tgindex
Ethio Negari ኢትዮ ነጋሪ

Ethio Negari ኢትዮ ነጋሪ

Статистика

#NewsaboutEthiopia & the #Horn ይህ የቴሌግራም ቻናል ትኩስ ዜናዎች፣ አዝናኝ መረጃዎች፣ ትንታኔዎች እና የስራ ቅጥር ማስታወቂያ የሚቀርብበት ነው። የዩቲዩብ ቻናላችንን ሰብስክራይብ አድርገው ቤተሰብ ይሁኑ። http://youtube.com/@ethionegari

Последний пост
13 авг.
Последнее чтение
15 авг.
Постов за неделю
4
Всего постов
172
Тип
открытый
Язык
ti
Категория
Видео
В каталоге с
12 авг.
Подписчики
1 868
+12 за 3 дн.
Сутки
−1
−0,05%
Неделя
 
Месяц
 
Просмотров на пост
496
40 постов
Вовлечённость
26,6%
к подписчикам
Постов в день
0,6
всего 172
Упоминаний
0
каналов
Охват размещения
оценка
1/24сутки в ленте
327
1/48двое суток
374
1/72трое суток
404

Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.

Посты

  • ኢትዮጵያ በፕሬዝዳንት እንድትመራ ስምምነት ላይ መደረሱ ተገለጸ ኢትዮጵያ በፕሬዚዳንት እንድትመራ በሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ላይ እየተሳተፉ የሚገኙ ተመካካሪዎች መግባባት መደረሳቸው ተሰምቷል። ይሁንና ፕሬዚዳንቱ በሕዝብ ይመረጥ ወይስ በፓርላማ በሚለው ጉዳይ ተመካካሪዎች ስምምነት ላይ አለመድረሳቸው ተገልጿል። ኢትዮጵያ በጠቅላይ ሚኒስትር ቀርቶ በፕሬዚዳንት እንድትመራ፣ የመንግሥት አደረጃጀትና ቅርጽ፣ እንዲሁም የፖለቲካ ሥርዓት፣ የፖለቲካ ውክልናና የምርጫ ሥርዓት አጀንዳ ላይ የ500 ቡድን ተመካካሪዎች ሙሉ በሙሉ በምክረ-ሐሳብ ደረጃ መግባባት ላይ ደርሰዋል ተብሏል። በዚሁ አጀንዳ ላይ ተወያይ የነበሩ ተመካካሪዎች ለሪፖርተር በሰጡት አስተያየት፣ በቀረቡት አብዛኞቹ ምክረሐሳቦች መግባባት ላይ መደረሱን ሆኖም ያላግባቡና ወደ ቀጣይ የተሻገሩ ጉዳዮች መኖራቸውንም ገልጸዋል። በዚህም የ500 ቡድን ተመካካሪዎች የአገሪቱ አስተዳደር ሥርዓት ፓርላሜንታሪ ሆኖ እንዲቀጥል፣ የአገሪቱ መሪ ፕሬዚዳንት እንዲሆን፣ አዲሱ ተመራጭ ፕሬዚዳንትም የጠቅላይ ሚኒስትሩና የፕሬዚዳንቱ ሥልጣንና ተግባርን ጠቅልሎ እንዲወጣ በምክረሐሳብ ደረጃ ከመግባባት ላይ መደረሱን፣ ይህም ጠቅላይ ሚኒስትር እንዲቀር የሚያደርግ መሆኑን ተናግረዋል። የአገሪቱ መሪ የሥልጣን ዘመን 6 ዓመት ሆኖ ለሁለት ዙር እንዲደረግ፣ የክልል መሪዎችም ከፌዴራሉ ጋር ተመሳሳይ እንዲሆን በምክረሐሳብ ደረጃ ከመግባባት ላይ መደረሱን ገልጸዋል። የሕገመንግሥት ጉዳዮች ተርጓሚ ፍርድ ቤት እንዲቋቋም፣ አሁን ያለው የፌዴሬሽን ምክር ቤት አሠራር ያልመለሳቸው የማንነትና የራስን በራስ የማስተዳደር ጥያቄዎች “ሕብረ ብሔራዊ አንድነት ኮሚሽን" የሚል ሥያሜ ያለው ገለልተኛ ተቋም በአስቸኳይ ተቋቁሞ በአጭር ጊዜ ውስጥ ምላሽ እንዲሰጥባቸው ለዚህም ይረዳ ዘንድም ልዩ የባለሙያዎች ቡድን እንዲቋቋም በምክረሐሳብ ደረጃ ከመግባባት ላይ መደረሱ ተገልጿል። ይህ በዚህ እንዳለም በፌደራል ከተማ ዋና መቀመጫ በሆነችው የአዲስ አበባ ከተማ ጉዳይ በቀረቡት ሁለት አማራጮች ላይ እስካሁን ከስምምነት ላይ እንዳልተደረሰ ተሰምቷል። ለበለጠ እና ትኩስ መረጃዎች ከስር ያሉትን ሊንኮች በመጫን ቤተሰብ ይሁኑ። �Telegram https://t.me/EthioNegarii �Twitter https://twitter.com/EthioNegari � YouTube https://youtube.com/channel/UCxywavkb3e3K7BY3BEh2piQ Facebook  https://www.facebook.com/EthioNegarii/ Website https://ethionegari.com/ LinkedIn https://www.linkedin.com/company/ethio-negari #ethiopia #Nationaldialogue #NDC #addisababa

  • ሔኒከን ቢራ ፋብሪካ ከግል ድርጅቶች ቁጥር አንድ ግብር ከፋይ ኩባንያ ተባለ ኢትዮጵያ በተጠናቀቀው የ2018 በጀት ዓመት ውስጥ 1.5 ትሪሊዮን ብር ከግብር የሰበሰበች ሲሆን ከግል ድርጅቶች ሔኒከን ቢራ ቁጥር አንድ ግብር ከፋይ ተቋም ሆኗል። ከአራት በላይ የቢራ ብራንዶችን ለኢትዮጵያ ገበያ በማምረት ላይ ያለው የጀርመኑ ሔኒከን ኩባንያ 26 ቢሊዮን ብር እንደከፈለ ተገልጿል። ሔኒከን እንደሀገር ከፍተኛ ግብር ከሚከፍሉ ተቋማት መካከል በአራተ ደረጃ ላይ ስሙ ተጠቅሷል። በዚህ በጀት ዓመት ለመንግስት 10 ከፍተኛ ግብር ከፋይ ድርጅቶች መካከል 7ቱ የመንግስት የልማት ድርጅቶች ናቸው። ኢትዮ ቴሌኮም 66  ቢሊዮን ብር  በመክፈል እንደ ሀገር ቁጥር አንድ ግብር ከፋይ ተቋም ነው። ሁለተኛው ግብር ከፋይ ተቋም የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሲሆን ከፈለው 37 ቢሊዮን ብር ሲከፍል የኢትዮጵያ አየር መንገድ ደግሞ 31 ቢሊዮን ብር እንደከፈለ ተገልጿል። የኢትዮጵያ መርከብና ሎጅስቲክ ድርጅት ደግሞ 22 ቢሊዮን ብር ሲከፍል የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሀይል 18 ቢሊዮን ብር እንዲሁም አብዛኛው ሼሩ በልማት ድርጅቶች የተያዘው አዋሽ ባንክ 15 ነጥብ 5 ቢሊዮን ብር መክፈሉ ተገልጿል። የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት 13 ነጥብ 5 ቢሊዮን ብር ሲከፍል ሌላኛው የቢራ አምራች ድርጅት ቢጂአይ ኢትዮጵያ 12 ነጥብ 6  ቢሊዮን ብር ከፍሏል ተብሏል።   ይህ በዚህ እንዳለም በውርስ ወይም በስጦታ በሚገኙ ገቢዎች ላይ አዲስ የታክስ ዓይነት ሊጣል መሆኑ ተገልጿል።   ከአንድ ሚሊዮን ብር በላይ የሆኑ የውርስና የስጦታ ገቢዎች ለዚህ ታክስ መክፈል ግዴታ ይሆንባቸዋል ተብሏል። ለበለጠ እና ትኩስ መረጃዎች ከስር ያሉትን ሊንኮች በመጫን ቤተሰብ ይሁኑ። �Telegram https://t.me/EthioNegarii �Twitter https://twitter.com/EthioNegari � YouTube https://youtube.com/channel/UCxywavkb3e3K7BY3BEh2piQ Facebook  https://www.facebook.com/EthioNegarii/ Website https://ethionegari.com/ LinkedIn https://www.linkedin.com/company/ethio-negari #ethiopia #Tax #Heinekenbeer

  • ሰባት አትሌቶች እና አሰልጣኞቻቸው በአሜሪካ ጥገኝነት ጠየቁ ከሰሞኑ በአሜሪካ ኦሬገን በተካሄደው የአለም አትሌቲክስ ከ 20ዓመት በታች ሻምፒዮና የተሳተፉ የኢትዮጵያ ልዑክ አባላት በአሜሪካ መጥፋታቸው ተሰምቷል። ለውድድሩ ወደ አሜሪካ ካቀናው ልዑክ ቡድን ውስጥ ሰባት ያህል አባላት መኮብለላቸው ተገልጿል። ከልዑክ ቡድኑ ጋር የማይገኙት አባላት 4️⃣ አትሌቶች እና 3️⃣ አሰልጣኞች መሆናቸው ተነግሯል። ወደ አሜሪካ ካመሩት አራት አሰልጣኞች ሶስቱ መቅረታቸውን ተከትሎ አሰልጣኝ መሰረት ብቻ ወደ ኢትዮጵያ በመመለስ ላይ ይገኛሉ ተብሏል። ኢትዮጵያ በውድድሩ 2️⃣ የወርቅ ፣ 3️⃣ የብር እና 1️⃣ የነሐስ ሜዳልያ በማሳካት ማጠናቀቋ አይዘነጋም። ምንጭ ሀትሪክ ስፖርት ለበለጠ እና ትኩስ መረጃዎች ከስር ያሉትን ሊንኮች በመጫን ቤተሰብ ይሁኑ። �Telegram https://t.me/EthioNegarii �Twitter https://twitter.com/EthioNegari � YouTube https://youtube.com/channel/UCxywavkb3e3K7BY3BEh2piQ Facebook  https://www.facebook.com/EthioNegarii/ Website https://ethionegari.com/ LinkedIn https://www.linkedin.com/company/ethio-negari #ethiopia #athletics

  • የኢትዮጵያ አየር መንገድ  ምዝገባ ተጀመረ! የኢትዮጵያ አየር መንገድ የበረራ አስተናጋጅ እና የአውሮፕላን ጥገና ቦታዎች ምዝገባ ዛሬ ተጀምሯል። እስከ ነሐሴ 8 ቀን 2018 ዓ.ም በሚቆየው በዚህ በኦንላይን ምዝገባ አመልካቾች የትምህርት ማስረጃዎቻቸውን እና መታወቂያቸውን በተለዩ ሁለት የፒዲኤፍ (PDF) ፋይሎች አዘጋጅተው ማቅረብ ይኖርባቸዋል። ​የምዝገባ ሂደቱ ሙሉ በሙሉ በኢንተርኔት የሚከናወን ቢሆንም የጽሁፍ ፈተና እና የኢንተርቪው ሂደቶች በአዲስ አበባ ብቻ የሚሰጡ በመሆናቸው የክፍለ ሀገር  አመልካቾች ይህንን ታሳቢ ማድረግ አለባቸው። የፋይል መጠኑም ከ1 ሜጋባይት መብለጥ የሌለበት ሲሆን ዝርዝር መረጃዎችን እና የአመዘጋገብ ቅደም ተከተሎችን በኩባንያው ይፋዊ ድረ-ገጽ  ይከታተሉ። ለበለጠ እና ትኩስ መረጃዎች ከስር ያሉትን ሊንኮች በመጫን ቤተሰብ ይሁኑ። �Telegram https://t.me/EthioNegarii �Twitter https://twitter.com/EthioNegari � YouTube https://youtube.com/channel/UCxywavkb3e3K7BY3BEh2piQ Facebook  https://www.facebook.com/EthioNegarii/ Website https://ethionegari.com/ LinkedIn https://www.linkedin.com/company/ethio-negari #ethiopia #Ethiopianairlines #aviation

  • የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ከ118 ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ ማግኘቱን አስታወቀ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት በተጠናቀቀዉ የ2018 በጀት ዓመት ከኢነርጂ ሽያጭ ፣ ከአዲስ ደንበኞች መስተንግዶ፣ ከማያገለግሉ ንብረቶች ሽያጭ እና ከሌሎች ልዩ ልዩ የገቢ ምንጮች በአጠቃላይ 118.91 ቢሊዮን ብር መሰብሰብ መቻሉን የተቋሙ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ኢንጅነር ጌቱ ገረመው ተናግረዋል፡፡ ይህም በዕቅድ ለመሰብሰብ ከተያዘው 115.86 ቢሊዮን ብር አንፃር 103 በመቶኛ አፈፃፀም ያለው መሆኑን ገልጸዋል፡፡ ዋና ስራ አሰፈፃሚው በ2018 በጀት ዓመት  ከኢነርጂ ሽያጭ ብቻ 76.53 ቢሊዮን ብር ገቢ መገኘቱን ገልፀው ገቢው  ከ2017 በጀት ዓመት ጋር ሲነፃፀር የ74.3 በመቶ እድገት አሳይቷል ። ከኢነርጂ ሽያጭ ከተሰበሰበዉ አጠቃላይ ገቢ ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሃይል ለተፈፀመዉ የኢነርጂ ግዢ 48.42 ቢሊዮን ብር ክፍያ መፈፀሙም ተጠቁሟል ። ኢንጅነር ጌቱ አክለውም በ2018 በጀት ዓመት 664 ሺህ 505 አዲስ ደንበኞችን የኤሌክትሪክ ኃይል ተጠቃሚ መደረጋቸዉን ጠቅሰዋል። ይህም ቁጥር በተቋሙ ታሪክ በዚህ ደረጃ ሲለካ የመጀመሪያው እንዲሁም ከአፍሪካ መሰል አገልግሎት አቅራቢ ኩባንያዎች አንፃር አንደኛ መሆኑ ተገልጿል። ለበለጠ እና ትኩስ መረጃዎች ከስር ያሉትን ሊንኮች በመጫን ቤተሰብ ይሁኑ። �Telegram https://t.me/EthioNegarii �Twitter https://twitter.com/EthioNegari � YouTube https://youtube.com/channel/UCxywavkb3e3K7BY3BEh2piQ Facebook  https://www.facebook.com/EthioNegarii/ Website https://ethionegari.com/ LinkedIn https://www.linkedin.com/company/ethio-negari #ethiopia #EEU #electricity

  • የጉምሩክ ኮሚሽን ከፍተኛ አመራርን ጨምሮ ከ91 በላይ ሰዎች በተደራጀ ወንጀ ተጠርጥረው ታሰሩ የኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር አዘዘው ጫኔ  በተደራጀ የኢኮኖሚ ወንጀል ተጠርጥረው በቁጥጥር ስር ከዋሉት 91 ግለሰቦች መሀል ይገኙበታል ተብሏል። ​በጉዳዩ ላይ ከተካሄደው ምርመራ ከተገኙ ግኝቶች መካከል፡- ​በገቢዎች እና ጉምሩክ አስተዳደር ውስጥ የተደራጀ ህገ-ወጥ መረብ መኖሩ ተጠቁሟል። የታክስ ምዘናዎችን ማሻሻጥ፣ ሀሰተኛ ደረሰኞችን ማስተናገድ እና የኤሌክትሮኒክስ መረጃዎችን መሰረዝ እንደ ዘዴ ጥቅም ላይ ውለዋል ተብሏል። ​ድርጊቶቹ የመንግስት ገቢ እንዲቀንስ ማድረጋቸው ተመልክቷል። ​በአሁኑ ወቅት ጉዳዩ በህግ አስከባሪ አካላት ተይዞ ምርመራው በዝርዝር እየተካሄደ እንደሚገኝ የመንግስት ኮሙንኬሽን ሚንስትር እናታለም መለሰ በሰጡት መግለጫ ላይ ተናግረዋል። ለበለጠ እና ትኩስ መረጃዎች ከስር ያሉትን ሊንኮች በመጫን ቤተሰብ ይሁኑ። �Telegram https://t.me/EthioNegarii �Twitter https://twitter.com/EthioNegari � YouTube https://youtube.com/channel/UCxywavkb3e3K7BY3BEh2piQ Facebook  https://www.facebook.com/EthioNegarii/ Website https://ethionegari.com/ LinkedIn https://www.linkedin.com/company/ethio-negari #ethiopia #corruption #crime

  • በኢትዮጵያ ሙስና አሳሳቢ ደረጃ ላይ መድረሱ ተገለጸ የፌዴራል ሥነ ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን ሙስናን አስመልክቶ ያለውን ግንዛቤ የተመለከተ የዳሰሳ ጥናት በማካሄድ፣ የመሬትና የገቢዎች ተቋማትን ጨምሮ በበርካታ ተቋማት ውስጥ ሙስና አሳሳቢ መሆኑን ማረጋገጡን አስታውቋል። የመሬት አስተዳደርና የይዞታ ምዝገባ፣ የገቢዎችና ታክስ ጽሕፈት ቤቶች፣ የኮንስትራክሽን ፈቃድ ቁጥጥር፣ የንግድና ትራንስፖርት ቢሮዎች፣ የወረዳና የቀበሌ አስተዳደሮች በከፍተኛ ደረጃ ለሙስና ተጋላጭ መሆናቸው በጥናቱ ተለይቷል ብሏል፡፡ ኮሚሽኑ ለዳሰሳ ጥናት በተወሰደ ናሙና ከ60 በላይ የሚሆኑት ኢትዮጵያውያን ሙስና በማኅበራዊ፣ በኢኮኖሚያዊና በፖለቲካዊ ተግባራት ከፍተኛ እንቅፋትና ችግር የፈጠረ አሳሳቢ ችግር መሆኑን እንደነገሩት ገልጿል፡፡ በአቋራጭ የመበልፀግ ፍላጎት፣ የሥነ ምግባር ጉድለት፣ ውስብስብና ግልጽ ያልሆኑ የአገልግሎት አሰጣጥ ሒደቶችና የሕግ ማስከበር ድክመቶች ለሙስና መስፋፋት ዋነኛውንና ቀዳሚውን ድርሻ እንደሚይዙ የኮሚሽኑ የጥናት ሪፖርት ያመለክታል፡፡ በጥናቱ ጉቦ ለመስጠት የሚገደዱ ሰዎች ለድርጊታቸው የሚያቀርቡት አንዱ ምክንያት አገልግሎቱን ለማግኘት ሌላ አማራጭ በማጣታቸው እንደሆነ ተገልጿል፡፡ ግለሰቦች ጉቦ የሚሰጡት የሚፈልጉት አገልግሎት እንዲፈጸምላቸውና የሚጠበቅባቸውን ባለማድረጋቸው ሊደርስባቸው የሚችለውን እንግልት ለማስቀረት መሆኑን ጥናቱ ያመለክታል፡፡ የሙስና ድርጊትን ለመጠቆም የሚፈልጉ ግለሰቦች ሊደርስባቸው የሚችል የበቀል ዕርምጃና የማስፈራራት ሥጋት በመኖሩ፣ አስተማማኝ የጠቋሚዎች ጥበቃ ሥርዓት ማነስ፣ እንዲሁም የጥቆማ አሰጣጥ ሒደቱ ረዥምና ውስብስብ መሆን ኅብረተሰቡ ሙስና ለመጠቆም ሥጋት እንዳለበት በጥናቱ መገለጹ ተነግሯል፡፡ ይህ በዚህ እንዳለ የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን አገልግሎት በማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያው እና በንግድ ሥርዓቱ ላይ እክል ፈጥረዋል በሚል በተጠረጠሩ አካላት ላይ ሰፊ እና የተቀናጀ የሕግ ማስከበር እርምጃ መወሰዱን ይፋ አድርጓል። ​የኮሙዩኒኬሽን ሚኒስትሯ ወይዘሮ እናትዓለም መለሰ በሰጡት መግለጫ፣ በንግድና ፋይናንስ ዘርፍ የታዩ ሕገ-ወጥ አሠራሮችን፣ የምርት እጥረቶችንና የዋጋ ንረትን ለመግታት በተካሄዱ የተቀናጁ ኦፕሬሽኖች ተከታታይ እርምጃዎች መወሰዳቸውን ገልጸዋል። ​በተካሄዱት ኦፕሬሽኖች በሕገ-ወጥ የገንዘብ ዝውውር የተጠረጠሩ 169 ግለሰቦች በቁጥጥር ሥር ውለዋል። በተጨማሪም ከ7,000 በላይ መጋዘኖችና የንግድ ድርጅቶች፣ 183 የኮንትሮባንድ ተሳታፊዎች እና 38 የቤቲንግ ድርጅቶች ላይ ሕጋዊ እርምጃና እገዳ ተጥሏል። ለበለጠ እና ትኩስ መረጃዎች ከስር ያሉትን ሊንኮች በመጫን ቤተሰብ ይሁኑ። �Telegram https://t.me/EthioNegarii �Twitter https://twitter.com/EthioNegari � YouTube https://youtube.com/channel/UCxywavkb3e3K7BY3BEh2piQ Facebook  https://www.facebook.com/EthioNegarii/ Website https://ethionegari.com/ LinkedIn https://www.linkedin.com/company/ethio-negari #ethiopia #corruption #crime

  • አቶ ተወልደ ገብረማርያም የህንድ አየር መንገድን እንዲመሩ ተሾሙ የቀድሞው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ስራ አስፈጻሚ አቶ ተወልደ ገብረማርያም የሕንድ አየር መንገድን እንዲመሩ ተሾመዋል። በአፍሪካ ካሉ ስኬታማ የአቪዬሽን ባለሙያዎች መካከል አንዱ የሆኑት አቶ ተወልደ ከአንድ ወር በፊት በኪሳራ ላይ የነበረውን የፓኪስታን አየር መንገድን እንዲመሩ ቢጠየቁም ሀላፊነቱን ሳይቀበሉ ቀርተዋል።   ለበለጠ እና ትኩስ መረጃዎች ከስር ያሉትን ሊንኮች በመጫን ቤተሰብ ይሁኑ። �Telegram https://t.me/EthioNegarii �Twitter https://twitter.com/EthioNegari � YouTube https://youtube.com/channel/UCxywavkb3e3K7BY3BEh2piQ Facebook  https://www.facebook.com/EthioNegarii/ Website https://ethionegari.com/ LinkedIn https://www.linkedin.com/company/ethio-negari #ethiopia #Tewelde #Aviation #Airindia

  • ደላሎችን ከጨዋታ ውጪ የሚያዱርገው አፕልኬሽን... የቤት ውስጥ ሰራተኛን ጨምሮ የግል አገልግሎት ሰራተኞች እና አሰሪዎችን የሚያገናኝ፣ ደላላን የሚተካ መተግበሪያ እየተዘጋጀ መሆኑ ተገልጿል። የግል አገልግሎት ቅጥር የሚባሉትን እንደ አትክልተኛ፣ የቤት ውስጥ ተንከባካቢ፣ የቤት ውስጥ አብሳይ (ሼፍ) እና ሌሎችም ዘርፎች የቅጥር ግንኙነት ከደላላ ጣልቃ-ገብነት የሚያላቅቅ መተግበሪያ እና አዲስ ደንብ እየተዘጋጀ እንደሆነ ተገለጸ። ዓለም አቀፍ የሥራ ድርጅት ኮንቬንሽን 189ን ታሳቢ አድርጎ የተዘጋጀው ደንብ ለፍትሕ ሚኒስቴር መቅረቡን እና በቅርቡ በሚኒስትሮች ምክር ቤት ይጸድቃል ተብሎ እንደሚጠበቅ ሥራ እና ክህሎት ሚኒስቴር አስታውቋል። አንድ ዓመት አካባቢ ለሚፈጅ ጊዜ ግብዓት በማሰባሰብ እና ባለድርሻ አካላትን በማወያየት የተዘጋጀው ደንብ፣ የቤት ሠራተኞች መመዝገቢያ ሶፍትዌር ሲስተም እንዲኖረው የሚያስችል መተግበሪያ እየተዘጋጀለት እንደሆነ የሥራ እና ክህሎት ሚኒስቴር የአሰሪና ሠራተኛ ጉዳይ ዘርፍ የኢንዱስትሪ ግንኙነትና የሥራ ሁኔታዎች ቁጥጥር መሪ ሥራ አስኪያጅ አቶ ጥዑመ-እዝጊ በርሔ መናገራቸውን አሀዱ ራዲዮ ዘግቧል። ስራ አስኪያጁ በማብራሪያቸው፤ አዲሱ አሰራር በተግባር ላይ በሚውልበት ጊዜ አሰሪ እና ሠራተኞች በመሀል ደላላ ሳያስፈልጋቸው በአፕሊኬሽን አማካኝነት ተገናኝተው በሕጋዊ ውል ቅጥር መፈጸም እንደሚችሉ ገልጸዋል። በተጨማሪም፤ ከዚህ ቀደም በቤት ውስጥ ሰራተኛ እና አሰሪ መካከል ይፈጠር የነበረ አለመግባባት በፍትሐ ብሔር ይታይ እንደነበር አስታውሰው፤ አዲሱ ደንብ ለፍትሕ ሂደቱ አስቸጋሪ የነበረን አሰራር በማረም ጉዳዩ በአሰሪ እና ሰራተኛ አዋጁ እንዲታይ ያደርጋል ብለዋል። ይህ መሆኑ የሠራተኛውንም ሆነ የአሰሪውን መብት እና ግዴታ ለማስጠበቅ እንደሚያግዝና ከሌሎች ሀገራት ተሞክሮ በመውሰድ የተዘጋጀ መሆኑ ተመላክቷል። የደሞዝ ጉዳይን በተመለከተ ለጊዜው በአሰሪና ሠራተኛ ስምምነት የሚወሰን መሆኑ ተገልጿል። ለወደፊቱም ዝቅተኛ የደሞዝ ወለል ሲወሰን በዚሁ መሠረት የሚካተት ይሆናል ተብሏል። የግል አገልግሎት ቅጥር የሚባሉት እንደ አትክልተኛ፣ የቤት ውስጥ ተንከባካቢ፣ የቤት ውስጥ አብሳይ ሼፍ እና ሌሎችም ዘርፎች በዚህ ሲስተም ውስጥ ይካተታሉ ተብሏል።   ለበለጠ እና ትኩስ መረጃዎች ከስር ያሉትን ሊንኮች በመጫን ቤተሰብ ይሁኑ። �Telegram https://t.me/EthioNegarii �Twitter https://twitter.com/EthioNegari � YouTube https://youtube.com/channel/UCxywavkb3e3K7BY3BEh2piQ Facebook  https://www.facebook.com/EthioNegarii/ Website https://ethionegari.com/ LinkedIn https://www.linkedin.com/company/ethio-negari #ethiopia #Jobs #brokers

  • በጻድቃኔ ማርያም ቤተክርስቲያን በተፈጠረ አደጋ የ14 ሰዎች ህይወት አለፈ በጻድቃኔ ደብረ ምጥማቅ ቅድስት ማርያም ገዳም ድንገት በተከሰተ ርዕደ መሬትና የመሬት መንሸራተት አደጋ የ14 ሰዎች ሕይወት ሲያልፍ በ5 ሰዎች ላይ ከፍተኛ ጉዳት መድረሱ ተገለጸ። በሰሜን ሸዋ ሀገረ ስብከት ደብረ ምጥማቅ ጻድቃኔ ቅድስት ማርያም ገዳም ከክረምቱ መግባት ጋር ተያይዞ በተከሰተው ከፍተኛ የዝናብና የመባርቅት ድምፅ በደረሰ ርዕደ መሬትና የመሬት መንሸራተት ለጸበል ፣ ለሱባኤና ለመሳለም ከአራቱም አቅጣጫ በተሰበሰቡ በጻድቃኔ ማርያም ልጆችና ወዳጆች ላይ ድንገተኛ አደጋ ደርሷል። በዚህ ድንገተኛ አደጋም የ14 ዜጎች ሕይወት ሲያልፍ በ5 ሰዎች ላይ ከፍተኛና እንዲሁም በ2 ዜጎች ላይ ደግሞ መለስተኛ ጉዳት መድረሱም ተመላክቷል። የሀገረ ስብከቱ ብፁዕ ሊቀ ጳጳስ አቡነ ቀሌምንጦስ በስፍራው ለመገኘት ወደ ገዳሙ ማምራታቸው ተገልጻል። ለበለጠ እና ትኩስ መረጃዎች ከስር ያሉትን ሊንኮች በመጫን ቤተሰብ ይሁኑ። �Telegram https://t.me/EthioNegarii �Twitter https://twitter.com/EthioNegari � YouTube https://youtube.com/channel/UCxywavkb3e3K7BY3BEh2piQ Facebook  https://www.facebook.com/EthioNegarii/ Website https://ethionegari.com/ LinkedIn https://www.linkedin.com/company/ethio-negari #ethiopia #Tsadkanemariam #landslide

  • አዲስ አበባ ዩንቨርስቲ ከ500 በላይ ሰራተኞቹን ማሰናበቱ ተገለጸ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ሙሉ የራስ-ገዝነት መብቱን ለመተግበር ባደረገው የመዋቅር ማስተካከያ ምክንያት ከ500 በላይ አስተዳደራዊ ሰራተኞች እና 50 መምህራን ያለ ምደባ ቀርተዋል። ይሁን እንጂ የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ዶ/ር ሳሙኤል ክፍሌ ማንም ሰራተኛ እንዳልተባረረ ገልጸው፣ የተጎዱት በጡረታ፣ በካሳ ወይም በቅርቡ በሚጀመሩ የንግድ እንቅስቃሴዎች እንደሚካተቱ አረጋግጠዋል። ​ምደባው ለአስተዳደር ሰራተኞች በፈተና፣ ለመምህራን ደግሞ በትምህርት ዝግጅት አግባብነት ላይ ተመስርቶ የተከናወነ ነው። ​በሀገሪቱ ከሚገኙ 46 የመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች መካከል የመጀመሪያው ሞዴል የሆነው የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የሪፎርም እርምጃ፣ ቀጣይ ተመሳሳይ እርምጃ ለመውሰድ ለሚዘጋጁት እንደ ጂማ፣ መቐለ፣ ባህር ዳር እና ጎንደር ዩኒቨርሲቲዎች ትልቅ ማሳያ እንደሚሆን ተገልጿል።። ለበለጠ እና ትኩስ መረጃዎች ከስር ያሉትን ሊንኮች በመጫን ቤተሰብ ይሁኑ። �Telegram https://t.me/EthioNegarii �Twitter https://twitter.com/EthioNegari � YouTube https://youtube.com/channel/UCxywavkb3e3K7BY3BEh2piQ Facebook  https://www.facebook.com/EthioNegarii/ Website https://ethionegari.com/ LinkedIn https://www.linkedin.com/company/ethio-negari #ethiopia #addisababa #Addisababauniversity

  • ለኢትዮጵያ ሚዲያዎች አዲስ ፈተና... የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን ለአርትስ ቲቪ እና አሀዱ ሬዲዮ የመጨረሻ የጽሁፍ ማስጠንቀቂያ መስጠቱን አስታውቋል። ባለሥልጣኑ በአዋጅ ቁጥር 1238/2013 በተሰጠው ሥልጣን መሠረት የሚዲያ ተቋማት ሕግና የሙያ ሥነ ምግባርን አክብረው መስራታቸውን እየተከታተለ ድጋፍና እርምት በማድረግ ላይ ይገኛል። በዚሁ መሠረትም አሐዱ ኤፍ ኤም 94.3 እና አርትስ ቴሌቪዥን የተሰጣቸውን የይዘት ግዴታዎች በመተላለፍ፣ ለተከታታይ ጊዜ ያልተረጋገጠ፣ ሚዛናዊ ያልሆነ እንዲሁም የሕዝብን ጥቅም የሚጎዳ መረጃ በማሰራጨታቸው የመጨረሻ የጽሑፍ ማስጠንቀቂያ በባለስልጣኑ ተሰጥቷቸዋል። ባለሥልጣን መስሪያ ቤቱ ከሬድዮ እና ከቴሌቪዥን ጣቢያዎቹ ኃላፊዎች ጋር በተስተዋሉ ተደጋጋሚ የህግና የሙያ ጥሰቶች ላይ ውይይቶች ያደረገ ቢሆንም ጉልህ ለውጥ ሳይታይ በመቅረቱ ማስጠንቀቂያ መስጠቱን ያስታውቃል፡፡ ስለሆነም ጣቢያዎቹ በቀጣይ ሥራቸውን በሕግና በሙያ ሥነ ምግባር መሠረት እንዲያከናውኑ ሲል ባለስልጣኑ አሳስቧል። ባለስልጣኑ ማስጠንቀቂያው በመገናኛ ብዙኃን አዋጅ ቁጥር 1238/2013 አንቀጽ 74/ሠ መሠረት የተሰጠ መሆኑን እየገለፀ ሚዲያዎቹ ተመሳሳይ የህግ መተላለፍ እና ጥሰት እየፈፀሙ የሚቀጥሉ ከሆነ በህጉ መሠረት ቀጣይ አስተዳደራዊ እርምጃ እንደሚወስድ ባለሥልጣኑ ያስታውቃል። ባለስልጣኑ የሚዲያ ተቋማት በሁሉም የዘገባ ስራዎቻቸው ላይ የመገናኛ ብዙኃን አዋጅ እና የሀገሪቱን ሕጎች እንዲሁም የዘርፉን የሙያ ሥነ ምግባር አክብሮ መስራት የሁሉም ግዴታ መሆኑን  ለአፍታም ሊዘነጉት እንደማይገባ ባለስልጣኑ አሳስቧል። ከአንድ ሳምንት በፊት ጄኤፍኤምን ለስድስት ወራት ከስርጭት ያገደ ሲሆን ከሁለት ወር በፊት ደግሞ የበይነ መረብ ሚዲያ የሆኑት ዋዜማ ራዲዮ እና አዲስ ስታንዳርድን ደግሞ ማገዱ ይታወሳል። ለበለጠ እና ትኩስ መረጃዎች ከስር ያሉትን ሊንኮች በመጫን ቤተሰብ ይሁኑ። �Telegram https://t.me/EthioNegarii �Twitter https://twitter.com/EthioNegari � YouTube https://youtube.com/channel/UCxywavkb3e3K7BY3BEh2piQ Facebook  https://www.facebook.com/EthioNegarii/ Website https://ethionegari.com/ LinkedIn https://www.linkedin.com/company/ethio-negari #ethiopia #Media #Artstv #Ahaduradio

  • ግብጽ የአባይን ውሃ በመጠቀማቸው ለኢትዮጵያ ካሳ እንድትከፍል ተጠየቀች ግብጾች ስለሚጠቀሙ ለኢትዮጵያ ሊከፍሉ እንደሚገባ  የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ዶክተር ኢ/ር ሀብታሙ ኢተፋ ተናግረዋል። የውኃና ኢነርጂ ሚኒስትር ዶክተር ኢንጂነር ሀብታሙ ኢተፋ ከፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ጋር ባደረጉት ልዩ ቆይታ፣ ግብፅ የአባይን ውኃ በነፃ እየተጠቀመች አገሯን እያለማች በመሆኗ ለኢትዮጵያ ተገቢውን ክፍያ ልትፈጽም እንደሚገባ ገለጹ። ሚኒስትሩ በቆይታቸው እንደጠቆሙት፤ ኢትዮጵያ የጎርፍ አደጋ በታችኞቹ የተፋሰሱ አገራት—በተለይም በግብፅ ላይ እንዳይደርስ ከፍተኛ የክትትልና የእንክብካቤ ሥራ እያከናወነች ትገኛለች። ሆኖም አገራቱ የኢትዮጵያን የተፈጥሮ ሀብት ያለምንም ክፍያ በመጠቀም አገራቸውን እያለሙ በመሆናቸው፣ ለሚጠቀሙበት ውኃ ለኢትዮጵያ ክፍያ ሊፈጽሙ እንደሚገባ አስገንዝበዋል። ግብጽ በተደጋጋሚ ለናይል ወንዝ 85 በመቶ አበርክቶ ያላት ኢትዮጵያን ፍትሀዊ የውሀ አጠቃቀም መርህን ጥሳለች በሚል ስሞታ ታሰማለች። የአሁኑ የኢትዮጵያ የውሀ ክፍያ ጥያቄ በታሪክ የመጀመሪያው ሲሆን ግብጽ በጉዳዩ ዙሪያ ምላሽ አልሰጠችም። ለበለጠ እና ትኩስ መረጃዎች ከስር ያሉትን ሊንኮች በመጫን ቤተሰብ ይሁኑ። �Telegram https://t.me/EthioNegarii �Twitter https://twitter.com/EthioNegari � YouTube https://youtube.com/channel/UCxywavkb3e3K7BY3BEh2piQ Facebook  https://www.facebook.com/EthioNegarii/ Website https://ethionegari.com/ LinkedIn https://www.linkedin.com/company/ethio-negari #ethiopia #egypt #nile

  • ኢትዮጵያዊያንን በህገወጥ መንገድ ወደ ደቡብ አፍሪካ ሲልክ የነበረው ተጠርጣሪ በኢንተርፖል አማካኝነት ተያዘ የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ከኢንተርፖልና ከማላዊ ፖሊስ ጋር በመተባበር አደገኛ ሕገ-ወጥ የሰዎች አዘዋዋሪ አድነው ባሻው ውዳሞን በቁጥጥር ሥር ማዋሉን ገልጿል። የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ከኢንተርፖል እና ከማላዊ ፖሊስ ጋር በመተባበር በበርካታ የሀገራችን ወጣቶች ላይ ከባድ ኢሰብአዊ ድርጊት ሲፈጽም የቆየውን አደገኛ ሕገ-ወጥ የሰዎች አዘዋዋሪ አድነው ባሻው ውዳሞን በማላዊ ሀገር በቁጥጥር ሥር እንዲውል በማድረግ ለኢትዮጵያ ተላልፎ መሰጠቱን አስታውቋል። አድነው ባሻው ውዳሞ በቁጥጥር ሥር ሊውል የቻለው ከግብረ አበሮቹ ጋር በመሆን ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በተለይም ከሀድያ እና ከንባታ ዞኖች በርካታ ወጣቶችን ሕይወት እንደሚያሻሽል በመሐላና በአጉል ተስፋ በማታለል በሕገ-ወጥ መንገድ ወደ ደቡብ አፍሪካ ሲያዘዋውር መቆየቱን ፖሊስ በሰውና በሰነድ ማስረጃ አረጋግጫለሁ ብሏል። ተጠርጣሪው ከእያንዳንዱ ተጓዥ ከ600 ሺህ እስከ 800 ሺህ ብር ይጠይቃል የተባለ ሲሆን፤ በቅድመ ክፍያ ኢትዮጵያ ውስጥ 100 ሺህ ብር እና ከዚያ በላይ ሲቀበል መቆየቱንም የምርመራ መዝገቡ አመላክቷል። ተጓዦችን በሞያሌ በኩል ወደ ኬንያ በማሻገርም በጋንቦ ጫካ ውስጥ በድብቅ በማስቀመጥ በየ 24 ሰዓት ትንሽ ሩዝ ከቁራጭ ዳቦ ጋር ብቻ በመስጠት፣ በከፍተኛ ረሃብና የውሃ ጥም እንዲሰቃዩ ከማድረጉም በላይ በሞተርና በእግር ሴሎ በረሃን ጭምር እንዲያቋርጡ አስገድዷቸዋል ሲል ፖሊስ ገልጿል። ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ተጎዦችን በሕገ-ወጥ መንገድ ናይሮቢ ከተማ ካደረሳቸውም በኋላ በአንድ ክፍል ውስጥ በማጎር፣ ተጨማሪ ገንዘብ ከቤተሰቦቻቸው እንዲያስልኩ በማስገደድ ከፍተኛ ግፍ መፈጸሙን ፖሊስ በሰውና በሰነድ ማረጃ ደርሼበታለሁ ብሏል። ከቤተሰብ ገንዘብ ማስላክ ያልቻሉትን ተጓዦችን በመደብደብና "እዚሁ ትሞታላችሁ" እያለ በማስፈራራት እንዲሁም በኤሌክትሪክ ንዝረት በማሰቃየት ጭካኔ የተሞላበት ድርጊት በመፈጸም ተጨማሪ አንድ መቶ ሺህ ብር እና ከዚያ በላይ በኢትዮጵያ ውስጥ ከሚገኙ ግብረ አበሮቹ በኩል በባንክ እንዲከፈለው ማድረጉን ፖሊስ ገልጿል። ከዚህም ባለፈ ተጓዦቹን ከናይሮቢ ወደ ሞምባሳ፣ ከዚያም ወደ ታንዛኒያ በዕቃ መጫኛ ኮንቴነሮች፣ በተሳቢና ከኋላ ክፍት በሆኑና በሸራ በተሸፈኑ መኪኖች ውስጥ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸውን ተጓዦች በመጫን ታንዛኒያ በሚገኝ ጫካ ውስጥ ጥሎ በመጥፋት ለአሰቃቂ አደጋ ዳርጓቸዋል ሲል ፖሊስ ገልጿል። አብዛኞቹ ወጣቶች ደቡብ አፍሪካ ሳይደርሱ በተለያዩ ሀገራት በፖሊስ ቁጥጥር ሥር ውለው በሕገ-ወጥ መንገድ ወደ ሀገር በመግባታቸው እስከ ሦስት ዓመት በሚደርስ እስራት እንዲቀጡና እስራቱን ሲጨርሱም እስከ 170 ሺህ ብር ከፍለው ወደ ኢትዮጵያ መመለሳቸውን የፖሊስ ምርመራ መዝገብ ያመላክታል። የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ  ከኢንተርፖል ጋር በመተባበር ከ2015 ዓ.ም ጀምሮ ባደረገው ከፍተኛ ክትትል በበርካታ የሀገራችን ወጣቶች ላይ ኢሰብዓዊ ድርጊት ሲፈጽምና የኢኮኖሚ ጉዳት ሲያደርስ የቆየውን አድነው ባሻው ውዳሞን የማላዊ ፖሊስ በቁጥጥር ሥር አውሎ ሐምሌ 22 ቀን 2018 ዓ.ም ለኢትዮጵያ አሳልፎ መስጠቱን አስታውቋል። ለበለጠ እና ትኩስ መረጃዎች ከስር ያሉትን ሊንኮች በመጫን ቤተሰብ ይሁኑ። �Telegram https://t.me/EthioNegarii �Twitter https://twitter.com/EthioNegari � YouTube https://youtube.com/channel/UCxywavkb3e3K7BY3BEh2piQ Facebook  https://www.facebook.com/EthioNegarii/ Website https://ethionegari.com/ LinkedIn https://www.linkedin.com/company/ethio-negari #federalpolice #crime  #ethiopia

  • የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከ9 ቢሊዮን በላይ ዶላር ገቢ ማግኘቱን ገለጸ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ በ2025/2026 በጀት ዓመት የዓለም አቀፍ ፈተናዎችንና የነዳጅ ዋጋ ጭማሪን በመቋቋም 9.1 ቢሊዮን ዶላር ገቢ ማግኘቱን ገልጿል። አየር መንገዱ በዓመቱ 20.7 ሚሊዮን ደንበኞችን በማጓጓዝ የ10 በመቶ እድገት ያሳየ ሲሆን፣ የጭነት አቪየሽን አገልግሎቱም ከቀደመው ዓመት ጋር ሲነጻጸር የ16 በመቶ ጭማሪ አሳይቷል። ​የአየር መንገዱ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ መስፍን ጣሰው በሰጡት መግለጫ፣ በበጀት ዓመቱ አራት አዳዲስ ዓለም አቀፍ መዳረሻዎችን በመጨመር አጠቃላይ የመዳረሻዎችን ቁጥር 150 ማድረሱን ገልጸዋል። በተጨማሪም የሀገር ውስጥ መዳረሻዎችን ከ22 ወደ 25 ከፍ በማድረግ የአየር መንገዱን ተደራሽነት ማስፋፋት ተችሏልም ብለዋል። ለበለጠ እና ትኩስ መረጃዎች ከስር ያሉትን ሊንኮች በመጫን ቤተሰብ ይሁኑ። �Telegram https://t.me/EthioNegarii �Twitter https://twitter.com/EthioNegari � YouTube https://youtube.com/channel/UCxywavkb3e3K7BY3BEh2piQ Facebook  https://www.facebook.com/EthioNegarii/ Website https://ethionegari.com/ LinkedIn https://www.linkedin.com/company/ethio-negari #Ethiopianairlines #Aviation #ethiopia

  • ደቡብ ኮሪያ የልጆች ውልደት መጠንን ለመመር በአንድ ልጅ 6 ሚሊዮን ብር ጉርሻ እንደምትሰጥ ገለጸች። ደቡብ ኮሪያ የወሊድ ምጣኔን ለማሳደግ ሰዎች ወደ ጋብቻ እንዲገቡ እና እንዲወልዱ ለማበረታታት 38 ሺህ ዶላር ወይም 6 ሚሊዮን ብር ለማበረታቻ እየሰጠች መሆኑ ተሰምቷል። 51 ሚሊዮን ህዝብ ብዛት ያላት ደቡብ ኮሪያ ዓመታው የውልደት መጠኑ ከአንድ በመቶ በታች ነው። በዚህ ስሌት መሰረት በሀገሪቱ በየ ዓመቱ የሚወለዱ ህጻናት ቁጥር ከ260 ሺህ በታች ነው። ይህን ተከትሎም ሀገሪቱ የውልደት መጠንን ለመጨመር የተለያዩ ማበረታቻዎችን በመስጠት ላይ ትገኛለች። ለበለጠ እና ትኩስ መረጃዎች ከስር ያሉትን ሊንኮች በመጫን ቤተሰብ ይሁኑ። �Telegram https://t.me/EthioNegarii �Twitter https://twitter.com/EthioNegari � YouTube https://youtube.com/channel/UCxywavkb3e3K7BY3BEh2piQ Facebook  https://www.facebook.com/EthioNegarii/ Website https://ethionegari.com/ LinkedIn https://www.linkedin.com/company/ethio-negari #Southkorea #childbirth

  • በስዊድን ጎቲያ ካፕ የተሳተፉ 20 ያህል ኢትዮጵያውያን ተሰወሩ በስዊድን ጎተንበርግ በተካሄደው የጎቲያ ካፕ የእግር ኳስ ውድድር ላይ የተሳተፉ 20 ገደማ ኢትዮጵያውያን ያረፉበትን ቦታ ጥለው መሰወራቸው ተገለጸ እንደ ፖሊስ መረጃ ከሆነ ከተሰወሩት መካከል እድሜያቸው ከ14 እስከ 17 ዓመት የሆኑ ታዳጊዎች እና የቡድኑ መሪዎች ይገኙበታል። የቡድኑ አባላት ያረፉበት ትምህርት ቤት አስተዳዳሪ ቡድኑ ሳይሰናበት ለቆ መውጣቱን በመግለጽ ለፖሊስ ጥቆማ መስጠቱ ተነግሯል። የስዊድን ፖሊስ እንደገለጸው፤ "ግለሰቦቹ ወደ ኢትዮጵያ እንዳልተመለሱና መሰወራቸው በራሳቸው ፈቃድ እንደሆነ ይታመናል፤ ምንም ዓይነት የህገ-ወጥ የሰዎች ዝውውር ወንጀል አመላካች የለም" ብሏል። ታዳጊዎችን የሚያሳትፈው ይህ ውድድር ከሀምሌ 5 እስከ 12 በስዊድኗ ጎተንበርግ ተካሂዷል። ለበለጠ እና ትኩስ መረጃዎች ከስር ያሉትን ሊንኮች በመጫን ቤተሰብ ይሁኑ። �Telegram https://t.me/EthioNegarii �Twitter https://twitter.com/EthioNegari � YouTube https://youtube.com/channel/UCxywavkb3e3K7BY3BEh2piQ Facebook  https://www.facebook.com/EthioNegarii/ Website https://ethionegari.com/ LinkedIn https://www.linkedin.com/company/ethio-negari #ethiopia #sport #Ethiopianatgothiacup #ethiopianingothenburg

  • የሮቦቲክ ሰርጀሪ ህክምና መስጠት የሚያስችል ማሰልጠኛ በአዲስ አበባ ተከፈተ ማሰልጠኛ ማዕከሉ የተከፈተው በቻይና እና አፍሪካ የህክምና አጋርነት አማካኝነት ሲሆን ዘመናዊ የሮቦቲክስ ሰርጀሪ ህክምናን በኢትዮጵያ እና ወደ ሌሎች የአፍሪካ ሀገራት ለማስፋፋት ያለመ እንደሆነ ተገልጿል። ​በቻይና እና አፍሪካ ትብብር ለአህጉሪቱ የጤና ዘርፍ ማዘመኛ የሚሆን አዲስ የህክምና አጋርነት ፕሮግራም በአዲስ አበባ ሲልከ ሮድ ጄነራል ሆስፒታል ተመርቋል። ሲልክሮድ ሆስፒታል በቻይናዊያን ከአምስት ዓመት በፊት የተቋቋመ ዘመናዊ ሆስፒታል ነው። ​በዕለቱ የሮቦቲክስ ሰርጀሪ እና የኢንዶስኮፒክ ቴክኖሎጂ ማሰልጠኛ ማዕከላት የተከፈቱ ሲሆን፣ ኘሮግራሙ አነስተኛ ቀዶ ጥገና ቴክኖሎጂን በስፋት ለማስፋፋት ያለመ ነው። ​በስነ-ስርዓቱ ላይ የተገኙት የኢትዮጵያ ፕሬዝዳንት ታዬ አፅቀስላሴ የዘመናዊ ቴክኖሎጂና የሰለጠነ የሰው ኃይል አስፈላጊነትን ገልጸው፣ የቻይና ባለሙያዎች የሚያደርጉትን የዕውቀትና ክህሎት ሽግግርን አድንቀዋል። ​የጤና ሚኒስትሯ ዶ/ር መቅደስ ዳባ እና በኢትዮጵያ የቻይና አምባሳደር ቼን ሃይ በበኩላቸው፣ ፕሮግራሙ በሁለቱ ወገኖች መካከል ያለውን ጠንካራ ወዳጅነት የሚያሳይና ለሌሎች አገልግሎቶች አርአያ የሚሆን መሆኑን ገልጸዋል። ​በመጀመሪያው ዙር ስልጠና ከኢትዮጵያ፣ ሱዳን፣ ታንዛኒያ፣ ኡጋንዳ፣ ጋና እና ሊቢያ የተጣጣሙ 40 ሰልጣኞች ተሳትፈዋል። ኢትዮጵያ ኤአይን ለመጠቀም የተለያዩ ስትራቴጂዎችን የቀረጸች ሲሆን የጤና ጉዳዮች ደግሞ ዋነኛው ነው። ከዚህ በፊት በኤአይ የታገዙ የቲቢ በሽታ ምርመራ እና ህክምና ፣ ድንገተኛ ወረርሽኞችን ለመቆጣጠር እንዲሁም በተመረጡ ሆስፒታሎች በኤአይ የታገዙ የህክምና ማሽኖችን መግጠሟን አስታውቃለች። ከዚህ በተጨማሪም የኤአይ ዩንቨርስቲ ለማቋቋም የሚንስትሮች ምክር ቤት ውሳኔ ያሳለፈ ሲሆን ይህን ተከትሎም ዩንቨርስቲው የሚቋቋምበት ቦታ መረጣ፣ ግንባታ እና ሌሎች ተያያዥ ጉዳዮች በመጠናቀቅ ላይ መሆናቸውም ተገልጿል። ለበለጠ እና ትኩስ መረጃዎች ከስር ያሉትን ሊንኮች በመጫን ቤተሰብ ይሁኑ። �Telegram https://t.me/EthioNegarii �Twitter https://twitter.com/EthioNegari � YouTube https://youtube.com/channel/UCxywavkb3e3K7BY3BEh2piQ Facebook  https://www.facebook.com/EthioNegarii/ Website https://ethionegari.com/ LinkedIn https://www.linkedin.com/company/ethio-negari #ethiopia #AIsurgery #roboticsurgery

  • በምስራቅ አርሲ ወረዳዎች ከ450 በላይ ሰዎች መገደላቸው ተገለጸ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ጉባዔ (ኢሰመጉ) በኦሮሚያ ክልል፣ ምስራቅ አርሲ ዞን በተለያዩ ወረዳዎች ከ2014 ዓ.ም እስከ ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ በተፈጸሙ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች ላይ ያካሄደውን የምርመራ ግኝት ይፋ ባደረገበት 158ኛ ልዩ መግለጫው፣ ቢያንስ ከ450 በላይ ንጹሃን ዜጎች መገደላቸውን አስታውቋል። ሀገር በቀሉ የሰብዓዊ መብቶች ተሟጋች ድርጅት 37 ገጾች ባሉት ሪፖርቱ መሠረት፣ በዞኑ በሚገኙ ዘጠኝ ወረዳዎች ውስጥ በታጣቂዎች ማንነትንና ኃይማኖትን መሰረት በማድረግ በተፈጸሙ ጥቃቶች የሰው ህይወት ከማለፉ ባሻገር፣ በርካታ ዜጎች ለአካላዊ ጉዳት፣ ለእገታ እና ለአስገድዶ መሰወር ተዳርገዋል። በተጨማሪም ከ14 ሺህ  በላይ ሰዎች ከቀያቸው የተፈናቀሉ ሲሆን፣ በርካታ አብያተ ክርስቲያናትና የግል ንብረቶች መዘረፋቸውንና መውደማቸውን አመልክቷል። ኢሰመጉ ባካሄደው የመስክ ምልከታና መረጃ የማሰባሰብ ስራ፣ በጥቃቶቹ ሳቢያ በየወረዳው የተመዘገበውን የሟቾች ቁጥር እንደሚከተለው አሰናድቶታል፡፡ በመርቲ ወረዳ፣ 117 ሰዎች፤ ሽርካ ወረዳ፣ 116 ሰዎች፤ ጀጁ ወረዳ፣ 101 ሰዎች ፤ ሮቤ ወረዳ፡ 47 ሰዎች ፤ ጉና ወረዳ፣ 26 ሰዎች ፤ ሆንቆሎ ዋቤ ወረዳ፣ 20 ሰዎች ፤ ሙኒሳ ወረዳ፣ 19 ሰዎች ፤ አሰኮ ወረዳ፡ 5 ንጹሃን ዜጎች እና 4 የህዝብ ሚሊሻዎች ፤ አርሲ ሲሬ ወረዳ፣ 3 ሰዎች በተጠቀሰው የጊዜ ሰሌዳ ውስጥ ሕይወታቸው አልፏል፡፡ ጉባኤው የሟቾችን ስም ዝርዝር ከነምስላቸው አስደግፎ በሪፖርቱ ላይ ጠቅሷል፡፡ ከግድያው ጎን ለጎን በሽርካ፣ ሮቤ፣ ጀጁ፣ መርቲ እና ሙኒሳ ወረዳዎች በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች በታጣቂዎች ታግተው የተወሰዱ ሲሆን፣ ቤተሰቦቻቸው ከፍተኛ የካሳ ገንዘብ ከፈለው ያስለቀቋቸው ቢኖሩም፤ የበርካቶች ያሉበት ሁኔታ እስካሁን ሳይታወቅ ቀርቷል። በጥቃቶቹ ወቅት በህጻናትና በአረጋውያን ላይ ከባድ የአካል ጉዳት መድረሱንም ሪፖርቱ ያስረዳል። የደህንነት ስጋቱ በዞኑ ከፍተኛ መሆኑን የጠቀሰው መግለጫው፣ በጀጁ (6,216)፣ በሽርካ (3,746)፣ በአሰኮ (2,133)፣ በሮቤ (1,270)፣ በመርቲ (1,036)፣ በሙኒሳ (29) እና በጉና (21) ወረዳዎች በጠቅላላው ከ14 ሺህ በላይ ዜጎች መፈናቀላቸውን አስረድቷል። በተጨማሪም ዕድሜ ጠገብ አብያተ ክርስቲያናት መቃጠላቸውን፣ መዘረፋቸውንና በስጋት ምክንያት መዘጋታቸውን ይፋ አድርጓል። ኢሰመጉ ድርጊቶቹ በህገ-መንግስቱና በዓለም አቀፍ ድንጋጌዎች የተረጋገጡ መሰረታዊ መብቶችን የጣሱና በሰብዓዊነት ላይ የተፈጸሙ ወንጀሎች ባህሪያትን የሚያሳይ ነው ብሏል። በመሆኑም የፌደራልና የክልል መንግስታት ለዜጎች ዘላቂ ጥበቃ እንዲያደርጉ፣ ጥሰት ፈጻሚዎችን ለፍርድ እንዲያቀርቡ፣ ለተጎጂዎች ካሳ እንዲከፈልና ተፈናቃዮች ወደ ቀያቸው እንዲመለሱ ጥሪ አቅርቧል። ተቋሙ አክሎም የኦሮሚያ ክልል ጸጥታ ሀይሎች ንጹሀንን ከጥቃት መጠበቅ ካልቻሉ የፌደራል የጸጥታ ሀይሎች ጣልቃ እንዲገቡም ጠይቋል። ለበለጠ እና ትኩስ መረጃዎች ከስር ያሉትን ሊንኮች በመጫን ቤተሰብ ይሁኑ። �Telegram https://t.me/EthioNegarii �Twitter https://twitter.com/EthioNegari � YouTube https://youtube.com/channel/UCxywavkb3e3K7BY3BEh2piQ Facebook  https://www.facebook.com/EthioNegarii/ Website https://ethionegari.com/ LinkedIn https://www.linkedin.com/company/ethio-negari #ethiopia #Oromia #Arsi #Humanrights

  • በአሜሪካ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን ስደተኞች እንዲባረሩ የሚፈቅደው ህግ ታገደ መነሻውን ትግራይ ክልል አድርጎ ወደ አማራ እና አፋር ክልሎች ተስፋፍቶ በነበረው የጦርነት ጊዜ በተለያዩ ምክንያቶች ወደ አሜሪካ አቅንተው የነበሩ 30 ሺህ ኢትዮጵያዊያን በሀገሪቱ እንዲኖሩ ልዩ ፈቃድ ተሰጥቷቸው ነበር። በፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት መፈረምን ተከትሎ እና ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ወደ ነጩ ቤተ መንግሥት መግባታቸውን ተከትሎ በጊዜያዊነት ተፈቅዶላቸው የነበሩ ኢትዮጵያዊያን ወደ ሀገራቸው እንዲመለሱ ተወስኖም ነበር። በሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት ወቅት በአሜሪካ የኢትዮጵያውያን ጊዜያዊ የመኖሪያ ፈቃድ (TPS) የሚሰጠው ይህ መመሪያ ከስድስት ወራት በፊት የፕሬዝዳንት ትራምፕ አስተዳድር ውሳኔ አሳልፎ የነበር ሲሆን ይህ መመሪያ በፍርድ ቤት ውሳኔ መታገዱ ተገልጿል። ​የአሜሪካው የፌደራል ዳኛ ብራየን መርፊ የትራምፕ አስተዳደር በስደት ላይ ባሉ ኢትዮጵያውያን ላይ የጣለውን የጊዜያዊ መኖሪያ ፈቃድ (TPS) የማቋረጥ ውሳኔ በጊዜያዊነት አግደዋል። ​ዳኛው ይህንን ውሳኔ ያሳለፉት የአሜሪካው ጠቅላይ ፍርድ ቤት ዝቅተኛ ፍርድ ቤቶች በኢሚግሬሽን ጉዳዮች ላይ ያላቸውን ስልጣን የሚገድብ ውሳኔ ባሳለፈበት ወቅት ነው። የመሀል ሀገር ደህንነት መስሪያ ቤት (DHS) ህግ አማካሪ ጄምስ ፐርሲቫል የዳኛውን ውሳኔ "በጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ላይ የተደረገ አመፅ" ሲሉ አጥብቀው ተችተዋል። ​ኢትዮጵያውያን በሀገራቸው በነበረው የጦርነትና ሰብአዊ ቀውስ ምክንያት በ2022 እ.ኤ.አ. ይህንን ጥበቃ ያገኙ ሲሆን፣ አዲሱ የትራምፕ አስተዳደር በታህሳስ ወር 2025 ጥበቃው እንዲያበቃ ወስኖ ነበር። ​ኢትዮጵያዊያኑ ሀገራቸው አሁንም ጦርነት ላይ መሆኗን ከአሜሪካ ወደ ሀገራቸው መመለስ የሚያስችል ምቹ ሁኔታ የለም በሚል ሲከራከሩ ቆይተዋል። ለበለጠ እና ትኩስ መረጃዎች ከስር ያሉትን ሊንኮች በመጫን ቤተሰብ ይሁኑ። �Telegram https://t.me/EthioNegarii �Twitter https://twitter.com/EthioNegari � YouTube https://youtube.com/channel/UCxywavkb3e3K7BY3BEh2piQ Facebook  https://www.facebook.com/EthioNegarii/ Website https://ethionegari.com/ LinkedIn https://www.linkedin.com/company/ethio-negari #ethiopia #US #Immigrants

Ethio Negari ኢትዮ ነጋሪ — tgindex