Healthify Ethiopia
СтатистикаWelcome to Healthify Ethiopia! At Healthify Ethiopia, we believe that access to quality health information is the foundation of a healthier society. It aims to empower all Ethiopians with reliable, evidence-based health knowledge, delivered a click away.
- Последний пост
- 25 мая
- Последнее чтение
- 13 авг.
- Постов за неделю
- 0
- Всего постов
- 20
- Тип
- открытый
- Язык
- английский
- В каталоге с
- 13 авг.
- 1/24сутки в ленте
- —
- 1/48двое суток
- —
- 1/72трое суток
- —
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
Healthify yourself by staying active!
የአሜሪካ የምግብ መመሪያ (Dietary Guidelines for Americans) 2025-2030 አዲሱ የአሜሪካ የምግብ መመሪያ ጃኑዋሪ 7 እለት ይፋ ተደርጓል። ለጤናችን የሚበጀውን እውነተኛ ምግብ እንመገብ በሚል አርስት የወጣው መመሪያ ጤንነት የሚጀምረው ከማእድ ነው ሲል አጽንኦት ሰጥቷል። በበሽታ ተከላካይ፣ ገንቢ እና ሌሎችም ለጤና ተስማሚ ንጥረ ምግቦች የበለጸገ ተፈጥሮአዊ ምግብን አበክሮ መክሯል። አትክልት እና ፍራፍሬ በበቂ እና አዘውትረን እንድንመገብ ሲያበረረታታ ለጤና ጎጂ የሆኑ (በተለይም መጥፎ ኮሌስትሮል የሚጨምሩ ስቦችን እና አልኮልን) ከአመጋገባችን እንድንገድብ አሳስቧል። ስኳር የተጨመረባቸው ምግቦችን እና መጠጦችን እንዲሁም አርቲፊሻል ማጣፈጫ (Artificial sweetener) ከነአካቴው ገዝቷል። ሙሉ መመሪያው በPDF ተያይዟል። በሚቀጥሉት ፖስቶች ስለዚህ የምግብ መመሪያ ተከታታይ ማብራሪያዎችን እና ከኢትዮጵያ የምግብ መመሪያ ጋር በንጽጽር የምናይ ይሆናል። @HealthifyEthiopia
без подписи
በእርግዝና ወቅት የሚከሰት የስኳር ህመም የህክምና ግቦች ምንድን ናቸው? ለጤናማ እርግዝና ስለስኳር ህክምናው ግቦች ጠንቅቆ ማወቅና መረዳት ይፈልጋል። ውጤታማ ህክምና የስኳር ቁጥጥር እቅድ ማውጣት እና ግልጽ የሕክምና ግቦችን በማዘጋጀት ይጀምራል።ይህም የደም ስኳር መጠንን ጤናማ በሆነ ክልል ውስጥ መቆጠጠርን ያካትታል። በአለም አቀፋዊ የሕክምና መመሪያዎች የሚደገፉት የስኳር ግቦች እንዲህ ናቸው፡- 1️⃣ የባዶ ሆድ የስኳር መጠን፡ ከ70 እስከ 95 mg/dL 2️⃣ ከምግብ ከአንድ ሰዓት በኋላ የስኳር መጠን፡ ከ140 mg/dL በታች 3️⃣ ከምግብ ከሁለት ሰአት በኋላ የስኳር መጠን፡ ከ120 mg/dL በታች እነዚህን ግቦች ማሳካት ለእናትም ሆነ ጽንስ ጤና ወሳኝ ነው። የጽንስ መፋፋትና ክብደት ከፍ ማለት ፣ ከምጥ ጋር የተያያዙ ችግሮች፣ የጽንስ መታፈን፣ ህጻኑ እንደተወለደ መተንፈስ መቸገር፣ ወዘተ ያሉ ተግዳሮቶችን ለመቀነስ ስኳርን እስከመጨረሻዋ ደቂቃ ድረስ ማስተካከል ይገባል። ስለ የእርግዝና ጊዜ ስኳር ጥያቄዎች አሉዎት? አስተያየትዎትን ይጻፉልን። https://youtube.com/shorts/5mPsVbR2PyU?si=lDaa0aEIpVer8V9c
የስኳር ቅድመ ምርመራ ለሁሉም እናት እንዴት ይሰራል? ለእርግዝና ጊዜ የስኳር ቅድመ ምርመራ ለመስራት በጣም የተለመደው የምርመራ ዘዴ የሚበጠበጥ 75 ግራም ግሉኮስ ፈሳሽ/ሽሮፕ በመጠጣት (Oral Glucose Tolerance Test, OGTT) የሚሰራው ነው። ይህ ምርመራ ሰውነትዎ ግሉኮስን እንዴት እንደሚቁቋም ይፈትሻል። መጀመሪያ በባዶ ሆድ (ለስምንት ሰአት ያክል ምንም ምግብ ሳይበላ) ያለውን የደም ግሉኮስ መጠን ለማወቅ ክንድ ላይ ካለው የደም ሥር የደም ናሙና ተወሰዶ ይመረመራል። ቀጥሎ የሚጠጣ 75 ግራም ግሉኮስ የያዘ ጣፋጭ ሽሮፕ/ፈሳሽ ይወሰዳል። ከዚያም ግሉኮሱን ከጠጡ በኋላ ከአንድ ሰአት እና በድጋሜ ከሁለት ሰአት በኋላ ክንድ ላይ ካለው የደም ናሙና ተወስዶ የደም የስኳር መጠን ይለካል። በብዛት ጥቅም ላይ የሚውሉት የምርመራ መመዘኛዎች ከሚከተሉት የስኳር ምርመራዎች ውስጥ አንዱ ከተሟላ ስኳር አለ ለማለት ያስችላል። 1️⃣ የባዶ ሆድ የደም ስኳር መጠን፡ ≥92 mg/dL 2️⃣ ግሉኮስ ከተጠጣ ከ1-ሰዓት በኋላ ያለው የደም ስኳር መጠን፡ ≥ 180 mg/dL 3️⃣ ግሉኮስ ከተጠጣ ከ2-ሰዓት በኋላ ያለው የደም ስኳር መጠን፡ ≥ 153 mg/dL ዛሬዉኑ የጂዲኤም ምርመራ ለማሰራት ከሐኪምዎ ጋር ይነጋገሩ። ስለ ጂዲኤም ጥያቄዎች አሉዎት? አስተያየትዎትን ይጻፉልን። https://youtu.be/yKMpgwgxZQg?si=3-FD4UYI8hIRtaib
የእነዚህ በርካታ የቡና ጥቅሞች ተካፋይ ለመሆን ምን ላድርግ? ✍️ ቡና በመጠኑ መጠጣት አስፈላጊ ነው። የቡና ጤና ትሩፋቶችን ለማግኘት ከልክ ያለፈ ቡና መጋት አይፈልግም። በቀን ከሶስት ስኒ ያልበለጠ በቂ ነው። ✍️ ጸረ ተባይ የበዛበት ከሚሆን ይልቅ ኦርጋኒክ የተፈጥሮ ቡናን ይምረጡ። ✍️ በጣም አምሽተው ቡና ከመጠጣት ይልቅ በመክሰስ ሰአት በፊት ቢሆን እንቅልፍ እንዳይረብሽ ይረዳል። ✍️ ቡናን ማብዛት የልብ ምት ሊያዛባ ይችላል። የእንቅልፍ መዛባትና ተያያዥ ጭንቀት ሊያስከትል ይችላል። ✍️ በተጨማሪም የቡና ጥቅሞችን ለማጣጣም ቡና ሲጠጡ ማጣፈጫ (ስኳር፣ ክሬም፣ ጨው ወይም ሌላ ጤናን ሊጎዳ የሚችል) አይጨምሩ። 👉 ያስታውሱ ቡና ለጤናማ አኗኗር አንዱ አካል ያድረጉት። ሙሉ ጤናን ለመጠበቅ እና ደስተኛ ህይወት ለመምራት የተስተካከለ አመጋገብ፣ መደበኛ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ፣ በቂ እንቅልፍ መተኛት፣ ጭንቀት አለማብዛት እና ከሱስ የጸዳ አኗኗር ዘይቤ ወሳኝ ነው። #CoffeeLovers #HealthBenefitsOfCoffee #CoffeeAndWellness #DrinkCoffeeLiveLonger #HealthyLifestyle #CoffeeScience #BrainHealth #HeartHealth #CoffeeForLongevity YouTube: https://www.youtube.com/@healthifyethiopia @HealthifyEthiopia
ቡና ለጤና ያለ ቡና መዋል ለብዙዎች የማይቻል ነው። ቀኔ የሚጀምረው የጧት ቡናየን ስቀምስ ነው የሚሉ ጥቂቶች አይደሉም። መልካም ዜና! ቡና በመጠኑ ሲጠጣ ከማነቃቃት ባሻገር በርካታ የጤና ጥቅሞች ይሰጣል። በመልካም መኣዛና ጥኡም ጣእም ከመደሰት በላይ ቡና ጤናን ይጠብቃል። 1️⃣ ቡና እድሜን ያረዝማል (Longevity) እንደ ጆን ሆፕኪንስ ተቋም መረጃ መሰረት ቡናን የሚያጣጥሙ ሰዎች በልብ ህመም፣ ስትሮክ፣ ስኳር ህመም፣ ኩላሊት ህመም ወዘተ ያሉ ገዳይ በሽታዎችን ስለሚቀንስ ጤናማ ረጅም እድሜ ለመኖር ይረዳል። ስለሆነም ቡና ከመጠጥነት በላይ የሆነ እድሜ የሚያረዝም የህይወት መድህን ነው ማለት ይቻላል። 2️⃣ የዘረመል (ዲ ኤን ኤ) ጤናን ይጠብቃል ቡና ተፈጥሯዊ የዲኤን ኤ ጠባሳ እና ብልሽት ሊቀንስ ይችላል የሚሉ ጥናቶች አሉ። 3️⃣ ለጉበት ጤና ይረዳል ቡና ጉበት ላይ የአደጋ እንዳይደርስ ይከላከላል። 4️⃣ የካንሰር ተጋላጭነትን ይቀንሳል በተለይም የአንጀት ካንሰር የመያዝ እድልን ይቀንሳል። 5️⃣ የደም ስኳር መጠን እንዳይጨምር ይረዳል ጥናቶች እንደሚያሳዩት ቡና በትንሹም ቢሆን የደም ስኳር መጠን እንዳያሻቅብ ይረዳል። ቡና የሚጠጡ ሰዎች የተሻለ የግሉኮስ ሜታቦሊዝም ስላላቸው በስኳር የመያዝ እድልን ይቀንሳል። 6️⃣ ለልብ ጤና ይጠቅማል በቀን ከአንድ አስከ ሶስት ስኒ ቡና መጠጣት ለልብ ጤንነት ይጠቅማል የሚሉ ማስረጃዎች አሉ። በልብ ድካም የመያዝ እድልን ይቀንሳል። 7️⃣ የአእምሮ/አንጎል ጤናን ይጠብቃል (Neuroprotective Effects) በቀን ከአንድ አስከ ሶስት ስኒ ቡና መጠጣት የመርሳት በሽታ (አልዛይመር) ስጋትን ይቀንሳል። በተጨማሪም ከእድሜ ጋር የሚመጣ የእጅ መንቀጥቀጥ (Parkinson's disease) ለመቀነስ ይረዳል። ሰውነት ፓራላይዝ የሚያደርገው የአንጎል መታዎክ (Stroke) በእጅጉ ይቀንሳል። #CoffeeLovers #HealthBenefitsOfCoffee #CoffeeAndWellness #DrinkCoffeeLiveLonger #HealthyLifestyle #CoffeeScience #BrainHealth #HeartHealth #CoffeeForLongevity YouTube: https://www.youtube.com/@healthifyethiopia @HealthifyEthiopia
የስኳር ህመም ሳይታወቅ የሚዘገየው ለምንድን ነው? በአለማችን የስኳር ህመም ተጠቂዎች ከግማሽ ቢሊዮን በላይ አሻቅቧል። በየአምስት ሴኮንዱ አንድ ሰው በስኳር ህመም ምክንያት ይሞታል። በየሰላሳ ሴኮንዱ አንድ ሰው በስኳር ምክንያት እግሩ ይቆረጣል። አጠቃላይ በምድራችን ላይ ለጤና ከሚመደበው በጀት ከ10 በመቶ በላይ ለስኳር ህክምና ብቻ ይውላል። የበለጠ የሚያሳስበው ደግሞ በቀጣይ አመታት ስርጭቱ ከፍተኛ ጭማሪ ያሳያል ተብሎ ይገመታል። ምንም የመቀነስ አዝማሚያ ጭራሽ እያሳየ አይደለም። ሌላው ገራሚ ነገር ደግሞ ስኳር ካለባቸው ግለሰቦች ግማሹ ስኳር እንዳለባቸው አያውቁም። ኢትዮጵያን ጨምሮ ሌሎች በማደግ ላይ ያሉ አገሮች ላይ ይህ ስኳር እንዳለባቸው የማያውቁት ሰዎች ቁጥር ወደ 70 በመቶ ይጠጋል። ለመሆኑ የስኳር ህመም ሳይታወቅ የሚዘገየው ለምንድን ነው? የስኳር ህመም በተለይም ዓይነት 2 ለብዙ ዓመታት ሳይታወቅ ሊቆይ የሚችል በሽታ ነው። ይህም የሆነበት ምክንያት በአመዛኙ ምልክት አልባ ስለሆነ ነው። ዝምተኛው ገዳይ (silent killer) የሚባለው ለዚያ ነው። አንደሌሎች ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎች ሁሉ ግልጽ መገለጫ ምልክቶች የሉትም። አብዛኛዎቹ ስኳር ያለባቸው ሰዎች ምንም አይነት የህመም ስሜት ሳይሰማቸው ለብዙ አመታት ሊቆዩ ይችላሉ። ነገር ግን ስኳሩ ሰውነታቸዉን እየጎዳው እንደሆነ ማስተዋል ይገባል። ስለዚህ ስኳር ህመምን ገና ሳይብስ ለማዎቅ ዋነኛው መፍትሄ በየጊዜው የስኳር ምርመራ በማድረግ ነው። ለዚህ ነው መደበኛ ምርመራ በጣም አስፈላጊ የሚሆነው። በተለይም ተጋላጭነት ያለባቸው ሰዎች ቢያንስ በአመት አንዴ ስኳራቸውን መታዬት ያስፈልጋቸዋል። በተለይ የስኳር መጠኑ በጣም ከፍ ሲል የሚታዩ ምልክቶች ለመጠቀስ ያህል የማያቋርጥና የማይረካ የዉሃ ጥም፣ ቶሎቶሎና አብዝቶ መሽናትና ሃይለኛ የድካም ስሜት ይገኙበታል። ብዙውን ጊዜ የሚታዩት ምልክቶች ተጓዳኝ የጤና እክሎች አመላካች ሊሆኑ ይችላሉ። እነዚህም የእይታ መደብዘዝ፣ የቁስል ቶሎ አለመዳንና ማመርቀዝ፣ የእግር መደንዘዝና መቆጥቆጥ፣ ስንፈተ ወሲብ ወዘተ ሊሆኑ ይችላሉ። ያስታውሱ፤ የስኳር ህመም ምንም አይነት የህመም ምልክት ላያሳይ ይችላል። ስለሆነም መደበኛ የስኳር ምርመራ በማድረግ ጤንነትዎን ይጠብቁ። Telegram: https://t.me/HealthifyEthiopia YouTube: https://www.youtube.com/@healthifyethiopia
አዘውትሮ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ካለማድረግ (sedentary time) የሚመጣውን የጤና መዘዝ ለመቀነስ ምን እናድርግ? 1️⃣ ለረጅም ሰዓት አለመቀመጥ በተለይም ከአንድ ሰዓት በላይ ካለእንቅስቃሴ አለማሳለፍ ዘመናዊ ህይወታችን በቴክኖሎጅ ቀላል እየሆነ ስለመጣ ብዙዎቻችንን ስንቅስቃሴ አልባ የአኗኗር ዘይቤ እንድንከተል ተገደናል። ካለእንቅስቃሴ ብዙ መቀመጥ ከበርካታ የጤና ችግሮች መንስኤ እንደሆነ ይታመናል። ለረጅም ሰአታት መቀመጥ ለበርካታ በሽታዎች የመጋለጥ እድልን በእጅጉ ይጨምራል። ስለዚህ ለረጅም ሰዓት አለመቀመጥ በተለይም ከአንድ ሰዓት በላይ ካለእንቅስቃሴ አለማሳለፍ ይመከራል። 2️⃣ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ መክሰስ (exercise snack) ማዘውተር የአካል ብቃት እንቅስቃሴ 'መክሰስ' ሲባል በተገኘው አጋጣሚ ሁሉ ለትንሽ ደቂቃም ቢሆን አጭር የሆነ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ መስራትን ነው። በተቻላችሁ ጊዜ በቤት ውስጥ ወይም በስራ ቦታ የመንቀሳቀስ እድሎችን መፍጠር እንደማለት ነው። በተለይም ስራ በዝቶብን ለስፖርት ጊዜ ስናጣ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ መክሰስ ‘መብላት' ባለንበት ቦታ ለትንሽ ደቂቃ ብናፍታታ አስገራሚ የጤና ጥቅሞችን ያስገኛል። ለምሳሌ ቢሮኣችን ጸሃፊያችንን ወረቀት አምጭልኝ ብለን ከማዘዝ እራሳችን ተንቀሳቅሰን ኮፒ ማድረግ፣ ደረጃ ወጣ ወረድ ማለት ሊሆን ይችላል። ወደ ምሳ ለመሄድ መኪና ከምንይዝ በእጋራችን የስፖርት ስናክ ማድረግ ማለት ነው። ስልክ ስናወራም እየተንቀሳቀስን ቢሆን ይረዳል። ከወዳጅ ጋር ስንቀጣጠር አንድ ቦታ ቁጭ ከማለት ወዳሉበት በእግር መሄድም ሊሆን ይችላል። አውቶቡስ ከተሳፈሩ ቀደም ብሎ ከፌርማታ ይውረዱ እና ቀሪውን መንገድ ይራመዱ። 3️⃣ በየቀኑ ከአስር ሺህ እርምጃ የማያንስ በእግር መጓዝ በቀን ከ10,000 እርምጃዎች በላይ መንቀሳቀስ ጤናማ ለመሆን ይረዳል። በስልካችን ወይም የእጅ ሰዓታችን የእንቅስቃሴ መከታተያ በመጫን በየቀኑ ምን ያህል እርምጃ እንደተጓዝን በማየት በየጊዜው ለማሻሻል መትጋት ጠቃሚ ነው። 4️⃣ በየቀኑ ከ30 ደቂቃ የማያንስ እስኪያልብ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማድረግ መደበኛ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማድረግ በተለይም መካከለኛና ከዚያ በላይ ኃይለኛ የኤሮቢክ እንቅስቃሴ እና ጡንቻን የሚያጠናክሩ ልምምዶችን መስራት ይመክራል። ✍️ የበለጠ በሰራን ቁጥር የላቀ የጤና ጥቅም እናገኛለን Telegram: https://t.me/HealthifyEthiopia YouTube: https://www.youtube.com/@healthifyethiopia
без подписи
без подписи
🎉 Celebrating 5 Years of Healthify Ethiopia on Telegram! 🎉 Dear Family, 5 years of healthifying Ethiopia! It’s been an incredible journey of sharing reliable health information, empowering our community, and growing together. Your support, engagement, and trust have made this platform what it is today! Thank you for being part of this mission, for every message, every share, and every moment you’ve spent spreading health awareness. Here’s to many more years of healthifying Ethiopia together! Stay informed, and stay healthy! 💙 #HealthifyEthiopia #5YearsStrong #ThankYou
የማህፀን መውጣት ችግር -------------------------------------------- የማህፀን መውጣት ችግር ማለት የውስጠኛው የማህፀን ክፍል ቦታውን በመልቀቅ ወደ ውጭ መውጣት ማለት ሲሆን፣ ይህ ችግር በአብዛኛው የውስጠኛውን የማህፀን ክፍል በቦታው የሚይዙት ጡንቻዎች በተለያዩ ምክንያቶች መደበኛ ስራቸውን መስራት ሳይችሉ ሲቀሩ የሚከሰት የህመም አይነት ነው፡፡ ዋና ዎና መንስሄዎች እርግዝናና ወሊድን ተከትሎ የሚከሰትና ከማረጥ ጋር ተያይዞ የሚከሰት ናቸው በተጨማሪም፡- ወደ ሆድ አካባቢ ግፊትን የሚጨምሩ ነገሮች ለምሳሌ፡- የረዥም ጊዜ ሳል፣ የሆድ ድርቀት እንዲሁም ከባድ ነገሮችን አዘወትሮ ማንሳት የመሳሰሉት ናቸው የማህጸን መውጣት ችግር ያለባቸው የሚያሳይዋቸው ምልክቶች አብዛኛው ታማሚዎች ምንም አይነት የህመም ስሜት ምልክት የላቸውም ምልክቱ መታየት ሲጀምር፡-ዋነኛው ምልክት የውስጠኛው ልጅ የሚይዘው ማህፀን ወደ ውጪ ሲወጣና ታማሚዋ በብልቷ በኩል የወጣ ስጋ መሰል ነገር ስታይ ነው :: በተጨማሪ የሚታዩ ምልክቶች ፡- የሽንት ምንም ሳይታወቅ መፍሰስ ወደ ዳሌ አጥንት አካባቢ ከባድነት ወይም ሙሉነት ስሜት መኖር ከማህፀን አካባቢ ያበጠ ነገር መኖር የወገብ ህመም የዳሌ አጥንት አካባቤ የግፊት ስሜት መኖር የማህጸን መውጣት ህክምና በመድሀኒት የሚደረግ ህክምና ፡- ማህጸን አንድ ጊዜ ከወጣ በራሱ የመመለስ እድል የለውም፡፡ በመድሀኒት የምናደርገው ህክምና የቀዶ ጥገና ህክምና ለማድረግ ምቹ ባልሆነበት ጊዜ ጊዚያዊ መፍትሄ ለመሰጠት ነው፡፡በቀዶ ጥገና የሚደረግ ህክምና ለማህፀን መውጣት ችግር መፍትሄ ነው የማህጸን መውጣት ችግር መከላከያ ዘዴዎች በእርግዝና ወቅት፡- የዳሌ አጥንት እንቅስቃሴ ማድረግ በወሊድ ወቅት፡- የማህጸን በር ሙሉ ለሙሉ እስከሚከፍት አለመግፈት ከወሊድ በኃላ ማህጸንን ወደ ታች ከሚገፋ ነገሮች እንደ ከባድ ነገሮችን ማንሳት፣ የሆድ ድርቀት እንዲሁም የዳሌ አጥንት እንቅስቃሴ ማድረግ ከማረጥ ጋር ተያይዞ ለሚመጣ የማህጸን መውጠት ችግር የሆርሞን መተካት ህክምና እንዲያገኙ ማድረግ የማህጸን መውጣት ችግር ባይታከም የሚያስከትላቸው ጉዳቶች የወጣው ማህጸን መቁሰል የማህጸን በር መላላጥ ፣የሽንት መታፍን/ ሽንት እንደልብ አለመውጣት፣የሽንት ቧንቧ ኢንፌክሽን እና የማህጸን መውጣት መባባስ ናቸው:: @HealthifyEthiopia https://www.youtube.com/@healthifyethiopia
🌟 ወሳኝ የጤና መረጃን እና ዜናዎች ለማግኘት የሚረዳ የቴሌግራም ቻናል 🌟 በዚህ ተለዋዋጭ አለም ውስጥ ሳይንሳዊ እና ወቅታዊ የጤና መረጃ ማግኘት ጤናን ለመጠበቅ አስፈላጊ ነው። Healthify Ethiopia በተለያዩ የጤና ጉዳዮች ላይ አዳዲስ መረጃዎችን የሚሰጥ ጠቃሚ የቴሌግራም ቻናል ነው። ✍️ የስኳር፣ ውፍረት፣ ኮሌስትሮል እና ሌሎችም የሆርሞን ጤና ✍️ የጥርስ እና አፍ ጤና አጠባበቅ ✍️ ጤናማ የአኗኗር ዘይቤ ዙሪያ ሰፊ መረጃ ✍️ በተለመዱ የቀዶ ጥገና ህክምናዎች እና ከኦፕሬሽን የማገገም ሂደት ✍️ የወንዶችና ሴቶች ስነ ተዋልዶ ጤና ✍️ አዳዲስ የጤና ዜና ✍️ በተለያዩ የጤና ጉዳዮች የጥያቄ እና መልስ መድረክ የጤና መረጃዎችን በቀላሉ እንዲቆረጠም አድረገው የሚያቀርቡ ትጉህ ባለሙያዎች የሚሰሩበት ቻናል ነው። የጤና ግንዛቤን ለማዳበር እና ጤና-ነክ መረጃዎች እንዲደርሳቸው ሌሎችን ብትጋብዙ ያተርፉበታል። Telegram: https://t.me/HealthifyEthiopia YouTube: https://www.youtube.com/@healthifyethiopia
የትራምፕ የጤና ፖሊሲ እርምጃዎች ምንድን ናቸው? የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ትራምፕ ስልጣን እንደተቆናጠጡ ከፈረሟቸው ፕሬዝዳንታዊ ትእዛዛት መካከል ጤናን የሚመለከቱ ስር ነቀል ፖሊሲዎች በዓለም አቀፍ ደረጃ መነጋገሪያ ሆነዋል። አሜሪካን ከአለም ጤና ድርጅት (WHO) ከማስወጣት እስከ ቁልፍ የጤና ኤጀንሲዎች እስከ መዝጋት ድረስ ሰፊ ክርክር አስነስተዋል። 1️⃣ ከዓለም ጤና ድርጅት (WHO) መውጣት፡ ፕሬዚዳንት ትራምፕ አሜሪካ ከዓለም ጤና ድርጅት ለመውጣት ሂደቱን የጀመሩት ድርጅቱ የዓለም ጤና ጉዳዮችን በተመለከተ ያለውን ቸልተኝነት በመንቀፍ ነው። ትራምፕ የዓለም ጤና ድርጅት የኮቪድ-19 ወረርሽኝን ለመግታት አፋጣኝ እና ግልጽ ስራ ባለመስራቱ ለቫይረሱ መስፋፋት አስተዋጽኦ አድርጓል ብሎ ያምናል። የቻይና ፖለቲካዊ ጣልጋ ገብነት አለበትም ሲሉ ከሰዋል። ይህ እርምጃ የአለም አቀፋዊ የበሽታ ልየታ፣ ክትትል እና ምላሽ አሰጣጥ ስርዓቶችን ያዳክማል በሚል ስጋት ፈጥሯል። 2️⃣ የአሜሪካ የጤና ተቋማትን ኮሚኒኬሽን መዝጋት፡ የአሜሪካ በሽታ መቆጣጠሪያና መከላከያ ማእከል እና የመድኃኒት ቁጥጥር ባለስልጣንን ጨምሮ ሁሉም የፌደራል ጤና ኤጀንሲዎች የውጭ ግንኙነቶችን እንዲያቆሙ ትእዛዝ ተላልፏል። ይህ ከዚህ በፊት ታይቶ የማያውቅ መመሪያ ሲሆን አዲስ የበሽታ ወረርሽኝ ሲነሳ ወቅታዊ መረጃዎችን ለተቀረው አለም መንግስታትና ህዝብ ለማሰራጨት መዘግየት ይፈጥራል የሚል ስጋትን ጭሯል። 3️⃣ የዲኢአይ (Diversity, Equity, and Inclusion, DEI) መታገድ ይህ ፕሮግራም በአሜሪካ ተቋማት ውስጥ አካታችነት፣ እኩልነት እና ፍትሃዊነትን ለማስፈን የወጣ ፕሮግራም ሲሆን ትራምፕ እንዲቆም ፈርሟል። ይህ እርምጃ በተቋማት ስራ ውስጥ ፍትሃዊ አካታችነት እና እኩልነት ለማስፈን የሚደረግውን ጥረት ወደኋላ ሊመልስ ይችላል ሲሉ ብዙዎች ተችተዋል። 4️⃣ የሮበርት ኬኔዲ የጤና ሚኒስቴር ሆኖ መሾም፡ ይህ ሰው በክትባት እና አንዳንድ የጤና አሰጣጥ ስርአቶች ላይ አወዛጋቢ አቋም እንዳለው ስለሚታዎቅ ስራዉን እንዴት ይመራው ይሆን የሚል የሰላ ክርክር አስነስቷል። ለታዳጊ ሃገራት ጤና ምን ተጽእኖ ያመጣል? እነዚህ እርምጃዎች የአሜሪካ መንግስት በጤና ፖሊሲ ላይ ከፍተኛ ለውጥ እያሳየ መሆኑን አመላካች ናቸው። ይህ ፖሊሲ በአሜሪካ ድጋፍ የሚሰሩ በርካታ የጤና ዘርፎችን፣ ህክምናዎችና እና ዓለም አቀፍ የጤና ትብብር ስራዎች ላይ ችግር ሊፈጥር ይችላል ሲሉ የጤና ባለሙያዎች እና ተሟጋቾች ስጋታቸውን አንጸባርቀዋል። ለብዙ ታዳጊ ሃገራት የጤና ወጪ ከፍተኛውን ድጋፍ የምታደርገው አሜሪካ ናት። ስለሆነም የዚህ ድጋፍ መቀነስ አስፈላጊ የጤና ፕሮግራሞች የገንዘብ እጥረት ያጋጥማቸዋል። ለምሳሌ 👉 የክትባት ዘመቻዎች፣ 👉 ኤችአይቪ/ኤድስ፣ 👉 ቲቢ እና 👉 ወባን መከላከል የመሳሰሉት ፕሮግራሞች በአሜሪካ ድጋፍ ላይ ጥገኛ ናቸው። የአሜሪካ ገንዘብ ድጎማ ከቀነሰ እነዚህ ወሳኝ የጤና አገልግሎቶች አደጋ ላይ ሊወድቁ ይችላሉ። እነዚህ ፖሊሲዎች በኢትዮጵያ ጤና አገልግሎት አሰጣጥ ላይ ምን አንድምታ ይኖራቸዋል ብለው ያስባሉ? ሃሳብዎትን ያጋሩን! ቴሌግራም @HealthifyEthiopia YouTube https://www.youtube.com/@HealthifyEthiopia
ፕሬዝዳንት ትራምፕ - ዩናይትድ ስቴትስን ከዓለም ጤና ድርጅት (WHO) የመውጣት ሂደት የሚያስጀምረውን የሥራ አስፈፃሚ ትዕዛዝ (Executive Order) ፈረሙ። አሜሪካ ለዓለም ጤና ድርጅት ከፍተኛ የገንዘብ ድጋፍ ከሚያደርጉ አገሮች ግንባር ቀደሟ እንደሆነች ይታወቃል። ከዚህ ቀደም ፕሬዝዳንቱ "ድርጅቱ ቻይናን ለኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ተጠያቂ ማድረግ ሳይችል ቀርቷል" ካሉ በሗላ አክለውም ቻይን ለመቅጣት የሚወስዷቸውን እርምጃዎች ይፋ ሲያደርጉ “ቻይና የዓለም ጤና ድርጅትን ሙሉ በመሉ ትቆጣጠረዋለች” ማለታቸው ይታወሳል። ቴሌግራም @HealthifyEthiopia YouTube https://www.youtube.com/@HealthifyEthiopia
የዓለም ጤና ድርጅት (WHO) ለህጻናት የስክሪን ጊዜ ገደብ መመሪያ ከልክ በላይ የስክሪን ጊዜ በልጆች አካላዊ እንቅስቃሴያቸው፣ በማህበራዊ ግንኙነታቸው እና ጤናማ የእንቅልፍ ስርዓታቸው ላይ አሉታዊ ተጽእኖ ያመጣል። የአእምሮ እደገትም ያዘገያል። የአይንና እይታቸው እድገት ላይም ተጽእኖ አለው። አሁን አሁን በርካታ ልጆች የእይታ መነጽር እምዲጠቀሙ ያስገደደው አንዱ ምክንያት ከልክ ያለፈ በልጅነት ኤሌክትሮኒክስ ስክሪን ላይ ማፍጠጥ እንደሆነ የሚጠቁሙ ጥናቶች እየተሰሙ ነው። ስለሆነም በተልቻለ መጠን ልጆች ስክሪን ላይ የሚያሳልፉትን ጊዜ መገደብ ይገባል። ለልጆችና ታዳጊዎች የስክሪን ጊዜ ገደብ መመሪያ ምን ያህል ነው? ከሁለት አመት በታች ያሉ ህጻናት ምንም አይነት ኤሌክትሮኒችስ ስክሪን ፈጽሞ ማየት የለባቸውም። ከሶስት እስከ አስራ ስምንት አመታ ያሉ ልጆች ደግሞ የስክሪን ጊዜያቸው ከሁለት ሰዓት መብለጥ የለበትም። የልጆቻችንን የስክሪን ጊዜ ለመቀነስ ምን እናድርግ? ህጻናት ለአጠቃላይ እድገታቸው መሳለጥ መጫወት፣ ማንበብ እና ከቤተሰብ ጋር ማህበራዊ መስተጋብር መፍጠር እንጅ ስልክ፣ ቴለቪዥን እንዲሁም ቪዲዮ ላይ እንዲያሳልፉ መፍቀድ የለብንም። የልጆችን ስክሪን ጊዜ ገደብ (screen time curfew) በማበጀት ልጆችን መቆጣጠር ያስፈልጋል። ነገር ግን ልጆችን በመከልከል መቆጣጠር ከባድ ነው። በዋናነት የሚማሩት ወላጆችን በማየት ስለሆነ ወላጆች ህጻናት ባሉበት ስልክ ባለመነካካት፣ ቴሌቪዥን በማጥፋት ለልጆቻቸው አርዓያ መሆን ይኖርባቸዋል። Youtube: https://www.youtube.com/@HealthifyEthiopia @HealthifyEthiopia
без подписи
የእባብ መነደፍ አደጋ ( Snake Bite ) ✅በአገራችን ካሉት እባብ አይነቶች ውስጥ መርዛማ የሆኑት ጥቂቶች ናቸው፡፡ ✅ የብዙዎቹ ንድፊያ ለህይወት አያሰጋም:: ስለዚህ ከተነደፈ በጣም መርበትበት ወይም አላስፈላጊ መረበሽ ውስጥ መግባት አያስፈልግም፡፡ መርዛማ አለመሆኑ እስኪጣራ ጊዜ ስለሚፈጅ የመጀመሪያ እርዳታ ማድረግ ተገቢ ነው፡፡ በእባብ የተነደፈ ሰው ምን አይነት ምልክቶችን ያሳይል ? ከንድፊያ በኋላ የእባቡ ጥርስ ያረፈባቸው ቁስሎች ይኖራሉ፣ አካባቢው ሊያብጥ ይችላል፡፡ የቆዳ ቀለምም በዚያ አካባቢ ሊለወጥ ይችላል፡፡ እንደ እባቡ አይነት ሌሎች ምልክቶች ማቅለሽለሽ፣ ማስታወክ፣ አይን ብዥ ማለት፣ ማላብ፣ መተንፈስ ችግር፣ የአፍ መኮላተፍ ፣ መዝለፍለፍ እና የአካል መንቀጥቀጥ ሊያስከትሉ ይችላሉ፡፡ ✅ የመጀመሪያ ህክምና እርዳታ ምን እናድርግ ? የተነደፈውን ሰው ከእባቡ ማራቅ። የተነደፈውን ሰው ማረጋጋት ፣ እንዲንጋለሉ ማድረግ፡፡ የባለሙያ እርዳታ ወዲያውኑ እንዲገኝ ማድረግ፡፡ መርዝን በአፍዎ ለመምጠጥ ሙከራ አያድርጉ፡፡ አይጠቅምም፡፡ የተነደፈውን የሰውነት ክፍል አለመነቃነቅ (መርዙን ስርጭት ለመቀነስ)፡፡ በረዶ ወይም ቀዝቃዛ ነገር ቁስሉ ላይ አያድርጉ፡፡ አይጠቅምም፡፡ የመርዙን ስርጭት ለመቀነስ ከቁስሉ በላይ (በቁሰሉና በልብ መሃከል) በፋሻ በጣም ሳይጠብቅ ይሰሩት፡፡ (በጣም ከጠበቀ የበለጠ አደጋ ይደርሳል):: ወደ ሐኪም ቤት መውሰድ ካለብዎ የተነደፈውን አካል እንዳይንቀሳቀስ ማድረግ ። እባቡን ከርቀት ፎቶ ማንሳት ( የእባቡን አይነት ለመለየት) :: ቴሌግራም @HealthifyEthiopia YouTube https://www.youtube.com/@HealthifyEthiopia
በእርግዝና ወቅት የሚከሰት የስኳር ህመም (gestational diabetes, GDM) የህክምና ግቦች ምንድን ናቸው? በእርግዝና ወቅት የሚከሰት የስኳር ህመም እንዳለቦት ከታወቀ — አትደንግጡ። የስኳር ቁጥጥርን በአስተማማኝ ግብ ውስጥ ካስተካከሉ እናት ጤና፤ ልጅም ደህና መሆን ይቻላል። ለጤናማ እርግዝና ስለስኳር ህክምናው ግቦች ጠንቅቆ ማወቅና መረዳት ይፈልጋል። ውጤታማ ህክምና የስኳር ቁጥጥር እቅድ ማውጣት እና ግልጽ የሕክምና ግቦችን በማዘጋጀት ይጀምራል። የደም ስኳር መጠንን ጤናማ በሆነ ክልል ውስጥ መቆጠጠርን ያካትታል። በአለም አቀፋዊ የሕክምና መመሪያዎች የሚደገፉት የስኳር ግቦች እንዲህ ናቸው፡- 1️⃣ የባዶ ሆድ የስኳር መጠን፡ ከ70 እስከ 95 mg/dL 2️⃣ ከምግብ ከአንድ ሰዓት በኋላ የስኳር መጠን፡ ከ140 mg/dL በታች 3️⃣ ከምግብ ከሁለት ሰአት በኋላ የስኳር መጠን፡ ከ120 mg/dL በታች እነዚህን ግቦች ማሳካት ለእናትም ሆነ ጽንስ ጤና ወሳኝ ነው። የጽንስ መፋፋትና ክብደት ከፍ ማለት (macrosomia)፣ ከምጥ ጋር የተያያዙ ችግሮች፣ የጽንስ መታፈን፣ ህጻኑ እንደተወለደ መተንፈስ መቸገር፣ ወዘተ ያሉ ተግዳሮቶችን ለመቀነስ ስኳርን እስከመጨረሻዋ ደቂቃ ድረስ ማስተካከል ይገባል። እነዚህ ግቦች ለእያንዳንዷ እናት በሚመች መልኩ በትንሹ ሊለያዩ ይችላሉ። የእያንዳንዷን እናት ጤና፣ የአኗኗር ዘይቤ፣ የአመጋገብ ምርጫዎች እና ለመድሃኒት ያላትን ምላሽ ከግምት ያስገባ መሆን ይገባዋል። ይህን ከጤና ባለሙያው ጋር በመመካከር ማስተካከል ይችላሉ። ስለ ጂዲኤም ጥያቄዎች አሉዎት? አስተያየትዎትን ይጻፉልን። ቴሌግራም @HealthifyEthiopia YouTube https://www.youtube.com/@HealthifyEthiopia