tgindex
አቡ ዑመይር

አቡ ዑመይር

Статистика

ወደ ጌታህ መንገድ በብልሃትና በመልካም ግሳጼ (በለዘብታ ቃል) ጥራ፡፡ (ሱረቱል ነህል 125) ማንኛውም አስተያዬት ሲኖራችሁ @Yabekeir ስህተት ባያችሁም ጊዜ አርሙኝ።

Последний пост
19 июн.
Последнее чтение
13 авг.
Постов за неделю
0
Всего постов
21
Тип
открытый
Язык
am
В каталоге с
13 авг.
Подписчики
4 244
−13 за 5 дн.
Сутки
+1
+0,02%
Неделя
 
Месяц
 
Просмотров на пост
823
21 постов
Вовлечённость
19,4%
к подписчикам
Постов в день
0,0
всего 21
Упоминаний
0
каналов
Охват размещения
оценка
1/24сутки в ленте
1/48двое суток
1/72трое суток

Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.

Посты

  • አሹራ ማለት ቃላዊ ትርጉም፦ "አሸራ" ወይም 1ዐኛው ከሚል የመጣ ሲሆን ይህም ሊሆን የቻለው በሙሃረም ወር በ1ዐኛው ቀን ስለዋለ ነው። የሙሃረም ወር በሂጅራ አቆጣጠር የአመቱ የመጀመሪያ ወር ነው። --> የሙሀረምን ወር ረሱል (ሰ•ዐ•ወ) የአላህ ወር ነው ሲሉ አልቀውታል። --> ከረመዳን በመቀጠል አላህ (ሱ•ዐ) ዘንድ በላጩ ፆም የሙሀረም ፆም ነው። የአሹራን ቀን በተመለከተ፦ [ ከኪታብ እና ከሱና ] * ኢብን አባስ (ረ•ዐ) እንደተናገሩት፦ የአላህ መልዕክተኛ (ሰ•ዐ•ወ) ወደ መዲና እየመጡ እያለ በአሹራ ቀን የሁዲዎች ሲጾሙ አይተው። ለምንድነው የምትጾሙት ብለው ጠየቋቸው። የሁዲዎቹም፦ አላህ (ሱ•ወ) ነቢ ሙሳን (ዐ•ሰ) እና የበኒ ኢስራኢል ልጆችን ከጠላቶቹ ነጃ ያደረጋቸው ቀን በመሆኑ እና ነቢ ሙሳም (ዐ•ሰ) ይህን ቀን በመፆማቸው ነው አሏቸው። ነብዩም (ሰ•ዐ•ወ) ነቢ ሙሳ (ዐ.ሰ) ከእናንተ ይልቅ ለእኛ የቀረበ ነው አሉ። ያንንም ቀን (የሙሃረም 1ዐኛውን ቀን) ጾሙ ሙስሊሞችም እንዲጾሙ አዘዘ። [ ሀዲሱን ሰሂህ አል ቡኻሪ ዘግበውታል፡፡ ] * የአሹራ ቀን ቅዱስ በሆነው በሙሀረም ቀን ውስጥ ያለች ቀን ናት ለዚህም ማስረጃው፦    ነብያችን (ሰ•ዐ•ወ) እንዲህ ብለዋል፦ "በአመት ውስጥ 12 ወራት አሉ፡፡ ከ12ቱ ውስጥ 4ቱ ወራት ቁድስ ናቸው፡፡ እነሱም ዙልቂዳ፣ ዙልሂጃ፣ ሙሃረም እና ረጀብ ናቸው።" [ሰሂህ አል ቡኻሪ] * በጃሂሊያህ ዘመን ቁራይሾች የአሹራን ቀን ይፆሙ ነበር፡፡ ይህንን የሚያደርጉትም የነብዩላሂ ኢብራሂም (ዐ•ሰ) ሱና ስለነበረ ነው፡፡ * የአሹራ ቀን ነቢ ሙሳ (ዐ•ሰ) እና የበኒ እስራኢል ልጆች ከፊርዓዎን ነጃ የወጡበት ቀን የአሹራ ቀን ነበር ለዚህም ማስረጃው በሱረቱል አሽ-ሹዓራህ የሰፈረው የአላህ ቃል ነው፦    63. ወደ ሙሳም «ባሕሩን በበትርህ ምታው» ስንል ላክንበት፡፡ (መታውና) ተከፈለም፡፡ ክፍሉም ሁሉ እንደ ታላቅ ጋራ ኾነ፡፡ 64. እዚያም ዘንድ ሌሎችን አቀረብን፡፡ 65. ሙሳንም ከእርሱ ገር ያሉትንም ሰዎች ሁሉንም አዳን፡፡ 66. ከዚያም ሌሎቹን አሰጠምን፡፡ * የአሹራ ቀን የነብዩላሂ ኑህ (ዐ•ሰ) መርከብ በጁዲ ተራራ ያረፈችበት ቀን ናት።    ኢማሙ አህመድ እንዘገቡት የነብዩላህ ኑህ (ዐ•ሰ) መርከብ በጁዲ ተራራ ላይ ያረፈችበት ቀን የአሹራ ቀን ነበር፡፡ * እናታችን አዒሻ (ረ.ዓ) እንደዘገቡት፦ የአላህ መልዕክተኛ (ሰ•ዐ•ወ) የአሹራን ቀን መፆማቸውን ጠቅሳለች፡፡ [ ሰሂህ አል ቡኻሪ ዘግበውታል፡፡ ] * ከረመዷን ቀጥሎ የአሹራን ቀን መፆሙ ትልቅ አጅር ያላት ቀን መሆኗን በሀዲስ ተገልጾአል፡፡     ነብዩ ሙሀመድ (ሰ•ዐ•ወ) እንተናገሩት ከረመዷን ቀጥሎ የሙሀረም ወር 1ዐኛው ቀን መጾም ትልቅ ደረጃ አለው፡፡ [ሰሂህ ሙስሊም ] * ኢብኑ አባስ (ረ•ዐ) እንደተናገሩት የአላህ መልዕክተኛ (ሰ•ዐ•ወ) ከረመዷን ወር ውጪ ለአሹራ ጾም ቅድሚያ ይሰጡ ነበር፡፡ [ ሰሂህ አል ቡኻሪ ዘግበውታል፡፡ ] * የአላህ መልዕክተኛ (ሰ•ዐ•ወ) እንደተናገሩት አንድ ሰው በአሹራ ቀን ቤተሰቡን ለማስደሰት ሰደቃ ከሰጠ አላህ (ሱ.ወ) አመቱን በሙሉ በሱ ላይ በረከቱን ያበዛለታል። [ አል በይሃቂ ዘግበውታል፡፡ ] * የአሹራን ቀን መጾም ትናንሽ ወንጀሎችን ሙሉ በሙሉ ያብሳል ለዚህም ማስረጃው፦    ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) እንደተናገሩት የአሹራን ቀን የጾመ ወንጀሉ ይማርለታል።[ በሰሂህ ሙስሊም ] * ኢማሙ ሻፊዕ፦ 9ኛው እና 1ዐኛውን  ቀን መጾም ተወዳጅ መሆኑን ገልጸዋል። ነብዩ (ሰ•ዐ•ወ) 1ዐኛውን ቀን ብቻ መጾማቸውንም አላህ ለቀጣዩ ካደረሷቸው 9ኛውንም እንደሚፆሙ ተናግሯል፡፡ ማሳሰቢያ፦ የአሹራን ፆም መፆም ግዴታ ባይሆንም 9ኛውን እና 1ዐኛውን ቀን መጾም ተወዳጅ ነው፡፡ ከሁሉም በላይ አላህ አዋቂ ነው። ✍ አቡ ዑመይር የቴሌግራም ቻናላችንን ተቀላቀሉ፦ https://t.me/Abu_Umair2

  • без подписи

  • 🛑ዝግጁ ናችሁ ለነገው ታላቅ ፆም? ያለፈውንና የመጪውን አመት ወንጀል የሚያስምረውን ቀን!

  • السلام عليكم ورحمة الله وبركاته የዙልሒጃ ወር ነገ ሰኞ አንድ ይላል። ስለዚህ የተለየ ዋጋ ያላቸውን የዙልሒጃ 10 ቀናት በተለያዩ ዒባዳዎች ማሳለፍ የምትፈልጉ ከዚህ ምሽት ጀምሮ መበርታት ያስፈልጋል።

  • 16 апр.1 2582

    በቴሌግራም ሰለምቴዎችን በማስቀራት በማገዝ የምናዉቃት እህታችን ሹሹ በ online ቢዝነስ መታለች በኦላይን የትኛውንም አይነት ነገር እናደርሳለን ሒጃብ መጽሐፍ የትኛውንም ነገር ጥለቡን እኛ ጋ የሌለው የለም ብቻ ነው። ብላቹዋለች ጅዳ እና ከጅዳ ዉጪ ያላችሁ ማዘዝ ትችላላችሁ ግሩፑዋንም ተቀላቀሉ ሹሹን በግል ለማግኘት👇 @Umusara10 የቴሌ ግራም ግሩፕ👇 https://t.me/SARAH_ONLINE_shoppings የቲክቶክ አካውንት👇 https://www.tiktok.com/@sarah.online.shopp?_r=1&_t=ZS-959agnvwyfM

  • 18 мар.1 35313

    ይድረስ! ~ 1- ይድረስ ሚስትህን ለፈታኸው፡ ልጆችህን ለዒድ አስበሃቸዋል? ወይስ እነሱንም ከእናታቸው ጋር ፈተሃቸዋል? 2- ይድረስ የየቲሞች አጎት ለሆንከው፡ የሟች ወንድምህን ልጆች ትጠይቃለህ? ወይስ ከቀበርከው ወንድምህ ጋር ረስተሃቸዋል? 3- ይድረስ ባሏ የሞተባት እህት ያለችህ: እህትህን ትኑር ትሙት ጠይቀሀል? በልታለች ወይስ ተርባለች? ወይስ እህትነቷ ቁጥር ብቻ ነው? 4- ይድረስ እናት አባትህን ለረሳሀው: ህይወትን እንዴት እየገፉ እንደሆነ ማሰብ ይገድሃል? በዒድስ በልባቸው ውስጥ ደስታን ማስገባት ያሳስብሃል? 5- ይድረስ ለሁላችን፡ እጃችንን የሚጠብቁ፣ ከኛ የቀረበ ሰው የሌላቸው ቤተሰቦቻችን በምን ላይ ናቸው? በዒድ በምን መልኩ እንዲያስታውሱን እንፈልጋለን? ያቅማችንን ያክል ከልባቸው ውስጥ ደስታ ማስገባት ያሳስበናል? ወይስ ሀዘን ትካዜያቸው ምንም አይመስለንም?! - ተነካክቶ ከዐረብኛ የተመለሰ (ኢብኑ ሙነወር፣ ሚያዚያ 22/ 2014) = Ibnu Munewor

  • 9 мар.1 1126

    "የአላህ መልክተኛ የረመዳን የመጨረሻ 10 ሌሊቶች ሲገቡ ሌሊቶችን ህያው ያረጉ ቀበቶዋቸውን ያጠብቁ ቤተሰቦቻቸውንም ያነሳሱ ነበር" ሰሂህ ሙስሊም

  • 7 мар.1 0475

    ጥቂት ስለ ኢዕቲካፍ! ~ * ትርጓሜው፦ ለአላህ ዒባዳ ለመፈፀም በማሰብ መስጂድ ውስጥ መቆየት ማለት ነው። * ብይኑ፦ በቁርኣን በሱና የተረጋገጠ ሙስተሐብ (የተወደደ) ዒባዳ ነው። ለመፈፀም ስለት ለተሳለበት ሰው ግን ግዴታ ይሆናል። አዕቲካፍ ለሴቶችም የተፈቀደ ነው። * አላማው፦ ልብንም አካልንም ስብስብ አድርጎ በዒባዳ መጠመድ ነው። ኢዕቲካፍ የገባ ሰው ከትርፍ ወሬ፣ ከትርፍ ቅልቅል፣ ከትርፍ እንቅልፍ መቀነስ ይገባል። * ጊዜው፦ አብዛኞቹ ዑለማእ ዘንድ በረመዷንም ይሁን ከረመዷን ውጭ መፈፀም ይቻላል። በላጩ ጊዜ ግን ረመዷን ነው። ከረመዷንም የመጨረሻዎቹ አስሮቹ የበለጡ ናቸው። * ቦታው፦ ለወንድም ይሁን ለሴት መስጂድ ውስጥ ብቻ ነው። * የጀመረ ሰው መጨረስ ግዴታ ነውን? የሚያስገድድ ማስረጃ የለም። * ዝቅተኛው ጊዜ ምን ያህል ነው? ገደብ የለውም። ያሰኘውን መጠን ያክል ነይቶ መቀመጥ ይችላል። * ኢዕቲካፍ የገባ ሰው ለመፀዳዳት መውጣት ይችላል። የታመመን ለመጠየቅ፣ ጀናዛ ለመሸኘትና መሰል ጉዳዮች ግን አይወጣም። የግብረ ስጋ ግንኙነት፣ ግብይት፣ ስራ መስራት አይቻልም። ኢዕቲካፍ ላይ እያለ የታመመ ሰው መታገስና መቆየት የሚችል ከሆነ መውጣት የለበትም። * የረመዷን የመጨረሻዎቹን አስር መግባት የፈለገ መቼ ይጀምር? የረመዷን 20ኛው ቀን ከመጥለቋ በፊት ቢሆን መልካም ነው። * የሚወጣበት ደግሞ ረመዷን ተጠናቆ የዒድ ሌሊት ሲገባ ነው። ወላሁ አዕለም። = Ibnu Munewor

  • የዘካ ፋይዳዎችና ዘካን ያለመስጠት አደጋዎች! ~ [ሀ] ለሰጪው የሚያስገኛቸው ፋይዳዎች፡- ① ዘካ ከአምስቱ የኢስላም ምሰሶዎች አንዱ እንደመሆኑ በትክክል የሚሰጥ ሰው ይህን የኢስላሙን ምሰሶ ነው ያፀናው። ባይሰጥ ደግሞ ይህን ምሰሶውን ነው ያናጋው። ② ዘካ በኢኽላስ እስከተወጣ ድረስ ኢማንን ይጨምራል፤ የአላህን ውዴታ ያጎናፅፋል። ③ ዘካ ወንጀልን ያብሳል። ነብዩ ﷺ "ውሃ እሳትን እንደሚያጠፋው ሶደቃ ሃጢአትን ያጠፋል" ብለዋል። ④ ዘካ ፈተናን መከራን ይመክታል። ⑤ ዘካ ማውጣት የአዛኝነት፣ የርህሩህነት፣ የተቆርቋሪነት ባህሪን ያላብሳል። ዛሬ ራስ ወዳድነት በነገሰበት ዘመን ለሙስሊም ወገን ከምላስ ባለፈ ከልብ መቆርቆርና ማዘን የእውነት ትልቅ መታደል ነው። ⑥ ዘካ የቀልብ መለዘብና በሞራል መገራትን ያጎናፅፋል። ከክፋት፣ ከስስት፣ ከድንበር ዘለል የዱንያ ፍቅር እንዲወጡ ሰዎችን ያግዛል። ⑦ ዘካ የህሊና እርካታን ፣ መንፈሳዊ ሰላምን፣ ስነ ልቦናዊ መረጋጋትን ያጎናፅፋል። ⑧ ዘካ ገንዘብን ያፋፋል፣ በረካ ይጨምርበታል። ⑨ ዘካ ለችግር ጊዜ ደራሽ ወገን እንዲኖረንም ይጠቅማል። መቼም ሁሌ ድሎት፣ ሁሌ ምቾት የለም። ዱንያ ተገለባባጭ ናት። [ለ] ለተቀባዩ ያሉት ፋይዳዎች:– ① በዘካ ድሃዎች ይደጎማሉ ወይም ይቋቋማሉ። ② ሃብታሙን በቅናትና በክፋት ከማየት እንዲታቀቡ ያግዛቸዋል። ③ ይህን የሚደጎሙበትን ህግ ለዘረጋው ጌታ ውዴታ ለሃይማኖታቸውም ቀናኢነትን እንዲያሳድሩ ይጠቅማቸዋል። ይህ ሳይሆን ሲቀር ግን ከፊሉ ጌታውን ሊያማርር፣ ኢማኑ ሊሸረሸር ይችላል። ④ ለገንዘብ ሲሉ እምነታቸውን ከመሸጥ፣ በጥፋት ላይ ከመሰማራት ያቅባቸዋል። [ሐ] የዘካ ማህበራዊ ፋይዳዎች ① በሰጭና በተቀባይ መካከል ትስስር እንዲጠነክር ያደርጋል። ዝምድናን ይቀጥላል። የሰመረ ጉርብትና እንዲኖር ያግዛል። ምክንያቱም ነፍስ በጎ ለዋለላት አካል ተዘንባይ ነችና። ② ዘካ በአግባቡ ከተወጣ በሀብታሙና በደሃው መካከል ያለውን የሃብት ርቀት ስለሚያጠብ ለጤናማ ኢኮኖሚ የማይናቅ አስተዋጽኦ ያበረክታል። ③ ዘካ ከድህነት ወለል በታች ያሉ ወገኖች ተስፋ በመቁረጥ ወደ ስርቆትና ዝርፊያ በማምራት ማህበራዊ ቀውስ እንዳይፈጥሩ ይታደጋል። ④ ዘካ ሀብታሙን ሃላፊነት እንዲሰማው ስለሚያደርግ ከስግብግብ የካፒታሊዝም አስተሳሰብ በማቀብ የሃገር ሐብት በጥቂቶች እጅ ብቻ እንዳይሆን ያግዛል። [መ] ዘካ አለመስጠት ያለው አደጋ ባጭሩ እስካሁን የተዘረዘሩትን ፋይዳዎች ያሳጣል። የዱንያም የአኺራም ኪሳራን ያስከትላል። ሰጪንም፣ ተቀባይንም፣ ማህበረሰብንም አገርንም ይጎዳል። ወገኔ ሆይ! ዘካ ወጅቦብሀል? እንግዲያውስ ውለታ ቢስ አትሁን። ላንተ የሰጠህ ጌታ ነው "ስጥ" ብሎ ያዘዘህ። በሰፊው ከሰጠህ ነው ጢኒጥየ ቆንጥረህ ስጥ ያለህ። ልብህ ፈታ ብሎ፣ ደስ ብሎህ ስጥ። ደስ እያለህ ጀነትን ትወርሳለህ። ደግሞ አትሸወድ! ዘካ ገንዘብህን ያፋፋዋል እንጂ አይቀንሰውም። ነብዩ ﷺ "የአንድን ባሪያ ገንዘብ ሶደቃ አይቀንሰውም" ብለዋል። በነገርህ ላይ የዘካው መጠን ያንተ ድርሻ፣ ያንተ ገንዘብ አይደለም። ዘካውን ባስቀረህ ጊዜ የሰው ሐቅ እየበላህ እንደሆነ ይታወቅህ። አይሰቀጥጥም? "ላቤን ጠፍ አድርጌ ያመጣሁት ነው" እያልክ የምትጎረር ከሆንክ ግን የነ ቃሩን ባቡር ላይ ተሳፍረሀል። ወዴት እንደሚወስድህ አልነግርህም። ወንድሜ! ያገኘኸሁ ባንተ ብልጠትም ብቃትም አይደለም። ስንት የበቁ የነቁ በድህነት እየማቀቁ መሰለህ?! ስንት መንቻካ ዶክተሮች ፕሮፌሰሮች እንዳሉ ሁሉ ስንት ቁልቁል መደመር የማይችሉ ቱጃሮች አሉ?! ይልቅ ልንገርህ! ሌሎችን በድህነት የሚፈትነው ጌታ አንተን በሃብት እየፈተነህ ነው። እራስህ በምታዝበት ገንዘብ ፈተናውን ከወደቅክ አሳዛኝ ክሽፈት ነው። ገንዘብህ ተከትሎህ ቀብር አይገባም። ወራሽ ወገኖችህ የቀብር ጥያቄን፣ የአላህን ምርመራ አይታደጉህም። ዛሬ ነገ አትበል! ሞት አለቅጥ የበዛበት ዘመን ላይ ነን። እንደ ወጣ የሚቀረውን ብዛት እያየን ነው። ነብዩ ﷺ ዘካ የማያወጣ ሰው ነገ በቂያማ ቀን የገዛ ገንዘቡ እባብ ሆኖ እንደሚያሰቃየው የተናገሩትን አስብ። ደግሞም ዙሪያ ገባህን አስተውል። እድለኛ ማለት ሌላው ላይ ከደረሰው የተመከረ ነው። አላህ ሃብት ከሰጣቸው በኋላ ዘካ ሳያወጡ፣ ሐጅ ሳይፈፅሙ አልፈው በቁጭት ወላፈን እየተለበለቡ ያሉ ስንት አግኝተው ያጡ ወገኖች አሉ?! ባጭሩ ገንዘብህ ወይ ጀነትህ ወይ እሳትህ ነው። ያሻህን መምረጥ ያንተ ድርሻ ነው። (ኢብኑ ሙነወር፣ ሚያዚያ 26/2013) Ibnu Munewor

  • без подписи

  • ◼️አንድ ሰው ሲያፈጥር የሚያደርገው ዱዓ ! ﻋﻨﺪ ﺍﻹﻓﻄﺎﺭ ﺗﻘﻮﻝ ﻣﺎ ﻛﺎﻥ ﻳﻘﻮﻝ ﺍﻟﻨﺒﻲ ﷺ ، ﻓﺈﻥ ﻣﻦ ﺳﻨﺘﻪ ﺻﻠﻰ ﺍﻟﻠﻪ ﻋﻠﻴﻪ ﻭﺳﻠﻢ ﺃﻧﻪ ﻛﺎﻥ ﺇﺫﺍ ﺃﻓﻄﺮ ﻗﺎل ( ﺫﻫﺐ ﺍﻟﻈﻤﺄ ﻭ ﺍﺑﺘﻠﺖِ ﺍﻟﻌﺮﻭﻕ ﻭﺛﺒﺖ ﺍﻷﺟﺮ ﺇﻥ ﺷﺎﺀ ﺍﻟﻠﻪ ) 📚[ ﺻﺤﻴﺢ ﺍﻟﺠﺎمع) [(4678) 👉በአማርኛ ሲነበብ፦ "ዘሃበ ዘመዑ ወብተለቲል ዑሩቁ ወሰበተል አጅሩ ኢንሻ አሏህ" ትርጉሙም፦" ጥም ተወገደ ጎሮሮዎችም ረጠቡ በአሏህ ፍቃድ አጅሩም ፀደቀ።" ማለት ነው።

  • ኢማም አል ነወዊ ኪታቡል አዝካር በሚለው ስለ ዚክር በሚያብራራው ኪታባቸው እንዲህ ይላሉ:‐ اعلم أن فضيلة الذكر غير منحصرة في التسبيح والتهليل والتحميد والتكبير ونحوها ، بل كل عامل لله تعالى بطاعة فهو ذاكر لله تعالى እወቅ ፤ አላህን ማስታወስ ብሎ ማለት በተስቢህ፣ በተህሊል፣ በተሕሚድ ፣ በተክቢር ብቻ የሚገደብ አይደለም። ይልቁንም ለአላህ (ሱ•ወ) ትዕዛዝ በመታዘዝ የሚሰራ ስራ ሁሉ ዚክር (አላህን ማስታወስ) ነው።” ኪታቡል አዝካር (1/9) ከሁሉም በላይ አላህ አዋቂ ነው። ✍ https://t.me/Abu_Umair2

  • 📮ተራዊሕ በመስገድ ከሚገኙ ጥቅሞች 🔹ተራዊሕ የረመዷን ወር ምሽቶች ላይ በጋራም ይሁን በተናጠል የሚሰገድ ነቢዩ صلى اللہ عليہ وسلم እና ሰሓቦቻቸው የተገበሩት "ሱናህ" ነው። በርካታ ጠቀሜታዎችና ምንዳዎችም አሉት። ከነዚህም በጥቂቱ:- ① ቀኑን በጾም ሌሊቱን በሰላት በማሳለፋችን ከደጋግ የአላህ ባሪያዎች እንመደባለን ② ቁርኣን በብዛት በማድመጣችን የአላህን እዝነት እናገኛለን ③ ተራዊሕ ብዙ ሩኩዕና ሱጁድ ስላለበት ሰፊ የዱዓና የዚክር እድል እናገኛለን ④ ከወንጀል ርቀን ጊዜያችንን በመልካም ስራ እናሳልፋለን ⑤ ዒባዳ ላይ ትዕግስትን እንማራለን ⑥ ሰላተል-ለይል እንለማመዳለን ⑦ በተደጋጋሚ ከኢማሙና ማእሙሞች ጋር "ኣሚን" በማለታችን ወንጀላችን ይማራል ⑧ መስጂድ ስንሄድና ስንመለስ በእርምጃችን ልክ ወንጀሎች ተራግፈው መልካም ስራዎች ይጻፉልናል ⑨ ሰላት እየጠበቀን በምናሳልፋቸው ጊዜያቶች መላኢካዎች ምህረት ይጠይቁልናል ①∅ የሙስሊሞችን ጀማዓ በማብዛት ሸይጣንና አጋዦችን እናስቆጫለን ①① ከመልካም ሰዎች ጋር በመቀላቀላችን መልካም ስራዎቻችን ወደ ሰማይ እንዲወጡና ተቀባይነት እንዲያገኙ እድል ይፈጥራል ①② ከአልባሌ ነገሮች ለመራቅ ለወጣቱ መልካም አርዓያ እንሆናለን ①③ ካመኑበትና ጥቅሙን ካወቁት ሁሉም ነገር ቀላልና የሚቻል መሆኑን በተጨባጭ እናይበታለን ①④ ቁርኣንን በብዛት በመስማት የአላህን እዝነት እናገኛለን እንዲሁም ብዙ በመስማት ትክክለኛውን የቁርኣን አቀራርም እንማራለን ①⑤ በቁኑት ዱዓ ወቅት ብዙ እኛ ያላሰብናቸውና መግለጽ የማንችላቸው ነገሮች ዱዓ ተደርጎ "ኣሚን" በማለታችን ትርፋማ እንሆናለን ①⑥ ከኢማሙ ጋር እስከሰላቱ ፍጻሜ ድረስ አብረን እየሰገድን ከቆየን ሌሊቱን በሙሉ ሲሰግድ ያደረን ሰው እጅር /ምንዳ እንሸምታለን ①⑦ የቂያማ ቀን መቆምን ያቀልልናል፥ዱኒያ ላይ ለጌታው ብሎ ረጅም ሰዓት የቆመ የቂያማ ቀን መቆም አይከብደውም ①⑧ ሰግደን ስንመለስ የውስጥ ደስታና እፎይታ እናገኛለን 💠ሌሎችንም የዲንም የዱኒያ በርካታ ጥቅሞችን እናገኛልንና ተራዊሕን በቋሚነት እንስገድ። አላህ ያግራልን! اللهم أعز الإسلام والمسلمين وأذل الشرك والمشركين ووحد صفوفنا وقنا شرور أنفسا يارب العالمين ✍ኡስታዝ አሕመድ ሼኽ ኣደም @ዛዱል መዓድ

  • ዘካ የሚሰጠው ለምን አይነት ሰው ነው? ~~~ የዘካ ባለሐቆች 8 ናቸው። በቁርኣን እንዲህ ተዘርዝረዋል:– (إِنَّمَا الصَّدَقَاتُ لِلْفُقَرَاءِ وَالْمَسَاكِينِ وَالْعَامِلِينَ عَلَيْهَا وَالْمُؤَلَّفَةِ قُلُوبُهُمْ وَفِي الرِّقَابِ وَالْغَارِمِينَ وَفِي سَبِيلِ اللَّهِ وَابْنِ السَّبِيلِ ۖ فَرِيضَةً مِنَ اللَّهِ ۗ وَاللَّهُ عَلِيمٌ حَكِيمٌ) "ግዴታ ምጽዋቶች (የሚከፈሉት) ለድሆች፣ ለምስኪኖችም፣ በርሷም ላይ ለሚሰሩ ሰራተኞች፣ ልቦቻቸውም (በእስልምና) ለሚለማመዱ፣ ጫንቃዎችንም (በባርነት ተገዢዎችን) ነፃ በማውጣት፣ በባለ እዳዎችም፣ በአላህ መንገድም በሚሰሩ፣ በመንገደኛም ብቻ ነው፡፡ ከአላህ የተደነገገች ግዴታ ናት፡፡ አላህም አዋቂ ጥበበኛ ነው፡፡" [አተውባ: 60] መጠነኛ ማብራሪያ ① ድሃ ማለት:– ለመኖር (ልብሱ፣ ጉርሱ፣ ትዳር ለመመስረት፣ ለመማር፣) ምንም ነገር የሌለው ወይም ትንሽ ነገር ያለው ማለት ነው። እነዚህን ፍላጎቶች ለማሟላት ዘካ ሊሰጠው ይችላል። ② ምስኪን ማለት: – ለመኖር የሚሆን ነገር በተወሰነ መጠን ያለው ሲሆን የሚበቃው ግን አይደለም። ③ ዘካ ላይ የሚሰሩ ሰራተኞች:– ዘካ እንዲሰበስቡ በመሪ የሚላኩ ሰዎች ናቸው። ዘካ ሶስት ነገሮችን ይፈልጋል። መሰብሰብ፣ መጠበቅና ማከፋፈል። በሶስቱም ዘርፍ ላይ የሚሰማሩ ሰራተኞች ሃብታም ቢሆኑ እንኳ ዘካ ይሰጣቸዋል። ልብ በሉ! ለዚሁ ስራ በመንግስት የሚሾሙትን እንጂ የግለሰቦች ወኪሎችን አይመለከትም። ደሞዝተኛ ሰራተኛም እዚህ ውስጥ አይገባም።   ④ ልቦቻቸው (በእስልምና) የሚለማመዱ ማለት ሁለት አይነት ናቸው። አንደኛ፡- ሙስሊም ያልሆነ ሰው ነው። ሙስሊም ባይሆንም ለተሻጋሪ ፋይዳ ሲባል ነው ሊሰጠው የተፈቀደው። – ቢሰጠው ይሰልማል ወይም ሌላ ፋይዳ ይገኝበታል ተብሎ ተስፋ የሚጣልበት ከሆነ፣ – የሚያደርሰው ጉዳት ኖሮ በዚህ ማስቆም የሚቻል ከሆነ ሁለተኛ፡- ሰለምቴ ነው። – በዲኑ እንዲጠነክር ወይም ለሌላ ሰው መስለም/ መጠንከር ሰበብ ይሆናል ተብሎ ከተገመተ – በሙስሊሞች ላይ ጉዳት የሚያደርስ ሆኖ በዚህ ማስቆም የሚቻል ከሆነ። [መጅሙዑል ፈታዋ፣ ኢብኑ ተይሚያ: 28/290] ⑤  እራሳቸውን ከአሳዳሪዎቻቸው በመግዛት ነፃ ለማውጣት የሚጣጣሩ ባሪያዎች ዘካ ከሚገባቸው ናቸው። የተጠለፉ/ የተማረኩ ሙስሊሞችን ማስለቀቅም ከዚሁ ውስጥ ይካተታል። ⑥ ባለ እዳ:– የተጣሉ ሰዎችን ለማስታረቅ አስቦ እዳ የገባ ሰው ሃብታም እንኳን ቢሆን ዘካ ሊሰጠው ይችላል። በራሱ ጉዳይ እዳ የተጫነው ከሆነ በኑሮው ባይቸገር እንኳ እዳውን ለመክፈል ሊሰጠው ይችላል። ⑦ በአላህ መንገድ የሚሰራ ማለት:– ለጂሃድ ዘማች ማለት ነው። ለትጥቅ፣ ለስንቅና አጠቃላይ ዝግጅት ዘካ ይሰጣል። ⑧ መንገደኛ:– አገሩ መግቢያ ከዘካ ገንዘብ ይሰጠዋል። Copy

  • አላህ ስራቸውን ይውደድላቸውና የነብያችን ﷺ ባልደረባ የነበሩት አቡ ሁረይራ እንዳስተላለፉት የአላህ መልእክተኛ ﷺ እንዲህ ብለዋል፡ “ምናልባት ለፆመኛ ከፆሙ ከረሃብ ውጪ ምንም የማያተርፍ አለ።  ምናልባት ለሊት ለሰላት የቆመ ሰው እንቅልፍ ከማጣት ውጭ ምንም ላይኖረው ይችላል።” ነብዩ ﷺ እንዲህ ብለዋል፦ «የሐሰት ንግግርን፣ በሀሰት መስራትን እንዲሁም የመሀይማንን ተግባር ያልተወ ሰው ምግቡንና መጠጡን መተዉ አላህ ደንታው አይደለም። » (ቡኻሪ ዘግበውታል) አላህ ከተራቡት ሳይሆን ከፆሙት ያድርገን

  • በጎ ሥራህ ካስደሰተክ ብሎም መጥፎ ሥራህ ልብክን አሳዝኖ ካስከፋክ ልብህ በሃያት አለች ማለት ነው። ኢማን ብሎ ማለት ፍጹም መሆን ማለት አይደለም። ኢማን ብሎ ማለት ትክክል የሆነውን ትክክል፣ ስህተት የሆነውን ስህተት ብላ የምትቀበል ልብ ባልተቤት መሆንንም ጭምር ነው። ነቢዩ ﷺ እንዲህ ብለዋል፦ إذا سرَّتك حسنتُك، وساءتْك سيئتُك فأنت مؤمنٌ “መልካም ስራህ ካስደሰተክ፣ መጥፎ ሥራህ ካሳዘነህ አንተ አማኝ ነህ።” • المسند أحمد (5/252) واللفظ له صحيح الجامع (٦٠٠)

  • በረመዷን በብዛት የሚፈፀሙ ስህተቶች ~ ① ሶላት ሳይሰግዱ መፆም፣ ② ሌሊቱን በጫት ካሳለፉ በኋላ ሰሑርን አስቀድሞ በመመገብ ሱብሕ ሳይሰግዱ መተኛት፣ ③ ቀኑን በእንቅልፍ፣ ሌሊቱን በተከታታይ ፊልም (ሙሰልሰላት) ማሳለፍ፣ ④ ረመዷንን ጠብቆ መንዙማና ነሺዳ እየለቀቁ ሰዎችን ከቁርኣን ማዘናጋት፣ ⑤ ተራዊሕን በንቃት እየሰገዱ ፈጅር ሶላትን በእንቅልፍ ማሳለፍ፣ ⑥ ተራዊሕ ላይ በየአራቱ ረከዐ መሐል የቢድዐ እና የሺርክ እንጉርጉሮዎችን ማስገባት፣ ⑦ የተራዊሕ ኢማሞች በጣም ረጅም የቁኑት ዱዓእ ማድረግ፣ ⑧ መግሪብ ሶላት ሲጠናቀቅ ስርአት በሌለው መልኩ ለፊጥራ መጣደፍ (ሰጋጆችን የሚያቋርጥ፣ የሰው ጫማ የሚያቀያይር፣… አለ) ⑨ ሌሊት ላይ "ተሰሐሩ" እያሉ መዞር፣ (10) የሱሑር ጊዜ ሳያልቅ ለጥንቃቄ በሚል ቀድሞ አዛን ማድረግ፣ (11) ሱሑር ላይ "ነወይቱ ሰውመ ገዲን" እያሉ በቃል መነየት፣ (12) እያንቀላፉ ተራዊሕ መስገድ፣ (13) ልጆች "እንፁም" ሲሉ ማበረታታት ሲገባ መከልከል፣ "ውሃ አያስፈጥርም፣ ተደብቀህ ብላና ትፆማለህ" እያሉ መዋሸትና ውሸት ማለማመድ፣ (14) ሴቶች በተጋነነ የምግብ ዝግጅት ሰፊ ጊዜያቸውን ማቃጠል፣ (15) ሴቶች ሽቶ ተቀብተው ለተራዊሕ መውጣት፣ (16) በተራዊሕ ወቅት የሴቶችና የወንዶች በየ ጎዳናውና በየካፌው አላስፈላጊ መዝረክረክ፣ (17) በዒሻእ ሶላት ላይ እየተዘናጉ አሳልፎ ዘግይቶ መግባት፣ (18) ፊጥራ ላይ ከመጠን በላይ መመገብ፣ (19) ቀኑን በካርታ፣ በዳማ እና መሰል አጉል ነገሮች ማሳለፍ፣ (20) ሙዚቃ ማዳመጥ፣ (21) የሰው ስራ የሚሰሩ ተቀጣሪዎች ጧት በሰዓት አለመግባት (አማና መጠበቅ፣ ቃልን ማክበር ግድ ይላል። ግዴታ ያልሆኑ ዒባዳዎች ተፅእኖ የሚያሳድሩብን ከሆነ መተው ወይም መቀነስ ነው)፣ (22) በተለይ በስራ ቦታዎች ላይ በመንዙማና በነሺዳ ማሳለፍ (መሆን ያለበት ከተመቼ ቁርኣን መቅራት፣ ካልሆነ ዚክር ማድረግ ወይም ደዕዋ ማዳመጥ፣ ካልሆነ ዝምታ ይሻላል።) (23) ለይለተል ቀድርን ለማየት ሰማይ ሰማይ እያንጋጠጡ ተሰብስበው እያወሩ መጠበቅ (የሚታይ ነገር የለም)፣ (24) አንዳንድ አካባቢዎች የዒሻእ ሶላትን በጣም በማዘግየት ሰው ጀማዐ ላይ እንዳይካፈል እንቅፋት መሆን፣ (25) አንዳንድ አካባቢዎች መስጂድ ውስጥ ጫት ይዞ ገብቶ መቃም፣ (26) አንዳንድ አካባቢዎች "ተርቲብ" ብለው ንፍሮ፣ ቆሎና መሰል ምግቦችን ወደ መስጂድ እንዲያቀርቡ ሰዎችን ማስገደድ፣ ወዘተ . Ibnu Munewor

  • 19 февр.6041из Abu_Umair2

    ውድ የዚህ ቻናል አባላት በሙሉ የምንፖስታቸውን ፖስቶች እየተመለከቱ ቢሆንም ቻናላችንነን #MUTE ካደረጉት ለኛ እንዳሉ አይቆጠርም። ምስሉ ላይ እንደምትመለከቱት ከታች #MUTE የሚል ካለ ምንም አይንኩት። #UNMUTE የሚል ካለ ደሞ አንድ ግዜ በመጫን MUTE ላይ በማድረግ የምንለቃቸውን ፖስቶች ስንት ሰው እንደሚያያቸው እንወቅ። https://t.me/Abu_Umair2

  • | | የጀሀነም በሮች ሊዘጉ የጀነት በሮች ሊከፈቱ ቀናት ይቀሩታል!!

  • Rammadan ቴሌግራም Channel፦  https://t.me/Abu_Umair2