Addis መረጃ™
Статистика@Addis_Mereja ቀዳሚ የመረጃ ምንጭ 🇪🇹 🇪🇹 . ⏬ምርት እና አገልግሎቶን ለማስተዋወቅ ከፈለጉ⏬ ⏬ ꜰᴏʀ ᴘᴀɪᴅ ᴘʀᴏᴍᴏᴛɪᴏɴ ⏬ መረጃዎችን ለመላክ @Adis_Merejaa_bot
- Последний пост
- 26 июл.
- Последнее чтение
- 12 авг.
- Постов за неделю
- 0
- Всего постов
- 22
- Тип
- открытый
- Язык
- und
- В каталоге с
- 12 авг.
- 1/24сутки в ленте
- 7 810
- 1/48двое суток
- 8 950
- 1/72трое суток
- 9 653
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
ባለሥልጣናቱ መታሰራቸው ተሰማ በሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የ ELMIS(የኢትዮጵያ የሥራ ገበያ መረጃ ሥርዓት) ፕሮጀክት ኃላፊ እና የውጭ ሀገር ሥራ ስምሪት ዋና ሥራ ፈጻሚን ጨምሮ በርካታ ከፍተኛ አመራሮች በፌደራል ፖሊስ በቁጥጥር ሥር መዋላቸው ተሰምቷል። ተጠርጣሪዎቹ በውጭ ሀገር ሥራ ስምሪትና በ ELMIS ሲስተም መረጃ በማጥፋት፣ በከባድ ሙስና፣ በሕገ-ወጥ የሰው ዝውውር እና የመንግሥትን የውጭ ምንዛሬ ለግል ጥቅም በማዋል ወንጀሎች የተጠረጠሩ ሲሆን፣ በአሁኑ ወቅት ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ በከፍተኛ የምርመራ ሂደት ላይ እንደሚገኝ የዘገበው ዘሀበሻ ነው። Via:- አዩዘሀበሻ @Addis_Mereja
የመጨረሻው ምዕራፍ ላይ ደርሰናል-ዶ/ር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል‼️ ዛሬ ሐምሌ 12/2018 ዓ.ም በመቀሌ ህዝቡን እና አመራሩን ሰብስበው አወያይተዋል። የትግራይ ህዝብ ጭቆናን የመሸከም ታሪክ የለውም ያሉት ዶ/ር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል፤ ይልቁንም መብቶቹ ለማረጋገጥ በመደራጀት ታግሏል፣ መብቶቹን አስከብሯል እንዲሁም የሌሎች ብሔረሰቦችን መብቶች አክብሮ የመጣ ህዝብ ነው ብለዋል። ለ17 ዓመታት በተደረገው የትጥቅ ትግል ውስጥ የትግራይ ህዝብ ከባድ መስዋእትነት በመክፈል አንባገነኑ የደርግ ስርዓት መደምሰሱን ያወሱት ዶክተር ደብረፅዮን፤ በአንባገነኑ መቃብር በሃገር ደረጃ ሰላም፣ ልማትና የዴሞክራሲ ግንባታ ማረጋገጡን ጠቅሷል፡፡ ሆኖም፣ ይህንን መቀበል ያልቻሉ ሐይሎች ጊዜና አጋጣሚውን በመጠበቅ፣ የትግራይን ህዝብ ከምድረገፅ ለማጥፋት በህዝባችን ላይ ጀኖሳይድ ፈፅሟል ያሉት ፕረዝዳንቱ፤ የትግራይ ህዝብ አንድነቱ በመጠበቅ ልህልውናው በከፈለው መስዋዕትነት ጭቆናን እና ህልውናውን ለማጥፋት ለመጣው ሐይል የማይቀበል መሆኑ በዓለም አደባባይ ያስመሰከረ እንደሆነ ጠቅሷል፡፡ የፕሪቶሪያው ስምምነት ሲፈረም፤ የትግራይ ሉዓላዊነት ለማረጋገጥ፣ ተፈናቃዮችን ለመመለስ እና ልማትን ለማረጋገጥ ከፍተኛ ተስፋ አድርገን ነበረ ያሉት ዶ/ር ደብረፅዮን ገብረሚካኤል፤የፌደራል መንግሥቱ በታቀደ ሁኔታ ትግራይን ዳግም ወደ ከበባና ክልከላ በማስገባት ለዳግም ጀኖሳይድ እየተዘጋጀ እንደሚገኝ አብራርቷል፡፡ እንደ ትግራይ፣ ለሰላም ስንል ከፍተኛ ትዕግስትና መስዋዕትነት እየከፈልን ነው፤ ይሁን እኛ ብቻ ሰላም ስለ ፈለግን ሊሳካልን አልቻለም ያሉት ዶ/ር ደብረፅዮን፤ አንድነታችን አጠናክረን የትግራይ መሰረታዊ ጥያቄዎች ማረጋገጥ ብቸኛ መፍትሔ ሆኖ መገኘቱ ተናግሯል፡፡ አሁን ባለንበት ሁኔታ መቀጠል አንችልም ያሉ ሲሆን እንደህዝብ የመከተ ዓቅሞቻችን በማደራጀት ህልውናችን ለማረጋገጥ በምንወስንበት ምዕራፍ ላይ እንገኛለን ብሏል፡፡ የፌደራል መንግስቱ ለሰላም በፍጹም ዝግጁ አይደለም፤ ስለዚህ ብሔራዊ ክብራችንና ሉዓላዊነታችንን ለመመለስ እንዲሁም የተፈናቀሉ ወገኖቻችንን መልሶ ለማቋቋም ትግላችንን ወደ ተጨባጭና ውጤታማ ደረጃ ማሸጋገር ይገባናል ብሏል፡፡ @Addis_Mereja
የአዲስ አበባ ታክሲዎች ጉዞ ከመጀመራቸው በፊት ክፍያ እንዲሰበስቡ ተወሰነ የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ የታክሲ አሽከርካሪዎች ከተወሰነው ታሪፍ በላይ እንዲሚያስከፍሉ ከማኅበረሰቡ የሚነሳውን ቅሬታ ለመፍታት ክፍያው ከመነሻው እንዲሰበሰብ የሚያስገድድ የአሠራር ሥርዓት መዘርጋቱን አስታውቋል። አሽከርካሪዎች በታሪፍ መመሪያው መሠረት ብቻ ከመነሻው የትራንስፖርት ክፍያ እንዲሰበስቡ ለማስቻል ተቆጣጣሪዎች በመነሻ መጫኛ ቦታዎች ላይ ተመድበው ሥራ መጀመራቸውን የቢሮው ምክትል ኃላፊ አቶ ዳኛቸው ሽፈራው ተናግረዋል። ይህ አሠራር በጉዞ ወቅት "ሒሳብ ጨምሩ" በሚል ከአሽከርካሪዎች የሚነሳውን አግባብነት የሌለው ጥያቄ ለመግታት የጎላ ፋይዳ እንደሚኖረው ታምኖበታል። ይሁን እንጂ አዲሱ አሠራር ተግባራዊ መደረጉን ተከትሎ አንዳንድ ተግዳሮቶች መፈጠራቸውን የቢሮው ኃላፊዎች ጠቁመዋል። በከተማዋ በሚገኙ መነሻዎች ላይ ክፍያውን አስቀድሞ በመሰብሰብ ሂደት የተወሰነ ጊዜ እየወሰደ መሆኑ በማኅበረሰቡ በኩል ቅሬታ መፍጠሩ ተገልጿል። በተመሳሳይ አንዳንድ አሽከርካሪዎች መንገድ ከጀመሩ በኋላ ታሪፍ የመጨመር አዝማሚያዎችን እያሳዩ መሆናቸውን ቢሮው አስታውቋል። ይህንን ችግር በዘላቂነት ለመቅረፍ ማኅበረሰቡ የጉዳዩን ፋይዳ በመገንዘብ ተገቢውን ትብብር እንዲያደርግና ህገ-ወጥ አሽከርካሪዎችን በተመለከተ ጥቆማዎችን በመስጠት የዜግነት ኃላፊነቱን እንዲወጣ አቶ ዳኛቸው አሳስበዋል። በሌላ በኩል ከዚህ ቀደም ያለ ረዳት በሚጭኑ አሽከርካሪዎች ላይ እርምጃ እንደሚወሰድ ሲገለጽ መቆየቱ የሚታወስ ቢሆንም፤ ቢሮው በአሁኑ ወቅት ትኩረቱን አዲሱ የአሠራር ሥርዓት ላይ ማድረጉን አመልክቷል። ይሁን እንጂ የረዳት አጠቃቀምን በተመለከተ ግልጽና ወጥ የሆነ የአሠራር ሥርዓት እንደሚያስፈልግ አቶ ዳኛቸው ገልጸዋል። @Addis_Mereja
አቶ ተወልደ ገብረማርያም የፓኪስታን አየር መንገድ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሆነው ተሸሙ የኢትዮጵያ አየር መንገድ የቀድሞ ዋና ሥራ አስፈጻሚ የነበሩት አቶ ተወልደ ገብረማርያም፣ የፓኪስታን ብሔራዊ አየር መንገድን (PIA) ከገጠመው ከፍተኛ ኪሳራ አውጥተው ወደ ትርፋማነት እንዲመልሱ በዋና ሥራ አስፈጻሚነት መመረጣቸውን ብሉምበርግ እና አረብኒውስ ዘግበዋል። ይህ ሹመት የተሰማው አየር መንገዱን ወደ ግል የማዛወሩ ሂደት የመጀመሪያ ምዕራፍ መጠናቀቁን ተከትሎ ሲሆን፣ "አሪፍ ሀቢብ ኮርፖሬሽን" የተባለው የግል ጥምረት የአየር መንገዱን የሥራ አመራር ቁጥጥር ተረክቧል። 👉አዲሶቹ ባለቤቶች የአየር መንገዱን የፋይናንስ አቅም ለማጠናከር፣ የበረራ አውሮፕላኖችን ለማዘመንና የበረራ መዳረሻዎችን ለማስፋፋት በመጀመሪያ ዙር 80 ቢሊዮን የፓኪስታን ሩፒ ( ወጪ አድርገዋል። አቶ ተወልደ ገብረማርያም የኢትዮጵያ አየር መንገድን በአፍሪካ ግዙፍና ስኬታማ አየር መንገድ በማድረግ ረገድ የነበራቸው ዓለም አቀፍ ዝና እና ልምድ ለዚህ ሹመት እንዳበቃቸው ተገልጿል። 👉ባለሀብቶቹ በአጠቃላይ 180 ቢሊዮን ሩፒ ለኢንቨስትመንት ያቀዱ ሲሆን፣ የአቶ ተወልደ መመረጥ አየር መንገዱን በክልላዊና በዓለም አቀፍ የኢንዱስትሪ ገበያ ውስጥ ተወዳዳሪ ለማድረግ ለተያዘው ስትራቴጂካዊ ዕቅድ ወሳኝ መሆኑ ታምኖበታል። በአሁኑ ወቅት የአቶ ተወልደ ሹመት በይፋ ከመታወጁ በፊት የተለመደው የመንግስት የጸጥታ ማጣሪያ እየተከናወነ መሆኑን የአየር መንገዱ የሥራ ኃላፊዎች ማረጋገጣቸውን ብሉምበርግ እና አረብ ኒውስ ዘግበዋል፡፡ መረጃው ለሌሎች እንዲደርስ ሼር ያድርጉ! @Addis_Mereja
ሕወኃት ኤርትራ እና ሱዳንን ያካተተ ጥምረት ፈጥሯል በማለት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ያቀረቡበትን ክስ ውድቅ አደረገ! «እኛ በራሳችን ኃይል ነው የምንተማመነው» ብሏል ሕዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ሕወኃት)ከኤርትራ እና ከሱዳን ጋር በጋራ እየሠራ ነው በማለትጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የሰነዘሩበትን ክስ ውድቅ አደረገ። ቡድኑ ከየትኛውም የውጭ አካል ወታደራዊ ድጋፍ እንደማይፈልግ እና «በራሱ ኃይል እንደሚተማመን» ገልጿል። ይህ ምላሽ የተሰጠው ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ባለፈው ማክሰኞ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በሰጡት ማብራሪያ ላይ፥ ሱዳን፣ ሕወኃት እና ኤርትራ በጋራ እየሠሩ መሆኑን በመጥቀስ፤ ይህንን ሁኔታ እ.ኤ.አ. በ1991 የደርግ ሥርዓት እንዲወድቅ ካደረገው ጥምረት ጋር በማመሳሰል ከሰጡት አስተያየት በኋላ ነው። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህ የተባለው ጥምረት በኢትዮጵያ ሉዓላዊነት ላይ የሚያመጣው አደጋ የለም ቢሉም፥ ስማቸውን ያልጠቀሷቸው የውጭ አካላት ከጀርባ ሆነው እየመሩት መሆኑን ጠቁመዋል። ለእነዚህ ክሶች ምላሽ የሰጡት የሕወኃት ቃል አቀባይ ሚካኤል አስገዶም፤ ድርጅታቸው አብረውት ተሰልፈው እንዲዋጉለት የውጭ አካላትን በፍጹም ጋብዞ አያውቅም ብለዋል። Via AS @Addis_Mereja
በአዲስ አበባ የቤት ኪራይ ጭማሪ ጣሪያ 11.5% ሆኖ ተወሰነ! 👉🏼የውል እድሳት ምዝገባም ከዛሬ ሐምሌ 1 ጀምሮ ይካሄዳል የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የዜጎችን የኑሮ ጫና ለመቀነስ እና በኪራይ ገበያው ላይ የሚስተዋሉ ህገ-ወጥና ዘፈቀዳዊ አሰራሮችን በዘላቂነት ለመግታት ታላቅ እርምጃ መውሰዱን ቀጥሏል። ከዚህ ቀደም በወጣው የቤት ኪራይ ቁጥጥር አዋጅ መሠረት፣ ለ2019 በጀት ዓመት የሚተገበረው ፍትሐዊ የቤት ኪራይ ዓመታዊ ጭማሪ ጣሪያ 11.5% ሆኖ መጽደቁን የቤቶች ልማትና አስተዳደር ቢሮ አስታወቀ። ይህንን ተከትሎ በመላው ከተማዋ የሚገኙ የግል መኖሪያ ቤቶች የአከራይ-ተከራይ አዲስ የውል እድሳት ምዝገባ ከዛሬ ሐምሌ 1 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ በሁሉም ክፍለ ከተማ ቤቶች አስተዳደር ፅ/ቤት በይፋ መተግበር ይጀምራል። ቢሮው እንዳመለከተው ፣ ይህ የዋጋ ማስተካከያ ውሳኔ በዘፈቀደ የተወሰነ ሳይሆን በከተማዋ ሰፊ ሳይንሳዊ ጥናት ተካሂዶ የነዋሪውን እውነተኛ የመክፈል አቅም ባገናዘበ መልኩ የተዘጋጀ ነው። ይህ አሰራር በአንድ በኩል አከራዮች ወቅቱንና የኢኮኖሚ ሁኔታውን ያገናዘበ ፍትሐዊ ገቢ እንዲያገኙ የሚያረጋግጥ ሲሆን ፤ በሌላ በኩል ደግሞ ተከራዮች ከገቢያቸው ጋር የተመጣጠነ ኪራይ በመክፈል ከተደጋጋሚ መፈናቀልና ከስነ-ልቦና ስጋት ድነው የተረጋጋ ሕይወት እንዲመሩ ያደርጋል። ውሳኔው በከተማዋ ያለውን የኑሮ ውድነት ጫና በከፍተኛ ደረጃ በመቀነስ ረገድ የጎላ ማህበራዊ ፣ ኢኮኖሚያዊ እና መልካም አስተዳደር ፋይዳዎች እንዳሉት ቢሮው አረጋግጧል። [አሐዱ] @Addis_Mereja
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ የደርግ ዘመንን ጥምረት በማንሳት ሱዳን፣ ሕወሓት እና ኤርትራ በጋራ እየሠሩ መሆኑን ገለጹ! - ስማቸው ያልተጠቀሱ ሌሎች የውጭ ተዋናዮች ተሳትፎ መኖሩንም ጠቆሙ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በዛሬው ዕለት በፓርላማ ተገኝተው በሰጡት ማብራሪያ፥ ሱዳን፣ ሕወሓት እና ኤርትራ በኢትዮጵያ ላይ በጋራ እየሠሩ መሆናቸውን የገለጹ ሲሆን፤ ድርጊቱን የደርግን ሥርዓት ለመጣል ከነበረው ጥምረት ጋር በሚመሳሰል መልኩ፣ ስማቸው ያልተጠቀሱ የውጭ ኃይሎች ከጀርባ እየተሳተፉ መሆኑን ጠቁመዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ቀርበው በሰጡት ማብራሪያ፤ ይህ ጥምረት በኢትዮጵያ ሉዓላዊነት ላይ የሚደቅነው ምንም ዓይነት ሥጋት እንደሌለ አስታውቀዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ለምክር ቤቱ ሲናገሩ «ሻዕቢያ፣ ወያኔ እና ሱዳን ይቅርና ሌሎችም ቢጨመሩ ለኢትዮጵያ ሉዓላዊነት ቅንጣት ታህል ሥጋት የላቸውም» ብለዋል። @Addis_Mereja
🔼🔼በአዲስ አበባ ከተማ፣ ፒያሳ አካባቢ የሚገኙ እና ዕድሜያቸው ከ70 እስከ 100 ዓመት የሚጠጉ በቅርስነት የተመዘገቡ ህንጻዎች ፈረሱ። የፌደራል የቅርስ ጥናት እና ጥበቃ ባለስልጣን በበኩሉ “ሲኒማ አምፒርን” ጨምሮ የፈረሱት ህንጻዎች “የቅርስ መመዘኛ መስፈርቶችን የሚያሟሉ አይደሉም” ብሏል። በመዲናይቱ አራዳ ክፍለ ከተማ ከፈረሱ ህንጻዎች መካከል ሸዋ ሆቴል፣ በስተኋላ ላይ ወደ ሄርሞን ሆቴል የተለወጠው የአጼ ኃይለ ሥላሴ በጎ አድራጎት ድርጅት ህንጻ እንዲሁም ቢያድግልኝ ሆቴል ይገኙበታል። ትላንት ሰኞ ሰኔ 29፤ 2018 ዓ.ም. ረፋድ ላይ በቦታው የተገኘችው የ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ዘጋቢ ህንጻዎቹ ሙሉ ለሙሉ ፈርሰው ዙሪያቸው በአረንጓዴ ቆርቆሮ መታጠር መጀመሩን ተመልክታለች። ከእነዚህ በተጨማሪ የወርቅ፣ የልብስ እና የህንጻ መሳሪያዎች መሸጫ ሱቆችም መፍረሳቸውን ታዝባለች። ህንጻዎቹ የፈረሱት ከሁለት ቀናት በፊት ቅዳሜ ሰኔ 27፤ 2018 እንደሆነ የዓይን እማኞች እና በአካባቢው ሱቆች የነበራቸው ባለቤቶች ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ተናግረዋል። ከፈረሱት የወርቅ ቤቶች በአንዱ የሚሰሩ ግለሰብ፤ እርሳቸው የሚሰሩበት መሸጫ ሱቅ የሚገኝበት “ሸዋ ሆቴል” በመባል የሚታወቀው ህንጻ እንደሚፈርስ ከአንድ ወር በፊት ተነግሯቸው እንደነበር ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ገልጸዋል። እኚሁ ግለሰብ ከወራት በፊት የኪራይ ውል ለማደስ ወደ ፌደራል ቤቶች ኮርፖሬሽን በሄዱበት ወቅት፤ ህንጻው የሚፈርስ በመሆኑ እስከዚያው ድረስ የወር ኪራይ እንዲከፍሉ እንደተነገራቸውም ጨምረው አስረድተዋል። ዕድሜ ጠገቡ “ሸዋ ሆቴል” እንዲፈርስ የተወሰነው፤ በአጠገቡ ለተገነባው ዘመናዊ ህንጻ ማስፋፊያ እንዲውል መሆኑን እንደተነገራቸውም አመልክተዋል። እርሳቸው የጠቀሱት ህንጻ፤ ከአድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየም ፊት ለፊት ተገንብቶ በመጠናቀቅ ላይ ያለውን “አራዳ ሌግዠሪ ሞልን” ነው። @Addis_Mereja
ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ከነገ በስቲያ ማክሰኞ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በመገኘት፤ የ2018 በጀት ዓመት የስራ አፈጻጸም እና የቀጣዩን ዓመት በጀት አስመልክቶ ከተሰናባቾቹ የፓርላማ አባላት ለሚቀርቡላቸው ጥያቄዎች ማብራሪያ እንደሚሰጡ ምንጮች ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ተናገሩ። የፓርላማ አባላቱ ጥያቄዎቻቸውን እንዲያስገቡ ቀነ ገደብ የተሰጣቸው እስካለፈው ሰኞ እኩለ ቀን ድረስ እንደነበር ምንጮቹ ገልጸዋል። በ2008 ዓ.ም የወጣው የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የአሰራር እና የአባላት ስነ ምግባር ደንብ፤ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በሚያዝላቸው ፕሮግራም መሰረት የመንግስትን የስራ አፈጻጸም ሪፖርት በዓመት ሁለት ጊዜ ለፓርላማው ማቅረብ እንዳለባቸው ይደነግጋል። ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ የፌደራል መንግስት የ2018 በጀት ዓመት የስድስት ወራት ሪፖርትን ለተወካዮች ምክር ቤት የላኩት ባለፈው ጥር ወር መጨረሻ ላይ ነበር። በተመሳሳይ መልኩ የበጀት ዓመቱ ዋና ዋና ስራዎች አፈጻጸም ሪፖርት ባለፈው ሳምንት አርብ ለፓርላማ አባላት ደርሷቸዋል። በ32 ገጽ የተዘጋጀው “ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” የተመለከተችው ይህ ሪፖርት፤ በኢኮኖሚ፣ በማህበራዊ ልማት፣ በፍትህ እና አስተዳደር ዘርፎች ያሉ የስራ ክንውኖች በዝርዝር የያዘ ነው። ሪፖርቱ የሰላምና ደህንነት ግንባታ ስራዎች፣ የውጭ ግንኙነት እና ዲፕሎማሲ እንዲሁም የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን አፈጻጸሞችንም ዳስሷል። የሰባተኛው ዙር ሀገራዊ ምርጫ ጉዳይም በሪፖርቱ በአጭሩ ተካትቷል። Via Ethiopia Insider @Addis_Mereja
видео или голосовое, без подписи
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 80 ቢሊየን ብር ትርፍ ሲያገኝ የመጀመሪያው የግል ባንክ አዋሽ ባንክ 40ነጥብ 7 ቢሊየን ብር ያልተጣራ ትርፍ ማግኘቱን ገለፀ! የመጀመሪያው በመንግስት የሚተዳደር ባንክ የሆነው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እና የመጀመሪያው የግል ባንክ አዋሽ ባንክ በተጠናቀቀው በጀት ዓመት እጅግ ከፍተኛ ውጤት ማስመዝገባቸውን ይፋ አድርገዋል።በዚህም መሰረት የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 80 ቢሊየን ብር ትርፍ ሲያገኝ፣ አዋሽ ባንክ ደግሞ 40 ነጥብ 7 ቢሊየን ብር ያልተጣራ ትርፍ ማስመዝገብ ችሏል። ሁለቱም የፋይናንስ ተቋማት በተቀማጭ ገንዘብ ማሰባሰብ፣ በብድር አቅርቦት፣ በዲጂታል አገልግሎት እና በውጭ ምንዛሬ ግኝት ዘርፎች ከፍተኛ ዕድገት ማሳየታቸውን በተናጠል በሰጡት መግለጫዎቻቸው አብራርተዋል። የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፕሬዚዳንት አቶ አቤ ሳኖ እንደገለጹት፣ ባንኩ በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ከ707.4 ቢሊየን ብር በላይ አዲስ ተቀማጭ ገንዘብ የሰበሰበ ሲሆን፣ ጠቅላላ ተቀማጭ ገንዘቡ ከ2.4 ትሪልዮን ብር በላይ ተሻግሯል። ይህ በአንድ ዓመት ውስጥ የተሰበሰበው መጠን በሀገሪቱ የባንክ ታሪክ የመጀመሪያው ሲሆን፣ አጠቃላይ ተቀማጩ ከ6 ዓመታት በፊት ከነበረው በ4 እጥፍ አድጓል ብለዋል። ባንኩ በበጀት ዓመቱ ከ648.02 ቢሊዮን ብር በላይ ብድር የሰጠ ሲሆን፣ ከዚህ ውስጥ ከ90.7 በመቶ በላይ (588.11 ቢሊዮን ብር) የሚሆነው ለግሉ ዘርፍ የተመደበ መሆኑንም ገልጿል። Via AS @Addis_Mereja
የዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት (አይ ኤፍ ኤም) የስራ አስፈጻሚ ቦርድ፤ ለኢትዮጵያ መንግስት 464 ሚሊዮን ዶላር ብድር “ወዲያውኑ እንዲለቀቅ” የሚያስችል ውሳኔ አሳለፈ። የድርጅቱ ስራ አስፈጻሚ ቦርድ ውሳኔውን ያሳለፈው፤ የኢትዮጵያን የተራዘመ ብድር አቅርቦት (ECF) አምስተኛ ዙር ግምግማን ከተመለከተ በኋላ ነው። የአይ ኤም ኤፍ ስራ አስፈጻሚ ቦርድ ለአራት ዓመታት የሚቆየውን የኢትዮጵያን የተራዘመ የብድር አቅርቦት ያጸደቀው በሐምሌ 2016 ዓ.ም ነው። ድርጅቱ ባለሙያዎችን ወደ ኢትዮጵያ በመላክ የሚያደርጋቸውን ግምገማዎች መሰረት በማድረግ፤ ከዚህ ቀደም ለአራት ጊዜያት ያህል የተለያየ መጠን ያላቸውን ብድሮች ለኢትዮጵያ መንግስት ሲለቀቅ ቆይቷል። የድርጅቱ የባለሙያዎች ቡድን አምስተኛ ዙር ግምገማ ለማድረግ ወደ ኢትዮጵያ መጥቶ የነበረው ባለፈው ሚያዝያ ወር መጨረሻ ላይ ነበር። ከቡድኑ ጉብኝት በኋላ ዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት እና የኢትዮጵያ መንግስት ባለስልጣናት “በባለሙያዎች ደረጃ ስምምነት ላይ መድረሳቸው” ባለፈው ግንቦት ወር መጨረሻ ላይ ይፋ ተደርጓል። አይ ኤም ኤፍ በዚሁ ወቅት ባወጣው መግለጫ፤ ስምምነቱ ለኢትዮጵያ 468 ሚሊዮን ዶላር ብድር መልቀቅ የሚያስችል እንደሆነ ገልጾ ነበር። ድርጅቱ ዛሬ ረቡዕ ሰኔ 24፤ 2018 ለሊት ባወጣው መግለጫ ይፋ ያደረገው የብድር መጠን ግን ባለፈው ግንቦት ወር ከተገለጸው በአራት ሚሊዮን ዶላር ያነሰ ነው። 🔴ለዝርዝሩ ➡️ https://ethiopiainsider.com/2026/18420/ @Addis_Mereja
"የሕወሃት አመራር ወደ አዲስ አበባም ሆነ ከኢትዮጵያ ውጭ የመጓዝ ፍላጎት የለውም!" -ፈትለወርቅ ገብረእግዚአብሔር የፌዴራል መንግሥቱ በአሁኑ ወቅት ወታደሮቹን ከምዕራብ ትግራይ ወደ ምስራቅ ትግራይ እያሠማራ መሆኑን የሕወሃት ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ፈትለወርቅ ገብረእግዚአብሔር በዛሬው ማምሻ ጋዜጣዊ መግለጫቸው አስታውቀዋል። በትግራይ ቴሌቪዥን በተላለፈው በዚህ መግለጫ ላይ ኃላፊዋ አሜሪካ በ"አክራሪ" የሕወሃት አመራሮችና አባላት ላይ የጣለችውን የቪዛ እገዳ አስመልክተው የተናገሩ ሲሆን፥ እገዳው በግለሰቦች ላይ ሳይሆን በሕወሃት "መርሆች" ላይ ያነጣጠረ ነው ብለዋል። ይሁን እንጂ ሕወሃት በመሠረታዊ መርሆዎቹ ላይ ፈጽሞ እንደማይደራደር አጽንዖት ሰጥተዋል። ፈትለወርቅ አክለውም፥ የሕወሃት አመራር ወደ አዲስ አበባም ሆነ ከኢትዮጵያ ውጭ የመጓዝ ፍላጎት እንደሌለው ለአሜሪካ ማሳወቃቸውን ገልጸዋል። የትግራይ ሕዝብና የድርጅቱ ጥያቄ ራስን በራስ የማስተዳደርና የራስን ዕጣ ፈንታ በራስ የመወሰን መሆኑን የጠቀሱት ኃላፊዋ፥ የአሜሪካ ጥቅም ሊረጋገጥ የሚችለው ሕወሃትን በማስፈራራት ሳይሆን አብሮ በመስራት ብቻ እንደሆነ አስገንዝበዋል። @Addis_Mereja
ስደተኞችን የተቃወመው የደቡብ አፍሪካውያን ሠላማዊ የተባለሠልፍ በተለያዩ አካባቢዎች እየተጀመረ ነው። የደቡብ አፍሪካ መገናኛ ብዙኃን ከማለዳው ጀምሮ ስደተኞችን በተቃወመው የደቡብ አፍሪካውያን አስፈሪ የተቃውሞ ሠልፍ ዙሪያ የሚያጠነጥኑ ሽፋኖችን በመስጠት ተጠምደዋል። በተለይም በጠዋቱ የዘገባ ሠዓታቸውየደቡብ አፍሪካ ፖሊስ ሙሉ በሙሉ ተዘጋጅቶ የተቃውሞ ሠልፉ ወደመጥፎ ክስተት እንዳይቀየር እየሰራ ስለመሆኑ በተለያዩ ከተማዎች ያሉ ሁኔታዎችን በማሳየት በስፋት ሲዘግቡተስተውለዋል። ከደቂቃዎች በፊት እየተሰሙ ያሉ መረጃዎች የማርች ኤንድ ማርች ንቅናቄ የሚመራው የተቃውሞ ሠልፍ በደርባን ኢተክዊኒ እና ምስራቅ ኬፕታውን አካባቢ ተጀምሯል። አፍሪካን ሬኔሳንስ ቴሌቪዥን ባገኘው መረጃ ሠልፉ በስፋት እንደሚከናወን ከተነገረባቸው ከተሞች አንዷበሆነችው ፕሪቶሪያ ፤ በተለይም የስደተኛ ሱቆች ሙሉ በሙሉ ማለት ይቻላል ተዘግተዋል።እንዲሁም በአካባቢው ያሉ የፀጥታ ኃይሎች በተጠንቀቅ ቆመው እየታዩ ነው። (Arts TV) @Addis_Mereja
በትግራይ ክልል አከራካሪው የግዳጅ ወታደራዊ ምልመላ አዋጅ በአስቸኳይ ተግባራዊ እንዲሆን ታዘዘ! ከሰሜኑ ጦርነት በፊት ከምርጫ ቦርድ እውቅና ውጭ በተካሄደ ምርጫ ተቋቁሞ የነበረውና በቅርቡ ወደ ሥራ የተመለሠው የትግራይ ክልል ምክር ቤት፣ ያጸደቀው የግዳጅ ወታደራዊ ምልመላ አዋጅ በአስቸኳይ ተግባራዊ እንዲሆን ትዕዛዝ አስተላልፏል። የምክር ቤቱ አፈጉባኤ ምኅረት ሃጎስ ለክልሉ ፍትሕ ቢሮ ሰኔ 17 ቀን በጻፉት ደብዳቤ፤ አዋጁ በክልሉ ነጋሪት ጋዜጣ ታትሞ እስኪወጣ ድረስ የክልሉ የፍትሕ አካላት፣ ጠቅላይ ፍርድ ቤት እና ፖሊስ ኮሚሽን በጊዜያዊነት በሕጉ እየሠሩበት እንዲቆዩ አዘዋል። ይህ አዋጅ በዶ/ር ደብረጽዮን ገብረሚካኤል የሚመራውና በቅርቡ የተቋቋመው ማዕከላዊ የጸጥታ ዕዝ በበላይነት ያስፈጽመዋል ተብሎ ይጠበቃል። ይህ በእንዲህ እንዳለ፣ ዓለም አቀፉ የሰብዓዊ መብቶች ተሟጋች ድርጅት ሂውማን ራይትስ ዎች (Human Rights Watch) የትግራይ ባለሥልጣናት ይህንን የግዳጅ ወታደራዊ ምልመላ አዋጅ “በዝባዥ” ሲል መኮነኑና በአስቸኳይ እንዲያነሱት ሰሞኑን በይፋ መጠየቁ ይታወሳል። ይሁን እንጂ የክልሉ ምክር ቤት ዓለም አቀፍ ግፊቶችን ወደ ጎን በመተው አዋጁ በፍጥነት መሬት ላይ እንዲወርድ ማዘዙ በክልሉና በአጠቃላይ በሀገሪቱ የሰላም ሂደት ላይ አዳዲስ ውጥረቶችንና ጥያቄዎችን እያስነሳ ይገኛል። @Addis_Mereja
በአይነቱ ልዩና ዘመናዊ የሆነው ዴማ ሆፕ ሪል ስቴት በእንግሊዝ ኢምባሲ አካባቢ የሚያስገነባው አዲሱ ሳይት ሙሉ መረጃ ከላይ በቪዲዮ እናገኘዋለን፡፡ ስለ ሙሉ መረጃ ለማግኘት ከታች በሚገኘው ስልክ ይደውሉ፡፡ +251941443188 @Addis_Mereja
видео или голосовое, без подписи
ብሄራዊ ባንክ ባካሄደው የ100 ሚ. ዶላር ጨረታ የዶላር ዋጋ ቀንሷል የኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ በዛሬው ዕለት ባካሄደው የ100 ሚሊዮን ዶላር የውጭ ምንዛሬ ጨረታ ላይ የብር ዋጋ መሻሻል ማሳየቱን አስታውቋል። በጨረታው ላይ 14 ባንኮች የተሳተፉ ሲሆን፣ የነበራቸው አጠቃላይ ፍላጎት ከ160 ሚሊዮን ዶላር በላይ ደርሶ ነበር። ይሁን እንጂ ማሸነፍ የቻሉት ዘጠኝ ባንኮች ብቻ ሲሆኑ፣ በዕለቱ አንድ ዶላር የተሸጠበት አማካይ እና ከፍተኛ ዋጋ 157 ብር ሆኖ ተመዝግቧል፤ ዝቅተኛው ዋጋ ደግሞ 152 ብር ደርሷል። ይህ የዛሬው የጨረታ ውጤት ካለፈው ሳምንት ጋር ሲነፃፀር የዶላር ፍላጎትም ሆነ የምንዛሬ ዋጋ መቀነሱን ያሳያል። ባለፈው ሳምንት በተካሄደው ተመሳሳይ የ100 ሚሊዮን ዶላር ጨረታ ላይ የባንኮች ፍላጎት 236 ሚሊዮን ዶላር ደርሶ የነበረ ሲሆን፣ አንድ ዶላር የተጫረተበት ዋጋም 158 ብር እንደነበር ይታወሳል። ይህ የዋጋ መቀነስ የብርን የመግዛት አቅም ለማጠናከር ተስፋ ሰጪ ምልክት እንደሆነ ተነግሮለታል። @Addis_Mereja
Addis መረጃ™ pinned a photo
видео или голосовое, без подписи