tgindex
WT Media

Voice of Marginalized Community

Последний пост
17:44
Последнее чтение
18:45
Постов за неделю
7
Всего постов
192
Тип
открытый
Язык
английский
Категория
Новости и СМИ (по похожим)
В каталоге с
13 авг.
Подписчики
4 389
−13 за 3 дн.
Сутки
−2
−0,05%
Неделя
 
Месяц
 
Просмотров на пост
803
40 постов
Вовлечённость
18,3%
к подписчикам
Постов в день
1,0
всего 192
Упоминаний
0
каналов
Охват размещения
оценка
1/24сутки в ленте
447
1/48двое суток
512
1/72трое суток
552

Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.

Посты

  • በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ጤና ቢሮ የህፃናትና እናቶች በጀት ለቅንጡ ስልክ ግዥ መዋሉ አነጋጋሪ ሆነ! ​ ​በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልላዊ መንግሥት ጤና ቢሮ የእናቶችና ህፃናት ጤና ዳይሬክቶሬት፤ ለህፃናት እና እናቶች ጤና የተመደበ በጀት ለቅንጡ ስልኮች ግዥ መዋሉ በሰነዶች መረጋገጡ ከፍተኛ አነጋጋሪ ሆኗል። ​የተገኙት የደብዳቤ እና የደረሰኝ ሰነዶች እንደሚያሳዩት፣ የበጀቱ የመጀመሪያ ዓላማ በምግብ እጥረት ለተጎዱ ህፃናትና እናቶች ድጋፍ ለማድረግ (ተሽከርካሪ ኪራይና ጥገና) እንዲሁም የህክምና መመሪያዎችን (AIMAM quick reference) ለማተም የታለመ ነበር። ይሁን እንጂ ከዚህ የተያዘ በጀት ላይ በማዘዋወር ሁለት iPhone 17 Pro Max (12GB/512GB Silver) ስልኮች እንዲገዙ ተደርጓል። ​በደብዳቤው ላይ እንደሰፈረው የአንዱ ስልክ ዋጋ 398,000 ብር ሲሆን ለሁለቱ ስልኮች በአጠቃላይ 796,000 ብር ወጪ ተደርጓል። ​በተያያዘው የንብረት ግቢ ውጪ ደረሰኝ ላይ የሲም ካርድ፣ የካርድ አየር ሰዓት እና የዳታ አገልግሎትን ጨምሮ አጠቃላይ ወጪው በአንድ ስልክ እስከ 398,091.05 ብር መድረሱ ተመላክቷል። ​በደብዳቤው የታዘዘው የስልክ ግዥ ሲሆን በደረሰኝ ላይ የሲም ካርድ እና የኤርታይም ወጪዎች መቀላቀላቸው የበጀቱ አጠቃቀም ሰፊ ምስቅልቅል ያለበት መሆኑን ያረጋግጣል። ​በምግብ እጥረት ለተጎዱ እና ለታመሙ ወገኖች መድረስ ያለበት የህዝብ ገንዘብ ለአንድ ስልክ ወደ 398 ሺህ ብር በሚጠጋ ወጪ መወሰኑ የሞራልና የአስተዳደር ጥሰት መሆኑን አመላክቷል። ስለሆነም የሚመለከታቸው የሚዲያ አካላት፣ የሲቪክ ማህበራት እና የፀረ-ሙስና ተቋማት በጉዳዩ ላይ ግልፅ ምርመራ እንዲያደርጉበት ጥሪ ቀርቧል። ​🎙️ ማሳሰቢያ፦ WT Media በደቡብ ኢትዮጵያ እና በሌሎች አካባቢዎች የሚከሰቱ የመልካም አስተዳደር እጦቶችን እና የሀብት አጠቃቀም ብክነቶችን በሰነድ አስደግፎ ማቅረቡን ይቀጥላል! ​Voice of Marginalized Community - WT Media ​#Ethiopia #SouthWestEthiopia #WTMedia #Corruption #HealthBureau #ደቡብምዕራብኢትዮጵያ https://wolaitatimes.com/?p=8175

  • ​አቶ አብርሃም በህይወታቸው ዘመን ሁሉ አምላካቸውን፣ ህዝባቸውን እና ሀገራቸውን በፍጹም ታማኝነት አገልግለው ባደረባቸው ህመም ምክንያት በህክምና ሲረዱ ቆይተው በተወለዱ በ72 ዓመታቸው ነሀሴ 8 ቀን 2018 ዓ.ም. ወደ አምላካቸው ተሰብስበዋል። ​አቶ አብርሃም በመልካም ተግባራቸው ምክንያት ስማቸው ሁል ጊዜ ከመቃብር በላይ ሆኖ ይኖራል። ​የአሁኑ ትውልድ ከወንድም አብርሃም የአላማ ፅናትን፣ ለህዝብ መኖርን፣ የሰው ፍቅርን፣ ለተወለዱበት ማህበረሰብ ባህልና ታሪክ መቆርቆርን፣ የልብና የእጅ ንፅህናን፣ በፍጹም ንፅህና ሀገርና ህዝብን ማገልገልን፣ አስታራቂነትን ወዘተ ይማራል ብለን ተስፋ እናደርጋለን። ​አቶ አብርሃም ለህዝብና ለሀገር ለከፈሉት መልካም ተግባር በተለይም ለዎላይታ ህዝብ ባህል፣ ታሪክና ቋንቋ እድገት ላበረከቱት ትውልድ ለማይረሳው ተግባራቸው ጉዳዩ የሚመለከታቸው የመንግስት ኃላፊዎች አንድ ቋሚ ማስታወሻ እንዲያቆሙላቸው በአክብሮት እንጠይቃለን። ​ለባለቤታቸውና ለልጆቻቸው እንዲሁም ለወዳጅ ዘመዶቻቸው ጌታ ኢየሱስ መጽናናትን ይስጣችሁ🙏 https://wolaitatimes.com/?p=8168

  • የዎላይታ ሕዝብ ታሪክ ተመራማሪ አቶ አብራሃም ባቾሬ ሥርዓተ ቀብር ተፈጸመ ​የዎላይታ ሕዝብ ታሪክ ተመራማሪና የሶዶ ከተማ የቀድሞ ከንቲባ አቶ አብራሃም ባቾሬ ሥርዓተ ቀብር በዛሬው ዕለት ተፈፅሟል። ​አቶ አብራሃም ባቾሬ በሕይወት ዘመናቸው በልማት፣ በአስተዳደር፣ በኮሙኒኬሽን፣ በባህልና ታሪክ ጥናት፣ በማኅበረሰብ ዕርቅ ዘርፍ ለሀገርና ለሕዝብ ጉልህ አሻራቸውን አሳርፈዋል። ​የዎላይታ ብሔር የዘመን መለወጫ "ጊፋታ" በዓል ሀገራዊና ዓለም አቀፋዊ እውቅና አግኝቶ በዩኔስኮ የዓለም የማይዳሰሱ ቅርሶች መዝገብ ላይ እንዲሰፍር ከፍተኛ አስተዋጽኦ አበርክተዋል። ​በኢትዮጵያ አየር ኃይል፣ በዓለም አቀፉ የሕፃናት አቀፍ ድርጅት እና በዎላይታ ልማት ማኅበር ውስጥ እንዲሁም የሶዶ ከተማ ከንቲባ በመሆን አገልግለዋል። ​በተጨማሪም የወላይታ የሀገር ሽማግሌ በመሆን በህዝብ ለህዝብ ግኑኝነት፣ በማስታረቅ እና በሌሎች ማህበራዊ ጉዳዮች ላይ በመሳተፍ በእድሜ ዘመናቸው የማይረሳ ታሪክ አኑረው አልፈዋል። ​አቶ አብራሃም ባቾሬ ባለትዳር እና የሶስት ልጆች አባት ነበሩ። ​የዎላይታ ሕዝብ ታሪክ ተመራማሪና የዎላይታ ሶዶ ከተማ የቀድሞ ከንቲባ የነበሩት አቶ አብራሃም ባቾሬ ባደረባቸው ሕመም በሕክምና ሲረዱ ቆይተው ነሐሴ 8 ቀን 2018 ዓ.ም ከዚህ ዓለም በሞት መለየታቸው ይታወሳል። ​የአቶ አብርሃም ባቾሬ አጭር የህይወት ታሪክ ​አቶ አብርሃም ባቾሬ ከአባታቸው ከአቶ ሽርኮ ሃላላ እና ከእናታቸው ከወ/ሮ ጋልዳሜ ባቾሬ በ1946 ዓ.ም በቀድሞ የዎላይታ አውራጃ በሶዶ ዙሪያ ወረዳ ዛላ ሻሻ ቀበሌ ተወለዱ። አቶ አብራሃም ይጠሩ የነበሩት በአያታቸው በአቶ ባቾሬ ስም ነበር። ​አቶ አብርሃም በልጅነት ዘመናቸው እንደማንኛውም የገጠር ልጅ እርሻ አርሰው እንጨት ሰብረው ውሃ ቀድተው ያደጉ ሲሆን ለወላጆቻቸው ታዛዥ በዕድሜ እኩዮቻቸው ተወዳጅ ልጅ ነበሩ። ​ዕድሚያቸው ለትምህርት ሲደርስ በቦሣ ሉትራን ሚሺን ት/ቤት ፊደል በመቁጠር የጀመሩ ሲሆን የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርታቸውን በሶዶ ጊዮርጊስ ትምህርት ቤት የሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን ደግሞ በሶዶ አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ተከታትለዋል። ​አቶ አብርሃም ባቾሬ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን በመከታተል ላይ እያሉ በ1967 ዓ.ም በጊዜው የነበረው መንግስት መሀይምነትን ለማጥፋት ባዘጋጀው የእድገት በህብረት የእውቀትና የሥራ ዘመቻ ለመሳተፍ ወደ ገጠሪቱ ኢትዮጵያ ዘመቱ። ​በዚህም ዘመቻ ከሌሎች ዘማቾች ጋር በመሆን ህዝቡን በማስተማር፣ በመንቃትና በማደራቸት መሬት ላራሹ የመሳሰሉ አርሶ አደሩን ተጠቃሚ ያደረጉ የጊዜው መንግስት አዋጆች መሬት ላይ እንዲወርዱ በማድረግ የህዝብ አገልጋይነትን መለማመድ ጀመሩ። ​ከዘመቻው ፍጻሜ በኋላ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን በማጠናቀቅ ከልጅነታቸው ጀምረው ሲመኙት ነበረውን ህልማቸውን ለማሳካት በ1969 ዓ.ም የኢትዮጵያ አየር ኃይልን በፍላጎት ተቀላቀሉ። ​በአየር ኃይል ቆይታቸው በአየር ትንበያ (ሜትሮሎጂ) ባለሙያነት በደብረዘይት፣ በጎዴ እና በአሥመራ ተዘዋውረው ፍጹም በሆነ የሀገር ፍቅር ስሜት ኃላፊነታቸውን ተወጥተዋል። ​በአየር ኃይል ቆይታቸው በቀድመው የሶቬት ህብረት የትምህት ዕድል በማግኘት በኪርጊዝስተን (Kyrgyzstan) ለአምስት ዓመት ተጨማሪ ትምህርት ተከታትለው ወደ ሀገራቸው ተመልሰዋል። ​ከ"Kyrgyzstan" በተጨማሪ በሥራ ዓለም በነበሩበት ጊዜ ወደ ዩክሬን፣ ኡዝቤኪስታን እና ደቡብ አፍሪካ ተጎዘው የሥራ ልምድ ቀስመዋል። ​አቶ አብራሃም ከሶቬት ህብረት ከተመለሱ በኋላ የተጨማሪ ትምህርት ፍላጎታቸውን ለማሳከት በተሰጣቸው ፈቃድ ወደ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በማታው ፕሮግራም በመመዝገብ ለትምህርት በነበራቸው ጽኑ ፍላጎት በየቀኑ ከደብረዘይት እስከ ስድስት ኪሎ በመመላለስ በፖለቲካል ሳይንስና ዓለም አቀፍ ግንኙነት በማዕረግ ተመርቀዋል። ​አቶ አብርሃም በ1983 ዓ.ም የመንግስት ለውጥ ተከትሎ ከሥራ ተፈናቅለው በነበሩበት ወቅት እጮኛቸው ከነበሩት የትዳር አጋራቸው ጋር በ1986 ዓ.ም በሐዋርያዊት ቤተክርስቲያን በተቀደሰ ጋብቻ ትዳር በመመስረት አንድ ወንድ እና ሁለት ሴቶችን በድምሩ ሦስት ልጆችን እና ሦስት የልጅ ልጆችን አፍርተዋል። ​አቶ አብራሃም ከልጆቻቸው በተጨማሪ እህት ወንድሞቻቸውን እንዲሁም የወንድምና የእህቶቻቸውን ልጆች ምንም ልዩነት ሳያደርጉ አስተምረው ለወግ ለማዕረግ ያበቁ በቤተሰቦቻቸው ዘንድ "ጎዶ" እየተባሉ በፍቅር ስም የሚጠሩ የሁሉም አባት ነበሩ። ​አቶ አብርሃም ትዳር ከመሠረቱ በኋላ ብዙም ሳይቆዩ "Save the Children" በተባለ ግብረሰናይ ድርጅት በከፍተኛ ደመወዝ ተቀጥረው ሥራ ጀመሩ። ​ይሁን እንጂ ለዎላይታ ህዝብ በኢኮኖሚ መለወጥ በነበራቸው ጽኑ ፍላጎት በአዲስ መልክ የተቋቋመው የወላይታ ልማት ማህበር ባደረጉላቸው ጥሪ መሠረት የተሻለ ደመወዝና ጥቅማጥቅም በመተው ከመጀመሪያው በግማሽ በሚያንስ ደመወዝ በመቀጠር የልማት ማህበሩ የመጀመሪያው ፕሮጀክት ማናጀር በመሆን አገልግለዋል። ​ለዎላይታ ሊቃ ትምህርት ቤት መመስረትም የመጀመሪያውን ሀሳብ በማቅረብ የሊቃ ት/ቤት ዕውን እንዲሆን በማድረግ የአቶ አብርሃም ድርሻ ከፍተኛ ነበር። ​ከዚህም ሌላ በልማት ማህበሩ እስከ ቦርድ ሰብሳቢነት በማገልገል ወልማ አሁን ለደረሰበት ደረጃ መሠረት የጣሉ የህዝብ ልጅ ነበሩ። ​አቶ አብራሃም በወልማ የጀመሩትን የህዝብ አገልግሎት አጠናክረው በመቀጠል የሶዶ ማዘጋጃ ቤት ሥራ አስኪያጅ በመሆን በጊዜው በከተማው ህዝብ ዘንድ ከፍተኛ ቅሬታ ያስከትሉ የነበሩትን የአገልግሎት አሰጣጥ ችግሮችን ለማሻሻል በነበራቸው ህልም ያለምንም ማጋነን ዘወትር ከጠዋቱ አንድ ሰዓት እስከ ምሽቱ ሦስት ሰዓት በቢሯቸው ተቀምጠው ባለጉዳይ አገልግሎት በመስጠት ራሳቸውን አደጋ ላይ ጭምር በመጣል ታሪክ የማይረሳውን ውለታ ለዎላይታ ሶዶ ከተማ ህዝብ ውለዋል። ​በዚህም የስራ አፈጻጸማቸው ተገምግሞ የሶዶ ከተማ ከንቲባ በመሆን ተሹመው ከተማዋ አሁን ለደረሰችበት ደረጃ የማይናቅ አሻራ አሳርፈዋል። ​የፖለቲካል ሳይንስ እና አለም አቀፍ ግንኙነት ምሁሩ አቶ አብራሃም ባቾሬ ከህዝብ አመራርነት በተጨማሪ በዎላይታ ዞን ባህል ቱሪዝምና የመንግስት ኮሙኒኬሽን መምሪያ የኮሙኒኬሽን ዘርፍ አስተባባሪ በመሆን በዕድሜ ጡረታ እስከተገለሉበት እስከ 2010 ዓ.ም. ድረስ አገልግለዋል። ​በዚህም ሙያቸው በሚፈቅደው መሠረት ለየዞኑ ህዝብ ወቅታዊ መረጃዎች ተደራሽ እንዲሆኑ በማስቻል፣ በህዝብና በመንግስት መካከል ጤናማ የመረጃ ፍሰት እንዲኖር በማድረግ ዘርፋን በዕውቀት መርተዋል። ከዚህም ሌላ የወላይታ ቴሌቪዥን የቦርድ አባል በመሆንም አገልግለዋል። ​አቶ አብራሃም ከመደበኛ ሥራቸው በጡረታ ከተገለሉ በኋላ የወላይታ ህዝብ የሀገር ሽማግሌ በመሆን የህዝቡ ባህልና ታሪክ እንዲሁም የፈጠራና የስነጥበብ ውጤት የሆኑ የሚዳሰሱና የማይዳሰሱ ቅርሶች ትውልድ ተሻጋሪ እንዲሆኑ የበኩላቸውን አስተዋጽኦ አበርክተዋል። ​በተለይም የዎላይታ ዘመን መለወጫ የጊፋታ በዓል የሰው ልጆች ወካይ የማይዳሰስ ባህላዊ ቅርስ በመሆን በUNESCO እንዲመዘገቡ ከፍተኛ አስተዋጽኦ አበርክተዋል። ​አቶ አብርሃም በመንፈሳዊ ህይወታቸው በሚያመልኩበት ቤተ እምነት ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስን ተቀብለው በስሙ በመጠመቅ በቅድስና እግዚአብሔርን በመፍራት የሐዋርያዊት ቤተክርስቲን የእምነት አንቀጽ ጠብቀው የኖሩ፣ በማገልግሎታቸው የበረቱ ወንድም ነበሩ።

  • 21:132871

    በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል አርሶ አደሮቹ በማሳቸው የእርሻ ሥራ ላይ እያሉ በታጣቂዎች መገደላቸው ተገለፀ። በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በኮሬ ዞን ጎርካ ወረዳ ቆሬ ቀበሌ በዛሬው ዕለት በፀረ-ሰላም ኃይሎች በተከፈተ ድንገተኛ ጥቃት የሁለት ንጹሐን አርሶ አደሮች ሕይወት ማለፉን የኮሬ ዞን አስተዳደር አስታውቋል። አርሶ አደሮቹ በማሳቸው የእርሻ ሥራ ላይ እያሉ የተፈጸመው ይህ እኩይ ድርጊት የሕዝቡን የጋራ ሰላም ለማናጋት፣ አብሮነትን ለማላላት እና የልማት ሥራዎችን ለማደናቀፍ የታለመ በመሆኑ በጽኑ መወገዙ ተገልጿል። ​የኮሬ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ረ/ፕሮፌሰር ሚሊዮን ደሳለኝ በሰጡት መግለጫ፤ ይህ አሳዛኝ ድርጊት ለሰላም ያለውን ቁርጠኝነት ከማጠናከር ውጪ ወደኋላ እንደማያስቀረው ገልጸዋል። በቀጣይም ከአጎራባች ዞኖች፣ ከክልል መንግሥት እና ከጸጥታ አካላት ጋር በመቀናጀት ለአካባቢው ዘላቂ ሰላም ለማስፈን እና የህዝቡን ደህንነት ለማረጋገጥ የሚደረጉ ጥረቶች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ አረጋግጠዋል። ​ሕዝቡ በዚህ አሳዛኝ ክስተት ሳይደናገጥ አካባቢውን በንቃት በመጠበቅ መደበኛ የዕለት ተዕለት እንቅስቃሴውን እንዲቀጥል ጥሪ የቀረበ ሲሆን ለአስተዳዳሪው መግለጫ መሠረት ለሟቾች ቤተሰቦች፣ ወዳጅ ዘመዶች እና ለመላው የኮሬ ሕዝብ መጽናናት ተመኝቷል። Read more on our official website 👇https://wolaitatimes.com/?p=8165

  • ​የዎላይታ ብሄር እና የሀገራችን ታላቅ የታሪክና የእውቀት ማህደር የሆኑት፣ የቀድሞው የዎላይታ ሶዶ ከተማ ከንቲባ እና የሀገር ሽማግሌ አቶ አብራሃም ባቾሬ ከዚህ አለም በሞት ተለዩ። ​አቶ አብራሃም ባቾሬ በህይወት ዘመናቸው ለዎላይታ ብሄር እና ለሀገራቸው ዕድገት፣ ሰላም እንዲሁም የጋራ እሴቶች ግንባታ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያበረከቱ ታዋቂ ሰው ነበሩ። በተለይም በዎላይታ ሶዶ ከተማ አስተዳደር ከንቲባነት በነበሯቸው የኃላፊነት ጊዜያት እና በሀገር ሽማግሌነታቸው ማህበረሰቡን በታማኝነትና በብቃት ሲያገለግሉ ቆይተዋል። ​አቶ አብራሃም የዎላይታን ታሪክ፣ ባህል እና ወግ ጠንቅቀው የሚያውቁ፣ ለትውልድም እንዲተላለፍ ጥረት የሚያደርጉ ትልቅ የታሪክ አዋቂ በመሆናቸው ይታወቃሉ። አቶ አብራሃም ባቾሬ የዎላይታ ብሄር ዘመን መለወጫ የሆነው ጊፋታ በአለም ቅርሰንት በዩኔስኮ እንዲመዘገብ ካደረጉ አካላት መካከል በቀዳሚነት የሚጠቀሱ ናቸው። ህልፈተ ህይወታቸው ለቤተሰቦቻቸው፣ ለዘመድ አዝማዶች፣ ለወዳጅ ዘመዶች እና ለጠቅላላው የዎላይታ ማህበረሰብ ከፍተኛ ሐዘን የፈጠረ መሆኑ ተገልጿል። ​ለሟች ቤተሰቦች፣ ለወዳጅ ዘመዶች እና ለህዝቡ መጽናናትን እየተመኘን፣ የቀብሩ ስነ-ሰርዓት የሚፈጸምበትን ተጨማሪ መረጃዎች መሠረት በማድረግ ዘገባውን እናጠናቅቃለን። https://www.facebook.com/share/1DGbC31XKk/

  • በዎላይታ ሶዶ የፍርድ ቤት ውሳኔ የተሻረው ህገ-ወጥ ግንባታ በሚዲያ ሽፋን ምክንያት ለጊዜው መታገዱ ተገለፀ ​"ግንባታው ለጊዜው ቢታገድም የፍርድ ቤት ውሳኔ አለመከበሩ በዎላይታ ሶዶ ከተማ የህግ የበላይነት ጥሰት ስጋት ፈጥሯል" ሲሉ ነዋሪዎች ቅሬታ አቅርቧል። የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መዲና በሆነቸው በዎላይታ ሶዶ ከተማ፣ መርካቶ ክፍለ ከተማ ፋና ቀበሌ (በዎላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ዋና መግቢያ ፊትለፊት) በህዝብ መተላለፊያ መንገድ ላይ የክልሉን ጠቅላይ ፍርድ ቤት ውሳኔ በመጣስ ይካሄድ የነበረው አነጋጋሪ ግንባታ፣ WT Media ያቀረበውን የምርመራ ዘገባ ተከተሎ ለጊዜው በቃል ትዕዛዝ እንዲታገድ መደረጉን ነዋሪዎች ተናግረዋል። ​WT Media ሰኔ 8 ቀን 2018 ዓ.ም (June 15, 2026) ባስነበበው አጋላጭ ዘገባ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት መዝገብ ቁጥር 68670 በዕለት 27/07/2016 ዓ.ም የዞኑን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ውሳኔ በመሻር፣ ቦታው የህዝብ መተላለፊያ መሆኑን ማረጋገጡንና ህገ-ወጥ የይዞታ ካርታውና ግንባታው እንዲሰረዝ መወሰኑን ይፋ ማድረጉ ይታወሳል። ​ዘገባው ይፋ በሆነ በሁለተኛው ቀን የከተማው አስተዳደር አካላት በቦታው ላይ ተገኝተው ግንባታው ለጊዜው እንዲቆም በቃል ትዕዛዝ አስተላልፈዋል። በተጨማሪም ጉዳዩን በአካል አጣርቶ እልባት የሚሰጥ ኮሚቴ በሳምንት ውስጥ እንደሚዋቀር ተገልጾ የነበረ ቢሆንም የተቀመጠው ጊዜ አልፎ ኮሚቴው ሳይመጣ ቀርቷል። ​የአካባቢው ነዋሪዎች WT Media የህዝብ ድምፅ በመሆን ላደረገው ሽፋን ከፍተኛ ምስጋናቸውን ያቀረቡ ቢሆንም ግንባታው በይፋ በጽሁፍ ደብዳቤ ሳይሆን "በቃል ብቻ" እንዲቆም መደረጉ ግን ከፍተኛ ስጋት ፈጥሮባቸዋል። የማዘጋጃ ቤቱ አመራሮች ህዝቡ እንዲረጋጋ ጊዜ በመግዛት፣ ግንባታውን ድጋሚ ለማስጀመር ይመቻል ያሉትን ሁኔታ እያመቻቹ ሊሆን እንደሚችል ነዋሪዎቹ ይጠረጥራሉ። ​ ​በአካባቢው የተፈጠረው ውዝግብ የማዘጋጃ ቤቱን ጥልቅ የአሰራር ብልሽት እና የጥቅም ግጭት ቁልጭ አድርጎ የሚያሳይ መሆኑን ነዋሪዎች ይናገራሉ። ​ቀደም ሲል የነበረውን የህዝብ መንገድ በመዝጋት የመጀመሪያውን ህገ-ወጥ አሰራር የዘረጉት አካል፣ አሁን ደግሞ ተመልሰው አመራር ሆነው መሾማቸው አሰራሩን ሙሉ በሙሉ ለግል ጥቅም የተጋለጠ አድርጎታል። ​ ከዚህ ቀደም ይኸው ማዘጋጃ ቤት መስጊድ የተነሳበትን ቦታ ለባለሀብት በመሸጥ፣ የማዘጋጃ ቤቱ የሥራ ኃላፊዎች ባገኙት ህገ-ወጥ ጥቅም በሌላ ከተማ መኖሪያ ቤት እስከ መግዛት መድረሳቸውን ነዋሪዎች በምሬት ይገልጻሉ። ​በአሁኑ ወቅት ግንባታው ቆሞ የሚገኝ ቢሆንም፣ "በቃል የተሰጠ እገዳ የነገ ተስፋችንን አይታደግም" የሚሉት ነዋሪዎቹ፦ ​የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የሰጠው የመጨረሻ ውሳኔ በመሬት ላይ ተተግብሮ የተዘጋው መንገድ ሙሉ በሙሉ እንዲከፈት፣ ​በህዝብ መንገድ እና መሬት ላይ ንግድ የሚያካሂዱ የማዘጋጃ ቤት አመራሮች ላይ ተጠያቂነት እንዲሰፍን፣ እንዲሁም ​ዘላቂ እና ህጋዊ ፍትህ እንዲሰጣቸው ጥሪያቸውን አሁንም በምሬት እያቀረቡ ይገኛሉ። ​WT Media የህዝብ ዓይንና ጆሮ በመሆን ይህ የፍርድ ቤት ውሳኔ ተከብሮ የህዝብ መንገዱ ሙሉ በሙሉ እስኪከፈት ድረስ ጉዳዩን በቅርበት መከታተሉን እና ማጋለጡን ይገፋበታል። Read more on our official website 👇https://wolaitatimes.com/?p=8155

  • ዩኒቨርሲቲው ለሁለት ምሁራን ሙሉ የፕሮፌሰርነት ማዕረግ መስጠቱን አስታወቀ። ​ ​የዎላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ አስተዳደር ቦርድ ባደረገው መደበኛ ስብሰባ በህዝብ ጤና (Public Health) የትምህርት ዘርፍ ሲያገለግሉ የቆዩትን ሁለት ምሁራን ዶ/ር ካሳ ዳካ ግዴቦ እና ዶ/ር መንግሥቱ መሥቀሌ ኮይራን ወደ ሙሉ ፕሮፌሰርነት (Full Professorship) ማዕረግ ማደጉን አፅድቋል። ​ዩኒቨርሲቲው ዛሬ ባወጣው ይፋዊ መረጃው እንዳስታወቀው የሁለቱም ምሁራን ማመልከቻዎች ከዲፓርትመንት ጀምሮ እስከ ዩኒቨርሲቲው ሴኔት ድረስ አጠቃላይ እና ጥብቅ ግምገማዎችን አልፈው ለአስተዳደር ቦርድ ለውሳኔ ቀርበዋል። ቦርዱም የትምህርት ዝግጅታቸውን እና ሙያዊ አስተዋጽኦዎቻቸውን በጥልቀት በመገምገም በአዲሱ መመሪያ መሰረት መስፈርቱን ማሟላታቸውን አረጋግጧል። ​ግምገማው ሁለቱም ፕሮፌሰሮች በትምህርትና ትምህርት፣ በምርምርና ህትመት፣ በማህበረሰብ አገልግሎት፣ በቴክኖሎጂ ሽግግር እና በተቋማዊ ልማት ላይ ያበረከቱትን የላቀ አስተዋጽኦ ያወቀ ሲሆን፤ የብቃት ማረጋገጫቸውም በሀገር ውስጥ እና በውጭ ሀገር ገምጋሚዎች ጭምር በአዎንታዊነት መገምገሙ ተገልጿል። ​የምሁራኑ አጭር የህይወት ታሪክና የትምህርት ዝግጅት፦ ​1. ፕሮፌሰር ካሳ ዳካ ግዴቦ (የህዝብ ጤና ፕሮፌሰር) ​የመጀመሪያ ዲግሪያቸውን (BSc) ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ፣ ማስተርስ ዲግሪያቸውን (MPH) ከጅማ ዩኒቨርሲቲ፣ እንዲሁም የዶክትሬት (PhD) ዲግሪያቸውን በህዝብ ጤና ከደቡብ አፍሪካ ዩኒቨርሲቲ በ2013 እ.አ.አ. አግኝተዋል። ​ከ33 ዓመታት በላይ የሙያ ልምድ ያላቸው (15 ዓመታት በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት እና 18 ዓመታት በጤና ስርዓት መሪነት) ሲሆኑ፤ የዎላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ጤና እና ህክምና ኮሌጅ የመጀመሪያ ዋና ስራ አስፈፃሚ (CED) በመሆን አገልግለዋል። ​በዓለም አቀፍ ደረጃ እውቅና ባላቸው መጽሔቶች ላይ ከ50 በላይ ግምገማ የተደረገባቸው ሳይንሳዊ ጽሑፎችን አሳትመዋል። ​ከ41 በላይ በሀገር ውስጥ እና በዓለም አቀፍ ደረጃ የገንዘብ ድጋፍ የተደረገላቸው የምርምር እና የማህበረሰብ አገልግሎት ፕሮጀክቶችን መርተዋል። ​2. ፕሮፌሰር መንግሥቱ መሥቀሌ ኮይራ (የህዝብ ጤና ፕሮፌሰር) ​የመጀመሪያ ዲግሪያቸውን በህዝብ ጤና ከሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ፣ ማስተርስ ዲግሪያቸውን (MPH) ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ፣ እና የዶክትሬት (PhD) ዲግሪያቸውን ከኳዙሉ-ናታል ዩኒቨርሲቲ በ2021 እ.አ.አ. አግኝተዋል። ​ከ18 ዓመታት በላይ የሙያ ልምድ ያላቸው ሲሆን (15 ዓመታት በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ውስጥ) አገልግለዋል። ​በዓለም አቀፍ ደረጃ እውቅና ባላቸው መጽሔቶች ላይ ከ45 በላይ ግምገማ የተደረገባቸው ሳይንሳዊ ጽሑፎችን አሳትመዋል። ​ከ15 በላይ በሀገር ውስጥ እና በዓለም አቀፍ ደረጃ የገንዘብ ድጋፍ የተደረገላቸው የምርምር እና የማህበረሰብ አገልግሎት ፕሮጀክቶችን መርተዋል። ​የዎላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ አስተዳደር ቦርድ ሁለቱም ፕሮፌሰሮች ለምርምርና አካዳሚክ የላቀ ውጤት ላደረጉት አስተዋጽኦ ምስጋና አቅርቦ፤ በቀጣይ ስራቸውም ስኬት ተመኝቶላቸዋል። https://www.facebook.com/share/1HE5ic3Nbr/

  • ​በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በዎላይታ ሶዶ ከተማ የተቀናጀና ዘመናዊ መልክ ያለው ግዙፍ የፋይናንስ ማጭበርበር ወንጀል መፈጸሙ ተሰምቷል። በወንጀል ድርጊቱ ከ500 ሚሊዮን (ግማሽ ቢሊዮን) ብር በላይ የሚገመት የበርካታ ወገኖች ገንዘብ የተበላ ሲሆን ሰለባ ከሆኑት መካከል ታዳጊ ወጣት ነጋዴዎች፣ ታዋቂ ባለሀብቶች፣ የዞን ከፍተኛ አመራሮች፣ የፖሊስ አዛዦች እንዲሁም የመንግሥት የፋይናንስ ዘርፍ ሰራተኞች እንደሚገኙበት ለ WT Media የደረሱ አዳዲስ ማስረጃዎች ያመላክታሉ። ​እንደ ምንጮቻችን ገለጻ የማጭበርበር ድርጊቱ የተካሄደው ከመደበኛው የባንክ አሠራርና ሕግ ውጪ በሆነ መንገድ ነው። ተጠርጣሪዎቹ የሰዎችን ልብ ለማማለልና ከፍተኛ መጠን ያለው ገንዘብ ለመሰብሰብ የተጠቀሙበት ዋነኛ ስልት "በአጭር ጊዜ ውስጥ ከፍተኛ የትርፍ ድርሻ ክፍያ" የሚል የተስፋ ቃል ነው። ​ ተጠርጣሪዎቹ "1 ሚሊዮን ብር ያስቀመጠ ሰው በሳምንት 70 ሺህ ብር (ወይም በወር እስከ 300 ሺህ ብር) የትርፍ ድርሻ ያገኛል" በሚል ማታለያ በርካታ ነጋዴዎችንና ግለሰቦችን ወደ መዋቅሩ አስገብተዋል። ​ለተቀበሉት ገንዘብ ዋስትና በሚል ከባንክ ሲስተም ውጪ የተዘጋጁ ደረቅ ቼኮችን (Unfunded Cheques) ለአስቀማጮቹ ይሰጡ የነበረ ሲሆን መጀመሪያ ላይ ለተወሰኑ ሳምንታት የትርፍ ክፍያዎችን በትክክል በመክፈል የሰዎችን አመኔታ አትርፈዋል። በሂደቱ እምነት ያደሩ በርካታ ግለሰቦች ያሏቸውን ጥሪትና የንግድ እንቅስቃሴ ገንዘብ በሙሉ ወደ መዋቅሩ ያስገቡ ሲሆን ከአንድ ግለሰብ ብቻ ከ2 ሚሊዮን ብር እስከ 30 ሚሊዮን ብር የሚደርስ ገንዘብ መወሰዱ ተረጋገጧል። ​ለ WT Media የደረሱት አዳዲስ ማስረጃዎች በወንጀሉ ሰንሰለት ውስጥ ያሉ ዋና ዋና ተሳታፊዎችን ማንነትና በአሁኑ ወቅት የሚገኙበትን ሁኔታ በዝርዝር ያመላክታሉ። ​ብሩክ እሸቱ (በእስር ላይ የሚገኝ) በማጭበርበር መዋቅሩ ውስጥ ዋና የቼክ አሰራጭና አስተላላፊ ሆኖ ሲሰራ የነበረ ግለሰብ ነው። ለአስቀማጮችና ለደንበኞች "በወር እስከ 300 ሺህ ብር ይከፈላችኋል" በሚል ቼክ የመስጠትና ገንዘብ የመሰብሰብ ሚና እንደነበረው የታወቀ ሲሆን በአሁኑ ወቅት በዎላይታ ሶዶ ከተማ ፖሊስ ጣቢያ በቁጥጥር ስር ውሎ በምርመራ ላይ ይገኛል። ​ዳዊት ሀይለማርያም (ያልተያዘ) ቀደም ሲል የመሉ ወንጌል ቤተክርስቲያን ገንዘብ ያዥ (Treasurer) የነበረ ግለሰብ ሲሆን ከፍተኛ መጠን ያለው ገንዘብ ወደዚሁ ህገወጥ የማጭበርበር አሠራር ማስገበቱ ተገልጿል። ግለሰቡ የፖሊስ አዛዥና ሌሎች ከፍተኛ አመራሮች ወዳጅ እንደሆነ የተጠቀሰ ሲሆን እስካሁን በቁጥጥር ስር እንዳልዋለና በነጻነት እንደሚንቀሳቀስ ምንጮች አረጋግጠዋል። ​ ​ተጠርጣሪዎቹ ከፍተኛ መጠን ያለው ገንዘብ ከሰበሰቡ በኋላ የታቀደውን የትርፍ ክፍያ ማቆማቸውንና ዋና ዋና አስተባባሪዎች መሰወራቸውን ተክተሎ በከተማዋ ትልቅ ውጥረት ነግሷል። ​የምርመራው ሂደት ሊንቀሳቀስ የቻለው የፖሊስ ከፍተኛ አመራሮች ራሳቸው በዚሁ የማጭበርበር ድርጊት የገንዘብ ተጎጂ መሆናቸው ከተረጋገጠ በኋላ እንደሆነ ይነገራል። ​ጉዳዩ ወደ ህግ ከተመራ በኋላ ግን ሂደቱ በሚፈለገው ፍጥነት እየሄደ እንዳልሆነ ተጎጂዎች ይናገራሉ። በወንጀሉ ውስጥ የዞኑ ከፍተኛ አመራሮች፣ የፖሊስ አመራሮች እና የፋይናንስ ዘርፍ ኃላፊዎች ስም በሰፊው በመነሳቱ "ምስጢሩ ይወጣል" በሚል ስጋት በምርመራው ላይ ተጽዕኖ የማሳደርና ሂደቱን የማደናቀፍ እንቅስቃሴዎች መኖራቸው ተጠቁሟል። ​በአሁኑ ወቅት በርካታ አመራሮች፣ ነጋዴዎችና ባለሀብቶች በእጃቸው ምንም ዋጋ የሌላቸው ደረቅ ቼኮችን ይዘው ዋጋ አጥተው ይገኛሉ። ተጎጂዎች ጉዳዩ በዞን ደረጃ ተሸፍኖ እንዳይቀር የፌደራልና የክልል የፍትህና የህግ ማስከበር አካላት በገለልተኝነት ጣልቃ በመግባት የህዝቡን ገንዘብ እንዲያስመልሱና አጥፊዎችን ለፍትህ እንዲያቀርቡ በጥብቅ እየጠየቁ ይገኛሉ። እየተካሄደ ያለውን የህግና የምርመራ ሂደት ላለማደናቀፍ እንዲሁም የህግ ሂደቱን ጥራት ለመጠበቅ ሲባል የገንዘብ ተጎጂ የሆኑ ግለሰቦችን ስም ዝርዝር እና ማስረጃዎችን WT Media ለጊዜው ይፋ ካደረጋቸው መቆጠቡን ያስታውቃል። ተጎጂዎች ጉዳዩ በዞን ደረጃ ተሸፍኖ እንዳይቀር የፌደራልና የክልል የፍትህና የህግ ማስከበር አካላት በገለልተኝነት ጣልቃ በመግባት የህዝቡን ገንዘብ እንዲያስመልሱና አጥፊዎችን ለፍትህ እንዲያቀርቡ በጥብቅ እየጠየቁ ይገኛሉ። በጉዳዩ ላይ አስተያየታቸውን የሰጡ የከተማዋ ነዋሪዎችና ተጎጂዎች "ሕግን ለማስከበር ኃላፊነት ያላቸው አካላት ጭምር በዚህ መንገድ ሕገወጥ ድርጊት ውስጥ ተዘፍቀው የሚገኙ ከሆነ ሕብረተሰቡ ሳያውቅ አሁንም ስንት ዓይነት ወንጀል እየተሠራ ይሆን?" ሲሉ ከፍተኛ ሥጋት እንዳደራባቸው ገልጸዋል። በመሆኑም ሁኔታው በገለልተኝነት እንዲጣራ እና ጥፋተኛ በሆኑት አመራሮችና አካላት ላይ አስፈላጊው ማጣራት ተደርጎ አርአያነት ያለው እርምጃ እንዲወሰድ በጥብቅ እየጠየቁ ይገኛሉ። ​WT Media ይህንን ግዙፍ የፋይናንስ ማጭበርበር ጉዳይ በጥልቀት መከታተሉን የሚቀጥል ሲሆን የከተማዋን ፖሊስ፣ የዞኑን አስተዳደር እና የሚመለከታቸውን የፍትህ አካላት ይፋዊ ምላሽ ለማካተት ጥረት በማድረግ ላይ ነው። Read more on our official website 👇https://wolaitatimes.com/?p=8136

  • ዎላይታ እና ጋሞ የሚያገናኝ ድልድይ ግንባታ በከፍተኛ አመራር ትዕዛዝ መቋረጡ በሕዝብ ዘንድ ከፍተኛ ቁጣ መቀስቀሱ ተነገረ ​ ​በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በዎላይታ ዞን እና በጋሞ ቁጫ መካከል እየተካሄደ የነበረው የደሜ ድልድይ እና የመንገድ ግንባታ በድጋሚ እንዲቋረጥ መደረጉ በአካባቢው ማህበረሰብ ዘንድ ከፍተኛ ቁጣና ቅሬታ መቀስቀሱ ተገልጿል። ​የክልሉ ገጠር መንገድ ባለሥልጣን ፕሮግራም አካል የሆነው ይህ ግንባታ፤ በዎላይታ ዞን በኩል የኪንዶ ዲዳዬ እና የካዎ ኮይሻ ወረዳ ሕዝብን ከጋሞ ዞን ቁጫ አልፋ ወረዳ ሕዝብ ጋር የሚያገናኝ ነው። በተለይም በታሪኩ ለሕዝብ ከሚሰጠው ጥቅም ይልቅ በጉዳቱ የሚታወቀውና በየዓመቱ በቁጥር መገመት የማይቻል የሰው ሕይወትና የቤት እንስሳትን ሲያሰምጥ የነበረው በደሜ ወንዝ ላይ እየተገነባ ያለው ድልድይ ሥራ «በከፍተኛ አመራር ትዕዛዝ» ባልታወቀ ሁኔታ መቆሙን በግንባታው የተሳተፉ አካላት ለ WT Media አረጋግጠዋል። የዚህ መንገድና ድልድይ ግንባታ አጀማመሩና ዋና ዓላማው ሁለቱ የዎላይታ እና የቁጫ ወንድማማቾች ሕዝቦች በማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ መስተጋብሮች እንዲሳሰሩ፣ በደስታም ሆነ በሐዘን አብረው እንዲኖሩ እና በውሃ ሙላት ምክንያት የሚደርሰውን የሰው ሕይወት መጥፋትን ለማስቀረት ታስቦ የነበረ መሆኑን የአካባቢው ነዋሪዎች ይገልጸሉ። ​በሌላ በኩል ይህ አከባቢ «የጥቁር ወርቅ» በመባል የሚታወቀውን የዚሁ አካባቢ አንጡራ ሀብት የሆነውን በርካታ የድንጋይ ከሰል ክምችት እና ሌሎች ማዕድናት የያዘ መሆኑ ይታወቃል። ስለዚህም መንገዱ ለህዝብ አገልግሎት ከመሰጠቱ ባለፈ ለመንግሥት ከፍተኛ ገቢ ለማስገኘት እና ለሥራ አጥ ወጣቶች የሥራ ዕድል ለመፍጠር የጎላ ሚና እንደሚኖረው ታሳቢ ተደርጎ ነበር። ​ ቀደም ሲልም በጋሞ ዞን በኩል በደረሰ ከፍተኛ ጫና እና በተቀነባበረ ሴራ ግንባታው እንዲቆም መደረጉን WT Media ከ8 ወር በፊት ይታወሳል። በወቅቱ በግንባታው ላይ ተሰማርተው የነበሩ ሠራተኞች ከጋሞ ዞን በኩል በደረሰባቸው ማስፈራሪያና ጫና ሥራቸውን ለማቆም ተገደዋል። እንዲያውም ግንባታውን ለማስቆም በታቀደ ሴራ በድንጋይ ላይ «አንድም ሰው በዚህ አካባቢ እንዳይንቀሳቀስ» የሚል ትዕዛዝ በታፔላ ተጽፎ መለጠፉ በሠራተኞቹ ላይ ከፍተኛ የደኅንነት ስጋት መፍጠሩ ተገልጿል። ​ጨረታውን አሸንፎ ወደ ሥራ የገባው Prop Construction PLC የተባለ ተቋራጭ በዎላይታ በኩል ያለውን የቁፋሮ ሥራ አጠናቆ ወደ ቀጣዩ ምዕራፍ ለመሸጋገር ሲሞክር በጋሞ ዞን በኩል በታጣቂዎችና በከፍተኛ አመራሮች ትዕዛዝ ጫናዎች ሲፈጠሩበት ቆይቷል። ዓላማውም ተቋራጩ ተስፋ ቆርጦና ቅድመ ክፍያውን ሳይወስድ ሥራውን ጥሎ እንዲወጣ ለማድረግ የሚደረግ ስልታዊ ጫና መሆኑን ምንጮች አመላክተዋል፤ በዚህም ሠራተኞች ለደኅንነታቸው በመስጋት ሥራ ለቀው መውታታቸው ተሰምቷል። ​ በወቅቱ የዎላይታ ዞን ትራንስፖርትና መንገድ ልማት መምሪያ ኃላፊ አቶ ሳሙኤል አይሳሮ እና የኪንዶ ዲዳዬ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ አበበ ዋኬ ግንባታው መጀመሩን እንደ ታሪካዊ ስኬት ቢገልጹትም በመሬት ላይ ያለው እውነታ ግን ከዚህ በተቃራኒ ሆኖ የክልሉ መንግሥት "ከምርጫው ማግሥት ጠንካራ መንግሥት" በሚል መሪ ቃል የገባቸውን የልማት ኪዳኖች በተግባር ማሳየት እንዳልቻለ አሳይቷል። ​ለበርካታ ዓመታት ታቅዶና ተጀምሮ ሳይሳካ የዘለቀውን ከ15 በላይ ቀበሌያትን የሚያገናኘውን ይህን ወሳኝ ፕሮጀክት አሁንም በፖለቲካዊ ሴራ ማደናቀፍ "ለዎላይታና ለቁጫ ሕዝብ ያለውን ጥላቻና ንቀት በገሃድ ማሳየት ነው" ሲሉ የአካባቢው ነዋሪዎች በብርቱ አውግዘዋል። ​የአካባቢው ነዋሪዎች ይህንን በግፍ የሚፈጸም የልማት ማደናቀፍ ተግባር የፌዴራል መንግሥትና የበላይ አካላት በቅርበት እንዲመለከቱትና ጣልቃ ገብተው እንዲያስቆሙ ጥሪ አቅርበዋል። WT Media በጉዳዩ ዙሪያ ከጋሞ ዞንና ከክልሉ መንግሥት ምላሽ ለማግኘት ያደረገው ጥረት እስካሁን ባይሳካም፣ የግንባታውን ሂደትና የሚፈጸሙ ማናቸውንም ሕገ-ወጥ መሰናክሎች በቅርበት መከታተሉን ይቀጥላል። ​🎙️ ማሳሰቢያ፦ WT Media በተለይ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በመንግሥት ሚዲያዎች ትኩረት ያላገኙ ለተጨቆኑ የሕብረተሰብ ክፍሎች ጉዳይ የቅድሚያ ቅድሚያ የምንሰጥ ሲሆን እውነትን፣ ሀቅንና ፍትሕን መሠረት በማድረግ፣ የመረጃ ሰጪዎችን ምስጢርና ደኅንነት በመጠበቅ በሌሎች ሚዲያዎች የማይሰሙ የጭቁኖች ድምፅ ዘውትር እዚሁ ይሰማልና ስለአብሮነታችሁ ምስጋናችን የላቀ ነው! የእናንተው የጭቁኖች አገልጋይ ነን 🙏 ​Voice of Marginalized Community - WT Media ​#Ethiopia #SouthEthiopia #WTMedia #ደቡብኢትዮጵያ #ዎላይታ #ጋሞ #ቁጫ #ደሜድልድይ Read more on our official website👇https://wolaitatimes.com/?p=8124

  • በአርባ ምንጭ ከተማ የኮሪደር ልማት የነካው ሾፌር 1 ሚሊዮን ብር መቀጣቱ የህግ አፈፃፀም ጥያቄዎችና የተነሳው ከፍተኛ የህብረተሰቡ ቅሬታ ​በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል አርባ ምንጭ ከተማ የኮሪደር መብራት በመግጨቱ ምክንያት በታደሰ ተሰማ የተባለ የሀዋሳ ሞሐ ለስላሳ መጠጥ ፋብሪካ ሾፌር ላይ የተጣለው ከፍተኛ የገንዘብ ቅጣት እና የህግ አፈፃፀም ሂደት በከተማዋ እና በማህበራዊ ሚዲያዎች ከፍተኛ አወዛጋቢ ሆኖ መቀጠሉ ተገልጿል። ከሰሞኑ በተከሰተው በዚህ ድርጊት ሾፌሩ ለስላሳ ጭኖ ወደ ከተማዋ ገብቶ በነበረበት ወቅት የኮሪደር መብራት መግጨቱ ታውቋል። ከተፈጠረው አደጋ ጋር ተያይዞ መጀመሪያ ላይ የሁለት መቶ ሺህ (200,000) ብር ቅጣት ተወስኖ የነበረ ቢሆንም የፋብሪካው ፋይናንስ ኃላፊ ቅጣቱን ለመክፈል ሲሄድ "ደረሰኝ አልቋል" በሚል ምክንያት ግለሰቡ በእስር ላይ እንዲቆይ መደረጉን WT Media ከተደበዳይ ቤተሰብ ያገኘው መረጃ ያመለክታል። ጉዳዩን አስመልክቶ የከተማው አስተዳደር በሰጠው ማብራሪያ በሂደት ላይ በነበሩ የህግ ማጣሪያዎች እና ቀጠሮዎች ምክንያት መቆየቱን የገለጸ ሲሆን በመጨረሻም ግለሰቡ ፩ ሚሊዮን (1,000,000) ብር በመክፈል ከእስር መፈታቱን አረጋግጧል። ይህንን ጉዳይ አስመልክቶ በማህበራዊ ሚዲያ እና በህዝብ ዘንድ በተደረጉ ውይይቶች በርካታ ጥያቄዎች እና ትችቶች መሰንዘሩን WT Media ተመልክቷል። ​ከተፈጠረው ትክክለኛ ጉዳትና አደጋ አንጻር መጀመሪያ ሁለት መቶ ሺህ ብር ተብሎ የነበረው ቅጣት በድንገት ወደ አንድ ሚሊዮን ብር ከፍ ማለት ጥያቄን የፈጠረ ሲሆን ይህ አሰራር ዜጎችንና ተቋማትን ለመቅጣት እና ለማስፈራራት ምቹ ሁኔታን የሚፈጥር እንጂ ፍትሃዊ አይደለም የሚሉ ሃሳቦች ተነስተዋል። ​ግለሰቡ ጥፋቱን አምኖ ቅጣቱን ለመክፈል ፈቃደኛ ሆኖ ሳለ "ደረሰኝ አልቋል" በሚል ሰበብ ብቻ ለሳምንታት በእስር እንዲቆይ መደረጉ እና ጉዳዩ ወደ ማህበራዊ ሚዲያ ሲወጣ ውሳኔዎች በፍጥነት መለወጣቸው የህግ ሂደቱን ገለልተኛነት ጥያቄ ውስጥ እንደሚከተው ተመላክቷል። ​ማንኛውም ህግ የጣሰ አካል በህግ አግባብ መጠየቅ እንዳበት የሚስማሙት አስተያየት ሰጪዎች የህግ አተገባበሩ ግን ከግል ግፊት፣ ከማዋከብ እና ከማጉላት የጸዳ መሆን እንዳለበት አጽንኦት ሰጥተዋል። ​ በአርባ ምንጭ ከተማ የተከሰተው የኮሪደር መብራት አደጋ እናይን ተከትሎ የተወሰደው የቅጣት እርምጃ እንዲሁም የሂደቱ አካሄድ በህብረተሰቡ ዘንድ ከፍተኛ ውዝግብና ስጋት ማስነሳቱ የህግ አተገባበርን ፍትሃዊነትና ግልጽነት ጥያቄ ውስጥ ከትቶታል። ​ከተፈጠረው ትክክለኛ ጉዳት አንጻር መጀመሪያ ተወስኖ ከነበረው የገንዘብ ቅጣት መጠን በድንገት ወደ አንድ ሚሊዮን ብር ከፍ ማለት እንዲሁም "ደረሰኝ አልቋል" በሚል ሰበብ ብቻ ዜጎች ለሳምንታት በእስር እንዲቆዩ መደረጉ አሰራሩ አድሎአዊና ግለሰቦችን ለማዋከብ የተመቻቸ መሆኑን የሚያሳይ ስጋት ፈጥሯል። ​በአጠቃላይ ህግና ስርዓት ሲከበር ከማንኛውም ግፊት ግልጽ ከልዩነት እና ከግል ጫና የጸዳ መሆን እንዳለበት የህብረተሰቡ አስተያየት በግልጽ ያሳያል። የህግ አካላትም ሆኑ የከተማዋ አስተዳደር ፍትሕን ከማስፈን አንጻር ሚዛናዊ፣ ግልጽ እና ተጠያቂነት ያለው አሰራርን ሊከተሉ እንደሚገባ ህዝቡ አበክሮ አሳስበዋል። https://wolaitatimes.com/?p=8118

  • በድቅድቅ ጨለማ ውስጥ ያለ ህዝብ፡ በቁጫ እና በዘይሴ ማህበረሰብ ላይ የተፈጸሙ ስልታዊ የሰብአዊ መብት ጥሰቶች እና የምርጫ አፈና በኢትዮጵያ የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ እና የሰላማዊ ትግል ምህዳር ላይ ከባድ ጥያቄዎችን የሚያስነሳው የሰባተኛው ሀገራዊ ምርጫ መጠናቀቅን ተከትሎ የቁጫ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ቁሕዴፓ) ፕሬዝዳንት ረዳት ፕሮፌሰር ገነነ ገደቡ ከሚዲያ ጋር ቆይታ አድርገዋል። በዚሁ ቆይታቸው ባለፉት አምስት ዓመታት ውስጥ በዘይሴ እና በቁጫ ሕዝብ ላይ የደረሱ መዋቅራዊ ጥቃቶችን፣ የምርጫ ሂደቱን አሰቃቂ ግፎች እና የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ላይ የሚታዩ ከባድ ክፍተቶችን በሰፊው ገልጸዋል። 📌 ዋና ዋና ነጥቦች፦ በቁጫ ምርጫ ክልል ውስጥ የነበሩ የፓርቲ ተሳትፎ ቤቶች ሙሉ በሙሉ እንዲፈርሱ ተደርገው፣ ንብረቶቻቸው መውደማቸው እና የአባላት መታወቂያዎች በአደባባይ እንዲቃጠሉ መደረጉ። አባላት በሻይ ቤት መቀመጥ፣ ገበያ መግባት ወይም መሰረታዊ መብቶቻቸውን መጠቀም እንዳይችሉ ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ማዕቀብ መጣሉ፤ አዛውንቶች ጭምር ከቀያቸው ተፈናቅለው ጎዳና ላይ መውደቃቸው። የቁጫ ህዝብን ወክለው የተንቀሳቀሱት ፕሬዝዳንቱ በክላሽኒኮቭ መሳሪያ ተደቅኖባቸውና በየመንገዱ ታግተው ከባድ እንግልት እንደደረሰባቸው። ጥቃት የፈጸሙ አካላት በህግ ቁጥጥር ስር እንዳይውሉ የክልል መዋቅሮች ጣልቃ መግባታቸው። #Zeyse #ZeyseGenocide #WTMedia #Ethiopia #GamoZone #HumanRights #የዘይሴ # 🔗 ሙሉውን ዜና ለማንበብ👇 https://wolaitatimes.com/?p=8107

  • የደቡቧ ሆርሙዝ፦ ዎላይታ ሶዶ! (የምጣኔ ሀብት እና የጂኦፖለቲካል ማዕከል) ​ዎላይታ ሶዶ ባለሰባት በር ናት ስንል ለማውራት ብቻ አይደለም። ዎላይታ ለብዙ አዋሳኝ ዞኖች እንዲሁም ለማዕከላዊ መንግስት መቀመጫ ቅርብና ማዕከል ናት ስንል የዎላይታ ካድሬ ተሰባስቦ የወሰኑትና የሰጡት ሳይሆን ፈጣሪ የቸራት የደቡቧ ሆርሙዝ ናት። ​በዚህ አካባቢ የሚሰራው የልማት ሥራ ለዎላይታ ብቻ ሳይሆን ለመላው ጎረቤት ህዝብ ጭምር ነው። የወላይታ ልማት ሲዳከም የጎረቤት ዞኖች ልማት ይዳከማል። ለምሳሌ፦ ​የዎላይታ-ጂንካ መንገድ መስተጓጎል ታታሪው የጎፋ፣ የአሪና ባስኬቶ እንዲሁም የቁጫ ህዝብ የሚያመርተው ሰሊጥ፣ ቡናና ቅመማ ቅመም ዝውውር ላይ ተፅዕኖ ይፈጥራል። ​ወደ ግቤ 3 ያለው መንገድ ሲስተጓጎል የዳውሮና ኮንታ ህዝብ የሚያመርተው ብራንድ ቅቤና ማር እንዲሁም ፍራፍሬ ምርቶች ይጎዳሉ። ​ከዎላይታ-ደቡብ ኦሞ መንገድ ልማት ሲስተጓጎል የኮንሶ፣ ኮሬ፣ ጋርዱላና ቡርጂ ማኛ ጤፍና ቡላ እንዲሁም ከደቡብ ኦሞ፣ ኮንሶና አሌ ኤክስፖርት የሚደረገው የፍየልና የበግ ሙክቶች፣ የጥጥ ምርት እና የጨንቻ አፕል ዝውውር ይስተጓጎላል። ​ከዚህ በተጨማሪ ዎላይታ ለሀላባ በርበሬ፣ ለካምባታና ጣንባሮ ቡናና ቆጮ፣ ለሀዲያው ስንዴና ጤፍ ምርት ትልቅ ገበያ ማዕከል ሆና የምታገለግል ትክክለኛ የደቡቧ ሆርሙዝ ናት ስንል ለዚህ ሁሉ ማዕከልና መተላለፊያ እንዲሁም የገበያ ዕድል በመሆኗ በዎላይታ ምድር የሌለ ነገር የምንለው በምክንያት ነው። ​ ​ከዚህ ባሻገር ዎላይታ ለኢንዱስትሪ ግብዓት የሚሆኑ ምርቶችን በከፍተኛ ሁኔታ በማምረት ለውጭ ገበያ ጭምር ኤክስፖርት የምታደርገው ቀይ የዎላይታ ቦሎቄ፣ ቡናና ቅመማ ቅመም፤ ለዘይት ምርት የሚሆን የጋሌ፣ የወይዴ፣ የስሶሬና የሆቢቻ አቮካዶ፣ እንዲሁም በሁሉም ወረዳዎች በስፋት እየተመረተ ገበያን ያረጋጋው ጣፋጭ ሙዝ፣ ማንጎ እና ፓፓያ በከፍተኛ ሁኔታ ይመረቱባታል። ​ከእንስሳትና ዓሳ ሀብት አኳያ ከዋዱ ጊዜ ጀምሮ በተሰራው ሥራ ከፍተኛ የሆኑ ዝርያቸው የተሻሻሉ ከ38 ሊትር በላይ ወተት የሚሰጡ ላሞች አሉ። በዎላይታ ሶዶ ከተማ ብቻ በአንድ ቤት ውስጥ ከ20 በላይ የወተት ላሞች በመኖራቸው የወተት ምርት በስፋት የሚመረት ሲሆን፣ የቁርጥ ሳንጋዎችን ማየት ይቻላል። ​የአባላና ሁምቦ እንዲሁም የኦፋና ኮይሻ የፍየል ቱማሌሳዎች፣ የዶሮ ስርጭትና ምርት ሲታይ፣ በቀድሞው ክልልም ሆነ በአሁኑ ወቅት ከፍተኛ የዶሮ ስርጭት ይገኛል። የዋዱ ዶሮ እርባታ ማዕከል ያለበት በመሆኑ ለየት ያሉ «የዎላይታ ዶሮዎች» ተብሎ በልዩነት የሚታወቁ ጣፋጭ ሥጋ ያላቸው ዶሮዎችና የዶሮ ምርቶች ይገኙበታል። ከዓሳ ሀብት አንጻር ትልቁ ኦሞ ወንዝ በግቤ 3 ግድብ ምክንያት ሐይቅ በመሆኑ ከ120 ኪሎ ግራም በላይ የሚመዝኑ የናይል ፓርች (አባያ ሐይቅ የሚወጣ ልዩ ጣዕም ያለው)፣ እንዲሁም ብላቴ፣ ሐመሳ እና ሌሎች የውሃ አካላት ሀብቶች በስፋት ይገኛሉ። ​ ​በአጠቃላይ ዎላይታ ሶዶ ለቀጠናው ያላት ጂኦፖለቲካዊ እና ኢኮኖሚያዊ ቁመና ከማዕከልነት የዘለለ ለጎረቤት ዞኖች ሁሉ ሕልውና እና ዕድገት ወሳኝ የደም ዝውውር ናት። የአካባቢው የንግድ፣ የትራንስፖርት፣ የግብርና እና የኢንዱስትሪ አቅም ማዕከል መሆኗ የደቡቧ «ሆርሙዝ» የሚያሰኛትን ታሪካዊ እና ተፈጥሯዊ ጸጋ በጉልህ ያሳያል። ስለዚህ የዚህችን ከተማ እና አካባቢ ሰላም፣ ልማት እና መሠረተ ልማት መጠበቅና መጠየቅ ለመላው አዋሳኝ ህዝቦች የጋራ ህልውና ቅድሚያ የሚሰጠው ጉዳይ ነው። https://wolaitatimes.com/?p=8104

  • በመከላከያ ሠራዊትና በትግራይ የጸጥታ ኃይሎች መካከል ተጀመረ የተባለው ውጊያ መቆሙ ተገለፀ በመከላከያ ሠራዊትና በትግራይ የጸጥታ ኃይሎች መካከል ሸረሪና በተባለ ቦታ ተጀመረ የተባለው ውጊያ መቆሙን የፈረንሳይ ዜና አገልግሎት ማንነታቸው ያልተገለጸ የመረጃ ምንጮች ዋቢ አድርጎ ዘግቧል። ከኢትዮጵያና ሱዳን ድንበር አቅራቢያ በሚገኘው ሸረሪና የተባለ ቦታ ውጊያ የተቀሰቀሰው ትላንት ቅዳሜ ከማለዳው 12 ሰዓት ገደማ እንደሆነ አንድ ስማቸው ያልተገለጸ የህወሓት አባል መናገራቸውን የዜና ወኪሉ ዘግቧል። በከባድ የጦር መሣሪያ እና በድሮን ጭምር የተደረገው ውጊያው ከ23 ሰዓታት ገደማ በኋላ እንደቆመ የፈረንሳይ ዜና አገልግሎት ዋቢ ያደረጋቸው የመረጃ ምንጭ ተናግረዋል። በግጭቱ ምን ያክል ሰዎች እንደተገደሉ ወይም እንደቆሰሉ መረጃ ከመስጠት ተቆጥበዋል። ስማቸው እንዳይገለጽ የጠየቁ ሌላ የጸጥታ የመረጃ ምንጭ በእርግጥም ውጊያው እንደቆመ ለፈረንሳይ ዜና አገልግሎት ተናግረዋል። ይሁንና ከህወሓት በኩል የቀረበው መረጃ ትክክለኛ መሆኑን በገለልተኝነት እንዳላረጋገጠ የፈረንሳይ ዜና አገልግሎት በዘገባው ጠቁሟል። በኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በተሰረዘው ህወሓት የሚመራው የትግራይ ክልላዊ መንግሥት ትላንት ቅዳሜ ባወጣው መግለጫ የኢትዮጵያ ፌድራል መንግሥት ከማለዳ ጀምሮ በሸረሪና በኩል ውጊያ ጀምሯል በማለት ወንጅሎ ነበር። የፌድራል መንግሥት ግን ስለ ጉዳዩ በይፋ የሰጠው ማብራሪያም ሆነ ምላሽ የለም። ይሁንና የመስኖ እና ቆላማ አካባቢ ሚኒስትሩ አብርሀም በላይ በተረጋገጠ የፌስቡክ ገጻቸው ባሠፈሩት ጽሁፍ ህወሓትን በሸረሪና በኩል ጦርነት በመክፈት ወንጅለዋል። በኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊትና በትግራይ የጸጥታ ኃይሎች መካከል ሐምሌ 25 ቀን 2018 ውጊያ መቀስቀሱ የተሰማው በአዲስ አበባና በመቐለ በሚገኙ ባለሥልጣናት መካከል ያለው ውጥረት በኃይል በተባባሰበት ወቅት ነው ሲል ዶቼቬሌ ዘግቧል። https://www.facebook.com/share/p/1FCNMQXge4/

  • በሳውዲ አረቢያ እስከ 200 የሚደርሱ ኢትዮጵያውያን ዜጎች የተበየነባቸውን የሞት ፍርድ አፈፃፀም በመጠበቅ ላይ እንደሚገኙ ተነግሯል። ይህም በሳውዲ አረቢያ በስደት ላይ በሚገኙ የውጭ ሀገር ዜጎች ላይ የሚሰጠው የሞት ፍርድ ውሳኔ በከፍተኛ ሁኔታ መጨመሩን የሚያሳይ ሆኗል። https://wolaitatimes.com/?p=8096

  • በኢትዮጵያ የሀገር ውስጥ ችግር ለመፍታት "ጦርነት ብቸኛው መፍትሔ ነው" ብለው የሚያስብ ትውልድ የሚያበቃው መቼ ነው?

  • የቀድሞ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ የCGIAR የመጀመሪያው የቦርድ ሊቀመንበር ሆነው ተሾሙ ​የቀድሞ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ ቦሼ በዓለም አቀፍ ደረጃ ትልቁ የግብርና ምርምር ጥረት ተቋም የሆነው CGIAR (Consultative Group on International Agricultural Research) አዲስ የተቋቋመው የቦርድ የመጀመሪያ ሊቀመንበር ሆነው መሾማቸው ተገልጿል። ሹመቱ እ.ኤ.አ. ከነሐሴ 1 ቀን 2026 ጀምሮ የፀና ይሆናል። ​የCGIAR የአስተዳደር ኮሚቴዎች ላለፉት ስድስት ወራት ሲያካሂዱት በቆዩት ጥብቅ የምልመላ እና የእጩነት ሂደት የተመረጡት አቶ ኃይለማርያም ተቋሙ በምግብ ዋስትና፣ በግብርና ምርታማነት፣ በቃለ-አየር ለውጥ የመቋቋም አቅም እና በተፈጥሮ ሀብት እንክብካቤ ዙሪያ በሳይንስ ላይ የተመሰረቱ መፍትሄዎችን ለማስፋፋት የሚያደርገውን ስትራቴጂካዊ መሪነት በበላይነት ይመራሉ። ​ተቋሙ እንደገለፀው አቶ ኃይለማርያም በግብርና ፖሊሲ ማሻሻያ፣ በባለብዙ ወገን የኮንፈረንስ ድርድሮች እና በምርምር ላይ በተኮረሱ ተቋማዊ አመራሮች ላይ ያላቸውን ሰፊ ልምድ ወደ አዲሱ የኃላፊነት ቦታ ይዘው ይመጣሉ። ​የስልጣን ዘመናቸውን ያጠናቀቁት እና የቀደመው የCGIAR ቦርድ ሊቀመንበር ፕሮፌሰር ሮኤል መርክስ (Prof. Roel Merckx) ለሹመቱ ያላቸውን ደስታ በመግለፅ፤ "ይህ ለCGIAR እጅግ አስፈላጊ አጋጣሚ ነው። አዲሱ ቦርድ በጥሩ ሁኔታ የተዋቀረ ሲሆን፣ ክቡር ኃይለማርያም ደሳለኝ ቦሼ በሊቀመንበርነት እንዲመሩት በመደረጉ እጅግ ደስተኛ ነኝ። እሳቸው በሳይንስ ላይ የተመሰረተ የግብርና ልማት ላይ ያላቸው ልምድ እና ቁርጠኝነት ለዚህ ቦታ እጅግ ተስማሚ ያደርጋቸዋል" ብለዋል። ​ቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ ከስልጣን ከወረዱ በኋላም በሀገር ውስጥ እና በዓለም አቀፍ ደረጃ በግብርና፣ በአየር ንብረት ለውጥ እና በተቋማት ግንባታ ዙሪያ ያሳዩት ቁርጠኝነት እና ሙያዊ አገልጋይነት በአርአያነት የሚጠቀስ እንደሆነ በርካቶች ምስክርነታቸውን በመስጠት ላይ ይገኛሉ። https://www.facebook.com/share/1Api6xyvBT/

  • የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በሟች ታዋቂው ተጫዋች አለልኝ አዘነ መዝገብ ላይ ትዕዛዝ ሰጥተዋል። ​በታዋቂው አለልኝ አዘነ የግድያ መዝገብ ላይ የፍትሕ ሂደቱ አዲስ ምዕራፍ ይዟል! ​ከዚህ ቀደም በጋሞ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት በሰውና በሰነድ ማስረጃዎች ተረጋግጦባቸው የ16 እና 15 ዓመት ፅኑ እስራት ተፈርዶባቸው የነበሩት የሟች ባለቤት ወ/ሮ አደይ ጌታቸው እና የእህቷ ባለቤት ሉንጎ ሉቃስ በይግባኝ ሰሚው ችሎት ሙሉ በሙሉ በነፃ እንዲሰናበቱ መወሰኑ ይታወሳል። ይህ ውሳኔ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ማህበረሰብን፣ የሟች ቤተሰቦችን እና ፍትሕ ናፋቂዎችን በእጅጉ ያሳዘነና በፍትሕ ሥርዓቱ ላይ ጥያቄ ያስነሳ መሆኑ በወቅቱ በሰፊው ተዘግቦ ነበር. ​ይሁን እንጂ ጉዳዩን ይዞት የቆየው የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በሰበር መዝገብ ቁጥር 010926 (ቀን 09/11/2018 ዓ.ም) ባሰፈረው ሐሳብ እና በሰጠው የፍሬ ትዕዛዝ፣ መዝገቡ ተጨማሪ ምርመራ እና ማጣራት እንዲደረግበት መወሰኑን አዳዲስ የፍርድ ቤት ሰነዶች ለ WT Media አረጋግጠዋል። ​ ​የፍርድ ቤቱ ሰነዶች እንደሚያመለክቱት፣ በቀድሞው የፍርድ ሂደት ውስጥ የሚከተሉት ነጥቦች በድጋሚ ሊመረመሩ እንደሚገባ ታዟል። ​መዝገብ ውስጥ መገኝት የሚገባው መረጋገጥ የሚገባው ድምፅ መኖሩ፣ የአርሶ አደር ምስክርነት ቃል የተሰጠበት ሁኔታ፣ እና ከሶስተኛ ወገን ወንጀል ጥፋተኛ የመሆን አለመሆን ጉዳይ። የዶክተር የምርመራ ውጤት እንደየሁኔታው ሊመረመር እንደሚገባ፣ እንዲሁም በእያንዳንዱ አካባቢዊ ማረጃ ቃል ላይ ጥርጣሬ የተፈጠረ በመሆኑ የፓቶሎጂ ወይም የአካባቢዊ ማረጃ ኘሩፍ አመጣጥ ሥርዓት ሕግ አግባብ በድጋሚ መታየት እንዳለበት ተመልክቷል። ​ሰበር ሰሚ ችሎቱ ጉዳዩን በጥልቀት ለመመርመር ያስችል ዘንድ ​መልስ ሰጪዎች (ተጠሪዎች) ለቀረበው የሰበር አቤቱታ የሚሰጡትን መልስ በጽሁፍ አዘጋጅተው ከፍ/ቤት መፃፍ ጋር እንዲያቀርቡ አዟል። ​ለዚህም መከላከያ መልስ ለመስጠት የችሎቱ ቀነ-ቀን 23/11/2018 ዓ.ም ተቆርጧል፤ ተጠሪዎችም በዕለቱ ላልተዘጋጀው መልስ በጽሁፍ አዘጋጅተው ለአርባ ምንጭ ለሚገኘው ተከታይ ችሎት እንዲያቀርቡ ተወስኗል። ​የሟች ቤተሰቦች ከዚህ ቀደም ለ WT Media በሰጡት ቃል፣ ወንጀሉ የተፈፀመበት ቦታ አርባ ምንጭ ሆኖ ሳለ የፍርድ ሂደቱ አግባብ ባልሆነ መንገድ ወደ ዎላይታ ሶዶ እንዲዛወር መደረጉ ለዚህ ውዛግብ መነሻ መሆኑን በዕንባ ገልጸው ነበር። በተለይም በጥፋተኝነት ተፈርዶባት በነበረችው በአደይ ጌታቸው ጀርባ የወቅቱን የክልሉን ባለስልጣናት የዝምድና ትስስር እና ስልጣን በመጠቀም ፍርዱን ለማዛባት ሲሸረብ የነበረው ሴራ የንብረት ባለቤትነት ክሶችን ጭምር ለማደናቀፍ የታለመ እንደነበር ቤተሰቡ በምሬት ይናገራል። ​በአሁኑ ወቅት የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት ያስቀመጠው አቅጣጫ እና የሰጠው ትዕዛዝ መዝገቡ በድጋሚ በህግ ማዕቀፍ ውስጥ ተፈትሾ እውነተኛው ፍትሕ እንዲሰፍን የሚያስችል ተስፋ የሰነቀ ቢሆንም የሟች ቤተሰቦች እና መላው የስፖርቱ ማህበረሰብ የጉዳዩን ሂደት በጥንቃቄ እየተከታተሉት ይገኛሉ። Read more on our official website 👇https://wolaitatimes.com/?p=8087

  • ​በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎችን ሕይወት የነጠቀው የኦቶና ሆስፒታል ዳግም ግንባታ መጀመሩ ቢገለፅም ፕሮጀክቱ መቼ ይጠናቀቃል? ​ከዓመት በፊት በእሳት አደጋ የወደመውና ከሦስት ሺህ በላይ አቅመ-ደካሞችና አርሶ አደሮች ለከፍተኛ የጤና እክልና ሕልፈተ ሕይወት መዳረጉ የሚነገርለት የታሪካዊው የዎላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ኮምፕረሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል (ኦቶና ሆስፒታል) ዳግም ግንባታ ውል ዛሬ ሐምሌ 23 ቀን 2018 ዓ.ም በይፋ መፈረሙ ተገልጿል። ​ከአንድ ወር በፊት WT Media ከባለሥልጣናት ባገኘው መረጃ የሆስፒታሉ ዳግም ግንባታ እንቅስቃሴ እንደሚጀመር ማጋራቱ ይታወሳል። ዛሬ ላይ ግንባታው መጀመሩ አዎንታዊ እርምጃ ቢሆንም የኅብረተሰቡ ድምጾች እንደሚያሳዩት ጅምሩ ብቻውን በቂ አይደለም። እንደ ከተማው አስፋልት መንገዶች እና ሌሎችም በአከባቢው መሠረተ ልማቶች ለዓመታት ተጀምረው በመጓተታቸው ከፍተኛ እንግልት እንደፈጠሩ ሁሉ የኦቶና ሆስፒታልም “ተጀመረ” በሚል ብቻ ለአመራሮች የጉብኝት ማዕከል ሆኖ እንዳይቀረድ ሥጋት አለ። ​የዎላይታ ውኃ ሥራዎች ኮንስትራክሽንና ጠቅላላ ሥራ ተቋራጭ ከዎላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ጤና ሳይንስና ሕክምና ኮሌጅ ኮምፕረሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል (ኦቶና ሆስፒታል) ጋር ከግማሽ ቢሊዮን ብር በላይ በሚወጣ በጀት ፕሮጀክቱን ለማከናወን ውል ተፈራርመዋል። ​የዎላይታ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ረዳት ፕሮፌሰር ሳሙኤል ተሰማ በበኩላቸው በእሳት አደጋ የተስተጓጎለው የሆስፒታሉ አገልግሎት በፍጥነት እንዲመለስ ፕሮጀክቱ ወሳኝ ሚና እንደሚጫወት ገልጸዋል። ​በተጨማሪም የኮንስትራክሽን ድርጅቱ ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ ሀብታሙ ፋንታ በይፋዊ ማህበራዊ ገጻቸው ባስተላለፉት መልእክት፤ «ኦቶና ሆስፒታል ታርካዊነቱን ጠብቀን ጥራትን አሻሽለን ለህዝባችን በአጭር ግዜ አጠናቀን ዳግም ብሥራተ እናደርጋለን» በማለት የቁርጠኝነት መግለጫ አጋርተዋል። ​🔗 ሙሉውን ዝርዝር ዜና ከ WT Media official Website ያንብቡ 👇 https://wolaitatimes.com/?p=8077 ​#WTMedia #OtonaHospital #Wolaita #Ethiopia

  • የተጀመሩ ፕሮጀክቶች መዘግየት፣ የኦቶና ሆስፒታል ውድመትና ለኮሪዴር ተብሎ የተቆፈሩ መንገዶች በነዋሪዎች የእለት ዕለት ኑሮው ላይ ከፍተኛ ጉዳት እያደረሰ ስለመሆኑ ተገለፀ። ​የዎላይታ ሶዶ ከተማ የታሪክ፣ የባህል፣ የንግድና የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ዋና ማዕከል መሆኗ ቢታወቅም በአሁኑ ወቅት በከተማዋ እየታዩ ያሉ የልማት ሥራዎች መስተጓጎልና መዘግየት የከተማዋን ነዋሪዎች በእጅጉ እያሳሰበ ይገኛል። ከተማዋ ወደፊት መራመድ ሲገባት በተጀመሩና በተንቀራፈፉ ፕሮጀክቶች ምክንያት ወደ ኋላ እየተሳበች ትገኛለች የሚሉ ቅሬታዎች ይሰማሉ። ​ከተማውን ከተደቀነባት የልማት ማነቆ ለማውጣት አስቸኳይ ምላሽ የሚያሻቸው ሦስት አንገብጋቢ ጉዳዮች በነዋሪዎች ዘንድ ተነስተዋል። ​ለከተማዋ ብቻ ሳይሆን ለመላው የአካባቢው ሕዝብ ዋነኛ የጤና ጋሻ በመሆን ከ1920 ዓ.ም ጀምሮ አገልግሎት እየሰጠ የነበረው ትልቁ የመንግሥት ሆስፒታል በድንገተኛ እሳት አደጋ ጉዳት ከደረሰበት ቆይቷል። በወቅቱ በፍጥነት ይጠገናል ተብሎ ቃል ቢገባም በተግባር ግን ዛሬም ድረስ ሙሉ በሙሉ አገልግሎት በሚያስችል ደረጃ አልተገነባም። ​ይህ መዘግየት በተለይም የጤና መድህን ተጠቃሚ በሆኑ አርሶ አደሮችና ቤተሰቦቻቸው ላይ ከፍተኛ ሰብዓዊ ቀውስ እያስከተለ ይገኛል። የሆስፒታሉ መልሶ አለመገንባትና የአገልግሎት መቋረጥ አቅመ-ደካሞችና አርሶ አደሮች ተገቢውን ሕክምና በሰዓቱ እንዳያገኙ በማድረጉ ሳነሳ ለከፍተኛ የሞት አደጋ እየተጋለጡ ይገኛሉ። ሆስፒታሉ በአስቸኳይ ተገንብቶ ለአገልግሎት ክፍት እንዲደረግ ነዋሪዎች ለ WT Media በሰጡት አስተያየት ላይ ጠይቀዋል። ​የከተማውን የትራፊክ ፍሰት ከማሳለጥም ባሻገር ለከተማው የውበት መገለጫ መሆን የሚገባው ከሌዊ ሪዞርት እስከ ዎላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ድረስ ያለው ዋነኛ የከተማ ውስጥ መንገድ ከተጀመረ ረጅም ጊዜ ተቆጥሯል። ፕሮጀክቱ በተንቀራፈፈ ጉዞው ምክንያት የንግድ እንቅስቃሴን ከማስተጓጎሉም በላይ በነዋሪው፣ በተማሪውና በትራንስፖርት ዘርፉ ላይ ከፍተኛ እንግልት እየፈጠረ ይገኛል። ለአመታት ተጓትቶ እስካሁን ባለማለቁ በኅብረተሰቡ ዘንድ ዘርፈ-ብዙ ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጉዳቶች እየደረሱ ይገኛሉ። ​ ​ከተማን ማዘመንና የኮሪደር ልማትን መሥራት መልካም ቢሆንም በየአቅጣጫው መንገዶችን ቆፍሮና አፍርሶ ያለ አንዳች መፍትሔ ማስቀመጥ ከተማዋን ወደ ፍርስራሽና አቧራ ቀጠና እየቀየራት ይገኛል። የተቆፈሩት መንገዶች በአስቸኳይ ተሠርተው ካላለቁ በቀር ልማቱ የነዋሪውን የዕለት ተዕለት ሕይወት የማስተጓጎል ሰበብ እየሆነ መምጣቱ ይነገራል። ​የዎላይታ ሶዶ ከተማ ነዋሪዎች የገባችበትን የልማት መቀዛቀዝ ቆም ብሎ በመፈተሽ እነዚህን የቆዩ ፕሮጀክቶች በአስቸኳይ ወደ ማጠናቀቂያው እንዲደርሱ የሚመለከታቸው አካላት ጥብቅ ምላሽ እንዲሰጡ ጥሪ እያቀረቡ ይገኛሉ። Read more on our official website 👇https://wolaitatimes.com/?p=8072

  • ሀገራዊ ምርጫ አስፈፃሚዎች የሥራና የትርፍ ሰዓት ክፍያ እስከ አሁን ባለመከፈሉ ተቃውሞ መግጠሙ ተገልጿል። ​የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በግንቦት ወር 2018 ዓ.ም ባካሄደው 7ኛው አጠቃላይ ምርጫ ላይ ተሰማርተው የነበሩ የምርጫ አስፈፃሚዎችን ክፍያ እስከ አሁን ባለመክፈሉ በሰራተኞች ዘንድ ከፍተኛ ቅሬታ መቀስቀሱን የደረሰን መረጃ ያመለክታል። ​ምርጫ ቦርድ የገባውን ውል በመጣስ እስካሁን ካልከፈላቸው ክፍያዎች መካከል ​የ60% ቀሪ ክፍያ፣ ​የሥልጠና ጊዜ ክፍያ እና ​በምርጫው ዕለት እስከ ሌሊቱ 6:00 ሰዓት ድረስ ለተሰራበት የትርፍ ሰዓት ክፍያ የሚገኙበት መሆኑንም ተበዳዮች ቅሬታ አቅርበዋል። ቦርዱ እነዚህን ክፍያዎች ምርጫው ከተጠናቀቀበት ከግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ሰኔ 15 ቀን 2018 ዓ.ም ባሉት ቀናት ውስጥ በውሉ መሠረት እከፍላለሁ ብሎ እንደነበር አስረድተዋል። ​ይሁን እንጂ እስከ ዛሬው ዕለት ሐምሌ 19 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ የተገባው ቃል ባለመጠበቁ እና አበልና ደመወዛቸው ባለመከፈሉ የምርጫ አስፈፃሚዎቹ ለከፍተኛ እንግልትና ምሬት መዳረጋቸውን እየገለጹ ይገኛሉ። አስፈፃሚዎቹ በምርጫው ወቅት ሌሊት ሳይሉ ላባቸውን አፍስሰው ለሀገር አቀፍ ሂደት መሳካት አስተዋጽኦ አድርገው ሳለ የተገባላቸውን ውል አክብሮ ክፍያቸውን መክፈት ተገቢ ሆኖ ሳለ ቦርዱ ዝምታን መምረጡ አግባብ እንዳልሆነ አስረድተዋል። በጉዳዩ ዙሪያ ምርጫ ቦርድ የሰጠው ምላሽ የለም። ​WT Media የምርጫ አስፈፃሚዎችን ፍትሃዊ ጥያቄዎች እና የኪን ማኅበረሰብ ድምጾች አጠናክሮ የሚቀጥል ሲሆን፤ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ለዚህ የዘገየ ክፍያ እና ለተፈጠረው ቅሬታ የሚሰጠውን ምላሽ የሚከታተል ይሆናል። Read more on our official website 👇https://wolaitatimes.com/?p=8069

WT Media — tgindex