tgindex
Последний пост
27 июл.
Последнее чтение
13 авг.
Постов за неделю
0
Всего постов
25
Тип
открытый
Язык
und
В каталоге с
13 авг.
Подписчики
15 510
−68 за 4 дн.
Сутки
−25
−0,16%
Неделя
 
Месяц
 
Просмотров на пост
3 260
25 постов
Вовлечённость
21,0%
к подписчикам
Постов в день
0,0
всего 25
Упоминаний
0
каналов
Охват размещения
оценка
1/24сутки в ленте
1 096
1/48двое суток
1 256
1/72трое суток
1 354

Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.

Посты

  • 27 июл.1 2496

    ሰበር''ኢሰመጉ በምስራቅ አርሲ ከ450 በላይ ሰዎች መገደላቸውን ይፋ አደረገ'' የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ጉባዔ (ኢሰመጉ) በኦሮሚያ ክልል፣ ምስራቅ አርሲ ዞን በተለያዩ ወረዳዎች ''ከ2014 ዓ.ም እስከ ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ'' በተፈጸሙ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች ላይ ያካሄደውን የምርመራ ግኝት ይፋ ባደረገበት 158ኛ ልዩ መግለጫው፣ ቢያንስ ከ450 በላይ ንጹሃን ዜጎች መገደላቸውን አስታወቀ።…

  • ሰበር''ኢሰመጉ በምስራቅ አርሲ ከ450 በላይ ሰዎች መገደላቸውን ይፋ አደረገ'' የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ጉባዔ (ኢሰመጉ) በኦሮሚያ ክልል፣ ምስራቅ አርሲ ዞን በተለያዩ ወረዳዎች ''ከ2014 ዓ.ም እስከ ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ'' በተፈጸሙ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች ላይ ያካሄደውን የምርመራ ግኝት ይፋ ባደረገበት 158ኛ ልዩ መግለጫው፣ ቢያንስ ከ450 በላይ ንጹሃን ዜጎች መገደላቸውን አስታወቀ። ሀገር በቀሉ የሰብዓዊ መብቶች ተሟገች ድርጅት በ37 ገጾች ቀንብቦ ባወጣው ሪፖርት መሠረት፣ በዞኑ በሚገኙ ዘጠኝ ወረዳዎች ውስጥ በታጣቂ አካላት ማንነትንና ኃይማኖትን መሰረት በማድረግ በተፈጸሙ ጥቃቶች የሰው ህይወት ከማልፉ ባሻገር፣ በርካታ ዜጎች ለአካላዊ ጉዳት፣ ለእገታ እና ለአስገድዶ መሰወር ተዳርገዋል። በተጨማሪም ከ14,000 በላይ ሰዎች ከቀያቸው የተፈናቀሉ ሲሆን፣ በርካታ አብያተ ክርስቲያናትና የግል ንብረቶች መዘረፋቸውንና መውደማቸውን አመልክቷል። ኢሰመጉ ባካሄደው የመስክ ምልከታና መረጃ የማሰባሰብ ስራ፣ በጥቃቶቹ ሳቢያ በየወረዳው የተመዘገበውን የሟቾች ቁጥር እንደሚከተለው አሰናድቶታል፡፡ መርቲ ወረዳ፣ 117 ሰዎች፤ ሽርካ ወረዳ፣ 116 ሰዎች፤ ጀጁ ወረዳ፣ 101 ሰዎች ፤ ሮቤ ወረዳ፡ 47 ሰዎች ፤ ጉና ወረዳ፣ 26 ሰዎች ፤ ሆንቆሎ ዋቤ ወረዳ፣ 20 ሰዎች ፤ ሙኒሳ ወረዳ፣ 19 ሰዎች ፤ አሰኮ ወረዳ፡ 5 ንጹሃን ዜጎች እና 4 የህዝብ ሚሊሻዎች ፤ አርሲ ሲሬ ወረዳ፣ 3 ሰዎች በተጠቀሰው የጊዜ ሰሌዳ ውስጥ ሕይወታቸው አልፏል፡፡ ጉባኤው የሟቾችን ስም ዝርዝር ከነምስላቸው አስደግፎም ነው በሪፖርቱ ይፋ ያደረገው፡፡ ከግድያው ጎን ለጎን በሽርካ፣ ሮቤ፣ ጀጁ፣ መርቲ እና ሙኒሳ ወረዳዎች በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች በታጣቂዎች ታግተው የተወሰዱ ሲሆን፣ ቤተሰቦቻቸው ከፍተኛ የካሳ ገንዘብ ከፈለው ያስለቀቋቸው ቢኖሩም፤ የበርካቶች ያሉበት ሁኔታ እስካሁን ሳይታወቅ ቀርቷል። በጥቃቶቹ ወቅት በህጻናትና በአረጋውያን ላይ ከባድ የአካል ጉዳት መድረሱንም ሪፖርቱ ያመላክታል። የደህንነት ስጋቱ በዞኑ ከፍተኛ መሆኑን የጠቀሰው መግለጫው፣ በጀጁ (6,216)፣ በሽርካ (3,746)፣ በአሰኮ (2,133)፣ በሮቤ (1,270)፣ በመርቲ (1,036)፣ በሙኒሳ (29) እና በጉና (21) ወረዳዎች በጠቅላላው ከ14 ሺህ በላይ ዜጎች መፈናቀላቸውን አስረድቷል። በተጨማሪም ዕድሜ ጠገብ አብያተ ክርስቲያናት መቃጠላቸውን፣ መዘረፋቸውንና በስጋት ምክንያት መዘጋታቸውን ይፋ አድርጓል። ኢሰመጉ ድርጊቶቹ በህገ-መንግስቱና በዓለም አቀፍ ድንጋጌዎች የተረጋገጡ መሰረታዊ መብቶችን የጣሱና በሰብዓዊነት ላይ የተፈጸሙ ወንጀሎች ባህሪያትን የሚያሳይ ነው ብሏል። በመሆኑም የፌደራልና የክልል መንግስታት ለዜጎች ዘላቂ ጥበቃ እንዲያደርጉ፣ ጥሰት ፈጻሚዎችን ለፍርድ እንዲያቀርቡ፣ ለተጎጂዎች ካሳ እንዲከፈልና ተፈናቃዮች ወደ ቀያቸው እንዲመለሱ ጥሪ አቅርቧል። ዘገባው የአዲስ ማለዳ ነው

  • 15 июл.1 8593

    https://youtu.be/Dn4oU50pyY0?si=-569-62L-TFzzWlN

  • ሳይነስን በ7ቀናት ማጥፋት https://youtu.be/Dn4oU50pyY0?si=_aFlvVOC83vN8Xsy

  • 25 июн.3 02372

    በወለጋ የንፁኋን ጭፍጨፋ!!! ተባብሶ የቀጠለውና ሶስተኛ ቀኑን የያዘው በጄት በሄሌኮፍተር እድሁም በሰው አልባ ድሮኖቺ ንፁኋኖቺና ከተማዎቺን እየደበደበ ይገኛል። በተጨማሪ ከአድስ አበባ እና ከተለያዩ አከባቢዎቺ የሲቢል ኢንቬሺን በጣሰ መልኩ በኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፕላን በኡኬ እያራገፈ መሆኑንና የጦር መሳርያዎቺን፣ወታደራዊ ትጥቆቺና ስንቆቺንም በዚሁ አየር መንገድ እያመላለሰ መሆኑና በዚሁ አየር መረፊያ ጥቃት እየፈፀመ በንፁኋኖቺ ላይ ኢላማ ያደረገ የአማራ ተወላጆቺን እየጨፈጨፈ ይገኛል። ማዕከላዊ ዕዝ በኦሮሚያ ሚኒሻና አድማ ብተና፣በገዳ ኮማዶ መሪነት አስከትሎ በምስራቅ ወለጋ ጊዳ አያና ወረዳ አዶዴ ዲቾ ቀበሌ ልዩ ስሟ አሊ በምትባል ከተማ በታክና ሞርተር በመደብደብ የሁለት እናቶቺን ህይወት ሲቀጥፍ ህዝቡን በከባድ መሳርያዎቺ በመደብደብ አከባቢያቸውን ለቀው እዲሄዱ ተገደዋል። ይህ ሀይልም ወደ ከተማዋ በመግባት ቤቶቺን በማቃጠልና ሀብት ንብረታቸውን በመዝረፍ የአማራን ህዝብ ጥላቻውን በግልፅ ያሳየበትና በርካታ ንፁኋን ወገኖቺ የጥቃቱ ሰለባ ሁነዋል። በሌላኛው ዋጃ ተብሎ በሚጠራው ከተማና አንዶዴ ድቾ ቀበሌ ልዩ ስሟ በፈንድቃ በተባሉ ቦታዎቺ በኤሌኮፍተርና በሰው አልባ ድሮን በመደብደብ በርካታ ንፁኋኖቺን ጨፍጭፏል። አፋብን ወለጋ(ቢዛሞ)አንሻ ሰይድ ዕዝ ህዝብ ግንኙነት መምርያ ሰኔ 18ቀን 2018ዓም

  • 15 июн.3 42253

    ይኸ ገጽ ከብልጽግና ጋር የሚሠራ ሲሆን ሰላማዊ ሰዎችን ለማጥቃት የሚንቀሳቀስ ነው። በየከተሞች ደህና የሚባሉትን ግለሰቦች ቀድመው ወደ ሚዲያ በማምጣት በማኅበረሰቡ ዘንድ ኢላማ እንዲደረጉ ያደርጋል። ወይም በእነሱ ቡድን እንዲገደሉ በማድረግ ከሞቱ በኋላ ሕዝቡ እንኳን ሞተ እንዲልና ፍትሕ እንዳይጠይቅ ያደርጋሉ። ባሕር ዳር ጎንደር አካባቢ ነው እንቅስቃሴ የሚያደርገው። የፋኖን ትግልም ተችቶ ጽፎ ያውቃል።

  • 2 июн.4 1031

    без подписи

  • 2 июн.4 412

    без подписи

  • 2 июн.3 917

    без подписи

  • 2 июн.3 909

    без подписи

  • 2 июн.3 504181

    ወለጋ /ቢዛሞ አንሻ ሰይድ ዕዝ

  • 2 июн.3 739152

    አርሲ የሟቾች ቁጥር አሻቅቧል'የንጹሃን ጭፍጨፋው ቀጥሏል' እስካሁን ቦታው ላይ የደረሰ መከላከያ ሀይል አልተገኘም። ከ49 በላይ ንጹሃን ክርስቲያኖች ህይወታቸውን ተነጥቀዋል። 230 የሚሆኑት ደግሞ ታፋነው ተወስደዋል ያሉበት አይታወቅም ብለዋል የአይን እማኞች። ነዋሪዎቹ የደራሽ ያለሽ እያሉ ቢሆንም አጋዥ ሀይል እንዳላገኙና አሁን በምስራቅ አርሲ ዞን በአሰኮ ወረዳ ታጣቂዎች ቀበሌዎችን ከበው መስመር በመዝጋት ህዝቡ እንዳይወጣ በማድረግ ጥቃት እየፈጸሚበት መሆኑም ተነግሯል። ግንቦት 25/2018

  • 1 июн.3 149122

    без подписи

  • 1 июн.2 8922210

    🔥#ገርጨጭ‼️ የልብ ኬዝ ያለባችሁና ነፍሰጡሮች ቪዲዮውን ባታዩት ይመከራል። ደቡብ ሜጫ መሃል ገነት (#ገርጨጭ) መሽጎ የነበረው የአብይ ሰራዊት በቴዎድሮስ ዕዝ 102ኛ ኮር 11ኛ ክፍለ ጦር ቃኝ እና መሀንዲስ ከዓለማየሁ ከቤ ሻለቃ ጋር በመቀናጀት በዚህ መልኩ የጠላትን #ጭንቅላት_ማፍረስ ተችሏል እድለኞች ተማርከዋል‼️ ደቡብ ሜጫ ወረዳ (ገርጨጭ ) የተገኙ ድሎች 🔸01ብሬን 🔸22 ክላሽ 🔸03 አይኮም መገናኛ 🔸1520 ተተኳሽ 🔸10 ምርኮኛ እና በርካታ ቁጥር ያለው ጠላት መደምሰስ ተችሏል።

  • 24 мая3 544232

    √ የትግሉ ግብ ብልፅግናን ማስወገድ ሊሆን አይችልም! ብዙዎቻችን የአማራ ህዝብ እያካሄደ ያለው ትግል የሕልውና ትግል መሆኑን እንገልፃለን፡፡ ትክክል ነው፡፡ ከምንገኝበት የሕልውና አደጋ የደረስነው በረጅም ዘመናት የቁልቁለት ጉዞ መሆኑን ግን ማስመር ይገባናል፡፡ የአማራ ህዝብ ችግር መዋቅራዊና ስርአታዊ ነው፡፡ ረጅም ዘመን ያስቆጠረ የቁልቁለት ጉዞ ነው፡፡ በአብይ አህመድ ፈላጭ ቆራጭ አገዛዝ የተጀመረ አይደለም፡፡ በወያኔ አምባገነናዊ አገዛዝ የተጀመረ አይደለም፡፡ በደርግ አምባገነናዊ አገዛዝ የተጀመረ አይደለም፡፡ በአፄው ዘመን የተጀመረም አይደለም፡፡ አጀማመሩ ከዚያም ያልፋል፡፡ በደንብ ለመረመረው ከፋሽስት ጣልያን የወረራ ዘመንም ያለፈ ነው፡፡ በተከታታይ አገዛዞች በችግር ላይ ችግር እየተከመረ እዚህ ላይ ደርሰናል፡፡ በጆግራፊም በዲሞግራፊም የሀገሪቱ ግንባር ቀደም ህዝብ ሆነን ሳለ፣ የፖለቲካ አናሳ (political minority) ወደመሆን አሽቆልቁለናል፡፡ በኢኮኖሚው መስክ ኋላ ቀርተናል፡፡ በትምህርቱ መስክ የለንም ማለት ይቻላል፡፡ በሌሎች ማህበራዊ መሰረተ-ልማቶች ያለንበት ሁኔታ እጅግ እጅግ አሳፋሪ ነው፡፡ ይህ ሁሉ ድርብርብ ጭቆና እና ፈተና ሳያንስ ሕልውናችንም አደጋ ላይ ወድቋል፡፡ ወገኖቻችን ባልተቋረጠ ሁኔታ በየቦታው በማንነታቸው ተለይተው እየተሳደዱ ነው፡፡ እየተገደሉ ነው፡፡ ታፍነው በብዛት እየታሰሩ ነው፡፡ አደጋው እጅግ ሰፊና ጥልቅ ነው፡፡ ከመቼውም ጊዜ በላይ የዘር ማጥፋት አደጋው መጠኑን አስፍቶና ተጠናክሮ የመጣውም አሁን ነው፡፡ ስለዚህ፣ የትግላችን ግብ የኦህዴድ/ብልፅግናን አገዛዝ ማስወገድ ሊሆን አይችልም፡፡ የትግሉ ግብ ከዚያ የተሻገረ ነው፡፡ አዎ የኦህዴድ/ብልፅግና አገዛዝ የህዝባችን የወቅቱ ጠላት በመሆኑ መወገድ አለበት፡፡ ይሁን እንጅ እሱን ማስወገድ በራሱ የአማራን ሕዝብ የሕልውና አደጋና የነፃነት ጥያቄ አይመልሰውም፡፡ የአማራን ህዝብ የሕልውና አደጋ አስወግደን ህዝባችን የራሱን እድል በራሱ እንዲወስን እና በነፃነት እንዲኖር ከፈለግን አስተሳሰባችን ማስፋት አለብን፡፡ የትግሉን ግብ አስፍተን መተለም አለብን፡፡ ኢትዮጵያ እስካለች ድረስ በወርዳችንና በቁመታችን ልክ የፖለቲካ ውክልናና የኢኮሚ ተጠቃሚነታችን ተረጋግጦ በእኩልነትና ፍትሃዊነት የምንኖርበት ስርአት እንዲኖር መታገል አለብን፡፡ ከሁሉም በፊት ግን አደጋ ላይ የወደቀው ሕልውናችን መወገድ ይኖርበታል፡፡ የኢትዮጵያ እንደ ሀገር መቀጠል አደጋ ውስጥ የሚገባ ከሆነም ራሳችን ችለን መኖር እንደምንችል ከወዲሁ ማረጋገጥ አለብን፡፡ ከወዲሁ ጠንካራ ተቋማትን በየመስኩ መገንባት ይገባናል፡፡ ዝግጅቱ እስከዚህ መሆን ይገባዋል፡፡ በዚህ ደረጃ አስበን ካልተዘጋጀን የኢትዮጵያ ሕልውና አደጋ ላይ ሲወድቅ ዛሬ ካለንበትም የባሰ መቀመቅ እንገባለን፡፡ እንደምናውቀው ከዚህ ቀደም የህዝባችን ቀንደኛ ጠላት ወያኔ/ኢህአዴግ ነው የሚል መነሻ ተይዞ እሱን ማስወገድ የትግሉ ዋነኛ ግብ ሆኖ ቀረበ፡፡ ወያኔ/ኢህአዴግ ተወገደ፡፡ ይሁን እንጅ ከወያኔ በኋላ የህዝባችን እጣ-ፈንታ ምን ይሆናል? የሚለውን ጥያቄ የጠየቀና አስፈላጊውን ዝግጅት ያደረገ ሃይል ባለመኖሩ ህዝባችን መስዋዕትነት ከፍሎ ያመጣውን ለውጥ እንደ ዘበት ተነጥቋል፡፡ ህዝባችን የራሱን ጉዳይ በራሱ እንዲወስንና በነፃነት እንዲኖር የሚያስችሉ ጠንካራ ተቋማትን ያልገነባን በመሆኑ ምክንያት በመስዋዕትነት ያመጣነውን ለውጥ ተነጥቀናል፡፡ ለዚህ ነው አሁንም የትግሉን ግብና ትግሉን አላማዎች፣ በሌላ አባባል የትግሉን መዳረሻ ከወዲሁ በጠራ ሁኔታ ቀርጾ እና የስራ ክፍፍል አድርጎ ሁሉም በየሚናው ኃላፊነቱን መወጣት መጀመር ያለበት፡፡ አይመጣምን ትቶ ይመጣልን ማሰብና መዘጋጀት ከውርደትና ከሞት ያድናል፡፡ ከዚህ ቀደም ሊመጡ የሚችሉ አደጋዎችን እየተነተንን አስፈላጊውን ዝግጅት አድርገን ቢሆን ኖሮ በዚህ ደረጃ ባልተጠቃንም ነበር፡፡ ከታሪካችን አንፃር፣ ከህዝብ ቁጥራችን አንፃር፣ ካለን የተፈጥሮና ሰው ሰራሽ ሀብት አንፃር አሁን የምንገኝበት ሁኔታ ፈፅሞ መሆን ያልነበረበት፤ ፈፅሞ አሳፋሪ ሁኔታ መሆን መቀበል አለብን፡፡ የገባንበትን መቀመቅ በልኩ ስላልተገነዘብነው ነው ከዚህ መቀመቅ ለመውጣት በእርዳ ተራዳ መንፈስ በህብረት ከመንቀሳቀስ ይልቅ በትንሹም በትልቁም እየተባለን የጠላት መጫዎቻ የሆንነው፡፡ ደግነቱ ባህል የማይቀየርና ዘላለም የሚኖር አለመሆኑ ነው፡፡ ባህልና ልማዳዊ ድርጊት ይቀየራል፡፡ ይሻሻላል፡፡ እኛም ዛሬ እርስ በርሳችን የመናከስ ክፉ ልማድ አለን ማለት ከዚህ እስር ቤት መውጣት አንችልም ማለት አይደለም፡፡ በበቂ ሁኔታ ያለመተባበር ችግር አለብን ማለት ይህን ሁኔታ ቀይረን መተባበር አንችልም ማለት አይደለም፡፡ ለልዩነት ቦታ እየሰጠን፣ አንዳንድ ስህተቶችንም እንዳላየን እያለፍን፣ ከስም ማጠልሸትና ሰብእና ገደላ ተላቀን፣ ሁላችንም አሸናፊ ከሚያደርግ የይዋጣልን እልህ ወጥተን በጋራ መቆም ምርጫ ሳይሆን ግዴታ ነው፡፡ ይህን የአሸናፊነት መንገድ ጥቂቶች ብንጀምረው የነ አቶ ህላዌ ዮሴፍን መዝሙር ተውሰን “ነገ እልፍ እንሆናለን ታሪክ መስክር ነው” ብለን እንዝጋው፡፡ ከጠላትም ቢሆን በጎ ነገር ሲገኝ መውሰድ መልካም ነውና ነው! የአማራ ብሄርተኝነት ይለምልም! ንቃ አማራ ©ታጋይ የሕዝብ ልጅ

  • 11 мая4 36422

    የተባበሩት ኢምሬቶች አዲሷ ኢምፔሪያሊስት ሆናለች። ከግማሽ ምዕተ ዓመት የማይበልጥ እድሜ ያላት፤ የአዲስ አበባን ሩብ ያህክል የህዝብ ቁጥር የሌላት ሀገር የሺህ ዘመናት የስልጣኔ ባለቤት እና በአፍሪካ የነፃነት አባት የሆነችዋን ኢትዮጵያ ቅኝ እየገዛች ትገኛለች። ትክክለኛ ሊደር ሺፕ እና የጋራ ርዕይ የሌለው ህዝብ እንዲህ ነው ሚሆነው። የኢትዮጵያ አየር ኃይል ከደመወዝ እስከ ቁሳቁስ በኢምሬቶች ይሸፈናል። ስራ ላይ ካሉት ድሮኖች መካከል ከአንቴና ውጭ ሳትኮም (ሳተላይት) እንዲጠቀሙ ተደርገው የተሻሻሉት TB2 ድሮኖች እና ከ 4 እስከ 24 ሮኬት ቦንቦች መሸከም የሚችሉ ዘመናዊወቹ አኪንቺ ድሮኖች ባለንብረቶች የሆኑት ኢምሬቶች ደብረ ዘይት፣ ባህርዳር እና አሶሳ ላይ የራሳቸውን ድሮኖች ኦፕሬት እያደረጉ ከትመዋል። AI ሲስተም የተገጠመላቸው እነዚህ እጅግ ዘመናዊ ድሮኖች ውድ ከመሆናቸው የተነሳ ኢትዮጵያ መታጠቅ ያልቻለቻቸው ናቸው። በግዜያዊነት ለስልጠና እና ክትትል የሚመጡትን ሳይጨምር ዛሬ ላይ ከ125 በላይ የአረብ ኤምሬት አየር ሃይል ስታፍ አባላት በደብረ ዘይት እና በሌሎች አየር ኃይል ግቢወች ይገኛሉ። በተለይ ከኢትዮጵያ ወደ ጎረቤት ሀገራት የሚደረገው ድንበር ዘለል የድሮን ኦፕሬሽን የሚከናወነው ሙሉ በሙሉ በUAE ዜጎች ሲሆን የሀገር ውስጥ ሰወች ምንም አይነት ተሳትፎ የላቸዉም። ምግብ ሳይቀር ከዱባይ የሚመጣላቸው እነኝህ የUAE ዜጎች አልፎ አልፎ የወርቅ ንግድ ቱጃሩ የሐምዳን ዳጋሎ ወንድም ከሚደግፋቸው በስተቀር የነዳጅ፣ የተተኳሽ እና የስታፍ ወጭ በሙሉ በሀገራቸው ይሸፈናል። የጀነራል ይልማ መርዳሳ ቢሮ መንደርደሪያወችን ከመፍቀድ የዘለለ ሚና የለውም። ከፖርት ሱዳን እስከ ዳሬ ሰላም ያሉ ፖርቶችን በመቆጣጠር የወደብ ተስፋፊ (Port- imperialist) ለመሆን የምትደክመው ሀገር በሊቢያ ጀነራል ቃፍታርን፣ በሱዳን ዳጋሎን፣ በሶማሊያ ጁባ ላንድ እና ፑንት ላንድ የመሳሰሉ ራስ ገዝ ክልላዊ ኃይሎችን፣ በቻድ የመሃማት ኢድሪስ ዴቢን ሽግግር መንግስት እና ሌሎችንም ስፖንሰር በማድረግ የአፍሪካን ወርቅ በመልቀም ላይ ትገኛለች። ኢትዮጵያ ውስጥም በሀገር ላይ ያመፀውን አብይን የምትደግፈው እና በተለይም የአማራን ህዝብ የምትወጋው ይህች ሀገር ፍላጎቷ ከእርሻ መሬት ፍለጋም አለፍ ያለ ፀረ-ኢትዮጵያዊ ፕሮጀክትንም ያካትታል። በነገራችን ላይ ፕሮፌሰር Alex de Waal ከመለስ ዜናዊ ጋር በተለያዬ ግዜ በነበረው ውይይት የያዘዉን ማስታወሻ እ.ኤ.አ 2018 ባካተተበት "The Future of Ethiopia: Developmental State or Political Market Place" በሚለው መጣጥፉ ስር መለስን በኢትዮጵያ ብሔራዊ ደህንነት ላይ ትልቁ ስጋትህ ምንድን ነው ሲል መጠየቁን አስፍሯል። መለስም ...ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ደህንነት አንፃር የሚያስቃዠኝ ጉዳይ ቢኖር የባህረ ሰላጤው ዘውዳዊ አገዛዞች (Gulf Monarchies) የአፍሪካ ቀንድን የፉክክር ሜዳቸው ሊያደርጉ የሚችሉበት እድል መኖሩ ነው... በተለይም ታዛዥነትን (loyalty) በስልጣን ሊያከራይ የሚደፍር አመራር ከመጣ ከባድ ችግር ይከተላል የሚል ይዘት ያለው ምላሽ ሰጥቷል። ይህ ፖለቲካዊ ምስቅልቅል ይከሰት ዘንድ በኢትዮጵያ ፖለቲካ የኃይል አሰላለፍ ስሌት ውስጥ ትልቅ ፖለቲካዊ ውስልትና በመስራት የፀረ-ኢትዮጵያዊ ኃይሎች አቅም ከልክ በላይ እንዲፈረጥም በሰራው ስትራቴጅካዊ ስህተት እርሱም ከደሙ ንፁህ ባይሆንም በበቂ ትንተና ላይ የተመሰረተው የሰውዬው የፖለቲካ ትንበያ አስገራሚ ነበር። ያ የተሰጋው የኢትዮጵያ ናሽናል ሴኩሪቲ አደጋ በመሐመድ ቢን ዛይድ እና በአብይ አህመድ ጥምረት እውን ሆኗል። ማንም ሀገሩን ማትረፍ የሚፈልግ ቢኖር ይህንን ስትራቴጅካዊ አሰላለፍ ተከትሎ ማስላት ይጠበቅበታል። ግብዝ ካልሆንን በስተቀር መወረር እና ቅኝ መገዛት ከዚህ በላይ መገለጫ ሊኖረው አይችልም። ደሃው የአማራ ገበሬ፣ ለነፍሱ ማይሰስተው ፋኖ እየተዋጋ ያለው የውስጥ አረመኔወችን ብቻ ሳይሆን የውጭ ቅኝ ገዥወችን ጭምር ነው። ©አርበኛ አስረስ ማረ ዳምጤ

  • 8 мая3 675151

    ከምስራቅ ጎጃም ዞን ደብረ ማርቆስ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የተሰጠ መግለጫ ሚያዚያ 30/2018ዓ.ም --------------------------------------------------------------------- "በምርጫ ሰበብ ያለአግባብ የታፈኑ 7 የኮሌጃችን መምህራን እና 28 የተቋማችን ተማሪዎች በምስራቅ ጎጃም ዞን ፖሊስ መምሪያ የደህንነት ሰዎች በትናትናው ዕለት ከኮሌጁ ቅጽር ግቢ ተወስደዋል። የትምህርት ተቋማት ለማንኛውም የፖለቲካ እንቅስቃሴ ማስፈፀሚያነት እንደማይውሉ እየታወቀ በአለፉት 30 ቀና ውስጥ በኮሌጁ ግቢ ተማሪዎችን ፣መምህራን እንዲሁም የአስተዳደር ሰራተኞች በግዳጅ ከ5-7 የሚደርስ የምርጫ ካርድ በተለያዩ ስሞች እንዲያወጡ በመገደዳቸው ተቋማችን ይህ ተግባር እንዲቆምለት ለሚመለከተው አካል ማቅረባችን የሚታወስ ነው። በተደጋጋሚ በተጻፈልን ደብዳቤ መሰረት በኮሌጁ ውስጥ የምርጫ ካርድ የወሰዱ እና ያልወሰዱ መምህራን ፣ሰራተኞችና ተማሪዎችን ለይተን ሪፖርት እንድናቀርብ በመጠየቃችን ሒደቱ የአልተገባ እና ህገ-ወጥ በመሆኑ ተቋሙ በምርጫ ሒደቱ በቀጥታ እንዲሳተፍ እየተገደደ መሆኑን ለሚመለከተው አካል ብናሳውቅም አጥጋቢ ምላሽ በማጣታችን ምርጫ ካርድ የወሰዱ እና ያልወሰዱ መምህራን፣ ሰራተኞችና ተማሪዎችን ለይተን በስም ዝርዝር ማሳወቃችንም የሚታዎስ ነው። ይህ በእንዲህ እንዳለ በቀን 29/2018 ዓ.ም የብልጽግና ፓርቲ በደብረ ማርቆስ ከተማ በጠራው የምርጫ ቅስቀሳ አልተሳተፋችሁም፤ የምርጫ ካርድም አላወጣችሁም፤ የተባሉ 7 የኮሌጃችን መምህራን እና 28 ተማሪዎቻችን በደህንነት ሰዎች ታፍነዋል። በመሆኑም በተደጋጋሚ ኮሌጁን ለምርጫ ማስፈፀሚያነት ከመጠቀም ባለፈ መምህራን፣ የአስተዳደር ሰራተኞችና ተማሪዎች በመንግስት የፀጥታ ኃይሎች ሲንገላቱ ቆይተዋል። የደብረ ማርቆስ ከተማ አስተዳደር ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ከተቋቋመለት ዓላማ ውጭ እንዲንቀሳቀስ መደረጉን አጥበቀን እየተቃወምን በቁጥጥር ስር የዋሉ መምህራን እና ተማሪዎቻችን እንዲለቀቁልን እንጠይቃለን። መላ ህዝባችንም ከተቋሙ ጎን እንዲቆም ጥሪ እናቀርባለን ። የደብረ ማርቆስ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ

  • 8 мая3 33911

    без подписи

  • 7 мая4 1792

    без подписи

  • 7 мая3 9972

    без подписи