Ministry of Revenues of Ethiopia/የገቢዎች ሚኒስቴር
Статистикаየገቢዎች ሚኒስቴር ኢኮኖሚው የሚያመነጨው ገቢ እንዲሰበስብ ኃላፊነት የተሰጠው የፌዴራል ተቋም ነው፡፡ የጉምሩክ ኮሚሽንን በስሩ ይዞ ተደራጅቷል፡፡
- Последний пост
- 14 авг.
- Последнее чтение
- 15 авг.
- Постов за неделю
- 26
- Всего постов
- 37
- Тип
- открытый
- Язык
- ti
- Категория
- Новости и СМИ (по похожим)
- В каталоге с
- 13 авг.
- 1/24сутки в ленте
- 5 313
- 1/48двое суток
- 6 088
- 1/72трое суток
- 6 566
Медиана по постам, которые мы застали свежими и померили через сутки.
Посты
https://youtu.be/lWr8dXo3YJw
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
በታክስ ሕግ ተገዢነት ማሻሻያ ረቂቅ እቅድ (Draft Compliance Improvement Plan) ሰነድ ላይ ሲያካሄድ የነበረው ወርክሾፕ ውጤታማ እንደነበር ተገለጸ ነሐሴ 07/2018 ዓ.ም (የገቢዎች ሚኒስቴር) የገቢዎች ሚኒስቴር በታክስ ሕግ ተገዢነት ማሻሻያ ዕቅድ ረቂቅ ሰነድ ላይ ለሲኒየር ማናጅመንት ሲያካሂደው የነበረው ወርክሾፕ የማጠቃለያ መርሃ ግብር ላይ የስራ አቅጣጫ የሰጡት በሚኒስቴሩ የታክስ ስርአት ዘርፍ ሚኒስቴር ዴኤታ ወ/ሮ መስከረም ደበበ ወርክሾፑ ጠቃሚ ግብዓት የተገኘበትና ውጤታማ እንደነበር ገልጸዋል። የወርክሾፑ ዓላማ ረቂቅ ሕጉን ይበልጥ ለማዳበር፤ ግብረ መልስ ለመሰብሰብ፤ እቅዱን ከተቋማችን ነባራዊ ሁኔታ ጋር ለማጣጣም እና በትግበራ ወቅት ሊያጋጥሙ የሚችሉ ችግሮችን አስቀድሞ ለመለየት፤ ዓለም አቀፍ መመዘኛዎች ላይ አስቀድሞ ዝግጁነትን ለማረጋገጥ የሚያስችሉ እንዲሁም የውሳኔ አሰጣጥ በመረጃ ላይ የተመሰረተ እንዲሆን የሚያስችሉ ግብዓቶችን ለማግኘት ያለሙ መሆናቸውን ወ/ሮ መስከረም አስታውሰዋል፡፡ ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ፡- https://shorturl.at/U8Zei
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
የኅትመት ውጤቶች የተሻለ የግብር መረጃ ለማቅረብ እንደሚረዱ ተገለጸ ነሐሴ 06/2018 ዓ.ም (የገቢዎች ሚኒስቴር) የኅትመት ውጤቶች ለግብር ከፋዮች ከፍተኛ ጠቀሜታ ያላቸው የግብር መረጃዎች እንደሚያስተላልፉ የገቢዎች ሚኒስቴር ከአዲስ ሚዲያ ኔትወርክ የኅትመት ዝግጅትና ሥርጭት ዳይሬክቶሬት ጋር ባደረገው የልምድ ልውውጥ ተጠቆመ፡፡ የኅትመትና ዶክመንቴሽን ላይ በተደረገው የልምድ ልውውጥ የኅትመት ዝግጅት፣ የይዘት ምርጫና አርትዖት፣ የዲዛይን ጥራት፣ የኅትመት ቴክኖሎጂና ሥርጭት ላይ ዝርዝር መረጃዎች በአዲስ ሚዲያ ኔትወርክ የኅትመት ዝግጅትና ሥርጭት ዳይሬክቶሬት ባልደረቦች ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል፡፡ በውይይቱ፤ የገቢዎች ሚኒስቴር በራሪ ወረቀቶችን፣ “እኛ ለእኛ” እና “ገቢ ለልማት” ጋዜጦችን፣ መጽሔቶችንና መጻሕፍትን በማዘጋጀትና በማሰራጨት ለማኅበረሰቡና ለውስጥ ሠራተኞች የታክስ መረጃን ተደራሽ እያደረገ እንደሚገኝ በሚኒስቴሩ የኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክተር አቶ በፍርዱ መሠረት አመላክተዋል፡፡ ዳይሬክተሩ፤ ከልምድ ልውውጡ የተገኙ ምርጥ ተሞክሮዎችን ሥራ ላይ በመተግበር የኅትመት ሥራዎች ለግብር ከፋዮች ከማቅረብ ባሻገር፣ የተቋሙን ታሪክ ለመጪው ትውልድ ሰንዶ ማስቀመጥ እንደሚገባ ጠቁመዋል፡፡ በተያያዘ መረጃ፤ ዳይሬክቶሬቱ ከኅትመት ውጤቶች ውስጥ አንዱ የሆነውን የገቢዎች ሚኒስቴር “የአራት ዓመታት ጉዞ” የሚያሳይ መጽሐፍ ለአንባቢ በቅርቡ ተደራሽ እንደሚደረግ አቶ በፍርዱ መሠረት አሳውቀዋል፡፡
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
የታክስ ሕግ ተገዢነትን ለማሻሻል እና በታክስ አስተዳደር ስራዎች ለማረጋገጥ በቀረበ ረቂቅ ሰነድ ላይ ወርክሾፕ መካሄድ ጀመረ ነሐሴ 05/2018 ዓ.ም (የገቢዎች ሚኒስቴር) የታክስ ከፋዩን ሕግ ተገዢነት በታክስ አስተዳደር ስራዎች ለማረጋገጥ በተዘጋጀ ረቂቅ እቅድ ሰነድ ላይ ግብዓት ማሰባሰቢያ ወርክሾፕ በዛሬው እለት ተጀምሯል፡፡ ዛሬ በተጀመረው የሲኒየር ማናጅመንት ወርክሾፕ ላይ የገቢዎች ሚኒስትር ዓይናለም ንጉሴ ባደረጉት ንግግር የቀረበው ሰነድ ከግብር ከፋዮች ምዝገባ አንስቶ እስከ ስረዛ ድረስ ያለውን የሚያጠቃልልና በሂደቱም የሚታዩ ጉድለቶችን ለመሙላት የሚያስችል ስትራቴጂክ ምሰሶዎችን የያዘ ሰነድ መሆኑን ገልጸዋል። ሚኒስትሯ አክለውም የግብር ከፋይ መረጃ ተደራሽነት፤ የብሔራዊ ሦስተኛ ወገን ትስስር፣ እንደየግብር ከፋዩ ባሕሪ የሚቀርብ አገልግሎት እና የአቅም ግንባታ ስራዎች በሰነዱ የቀረቡ ዋና ዋና ጉዳዮች መሆናቸውን በማውሳት ትኩረት ሊደረግባቸው እንደሚገባ አመላክተዋል። የታክስ ከፋዩን የሕግ ተገዢነት በታክስ አስተዳደር ስራዎች ለማረጋገጥ የተዘጋጀው ይህ የረቂቅ ሰነድ ስትራቴጂ አመላካችና አገር አቀፍ የታክስ አስተዳደር ስርአትን ለመገንባት የሚያስችል እንደሆነም ተነግሯል። በዚሁ የታክስ ትራንፎርሜሽን ጽ/ቤት ባዘጋጀው የረቂቅ ሰነድ ውይይት መድረክ የገቢዎች ሚኒስቴር ሚኒስትር ዲኤታዎችና የሚኒስቴሩ ሰኒየር ማናጅመንት አባላት ተሳታፊ መሆናቸው ታውቋል። በገዛኸኝ መካሻ ፎቶ:- ክፍሌ አዳፍሬ
#የሐዘን_መግለጫ ነሐሴ 05/2018 ዓ.ም (የገቢዎች ሚኒስቴር)
видео или голосовое, без подписи