- Последний пост
- 14 авг.
- Последнее чтение
- 15 авг.
- Постов за неделю
- 5
- Всего постов
- 25
- Тип
- открытый
- Язык
- арабский
- Категория
- Новости и СМИ (по похожим)
- В каталоге с
- 13 авг.
- 1/24сутки в ленте
- 457
- 1/48двое суток
- 523
- 1/72трое суток
- 564
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
©የተርቢያ ጥቆማ🆕 «የልጆችን የስብዕና ማገር ከስሩ የሚቀስፈው ትልቁ አባዜ፤ የሕይወታቸውን ውጣ ውረድ ሁሉ በእጃችን ልንቃርምላቸው መፍጨርጨራችን፣ ከዚያም በኋሊኛው ዘመን የራሳቸውን እግር ጥለው በእኛ ትከሻ ላይ ተንጠልጥለው ሲያርፉ ተመልሰን መቆጨታችን ነው። ትከሻቸው የሕይወትን ከባድ ዕዳ እንዳይሸከም ጋርዶ የሚያቅፋቸው አልሞቅ ባይ ፍቅር፤ ሳይታሰብ ለነፍሳቸው ብስለትና ለእድገታቸው ከፍታ ትልቅ ስውር እንቅፋት ይሆንባቸዋል።» د. عبدالكريم بكار https://t.me/abdurezaq27
без подписи
📚ሱረቱ'ል ከህፍ ➖ سورة الكهف 😀خليفة الطنيجي 🔣የተረጋጋና አስተወሎት የሚያሰርፅ ቂርኣት❗️ https://t.me/abdurezaq27
«የመቃብር ባለቤቶች (ሙታን) መስማታቸው የተረጋገጠ ነው፤ በዚህም ዙሪያ ከነቢዩ ﷺ የተወሩ በርካታ ሐዲሶች አሉ። የቀብር ላይ ተልቂን (ሙታንን ማስተማር/ማስታወስ)፣ ከሙታን ጋር ማውራትና ጥቅም ያገኝ ዘንድ እሱን ማናገር ግን ከኢስላም መልእክተኛ ﷺ የተረጋገጠ ምንም ዓይነት መረጃ (ሐዲሥ) የለም።» الطريفي https://t.me/abdurezaq27
«አንድ ሰው ጠላቱን ሊገጥም በጉዞ ላይ እያለ፤ የጦር ልብሱ (መከላከያው) ሲከብደው ቢያወልቀው፣ ሰይፉ ሲከብደው አውልቆ ቢጥለው፣ እንዲሁም ምግቡና መጠጡ ሲከብደው ቢተወው፤ ከዚያም ምንም ዓይነት መከላከያና ትጥቅ ሳይኖረው፣ በዚያውም ላይ ተርቦ ጠላቱን ቢገናኝ፤ ታዲያ እንዴት አድርጎ ሊያሸንፍ ይችላል?! ልክ እንደዚሁ ዚክር (አላህን ማውሳት) ከብዶት የተወ፣ የሱና ሶላቶች (ሱነኑ ረዋቲብ) ከብደውት ቸል ያለ፣ ግዴታ (ፈርድ) ተግባራትን ከብደውት ያዘገየ፣ እንዲሁም አላህ ያዘዛቸውና የከለከላቸው ነገሮች ከብደውት ያቃለለ ሰውም ከዚህ አይለይም፤ ይህን ሁሉ አድርጎ ከዚያም ሰይጣን ልቡ ላይ እንደሰለጠነበት ያማርራል! ይህ ሰው እኮ ጠላቱ ሳይጥለው በፊት ራሱን በራሱ ነው የጣለው።» ➖ኡወይስ አል-ቀረኒይ(አላህ ይዘንላቸው) 📱https://t.me/abdurezaq27
🛡ከኃጢአት አስፈሪ ጉዳቶች አንዱ💥 ኃጢአት የልብን ፍላጎት (ቁርጠኝነት) ያዳክማል። የኃጢአት ፍላጎት ይጠነክራል፣ የንስሐ (ተውባ) ፍላጎት ደግሞ በሂደት እየደከመ ይሄዳል፤ እስካጠቃላይ ንስሐ የማድረግ ፍላጎት ከልቡ እስኪወጣ ድረስ በወንጀል ይመነምናል። በዚህ ሁኔታ ግማሹ አካሉ ቢሞት እንኳ ወደ አላህ ንስሐ አይገባም። በአንደበቱ ብዙ ምህረት (እስቲግፋር) ቢጠይቅም፣ እርሱ የውሸተኞች ንስሐ ነው፤ ልቡ…
🛡ከኃጢአት አስፈሪ ጉዳቶች አንዱ💥 ኃጢአት የልብን ፍላጎት (ቁርጠኝነት) ያዳክማል። የኃጢአት ፍላጎት ይጠነክራል፣ የንስሐ (ተውባ) ፍላጎት ደግሞ በሂደት እየደከመ ይሄዳል፤ እስካጠቃላይ ንስሐ የማድረግ ፍላጎት ከልቡ እስኪወጣ ድረስ በወንጀል ይመነምናል። በዚህ ሁኔታ ግማሹ አካሉ ቢሞት እንኳ ወደ አላህ ንስሐ አይገባም። በአንደበቱ ብዙ ምህረት (እስቲግፋር) ቢጠይቅም፣ እርሱ የውሸተኞች ንስሐ ነው፤ ልቡ ግን በወንጀሉ ላይ የተሳሰረና ባገኘው አጋጣሚ ሁሉ ለመስራት የቆረጠ ነው። ይህም ከትልልቅ በሽታዎችና ወደ ጥፋት ከሚያቀርቡት ነገሮች አንዱ ነው። ▶️ابن القيم 📣 🔥الداء والدواء© 📱https://t.me/abdurezaq27
فكثير من الإنحرافات المعاصرة في المجال العقدي والفكري والثقافي ليس عائدًا في حقيقته إلى إشكالية معرفية علمية تدخل في إطار الشبهة وإنما ثمة محركات أخر تقف خلف المشهد هي من يسهم في تشكيل كثير من القناعات والتصورات المنحرفة . ومن تأمل في كثير من الإنحرافات الفكرية في هذا الزمان فسيجد أنها عائدة إلى مركب هيمنة النموذج الثقافي الأجنبي مع ضعف التسليم لله ورسوله صلى الله عليه وسلم ينبوع الغواية الفكرية ، عبدالله العجيري
💎ኢብኑ ተይሚያህ💎 በእውቀት ያላቸው ታላቅነት፣ ትሩፋታቸው፣ ዝናቸው፣ የመጽሐፎቻቸው መዘዋወር እና በርካታ ታላላቅ ምሁራን ተማሪዎቻቸው ቢሆኑም፤ የእሳቸውን ትሩፋት መግለጽ የፈለጉ ሰዎች ደጋግመው እንዳነሱት፣ የእሳቸውን ታላቅነት ለማሳየት ኢብኑል ቀይም የእሳቸው ተማሪ መሆናቸው ብቻ በቂ ነው። ይህም ኢብኑል ቀይም በጥንቱ ዘመን የነበራቸውን የእውቀት ስርጭት፣ የውእውቀታቸውን ከፍታ እና በመጽሐፎቻቸው ምን ያህል ጥቅም እንደተገኘባቸው ያሳያል። ➖ኢብኑ ሐጀር እንዲህ ብለዋል፦ "ሸይኽ ተቂዩዲን (ኢብኑ ተይሚያህ)፣ ተስማሚውም ሆነ ተቃራኒው ከተጠቀመባቸው ጠቃሚ እና ተሰራጭ መጽሐፎች ባለቤት ከሆኑት ከታዋቂው ተማሪያቸው ሸይኽ ሸምሱዲን ኢብኑ ቀይመል-ጀውዚያህ ውጭ ሌላ ምንም ትሩፋት ባይኖራቸው ኖሮ፣ ይህም ለደረጃቸው ታላቅነት ከፍተኛ ማሳያ በሆነ ነበር።" ➖አት-ተፍሁኒ አል-ሐነፊ ደግሞ እንዲህ ብለዋል፦ "ሸይኽ ተቂዩዲን ኢብኑ ተይሚያህ አብረዋቸው ከነበሩ ሰዎች ወደ እኛ እንደተላለፈው እና መጽሐፎቻቸው በዓለም ላይ ከተሰራጩት ከተማሪያቸው ኢብኑ ቀይመል-ጀውዚያህ ንግግር ላይ እንደተረዳነው፤ እርሳቸው በተለያዩ የዕውቀት ዘርፎች የተካኑ፣ ለዱንያ (ለዓለማዊ ህይወት) ያላቸው ፍላጎት አነስተኛ የሆነና ከእሷም የራቁ፣ በተቃራኒዎቻቸው ላይ መረጃን በማቅረብ ብቁ የነበሩ፣ ሱናን የሸመደዱና መንገዶቿንም ያወቁ፣ በሁለቱ መሠረታዊ ዕውቀቶች (የዲን መሠረቶች - ኡሱሉዲን እና የፊቅህ መሠረቶች - ኡሱሉል ፊቅህ) አዋቂ የሆኑ፣ ጥልቅ ትርጉሞችን የማውጣት (ኢስቲንባጥ) ችሎታ ያላቸው፣ በእውነት ላይ የማንንም ወቀሳ የማይፈሩ፣ እንዲሁም በቢድዓ ሰዎች (እንደ ሙጀሲማ፣ ሑሉሊያ፣ ሙዕተዚላ፣ ረዋፊድ እና ሌሎችም) ላይ በጽናት የሚቆሙ ምሁር ነበሩ። አንድን ሰው ከእርሱ ጋር ካልተቀላቀሉና አብረውት ካልኖሩ፣ ስለ ሁኔታዎቹና ባህሪያቱ ትቶት ባለፈው አሻራ ማስረጃ ይወሰዳል። ትቶት ካለፈው አሻራም፣ ተማሪያቸው ኢብኑ ቀይመል-ጀውዚያህ ከተላበሱት ዕውቀት ውጭ ሌላ ባይኖር ኖሮ፣ ላስቀመጥነው ነገር በቂ ማስረጃ በሆነ ነበር።" https://t.me/abdurezaq27
አል-ወሊድ ኢብኑ'ል ሙጊራህ በትንሣኤ (ከሞት በኋላ መነሣት)፣ በጀነትም ሆነ በእሳት የማያምን ጣዖት አምላኪ (ሙሽሪክ) የነበረ ቢሆንም — ቁርኣንን በሰማ ጊዜ እንዲህ ብሏል፦ ✨"والله إن له لحلاوة، وإن عليه لطلاوة، وإن أعلاه لمثمر، وإن أسفله لمغدق، وما يقول هذا بشر، وإنه ليعلو وما يعلى عليه" «በአላህ ይሁንብኝ! ለእርሱ (ለቁርኣን) ልዩ ለዛና ጣዕም አለው፤ በእርሱም ላይ ውበትና ግርማ አለ፤ በላይኛው ፍሬያማ ነው፤ በታችኛውም ለም (ውሃ አዘል) ነው፤ ይህንን የሰው ልጅ ሊናገረው አይችልም፤ እርሱ የበላይ ይሆናል እንጂ በእርሱ ላይ የበላይ የሚሆን የለም።» https://t.me/abdurezaq27
🔣ራስን በማሻሻል ላይ ጽናትና ተስፋ አለመቁረጥ❗️ ሙዐላ ኢብኑ ዚያድ እንዲህ ብለዋል፦ ሙወሪቅ አል-ዑጀሊይ እንዲህ አለ፦ «ላለፉት አሥር ዓመታት ስፈልገው የነበረና ማግኘት ያልቻልኩት ነገር አለ፤ ነገር ግን ፍለጋውን በፍጹም አልተወውም።» እርሱም «አቡ አል-ሙዕተሚር ሆይ! እሱ ምንድን ነው?» አለው። እርሱም፦ «የማያገባኝ ነገር ላይ ዝም ማለት (ከመናገር መቆጠብ) ነው» አለ። (ምንጭ፦ «አል-ሙሰነፍ»፣ ኢብኑ አቢ ሸይባህ፣ 19/352) 🔣ሙወሪቅ ታቢዒይ (የሶሃቦችን ዘመን የደረሰ) ሲሆን፤ ኢማም አሕመድ ስለ እርሱ ሲናገሩ፦ «ከመልካም የአላህ ባሪያዎች አንዱ ነበር» ብለዋል። ✅አላህ ሆይ! ለሚጠቅመን ነገር ምራን፤ የማይጠቅሙና ከንቱ ነገሮች ውስጥ መግባትና ማውራት በዝቶብናልና! 📱https://t.me/abdurezaq27
በርቀት ተምሮ "የተግባር ፈተና" (practical exam) ያላለፈ ባለሙያ የሰራው ነው የሚመስለው!
﴿كُلُّ مَنْ عَلَيْهَا فَانٍ وَيَبْقَىٰ وَجْهُ رَبِّكَ ذُو الْجَلَالِ وَالْإِكْرَامِ﴾ [الرحمن: 26 - 27]
﴿إِنَّ الْمُجْرِمِينَ فِي ضَلَالٍ وَسُعُرٍ يَوْمَ يُسْحَبُونَ فِي النَّارِ عَلَىٰ وُجُوهِهِمْ ذُوقُوا مَسَّ سَقَرَ إِنَّا كُلَّ شَيْءٍ خَلَقْنَاهُ بِقَدَرٍ وَمَا أَمْرُنَا إِلَّا وَاحِدَةٌ كَلَمْحٍ بِالْبَصَرِ وَلَقَدْ أَهْلَكْنَا أَشْيَاعَكُمْ فَهَلْ مِن مُّدَّكِرٍ وَكُلُّ شَيْءٍ فَعَلُوهُ فِي الزُّبُرِ وَكُلُّ صَغِيرٍ وَكَبِيرٍ مُّسْتَطَرٌ إِنَّ الْمُتَّقِينَ فِي جَنَّاتٍ وَنَهَرٍ فِي مَقْعَدِ صِدْقٍ عِندَ مَلِيكٍ مُّقْتَدِرٍ﴾ [القمر: 47 - 55] «በእርግጥ አጥፊዎች (ከሓዲዎች) በስህተትና በነበልባል እሳት ውስጥ ናቸው።» (47) «በፊቶቻቸው ላይ ወደ እሳት በሚጎተቱበት ቀን “የሰቀርን (የጀሃነምን) ንክኪ ቅመሱ” (ይባላሉ)።» (48) «እኛ ማንኛውንም ነገር በወሰን (በልክ) ፈጠርነው።» (49) «ትእዛዛችንም እንደ ዓይን ቅጽበት አንዲት (ቃል) እንጂ ሌላ አይደለችም።» (50) «ቢጤዎቻችሁንም (እንደ እናንተ ያሉትን ከሓዲዎች) በእርግጥ አጠፋን፤ ታዲያ ተገሣጭ አለን?» (51) «የሠሩትም ነገር ሁሉ በጽሑፎች (በመዛግብት) ውስጥ አለ።» (52) «ማንኛውም ትንሽና ትልቅ ነገር ሁሉ የተመዘገበ ነው።» (53) «በእርግጥ ጥንቁቆቹ (አላህን ፈሪዎች) በገነቶችና በወንዞች ውስጥ ናቸው።» (54) «እውነተኛ በሆነ መቀመጫ ውስጥ ሁሉን ቻይ ከሆነው ንጉሥ ዘንድ።» (55)
➖የአላህን ዚክር መተው ለዐቂዳና ለሥነ-ምግባር መዛባት መንስኤ ነው❗️ ✔️ሸይኹ'ል ኢስላም ኢብኑ ተይሚያ (አላህ ይዘንላቸውና) እንዲህ ይላሉ፦ "ሰይጣን 'ወስዋስ' (በክፉ ጎትጓች) እና 'ኸናስ' (አፈግፋጊ) ነው። አንድ ባሪያ ጌታውን ባወሳ (ዚክር ባደረገ) ጊዜ ሰይጣን ወደኋላ ያፈገፍጋል፤ ከዚክር በዘነጋ ጊዜ ደግሞ ይወሰውሰዋል። በዚህም የተነሳ የአላህን ዚክር መተው፤ በልብ ውስጥ ለሚፈጠሩ የውሸት እምነቶች እና ብልሹ ፍላጎቶች ዋነኛ መነሻና መንስኤ ሆኗል።" የአላህን ኪታብ (ቁርኣንን) ማንበብ፣ ትርጉሙን ማስተዋልና በእውቀት ዙሪያ መወያየት ከዚክር ይመደባሉ። ታላቁ ሶሐቢይ ሙዓዝ ኢብኑ ጀበል (ረ.ዐ) ስለዚህ ጉዳይ ሲናገሩ፦ "እውቀትን መወያየት ተስቢሕ (አላህን ማጥራት) ነው" ብለዋል። 📚 ምንጭ፦ አል-ኢንቲሳር ሊአህሊል-አሠር (الانتصار لأهل الأثر) | ገፅ 52 📱https://t.me/abdurezaq27
«ወሊይ (የሴት ልጅ አባት/ወኪል) ሴት ልጁን በዕድሜ እጅግ ከሚበልጣት ሰው ጋር ሊያጋባት አይገባም። ይልቁንም በዕድሜ መቀራረባቸውን ግምት ውስጥ ሊያስገባ ይገባል፤ ነሳኢይ በትክክለኛ የኢስናድ መስመር ከቡረይዳህ ቢን ሑሰይብ እንደዘገቡት፡- አቡ በክር እና ዑመር (ረዲየላሁ ዐንሁማ) ፋጢማን ለማጨት(ለማግባት) በተለያየ ግዜ ጠየቁ፤ የአላህ መልእክተኛም (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) “እሷ ገና ትንሽ ልጅ ናት” አሉ። ከዛም ዐሊይ ጠየቃትና አጋቧት።» 🔍ታላቁ ዓሊም አል-አልባኒ (ረሒመሁላህ) 📕 (አት-ተዕሊቃት አር-ረዲያህ 2/151) 📱https://t.me/abdurezaq27
ابن عساكر في تاريخه بسنده قال صلى الله عليه وآله وسلم «በዕለተ ቂያማ (በተውላደ መቃብር/በትንሣኤ ቀን) ከሰው ሁሉ ይበልጥ በጽኑ ቊጭትና ጸጸት የሚቃጠለው፦ በዱንያ (በምድራዊ ሕይወቱ) እውቀትን የመቅሰም ሰፊ ዕድልና አቅም ኖሮት ሳይማር የቀረና ዕድሉ ያመለጠው ሰው ነው። https://t.me/abdurezaq27
إِنَّ اللَّهَ وَمَلائِكَتَهُ يُصَلُّونَ عَلَى النَّبِيِّ يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا صَلُّوا عَلَيْهِ وَسَلِّمُوا تَسْلِيمًا
«"እኔ አፈር ጠጠር ግጬ፣ የትምህርት ማማን ስቧጠጥ ከርሜ፣ የሁለተኛና የሶስተኛ ዲግሪ ወረቀት አቅፌ በየታክሲው ተራ ስጋፋ፤ ያ ፊደል የጠላውና ከስድስተኛ ክፍል የተፋታው አብሮ አደጌ ግን መኪና እንደ ሸሚዝ ይቀያይራል..." የሚለው የዘመኑ የፊደል ቆጣሪዎች እንጉርጉሮ መቼም ከየሰዉ አንደበት ጠፍቶ አያውቅም። ይህ ብሶት ሲውል ሲያድር የገዛ መልኩን እየቀየረ፣ የሆነ አንዳች ሰማያዊ በደል የተፈፀመበት ያህል፣ ያን ሳይማር በጥቅምት አጥንቱ ታግሎ ያለፈውን ሁሉ በጅምላ 'ሌባና ዘራፊ' አድርጎ እስከመፈረጅ አድርሶናል። እውነቱን እንነጋገር ከተባለ፣ በመሀሉ መግል የቋጠረ ድብቅ 'ምሁራዊ ምቀኝነት' የለም ብሎ መካድ አይቻልም። መቼም ትምህርት፣ ብራና መፈተግና እውቀት መሸመት ክፋት የለውም። የነጠረ ክብር ነው፤ የዓይን ብርሃንም ነው። ነገር ግን፣ ቀለም መበጠስ ብቻውን ለድሎት ኑሮ የብራና ላይ ማህተም፣ ወይም ሰማያዊ ዋስትና ሊሆን እንደማይችል መገንዘብ ተገቢ ነበር። መማር የኑሮን በር ያንኳኳል እንጂ፣ ደጃፉን ሰብሮ ሀብት አያጎርፍም። ያንን የዘመኑን አቋራጭ መንገድና የሌብነት ትርክት ለጊዜው ወደጎን ትተን ስንመዝነው፤ በሚሊዮን የሚቆጠሩ የሰው ልጆች የትምህርት ቤት ደጃፍ ሳያዩ፣ በላባቸው ጭቃ አቡክተው፣ በእልህና በቆራጥነት የኑሮን ቋጥኝ ጥሰው ከከፍታው ማማ ላይ ተንጠላጥለዋል። እነዚህ ሰዎች ያለፉበት የእሾህ መንገድ፣ ያ ፊደል የቆጠረው ወገናችን ለትምህርት ከከፈለው ዋጋ በላይ ጆሮ ጭው የሚያደርግ፣ አጥንት የሚሰብርና ነፍስን የሚያላውስ መስዋዕትነት የተከፈለበት መሆኑን መዘንጋት የህሊና ዳኝነት አይሆንም። ምናልባትም፣ ያ 'ምሁር' ነኝ ባዩ ክፍል ሊያልፍበት ቀርቶ በሀሳቡ ሊስለውና ሊያስበው የሚሰቀጥጠውን የሕይወት ውጣ ውረድ፣ ርሃብና እርዛት ተጋፍጠው ለወጡት ለእነዚህ ብርቱዎች፣ ያ የንቀት ፌዝና የሰነፍ ለቅሶ ከቶም ሊመጥን አይችልም። የተማረም ሆነ ያልተማረ የየራሱ የሆነ የህይወት መስቀል አለውና፣ ሁሉም እንደየብርታቱ ይሸከመዋል እንጂ አንዱ በአንዱ ላይ ጣት የሚቀስርበት አንዳችም የሞራል ከፍታ የለውም።» ➖መልዕክቱን ስለወደድሁት ትንሽ ተነካክቶ የቀረበ
📚ሱረቱ'ል ከህፍ ➖ سورة الكهف 😀خليفة الطنيجي 🔣የተረጋጋና አስተወሎት የሚያሰርፅ ቂርኣት❗️ https://t.me/abdurezaq27