ሞዐ ተዋሕዶ ልጆች ፔጅ
Статистика"ነፍሳችን በስጋ ስንኖር ብዙ መከራ አለባት። እንዲሁም ከስጋችን ከተለየች በኋላ እንደሰራነው ስራ ጥሩ ወይም መጥፎ እጣፈንታዎች ይገጥሟታል። ታዲያ በህይወት ስንኖር ነፍሳችንን የምታሻግር አንድ መንገድ አለች ይህችም ቀጥተኛዋ የኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነት ናት። " https://t.me/MoaeTewahedoB አስተያየት ና ጥያቄ ያለው ብቻ‼️ @sosi5555 ይህ ፔጅ ታህሳስ 30/4/2014
- Последний пост
- 15 авг.
- Последнее чтение
- 13 авг.
- Постов за неделю
- 38
- Всего постов
- 70
- Тип
- открытый
- Язык
- ti
- В каталоге с
- 13 авг.
- 1/24сутки в ленте
- 558
- 1/48двое суток
- 639
- 1/72трое суток
- 689
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
без подписи
без подписи
без подписи
без подписи
без подписи
без подписи
без подписи
без подписи
без подписи
без подписи
без подписи
без подписи
без подписи
без подписи
🕰🔔 11:00 ተንስኡ ለጸሎት በዚህ ሰዓት ይህንን የምታይ ሰው የምታደርገውን ለ2 ደቂቃም ብትሆን ተውና ልዑል እግዚአብሔር እያሰብን ቢያንስ አንድ አባታችን ሆይ እንጸልይ እግዚኦ ተሰኃለነ❖ እግዚኦ ተሰኃለነ❖ እግዚኦ ተሰኃለነ❖ አቤቱ ማረን ይቅርም በለን✥ አቤቱ ማረን ይቅርም በለን✥ አቤቱ ማረን ይቅርም በለን✥ አገር ውስጥ ያላቹሁ በስደትም በስራም እንኳን ቢሆን አንድ አባታችን ሆይ እንበል🥰 @MoaeTewahedoB
🕰🔔 9:00 ተንስኡ ለጸሎት በዚህ ሰዓት ይህንን የምታይ ሰው የምታደርገውን ለ2 ደቂቃም ብትሆን ተውና ልዑል እግዚአብሔር እያሰብን ቢያንስ አንድ አባታችን ሆይ እንጸልይ እግዚኦ ተሰኃለነ❖ እግዚኦ ተሰኃለነ❖ እግዚኦ ተሰኃለነ❖ አቤቱ ማረን ይቅርም በለን✥ አቤቱ ማረን ይቅርም በለን✥ አቤቱ ማረን ይቅርም በለን✥ አገር ውስጥ ያላቹሁ በስደትም በስራም እንኳን ቢሆን አንድ አባታችን ሆይ እንበል🥰 @MoaeTewahedoB
አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም ነሐሴ ሰባት በዚች ቀን እግዚአብሔር የመላእክት አለቃ ቅዱስ ገብርኤልን ወደ ከበረና ከፍ ከፍ ወዳለ ጻድቅ አ.ያቄም ላከው አምላክን የወለደች የእመቤታችን የድንግል ማርያምን ፅንስቷንና ልደቷን በእርሷም ለዓለሙ ሁሉ ድኅነትና ተድላ ደስታ እንደሚሆን ነገረው ። ይህ ጻድቅም ሰው ኢያቄምና የከበረች ሚስቱ ሐና ልጅ ሳይወልዱ ሸመገሉ የከበረች ሐና መካን ሁናለችና ስለዚህም እጅግ ያዝኑ ነበር የእስራኤል ልጆች ልጅ ያልወለደውን ከእግዚአብሔር በረከትን ያጣ ነው እያሉ ያቃልሉት ነበርና ። እነርሱም ልጅን ይሰጣቸው ዘንድ ወደ እግዚአብሔር ዘወትር ፈጽሞ ይለምኑ ነበር ። ከዚህም በኋላ ወንድ ልጅን ወይም ሴት ልጅን ቢወልዱ ለእግዚአብሔር ቤት አገልጋይ ሊያደርጉ ስለትን ተሳሉ ። የከበረ ኢያቄምም በተራራ ላይ ሳለ ሲጸልይና ሲማልድ እነሆ በላዩ እንቅልፍ እንቅልፍ ብሎት አሸለበ ያን ጊዜ ከእግዚአብሔር የተላከ የመላእክት አለቃ ቅዱስ ገብርኤል ተገለጸለት እንዲህም አለው ሚስትህ ሐና ትፀንሳለች ዓለሙ ሁሉ ደስ የሚሰኝባትን የብዙዎችም ዐይነ ልቡ ናቸው በእርሷ የሚበራላችውን በእርሷም ድኅነት የሚሆንባትን ሴት ልጅን ትወልድልሃለች በነቃ ጊዜም ወደ ቤቱ ሒዶ ለሚስቱ ለቅድስት ሐና ነገራት ራእይዋን እውነት እንደሆነች አመኑዋት ከዚህም በኋላ ነሐሴ ሰባት በዚች ቀን የከበረች ሐና ፀነሰች ለዓለም ሁሉ መመኪያ የሆነች በሁለት ወገን ድንግል የሆነች የአምላክ እናት እመቤታችንን ማርያምን ወለደቻት ። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በከበሩ ኢያቄምና ሐና ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋር ይኑር ለዘላለሙ አሜን ። https://t.me/MoaeTewahedoB
🕰🔔 6:00 ተንስኡ ለጸሎት በዚህ ሰዓት ይህንን የምታይ ሰው የምታደርገውን ለ2 ደቂቃም ብትሆን ተውና ልዑል እግዚአብሔር እያሰብን ቢያንስ አንድ አባታችን ሆይ እንጸልይ እግዚኦ ተሰኃለነ❖ እግዚኦ ተሰኃለነ❖ እግዚኦ ተሰኃለነ❖ አቤቱ ማረን ይቅርም በለን✥ አቤቱ ማረን ይቅርም በለን✥ አቤቱ ማረን ይቅርም በለን✥ አገር ውስጥ ያላቹሁ በስደትም በስራም እንኳን ቢሆን አንድ አባታችን ሆይ እንበል🥰 @MoaeTewahedoB
🕰🔔 3:00 ተንስኡ ለጸሎት በዚህ ሰዓት ይህንን የምታይ ሰው የምታደርገውን ለ2 ደቂቃም ብትሆን ተውና ልዑል እግዚአብሔር እያሰብን ቢያንስ አንድ አባታችን ሆይ እንጸልይ እግዚኦ ተሰኃለነ❖ እግዚኦ ተሰኃለነ❖ እግዚኦ ተሰኃለነ❖ አቤቱ ማረን ይቅርም በለን✥ አቤቱ ማረን ይቅርም በለን✥ አቤቱ ማረን ይቅርም በለን✥ አገር ውስጥ ያላቹሁ በስደትም በስራም እንኳን ቢሆን አንድ አባታችን ሆይ እንበል🥰 @MoaeTewahedoB
+++ "እግዚአብሔር የጣላት እሳት" +++ በደብተራ ኦሪት በመሠዊያው ላይ የሚነደውና መሥዋዕቱ ይቃጠልበት የነበረው እሳት ከሰማይ የወረደ ነበር። ይህም እሳት ዘወትር እንዳይጠፋ የአሮን ልጆች (ካህናቱ) ማለዳ ማለዳ እንጨት እየጨመሩ እንዲያቀጣጥሉና እንዲያነዱት እግዚአብሔር አዝዟቸዋል።(ዘሌዋ 6፥12) ከማዕጠንት ጀምሮ እስከ እንስሳት በድንኳኑ የሚቀርቡ ማናቸውም የሚቃጠሉ መሥዋዕቶች ሁሉ የሚበሉት ከሰማይ በወረደው በዚህ "የእግዚአብሔር እሳት" ነው። ታዲያ ከእለታት በአንዱ ቀን የአሮን ልጆች ናዳብና አብዩድ እንዲህ አደረጉ። ለእግዚአብሔር የእጣን መሥዋዕት ማቅረብ ፈልገው ለየራሳው ጥናውን (ማዕጠንት) አነሡ። ነገር ግን በጥናው ውስጥ ያደረጉት ከሰማይ የወረደውን "የእግዚአብሔር እሳት" ሳይሆን፣ ከመንደር ጭረው ያመጡትን ወይም ራሳቸው ያቀጣጠሉትን "ሌላ እሳት" ነበር። በዚህም እግዚአብሔር ያላዘዛቸውን ሌላ እሳት ስላቀረቡ አምላክ ተቆጣ። በፊቱም እሳት ወጥቶ እንዲበላቸው አደረገ። እነርሱም ወዲያው ሞቱ።(ዘሌ 10፥1-3) ሊቀ ካህናቱ አሮንን እየተከተሉ እንዲያገለግሉ የተመረጡት ሁለቱ ልጆቹ ገና አገልግሎታቸውን በቅጡ ሳይጀምሩ ተቀሰፋ። ለመሆኑ እነዚህ ሁለት የኦሪት ወጣት ካህናት የተቀጡበት "የሌላ እሳት" ታሪክ ለሐዲስ ኪዳኑ ዘመን ምን ምሳሌ ይኖረው ይሆን? እግዚአብሔር በኦሪቱ ድንኳን እሳትን እንዳወረደ፣ በሐዲስ ኪዳንም የሰውን ልጅ ለማዳን ከሰማይ ሲወርድ ይዞልን የመጣው እሳት አለ። "እሳተ አምጻእኩ ለብሔር፤ ወምንተ እፈቅድ ዘእንበለ አንድዶታ" - "በምድር ላይ እሳት ልጥል መጣሁ፥ አሁንም የነደደ ከሆነ ዘንድ ምን እፈልጋለሁ?" እንዳለን።(ሉቃ 12፥49) ይህ መድኃኒታችን በምድር ላይ የጣለው እሳት ምንድር ነው? አገልግሎቱስ እንዴት ነው? ጌታችን በምድር የጣላት እሳት "ወንጌል" ትባላለች። ሰው ሰውነቱን ንጹሕና የተቀደሰ ሕያውም መሥዋዕት አድርጎ የሚያቀርብባት "የእግዚአብሔር እሳት" ወንጌል ነች። ይህች ወንጌል ጌታ አንድ ጊዜ በምድር የጣላት፣ እኛ ደግሞ ለዘወትር እንዳትጠፉ የምናቀጣጥላትና የምናነዳት እሳት ነች። የማቀጣጠያው እንጨቶችም ቃለ እግዚአብሔርን መስማት እና ማንበብ ናቸው። ያለ ወንጌል እሳትነት ምንም መሥዋዕት እንድናቀርብ አልተፈቀደልንም። ነገር ግን እንደ አሮን ልጆች ናዳብና አብዩድ ከመንደር ቆስቁሰን ወይም ራሳችን አቀጣጥለን የምናመጣቸው "ሌላ እሳት" የተባሉ ከንቱ ፍልስፍናዎችና እንግዳ ትምህርቶች የእግዚአብሔርን ቁጣ ይቀሰቅሱብናል። ዳግመኛም እሳት የተባለው በጥምቀት ጊዜ በሁላችንም ላይ የወረደው ጸጋ እግዚአብሔር ነው። ይህም ጸጋ ለመዳናችን ዓይነተኛ ሚና አለው። ይሁን እንጂ ልክ በደብተራ ኦሪት እንደ ወረደው እሳት ካልተንከባከብነው እና ካላቀጣጠልነው ሊዳፈን እና የሌለ ሊመስል ይችላል። ለዚህም ነው ቅዱስ ጳውሎስ ለመንፈስ ልጁ ጢሞቴዎስ "እሳት እንደሚያቀጣጥል ሰው...በአንተ ያለውን የእግዚአብሔርን ሥጦታ እንድታነሣሣ አሳስብሃለሁ" በማለት የሚመክረው።(2ኛ ጢሞ 1፥6) እግዚአብሔር ለሰጠን ጸጋ ማቀጣጠያዎቹ ደግሞ ጾም፣ ጸሎትና መንፈሳዊ ትሩፋት ሁሉ ናቸው። እርሱ የሰጠህን የጸጋ እሳት ከማቀጣጠል ይልቅ "ሌላ እሳት" ላምጣ ያልህ ቀን ግን ታላቅ ጥፋት ያገኝሃል። @MoaeTewahedoB