላቅ እህት አለችኝ። ሰዎች መንፈስ ይዟት ነው እያሉ ያወራሉ። እኔ ግን ባሏን ፈትታ ከመጣች ቡኃላ የዘመድ አዝማዱን ወሬ አትችለው ብላ እንዳበደች አውቃለሁ። ከዛ ጊዜ ጀምሮ ፀሎቴ አንድና አንድ ብቻ ነው። «ጌታ ሆይ የምወደውን ሳይሆን የሚወደኝን ስጠኝ!» ለዛ ነው ሻማዬ የፀሎቴ መልስ ነው የምለው። የመጀመሪያ ቀን ሰውነቱ በላብ ተጠምቆ፣ እጁ እየተንቀጠቀጠ፣ መተንፈስ አቅቶት እየቃተተ ሲጠይቀኝ እንደማገባው ወስኜ ነበር። የግቢውን ወንዶች ሁሉ መልሼ እሱን የጠበስኩት እነሱ እንደሚሉት የተለዬ ነገር አግኝቼበት አይደለም። ሪስክ መውሰድ ስለማልችል ነው። የፈሪ ሰው ጥቅም?...ቀድሞ አያጠቃም! ግቢ ውስጥ በኔ ምክኒያት ያልደረሰበት ግፍ የለም። ለሁሉም ታዋቂ ካፕሎች ቅፅል ስም ሲሰጡ እኛን ማን ቢሉን ጥሩ ነው? "Beauty And The Beast" ሆሆ! ተረባውን ችሎ አለፍ ሲል ደግሞ መምህራኖች ግሬድ ያበላሹበታል። ጉልበተኞች ዱላ የቀላቀለበት ማስፈራሪያ ያዘንቡበታል። ዘበኞች እንኳን ባቅማቸው ያዋክቡታል። ሁሉም እንደየስልጣኑ ይበድለዋል። «ሻማዬ ከዚህ በላይ እንድትጎዳ አልፈልግም» ስለው «ቀላል ነው ብዬ አልዋሸሽም። ሽልማቴ አንቺ እንደሆንሽ ሳስበው ግን 'ኧረ ያንሰኛል ጨምራችሁ ምቱኝ' ልላቸው ሁላ ያምረኛል!» እያሳዘነ ያስቀኛል። ገፍተው ገፍተው ለራሱ ያለውን አመለካከት እንዳወረዱበት የገባኝ የአመቱ መጨረሻ ላይ ነው። እሱ ተመራቂ ስለነበር ቀጣይ አመት እንደማንገናኝ ገብቶት እያለቀሰ መጣ። «አንተም ስራ ልታገኝ የምትችለው እዚሁ አዲሳባ ነው። እኔም እዚሁ ነው የምማረው! ምን የተለዬ ነገር ተፈጠረና ነው የምታለቅሰው?» «አንድ ነገር ብቻ ቃል ግቢልኝ!» አለ አሁንም እያለቀሰ! «እሺ ምንድን ነው?» «እስክትመረቂ ድረስ የፈለግሽው ወንድ ጋር ሁኚ! ከዛ ቡኃላ ግን ተመልሰሽ ወደኔ ልትመጭ ቃል ግቢልኝ!» ምንም አላልኩትም። በቆመበት ጥዬው ሔድኩ። ምን ባደርገው ነው ሊተማመንብኝ የሚችለው? እኔስ በዚህ ደረጃ ከሚወደኝ ወንድ ውጭ ሌላ ምን እፈልጋለሁ? ከሶስት ቀን ቡኃላ የሻማዬን ልብ ያረጋል ብዬ ያሰብኩትን ትልቅ ውሳኔ ወሰንኩ። ሲያዬው አዲስ እንደተወለደ ህፃን ስቅስቅ ብሎ ማልቀስ ጀመረ። ለነገሩ እኔም ከዛ ያነሰ ግብረመልስ አልጠበኩም። ይሔንን ፊት ለዘላለም እንዳይጠፋ አድርጌ ጀርባዬ ላይ ተነቅሼለት ለቅሶ ሊበዛብኝ ነው? የሚያስቀው እንራራቃለን ብዬ ፊቱን ተነቅሼለት ሌክቸረር ሁኖ እዛው ግቢ ቀረ። የሚያሳዝነው ደግሞ ተማሪዎች በገቡ በመጀመሪያው ሳምንት ሁሉም ስለታቱዬ አወቁ። የፈሪ ትልቁ ችግር?....ምርኮኛ አያያዝ አይችልም! «ለማን ተናግረህ ነው?» ብዬ ሳፈጥበት...አብሮት ሌክቸረር ለሆነ ሰቃይ ጓደኛው ብቻ መናገሩን ነግሮ ይቅርታ ጠየቀኝ። እኔም ከተያዙ ቡኃላ መንፈራገጥ ጥቅም የለውም ብዬ ተውኩት። የግቢው አየር ባንድ ጊዜ ተገለበጠ። ሻማዬ የግቢው ቁጥር አንድ ተፈላጊ ወንድ ሆኖ ቁጭ አለ። እኔ ደግሞ ስወጣ ስገባ የተረባ መለማመጃ ሆንኩ። አንዴ ወጣቶች ተወራርደው አስገድደው ልብሴን ገልጠው፣ ታቱዬን ካዩብኝ ቡኃላ ከሀዘን የወጣሁበት ቀን ትዝ አይለኝም። ሻማዬ ሊጠብቀኝ ቀርቶ ቶሎ ቶሎ ሊያገኘኝ ራሱ ጥረት አያደርግም። እኔ ነኝ የምደውልለት። እንዲያውም አልናገርም ብዬ እንጂ አልፎ አልፎ የግቢው ታዋቂ ሴቶች ከቢሮው ሲወጡ አያለሁ። በአንድ ወቅት ሊነካኝ ከብዶት ሲንቀጠቀጥ የነበረ ሰው፤ ዛሬ መዳፉ ላይ ሲያገኘኝ ጨብጦ ሊያፈርጠኝ ሲዳዳ ባዬው...ለመረዳት ከበደኝ። የሆነ ቀን ጉዳዩን ጨራርሰን እንደተቀመጥን «ሰሞኑን መድሀኒት ስትጠቀሚ አላይሽም! ሌክቸረር ሆነ ብለሽ ልታረግዥብኝ ነውዴ?» አለኝ። በዚች ንግግሩ ታሪኬን ቀዬረው። ትምህርቴን አቋርጨ አዲስ ህይወት ጀመርኩ። ስሜንም ቀየርኩ። ታቱዬን ሙሉ ጥቁር አድርጌ "ብላክ ሆል" ነው እያልኩ መንገር ጀመርኩ። ሰላም ያለው ህይወት ለመኖር የነበረኝ አንድ አማራጭ ነበር። ሁሉንም ሰው ከህይወቴ አስወጥቼ ልጄን ማሳደግ። የዚያኔ እንደዛ ባለኝ ሰዓት ፀባዩ ሲስተካከል እነግረዋለሁ እያልኩ ያረፈድኩባት ፅንስ ነበረችኝ። አሁን አሁን ሳስበው ታሪኬ ረጅም ይመስላል እንጂ አጭር ነው። ይቺው ናት ውጣ ውረዴ! ልጄን እስካሳድግ ድረስ ሁለት ጊዜ ብቻ ነው ከቤተሰቦቼ ጋር የተገናኘሁት። እነሱም እምብዛም ሊያዩኝ አይፈልጉም። መላቀቅ ነው! ይቅሩብኝ ከነምላሳቸው! ምላስ ሽሽት ነው ነው ኑሮዬ! አልፎ አልፎ ስር እንዳይሰድ አድርጌ የወሲብ ግኑኝነት እጀምራለሁ። እነሱም ስለኔ ትንሽ ማወቅ ሲጀምሩ ጥያቸው ዲዲዲዲዲዲ! በዚህ ርዕስ ላይ ከማወራ ይሻለኛል። ልጄ በኔ መልክ ባባቷ ጭንቅላት በመውጣቷ ያገኛት ሁሉ ይወዳታል። እኔም በሷ እየተፅናናሁ እኖራለሁ። በቃ። ይሔን ሁሉ ቁጭ ብዬ የማስበው ዛሬ «አባቴ ማነው?» ብላ ጠይቃኝ ነው። ለመጀመሪያ ጊዜ ሩጨ የማላመልጣት ሰው ገጠመችኝ። የመመለስ ግዴታ እንዳለብኝ አውቃለሁ። ግን እንዴት ነው የአ'ምሮ በሽተኛ ሳላደርጋት ስለአባቷ ልነግራት የምችለው? ተረት ላድርገው ይሆን? እምብዛም የማይንቁት...እምብዛም የማያደንቁት የ'ንደኔ አይነቷ ኖርማል ሰው ህይወት እንዴት ነው የሚተረተው? «ተረት ተረት!» «የመሰረት!» «በድድሮሮሮሮ ጊዜ አንዲት ሔለን የምትባል፤ ከብርጭቆዋ ጋር ጨለማ ክፍል ውስጥ የምትኖር ልዕልት ነበረች።» «እእእሽ» «ሁሌም ሌቦች ብርጭቆዬን ይሰርቁብኛል ብላ ስለምትሰጋ ጨለማው ያስፈራት ነበር። ከዛ አንድ ቀን ምን ብታገኝ ጥሩ ነው?» «ምን?» «ሻማ!...በጣም ደስ አላት። ሻማዋን አብርታ እያዬች ደስ አላት። 'ይቺ ሻማ እስካለች አልሰጋም' ስትል አሰበች። ሻማዋ ግን 'እጠፋለሁ' ብላ ትሰጋ ነበር። ንፋስ በመጣ ቁጥር ትንፋሿ ቁርጥ ቁርጥ ይላል። ልዕልቷም ሻማዋን ከንፋስ ለማስጣል ብላ አንድ የሞኝ ውሳኔ ወሰነች!» «ምን አደረገች?» «በብርጭቆዋ ሸፈነቻት።» «ከዛስ?» «ከዛማ ሌባ ይገባል ብላ በር በሩን እያዬች ከኋላዋ ቃቃቃቃቃቃ የሚል ድምፅ ተሰማት። ደንግጣ ስትዞር የምትሳሳላት ብርጭቋዋ ናት። ንፋስ መቋቋም አቅቷት ልትጠፋ የነበረችው ሻማ በሙቀቷ ብርጭቆዋን ሰንጥቃባታለች። ልዕልቲቱ አዘነች። ውሀ አጣጯ ቢመጣም ውሀ መጠጫ እንደሌላት እያሰበች አለቀሰች! አለቀሰች!..» እያለ የሚቀጥል ተረት! ፨፨፨ March 19 2022 Mickel Azmeraw @WAS143 @WAS143
እስቲ ዛሬ ደግሞ ለለውጥ ያክል አለቃ ክንፌ የላኩልኝን ግጥም መሳይ ምክር ልጋብዛችሁ! (ለለጅ ምክር የአባት መታዘቢያ) ልዠ ሆይ! ሙቫይልህን አስቀምጥ ምክሬን አድምጥ ! ጦርነትን የሚጠምቀው እድሜውን ብትጠይቀው የማቱሳላ ገራዥ የአብርሀም ዣንጥላ ያዥ በጎሽ ያረሰ አዳምና ሄዋን ገምጠው የተፉትን በለስ አንስቶ የጎረሰ የሎጥን ሚስት ሀውልት የላሰ ሆኖ ታገኘዋለህ ፤ ልዠ ሆይ! ጦርነትን የሚያውጀው ያረጀው ነው የጃጀው ግና ጦርሜዳ ላይ የሚዋጋው ያንተ ብጤ ነው ለጋው፤ ሜሲ አንደመታት ኩዋስ ወደ መቃብር የሚልለጋው፤ ልዠዋ! በጀግኖች ዘመን እንኩዋ-“ከመሞት መሰነበት” ይባላል የሰማእት ሀውልት ሆኖ ተመቆም ህያው ሆኖ መተኛት ይሻላል ልዠ ሆይ! በሀያላን እንዳትታፈስ ሁንባቸው መንፈስ መንፈስ መሆን ቢሳንህ ; ሁንባቸው የጎመን ፈስ ቀን እስኪያልፍ ድረስ ወደ ጎረቤት አገር ንፈስ፤ ልዠ ሆይ ! ጦርነት ማለት አንድ ሀሙስ የቀራቸው ሸባዎች፣ አንድ ሀሙስ ብቻ የኖሩትን አበባዎች የሚያስቀጥፉበት አዝመራ ነውና በሰማእትነት ስም ምትክ አልባ ሕይወትህ ሳይከስም እሸት አካልህን ሳይለውጡት ወደ ፍግ ተግተህ አፈግፍግ፤ ልጄ ሆይ! ለማንም ኩስለመናም ነፍስ ይማር ለማለት አንኩዋ ጊዜ ለሌለው የሙቫይልህን ካሜራ አንጂ ጠመንጃህን አትወልውለው፤ አለቃ ክነፌ በተሳትፎዎ ይቀጥሉበት! @WAS143 @WAS143
ወጣቶች ነበርን በእውቀቱ ስዩም ጊዜ ሲራመድ ኮቴው ድምጥ አልባ ከየት ተነስቶ ወደ የት ገባ ከየት ተነስቶ ወዴት ደረሰ ጠጉር መንጥሮ፣ ፊት እያረሰ፤ ወጣቶች ነበርን ቅጽር የሰራን ፤ አምባ የሰበርን ኮካ ኮላውን ባሲድ በርዘን ብንጎነጨው፤ የማይመርዘን፤ በራዱን ያጋልን፣ ሙት ልብ ያስነሳን ግራዋ በልተን ፤ ሎሚ ያገሳን፤ ተስፋችን ብዙ፤ እድሚያችን ለጋ ስንሰማራ፣ ትርጉም ፍለጋ ገላችን አይፈዝ፣ ጭቃ ቢለሰን የማናስቀይም፤ ቡትቶ ለብሰን ገጻችን ብሩህ፤ ልባችን ሽፍታ ስንመነጠቅ፤ ወደ ከፍታ የስኬት ገነት፣ ደጃፏን ከፍታ ምትቀበለን ፣ እየመሰለን ከቁመታችን በላይ፣ የዘለልን፤ ወጣቶች ነበርን ዛሬ እንደዋዛ ዘንድሮን ምሰን፤ ታችአምናን ቀበርን፤ @WAS143 @WAS143
የጋራ ድል (በእውቀቱ ስዩም) የስፔን ደጋፊ ብሆን ምን ያስገርማል? ስፔን በስነፅሁፍ አክብራ የጋበዘችኝ አገር ናት፤ ስፔን ሁለተኛ አገሬ ናት ብል ኩሸት አይሆንም፤ ስፔን እንድታሸንፍ ፈልጊያለሁ፤ ያም ሆኖ፣ ከጉዋደኛየ ከካሳ ጋራ አር-ጄንቲና ታሸንፋለች ብየ በአራት ሺ ብር ተወዳደርሁ፤ ስፔን ካሸነፈች እፈነጥዛለሁ፤ አርጄንቲና ካሸነፈች ደግሞ ላብ ያልገነፈለበት ፣ እንቅልፍ ያልተሰዋበት አራት ሺ ብር አካውንቴን ያጠበድላል ብየ አሰብኩ፤ በሁለቱም በኩል አሸናፊው ነኝ የሚል መላ መጣልኝ፤ በመጨረሻ እንዳያችሁት ስፔን፣ በረኛ ሳይሆን በር የሆነውን የአርጀንቲናን ግብጠባቂ ጣጥሳ አገባች፤ ዋንጫውን ጨበጠችው፤ደስ አለኝ፤ግን ደስታየ ወደ ፈንጠዝያ አልተሸጋገረም፤ ለካ ደስታ ስነልቦናዊ ነገር ሲሆን ፈንጠዝያ ግን የዳበረ ኢኮኖሚ የሚጠይቅ ነገር ኑሩዋል! እያደር የአለም የእግር ኩዋስ የእግር እሳት ሆነብኝ☹ የአራት ሺ ብሬ መሄድ ፣አካውንቴ ላይ ያለው ቁጥር መመናመን ዋንጫውን መራራ ጥዋ አደረገብኝ፤ -“ ካሸነፍኩህ አራት ሺ ብሩን ፣ ስፔን ኢምባሲ ፊትለፊት ለሚቀመጡ ነዳያን እመጠውተዋለሁ- “ሲለኝ የነበረው ካሳ ዛሬ በማለዳው ወደ ፍቅሬ ኩንስፓኛ ሲገባ አየሁት፤ ቅን ስለማስብ፣ ለናዳያኑ ዱለት ሊያስቁዋጥርላቸው እንደሆነ ገመትኩ፤ ካሳ ወደ ምግብ ቤቱ ሲገባ ጀርባውን እያየሁ የቆየ ወግ ትዝ አለኝ፤ አንድ ባለሀገር ተጎጃም መጥተው ጎጃም በረንዳ አካባቢ ሲማስኑ ቆይተው ሱርያቸውን ቢዳብሱ በምስጢር ኪሳቸው የቁዋጥሩዋት ሶስት መቶ ብር የለችም ፤ መገን ያራዳ ልጅ መንትፎዋቸዋል፤ ከዚያ ፣አንድ የተሳቢ መኪና ሹፌርን እርዳታ ለምነው ከማዳበርያ ጋር ተደርበው ተጭነው ወደ አገራቸው መመለስ ጀመሩ፤ ግን እንጦጦ አፋፍ ላይ ሲደርሱ ፊታቸውን ወደ ሸገር በር መለስ አድርገው ቁጭት ባጠላበት ድምጥ አንዲህ አሉ፤ “ ሸዋ! እንግዲህ ተኝተህ ብላ” @WAS143 @WAS143
"ባጭር ቀረን" ስንል - እድሜ ላበደሩን ቀርፀው ላሳመሩን ለኩሰው ላበሩን ቺርስ!! ።።።። ፊታችንን ዐይተው እንደተቸገርን - ካይናችን ላወቁ ስለማርያም ብለን እስክንለምናቸው - ቆመው ላልጠበቁ ቺርስ!!! ።።።። ወድቀው ለማይጥሉ -ነግሰው ለሚያነግሱ ነውራችንን ዐይተው ልክ እንደ ድመት ኩስ ፣ ለሚያለባብሱ ብድር አበድረው ፣ ፈጥነው ለሚረሱ😉 ቺርስ!!!! ።።።።።። ላባ ላረጉልን ፣ የመከራ ሸክሙን ቀልደው ላሳቁን ፣ ተጫውተው ላከሙን በቸከ ዘመን ላይ... ስጋ ለበስ ትንግርት -ሆነው ላስደመሙን ቺርስ!!!!! ።።።።።።።።።።። (✍️ Bewketu Seyoum ) መልካም ልደት በውቄ!!! @WAS143 @WAS143
ኦሮማን (በእውቀቱ ስዩም) ሰሞኑን እንደ አዲስ አስቴር አወቀን ሳደምጥ፣ በአሉ ግርማ ትዝ አለኝ፤ የበአሉን ኦሮማይ ታስታውሱታላችሁ ? ፀጋየ ሀይለማርያም ጋዜጠኛ ነው፤ ሮማን የተባለች ውብ ኩሩ እጮኛ አለችው፤ ሊጋቡ ጥቂት ወራት ሲቀራቸው በቀይ ኮከብ ጥሪ አስመራ ለግዳጅ ተላከ፤ በዚያም በዘመቻው መሀል ፊያሜታ የተባለች ያስመራ ሴት ተዋወቀ፤ ከባድ ፎንቃ ገባለት፤ ባስመራይቱና በሸገሪቱ ሴቶች ፍቅር መሀል ተወጥሮ በታሪካዊው ዘመቻ ላይ ተሳተፈ ፤ በመጨረሻ ሮማን አስመራ መጥታ ከሌላ ሴት ጋር ፍቅር አንደያዘው ተረዳች፤ ፊያሜታ ለሱ ብላ ህይወትዋን ትሰጣለች፤ በመጨረሻም ፊያሜታን በሞት ሮማንን በቅያሜ አጥቶ አጥቶ ብቻውን ሲቀር ልቦለዱ ይጠናቀቃል፤ ሮማን አዲስአበባ ሆና የአስቴር አወቀን ክር ካሴት ልካለት ነበር፤፤ ፊያሜታ ሮማን የላከችውን ካሴት ሰባብራ ክሩን ጎልጉላ ፊቱ ላይ የምትነበትንበት ትእይንት አይረሳኝም፤ አሁን ድንገት ጉደኛ ሀሳብ ብልጭ አለልኝ ፤ ኦሮማይን የደረሰው ስብሀት ቢሆን ኖሮ ብየ አሰብሁ፤ አንዲህ ነበር የሚሆነው፤ ሮማን እና ፊያሜታ አስመራ ተገናኝተው እየተጨዋወቱ ነው፤ -ስትገናኙ እጮኛው መሆኔን ነግሮሽ ነበር ? “አለች ሮማን ፊያሜታ ራስዋን በአዎንታ ነቀነቀች፤ “እና እጮኛ አንዳለው እያወቅሽ አፈቀርሽው?” ፊያሜታ ጸጉሯን ነስንሳ “አዝናለሁ፤ ነገሩ እዚህ ይደርሳል ብየ አላሰብኩም ነበር፤ ሕይወት አንደ ደራሽ ውሀ ገፍቶ የት አንደሚያደርሰን አናውቅም’ አለችና በስፕራይት ጠርሙስ የተቀዳ ቢራዋን ተጎነጨች፤ የቢራ ጠርሙሶች ተለቅመው ለምሽግ መስርያ ወደ ናቅፋ ስለተወሰዱ አስመራ ውስጥ የቢራ ጠርሙስ እጥረት ሰፍኑዋል፤ ለጥቂት ሰከንዶች በዝምታ ተዋጡ፤ “ ጸግሽ ነገ ወደ ግንባር ይሄዳል” አለች ሮማን፤ “ አውቃለሁ “ መለሰች ፊያሜታ፤ “ በወጣበት ይቀራል የሚል ስጋት አለኝ ‘ አለች ሮማን እንባ ባቀረረ አይን የናቅፋ ተራራ ወዳለበት አቅጣጫ እየተመለከተች” “ አትስጊ፣ ሻእቢያ ጋዜጠኛ አይገድልም” አለች ፊያሜታ በውስጥ አዋቂ ስሜት ; “አይምሰልሽ፤ ሻቢያ ከመድፍ በላይ ብእር፣ ወረቀትና ካሜራ ያሰጋዋል፤ ጠመንጃቸውን የሚያሙዋሹት ፀግሽን በመግደል ይሆናል” ፊያሜታ ዝም አለች፤ ሮማንም በጸጥታ ስታስብ ከቆየች በሁዋላ፤ “የምታግዥኝ ከሆነ ለጸግሽ አንድ የመጨረሻ ስጦታ ልሰጠው አስቢያለሁ” “ምን ?” አለች ፊያሜታ፤ ‘ ጸግሽ አንችንም እኔንም እኩል አንደሚያፈቅር አውቃለሁ፤ ለሚያፈቅራቸው ሴቶች አንደ ሞት ማበላለጥ አያውቅም፤ስለዚህ በህይወቱ የመጨረሻዋን ሌሊት አብረነው አንድናሳልፍ እፈልጋለሁ፤ “የምርሽን ነው?” ፊያሜታ በግርምት ጠየቀች፤ “አንድ ጀግና ለብዙሀን ህይወቱን መስጠቱ አግባብ ከሆነ ፣ ብዙሀን ላንድ ጀግና እቅፋቸውን መስጠታቸው ተገቢ ነው” አለች ሮማን ፍርጥም ብላ፤ ያን እለት ማታ፣ ፀጋየ በሮማንና በፊያሜታ መሀል ፣ባራት ጡቶች መሀል፣ አንደተንጋለለ በልቡ አንዲህ አለ፤ “ ይገርማል ! ሻእቢያና ደርግ ስልጣንን እንዲህ መጋራት ቢያውቁ ኖሮ ባፍሪቃ ቀንድ ለዘላለም ሰላም ይነግስ ነበር” @WAS143 @WAS143
በረንዳ (በእውቀቱ ስዩም) ባለፈው ከያሬድ ሹመቴ እና ከምኡዝ ጋራ የሆነ ምግብ ቤት በረንዳ ላይ ቁጭ ብለን ምሳ ስንበላ አንድ ጎስቆል ያሉ አዛውንት መጡና “ልጆቸ ርቦኛል “አሉን ምኡዝ ፣ “ካለ ይስጥዎት” አላቸውና መብላቱን ቀጠለ፤ ያሬድ ምኡዝን ክፉኛ ገላመጠውና’ ‘ አባቴ ቁጭ በሉና ከኛ ጋር ይብሉ” ብሎ ጋበዛቸው፤ እኔ አዛውንቱ እንዲበሉ ፈልጊያለሁ፤ ግን አብሮ መብላቱን ልቀበለው አልቻልኩም፤ ስለዚህ “በልተን ሲበቃን የተረፈውን እንሰጣቸዋለን” የሚል ለጽድቅ የማያበቃ ለኩነኔም የማይዳርግ ሀሳብ አቀረብኩ፤ ያሬድ ግን አመረረ “ሂዱና ታጥበዎ ይምጡ አባቴ” አላቸው፤ ምኡዝ በንዴት ጨሰ፤ “ለምን ሜቄዶኒያ ቁጥር 2 ብለህ አትከፍትም?” ብሎ አንባረቀበት፤ “ምንድነው ችግርህ ? “ አለው ያሬድ; ምኡዝ ለወሬ የማይመች ሰፊ ሀተታ አቀረበ፤ ሲጨመቅ ይህን ይመስላል፤ (አንድ ሰው ራሱን መመገብ የማይችል ከሆነ፤ ሰነፍ ነው፤ አለያም ደደብ ነው፤ አለያም አቅመቢሰ ነው፤ ወይም አመለ ቢስ ነው፤ ከሰዎች ጋር ተስማምቶ መስራት አይችልም፤ ታድያ አንዲህ ያለው ሰው ለመኖር አይመጥንም፤ ብትረዳው አታሻሽለውም፤ ስታበላው በምድሪቱ ላይ ሸክም የሚሆንበትን ጊዜ ታራዝምበታለህ እንጂ አትጠቅመውም ) ሰውየው ታጥበው መጥተው ከኛ ጋራ መብላት ጀመሩ፤ ሰማንያ ያህል የቴኒስ ኩዋስ የሚያካክሉ ጉራሾችን ወዳፋቸው ከወረወሩ በሁዋላ በረጅሙ ተንፍሰው “ ሆሆ ለዚህ ሆዴ ይጠላኛል ዘመዴ አለች እርያ” ብለው ተረቱ፤ ከዚያ ወደኔ ዞር ብለው - “ አጅሬው ለካ ይቺን እየዋጥህ ነው የጉሬዛ ሙሽራ የመሰልከው” አሉና ብቻቸውን ሳቁ፤ ከዚያ ወደ አስተናጋጁዋ ዞረው “አንቺ ቂንጥራም እስቲ አንድ ሲንግል ድራፍት ወዲህ በይ “ ብለው ጮሁ፤ ‘አባቴ ስሚናገሩት ነገር ጥንቃቄ ያድርጉ፤ ደሞ እዚህ ድራፍት አይሸጥም” አለ ያሬድ፤ አዛውንቱ የያሬድን ግሳፄ ከመ ገብስ አልቆጠሩትም፤ በር ላይ ቆሞ ለውዝ ወደ ሚሸጠው ልጅ ልጅ እየጠቆሙ” ያን ጥንዚዛ ባርያ ብንለከው ከጎረቤት አያመጣልንም ?” አሉ፤ በመጨረሻ ያሬድ “ሚስት አለዎት ? ` በማለት ጠየቃቸው፤ “እሱማ አለችኝ” አሉ በታከተ ድምጥ፤ “የተረፈውን ይውሰዱላት” አዛውንቱ ፈገግ ብለው የመለሱትን ባልፅፈው ደስ ይለኝ ነበር; “ምሽቴማ ይሄን ተቀመሰች ጥጋብዋን አልችለውም፤ ባይሆን ለውሽማየ እቁዋጥርላታለሁ’ @WAS143 @WAS143
ቅንጦትን ስሻ (በእውቀቱ ስዩም) ለነገ አይልም ፣ ከላይ ሲያዳላ ላንደኛው ቴስታ፣ ለሌላው ቴስላ፤ እኔም በፈቃድ፣ ዝተት ለብሼ በፎቆች መሀል፤ ድንኩዋን ቀልሼ ቃርሚያ ፈጭቸ፤ ኩርማን ጋግሬ ጎመን አስግሬ እንጀራ አጥምጄ በቃኝ ማለትን ፣ተለማምጄ ስኖር፣ ከሌላው፣ አያዳላልኝ ቅንጦትን ስሻ፣ አንቺን ላከልኝ:: @WAS143 @WAS143
የዛሬ 4 አመት የባለፈው የአለም ዋንጫ ሲካሄድ የት ነበራችሁ? ከነማን ጋ ኳሱን አያችሁ? ያኔ ስራችሁ ምን ነበር? ህይወታችሁስ እንዴት ነበር? ጊዜውን ዞር ብለን ስናየው 4 ሳይሆን 40 አመት ያለፈ ነው ሚመስለው፡፡ብዙ ነገር ተቀያይሯል፡፡ከጊዜው በላይ ብዙ ነገር ያየን ይመስለኛል፡፡ያገባው ፥ የወለደው ፥ የተሰደደው ፥ የሞተው ፥ የታገተው ፥ የጦርነቱ ብዛት ፥ የትርምሱ ብዛት ፥ የሚያስደነግጠው እና የሚረብሸው ነገር ብዛት ፥ ብቻ ማየት የማይገባንን ብዙ ነገር አየን፡፡እንደው እኔ ለዚህች ሀገር ብቸኛ የምመኝላት ነገር ሁከት አልባ 4 አመት ሳይሆን 4 ወር እንዲኖረን ነው፡፡ከዚያ እዚህ ግን ይቺን ምርጥ የhabtamu hadera ግጥም ጣል ታረግባታለህ አንዴ ብቻ ይድላኝ አንዴ ብቻ ልረፍ አንዴ ብቻ ልኑር አንዴ ብቻ ልትረፍ ፋታ ብቻ ላግኝ እንደምፈልገው እንዴት እንደማለቅስ እኔ ነኝ የማውቀው ። @WAS143 @WAS143
ወይ ወደ ልጅነት ፥ መመለስ ሳያምረው ወይ ተስፋ ሚሆነው ፥ ወደፊት ሳይኖረው እንዴት ነው የሰው ልጅ ፥ ዝም ብሎ ሚኖረው ? ለድሮው ያደላል ፥ የሰው ልጆች ሚዛን ከዛሬዋ ፀሐይ የአምና ጨለማ ነው ፥ እኛን የሚገዛን ። ትዝታ ያጠግባል ትናንት ሆድ ያባባል የናፈቅነው "ነገ" ፥ ያንሳል "ዛሬ" ሲባል ። አምና የሰማነው አምና ያነበብነው ዘፈን እና ግጥም ከዛሬው ባይበልጥም ስላለፈ ብቻ ፥ እንዴት እንደሚጥም ! ጎዳናው ፣ መንገዱ ቢደምቅ ዘመኑ ፥ እንደ ጉድ ቢረቅ እንደ አምና የለውም አቅም የድሮውን አያስንቅም ሰው ባሳለፈው ትዝታ እንጂ ፥ በዛሬው ረክቶ አያውቅም ። @WAS143 @WAS143
ወይራው (በእውቀቱ ስዩም) ስለባርሴሎና ቆይታየ በቁምነገርና በጨዋታ የመዘገብኩት አለ፤ ቁምነገሩን ላዘቦት ቀን ላዘግየውና ጨዋታውን ላቃምሳችሁ፤ ባርሴሎና ወደ ሜዲትራንያን ውቅያኖስ የቀረበች ከተማ ናት፤ ባርሳዎች ወደ ሰሜን አፍሪካ ዘንበል ይላሉ ፤ ከሞሮኮዎች ጋራ ሲገናኙ አኛ የወንዜ ልጅ እንደምንባባል እነሱም የውቅያኖሴ ልጅ ይባባላሉ፤ ከተማ ውስጥ የሚርመሰመሰው የደላው፣ ያማረ የተዋበ ህዝብ ነው፤ የሴቶች ቁንጅና ከመብዛቱ የሆነ ጊዜ ላይ የተነሳ እጅ እጅ ይልሀል፤ አራት ቀናት ያክል ሆቴል ተቀምጫለሁ፤ አዘጋጆች፣ ከቁርስ በቀር ምሳና ራት የምበላበት ስምንት ያህል ካርድ ሰጥተውኛል፤ እኔ ግን የሰጡኝን ካርዱን ሁሉ አሙዋጥጨ አልተጠቀምኩበትም፤ በቀን አንድ ጊዜ ብቻ እየበላሁ ፤ ኣራት ካርድ ብቻ ተጠቅሜ ሌላውን መለስኩላቸው፤ ኤርምያስ አመልጋ በቀን አንዴ ቢበላ ለጤናው ሄኖክ ወንድም ደግሞ ለኪናዊ ተልእኮው ነው፤ አንተስ ለምን ብትሉኝ መልሴ ግልጥ ነው፤ በምግብ ከተጎዳ አገር መጥቶ ፣ አገኘሁ ብሎ ሲወጥቀው ሰነበተ አንዲሉኝ አልፈለኩም፤ ( ላንቺ ነው ኢትዮጵያ፤ ያንን የመሰለ ሳልመን ጥብስ እያማረኝ የማርኩት አንቺን ላለማስፎገር ነው🙂 ) የአውሮፓ ምግብ ብዙ አይመቸኝም፤ ያማረና የጣፈጠ ነገር በመስራት ጥልያን ፈረንሳይ ይሻላሉ መሰል፤ ግም መብል ያለው እንግሊዝና ጀርመን ነው፤ ጀርመን በድንች የቆረበ ህዝብ ነው ማለት ይቻላል፤ ግብዳ የተቀቀለ ድንች ይሰነጥቁና በውስጡ ሌላ ሚጢጢ ድንች ይቀረቅሩበታል፤ ከዚያ እንደደና ነገር አንስተው በጥርሳቸው ይመግዙታል፤ ዶነር የተባለ ምግብ መሰል መኖም አላቸው፤ ያንን ከበላህ ጤፍ የለመደ ሆድህ በጀርባህ ይዞራል፤ ለመፍሳትም ራሱ የሀኪም እገዛ ያስፈልግሀል፤ ባርሳዎች ምግባቸው የጨዋ ፣ መጠጣቸው የአማልክት ነው ፤ በየመብሉ ውስጥ ወይራ በተለያየ መንገድ ይገባል)፤ሰላጣው አሳው በወይራ ዘይት ነው ሚሰራው ፤ ዳቦው ሳይቀር ወይራ ገብቶበታል፤ እኛ ለመቆዘምያ ቆሉ አንደምንቆረጥም እነሱ ደግሞ የወይራ ፍሬ እየቀማመሱ ይደብራሉ፤ ካንዱ ጋራ ስናወራ “እናንት አገር ምን አይነት ዘይት ነው የምትጠቀሙት?” ሲል ጠየቀኝ፤ “ ልጅ ሳለሁ ከአባ ታምሩ ወፍጮ ቤት የተጨመቀ የኑግ ዘይት ነበር የምንጠቀመው፤ አሁን ዘይት ብለው የሚሸጡልንን ፈሳሽ ግን የሱፍ ይሁን ያደይ አበባ ማወቅ አልቻልኩም “ በማለት መለስኩለት፤ “ወይራ የላችሁም?” ‘ትቀልዳለህ እንዴ? አስቴር አወቀ “ክትክታና ወይራ ‘ብላ ስትዘፍን አልሰማህም ?ወይስ ጭራሽ አስቱነትን ታውቃትም? እኛኮ የናንትን አገር ኩዋስ ተጫዋቾት የጫማ ቁጥር ሳይቀር እናውቃለን ፤ እስከመቸ አናንተን ብቻ እያወቅን እንኖራለን ? በፈረቃ አንተዋወቅ እንጂ! ለማንኛውም ወደ ጥያቄህ ስመለስ ወይራ አለን፤ ግን ወይራውን የምንጠቀመው ለዘይት አይደለም፤ እናቴ ጠላ ከመጥመቁዋ በፊት ጋኑን በወይራ ታጥነው እንደነበር አልረሳም፤ በወይራ የታጠነ ጋን ጠላ ያጣፍጣል ሲባል ሰምቻለሁ፤ ከዚያ በተረፈ ደግሞ አባቴ የወይራ ሽመል ነበረው” “ጣሙ አንዴት ነው ታድያ ?” “የጠላውን የመቅመስ እድል አልነበረኝም፤ የሽመሉን ግን ካንድም ሁለቴ አጣጥሜዋለሁ፤ አና ይሄውልህ፤ በልጅነቴ ያስመረረኝን ወይራ እናንተ አገር መጥቸ ተበቀልሁት “ @WAS143 @WAS143
መታያ (በእውቀቱ ስዩም) በማህበራዊ ሚድያ የሚታወቅ ጉልቤ ልጅ አለ፤ ስፖርትን አጥብቆ ይሰራል፤ መብል ላይም አይሰንፍም ፤ ደግነቱ በልቶ አስመሰጋኝ ነው፤ የተትረፈረፈ ጉልበት እንዳለው ያስታውቃል፤ የመኪና ጎማ በርግጫ መትቶ ወደ በረባሶ መቀየር የሚችል ፍጡር ነው፤ ችሎታውንና ጉልበቱን ለማሳየት ከሚጠቀምባቸው ነገሮች አንዱ ያስገርመኛል፤ ችግር ከክፍለሀገር አባርሮ ያመጣቸው ሊስትሮዎችን በርጥብ አፋቸውን እንዲሽሩ ካደረገ በሁዋላ የራስቅላቸውን በኩርኩም እየደፈጠጠ ይቦድድባቸዋል ፤ የሆነ ጊዜ ላይ አንዱን ምስኪን “ አንገቴ አንቀህ ያዘኝ “ብሎ አዘዘው ፤ እነቀኝ ባዩ ሲጀመር አንገት የለውም፤ የጎማ ክምር በቴስታ አብዝቶ ከመምታቱ የተነሳ አንገቱ ወደ ደረቱ ሰጥሞ ከሳንባው አጠገብ ጥገኝነት ጠይቁዋል፤ ምስኪኑ አንገቱን ከደረቱ ለመለየት ሲዳብስ ጉልቤው ዠለስ ከታች በጠረባ አንሳፈፈው፤ ጠረባው የተለመደው ያደግንበት ጠረባ እንዳይመስላችሁ፤ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት በፈንጅነት መመዝግብ ያለበት ነው፤ ይህ በእንዲህ እያለ የኪክ ቦክሰር ግጥሚያ አዘጋጆች የበቀደሙን አሸናፊ አንዲገጥም ጥሪ አቀረቡለት ፤ አጅሬ በክፍያ ማነስ እያሳበበ ማፈግፈግ ጀመረ፤ የቲኬቱን ሙሉ ክፍያ ቢሰጡት ራሱ የሚወዳደር አይመስለኝም፤ ይሄ ሰውየ የብዙዎቻችን ምሳሌ ነው፤ በዚህ አለም ጀግና ተብለው የሚጠሩ ሰዎች የሆነ መስዋእትነት የከፈሉ ናቸው ፤ አካልህን ሰላምህን ፣ምቾትህን ይባስ ብሎም ሕይወትህን ሳትገብር የጀግንነት አክሊል የድል ብስራት የለም፤ “ትግሉን ስትጀምር በነበረው ቁመናህ ትግሉን ከጨረስህ አልታገልህም ማለት ነው” ይላል ምኡዝ ፤ ብላቴና እያለሁ፤ በከተማችን እንዲህ ሆነ፤ ደረቱ ላይ ድንጋይ ያስፈልጣል የሚባል ሰውየ ወደ ከተማችን ብቅ አለ፤ ህዝቡ ያንድ ብር ትኬት ገዝቶ በመግባት ትርኢቱ የሚታይበትን የቀበሌ አዳራሽ አጨናነቀው፤ አስፈላጩ በጀርባው ተኛ ፤ ረዳቱ ለአቅመ ወፍጮ የደረሰ ድንጋይ ደረቱ ላይ አስቀመጠለት፤ አስፈላጩ በረጅሙ ተነፈሰና” አንት የድንባዣም ልይ! እምብርቴ ላይኮ ነው የጎለትከው፤ ምነ ትንሽ ወደ ላይ ፈቀቅ ብታረገው “ብሎ አዘዘው፤ ረዳቱ እንደታዘዘው አደረገ፤ ከዚያ ረዳቱ የበርሊን ግንብን ለማፍረስ ያገለገለ ግብዳ መዶሻ አንስቶ ድንጋዩ ላይ ማነጣጠር ጀመረ፤ አስፈላጩ ሰውየ “ ቆይ ለማሙዋሻ ያህል በመርቴሎ ሞክረው” ሲል ለመነው ፤(መርቴሎ ሚስማር ማስገቢያና መንቀያ ቲንሽ መዶሻ ናት ) ከብዙ ደቂቃዎች በሁዋላ ህዝቡ ማጉረምረም ጀመረ፤ “የምታረጉትን አድርጉና አሰናብቱን እንጂ፤ ስራ አለብንኮ ‘ አለ ህዝቡ፤ ይህን ጊዜ አስፈላጩ በጀርባው አንደተንጋለለ አንዲህ አለ፤ “ተቸኮላችሁ ህዱ ! ውጤቱ በማታው የስፖርት ዘገባ መቅረቡ አይቀርም፤ በዚያ ታልቀረበ በፖሊስና ህብረተሰብ ፕሮግራም ላይ ጠብቁት”🙂 @WAS143 @WAS143
ናፈኩህ ብትይኝ ሰራው መቅደስሽን ሰርክ ዘመምኩልሽ የፍቅር ወረብሽን። : ቃልሽን አምኜ እምነቴን ገነባሁ በይ እስኪ ንገሪኝ.... ጠላሁ ብትይኝ የት ነው የምገባው? @WAS143 @WAS143
ቀስቃሽ (በእውቀቱ ስዩም) “ቲክቶክ ላይ ወሲብ ቀስቃሽ ዳንስ እየደነሱ”፤ የሚል ውንጀላ በወይዛዝርት ላይ የምታቀርቡ ቅዱሳን፤ እስቲ ስሙኝ አንተ አንድ ሴት ሰትደንስ ባየህ ቁጥር የሚቀሰቀስብህ ከሆነ ችግሩ ከሞተርህ ነው፤ ከዳንሱ ወይም ከሴቲቱ ወይም ካለባሷ አይደለም፤ ይሄ የቆላ እባብህ ቀጠን ያለ ድምጥ በሰማ ቁጥር እንደ ሰርኬስ ባቡር የሚገተር ከሆነ እኛ ምን እናድርግ! አባብለህ ወይም ቆንጥጠህ አስተኛው! ከሰባት አመታት በፊት ሚኒሶታን ስጎበኝ ጉዋደኞቼ የልደት ቀኔን በማስመልከት የሆነ ክለብ ይዘውኝ ገቡ፤ ክለቡ ቆነጃጅት ሴቶች በምሶሶ ዙርያ እየተንጯዋለሉ የሚደንሱበት ነው፤ ከዲያፖራ ጉዋደኞቼ አንዱ ተንኮለኛ፣ ላንዲቱ ደናሽ ጉርሻ ሰጠጣትና ወደኔ ጠቆማት ፤ በተቀመጥኩበት መጥታ ጭኔ ቁጭ ብላ መደነስ ጀመረች፤ ሌላ ሰው ቢሆን እዚያው አንድ ጀሪካን ዲዲቲ ይረጭ ነበር፤ እኔ ወንድማችሁ ግን ራሴ ለመግዛት አጥብቄ ተጣጣርሁ ፤ በሰው አገር አንዳይቀሰቀስብኝ ስለሰጋሁ ስለ ስድሳ ስድስቱ ደርቅ እና ስለ ህዳር በሽታ በማሰብ ሞተሬ ፀጥ ለጥ ብሎ እንዲቆይ አደረግሁት፤ ዳንሰኛዋም በጭምትነቴ እጅጉን ተደንቃ ከተሸለመችው በርካታ ዶላር የተወሰነውን የሸሚዜ ጎንፍ ውስጥ ከተተችልኝ ፤ እኔም በዶላሩ በሚኒሶታ ለሚኖሩ የጎዳና ታዳዳሪዎች ብርድልብስ ገዛሁበት፤ “መቀመጫቸውን በዳንስ እየወዘወዙ “እያላችሁ ሴቶቹን የምትከሱ ራሳችሁን የሾማችሁ፤የስነምግብአር ጠበቃዎች ሆይ ስሙኝ! ሲጀመር፣ መቀመጫ ከእግር ራስጌ ስለተሰራ ባይደንሱበትም መወዛወዙ አይቀርም፤ ተፈጥሮው ውዝዋዜ ነው፤ እሱን ትታችሁ ትከሻ ማጅራትና ክርን ላይ በማተኮር ከቅስቀሳው ለመዳን ሞክሩ! በርግጥ፣ የምትወዛወዝ ሴት ስታይ የሚቆምብህ ከሆነ የሚወዛወዝ ዛፍ አይተህ እንደማይቆምብህ ርግጠኛ ልንሆን አንችልም፤ ከቻልህ ራስህን ግዛ ፤ ካልቻልህ ደግሞ ማለስለሻውን ግዛ፤ @WAS143 @WAS143