ጥልቅ እይታ - Insight Motion
Статистика"ጥልቅ እውቀት ለተግባራዊ ለውጥ! 🚀 ስለ ቢዝነስ፣ ስራ አመራር (Management)፣ ማርኬቲንግ እና የግል ክህሎት እድገት የሚማሩበት የኢትዮጵያውያን የዕውቀት ማዕከል። 👉ገፁን በመከተል የለውጡ አካል ይሁኑ!"
- Последний пост
- 7 авг.
- Последнее чтение
- 13 авг.
- Постов за неделю
- 0
- Всего постов
- 33
- Тип
- открытый
- Язык
- ti
- В каталоге с
- 13 авг.
- 1/24сутки в ленте
- 174
- 1/48двое суток
- 199
- 1/72трое суток
- 215
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
#ጀግንነት፡- በውስጥህ የተሸሸገው ታላቅ ኃይል! ብዙ ሰዎች ጀግንነት ሲባል በጦር ሜዳ የሚፈጸም ተአምር ወይም ፍርሃት አልባ መሆን ብቻ ይመስላቸዋል። ነገር ግን እንደ እውነቱ ከሆነ፣ እውነተኛ ጀግንነት የፍርሃት አለመኖር ሳይሆን፣ ፍርሃትን ተሻግሮ ለዓላማ መቆም ነው! ጀግንነት በዕለት ተዕለት ሕይወታችን ውስጥ የምንወስዳቸው ጥቃቅን ነገር ግን መሠረታዊ ውሳኔዎች ድምር ውጤት ነው። የእውነተኛ ጀግንነት 3 ወርቃማ መሪ ሀሳቦች፡- 1. ለመጀመር ደፋር ሁን ( The Courage to Start ) ያለህን ህልም ለማሳካት የመጀመሪያውን እርምጃ መውሰድ ትልቁ ጀግንነት ነው። ሌሎች «አይቻልም» ብለው በተዉት መንገድ ላይ አንተ «እችላለሁ» ብለህ ስትነሳ፣ የጀግንነት መንገድህን ጀምረሃል። 2. ከውድቀት በኋላ የመነሳት ጽናት ( The Power of Resilience ) ጀግንነት መውደቅ አለመቻል ሳይሆን፣ በወደቅክ ቁጥር አቧራህን አራግፈህ ለመነሳት የምታደርገው ጥረት ነው። ትልቁ ስኬት የሚመጣው ከተደጋገሙ ውድቀቶች በኋላ እጅ ባልመስጠት ውስጥ ነው። 3. እውነትንና እሴትን አጥብቆ መያዝ ( Standing for Values ) ማንም ባላየህበትና ባልታዘበህበት ሰዓት ቢሆን እንኳ ትክክለኛውን ነገር ማድረግ፣ ደካሞችን መደገፍ እና ለእውነት መቆም ከፍተኛው የሰብዕና ጀግንነት ደረጃ ነው። 👉ጀግንነት ማለት ሁልጊዜ በታላቅ ድምፅ የሚጮኽ ነገር አይደለም፤ አንዳንዴ ጀግንነት ማለት በቀኑ መጨረሻ ላይ 'ነገ ደግሞ ድጋሚ እሞክራለሁ' ብሎ በጸጥታ ለራስ የሚሰጥ ቃል ኪዳን ነው። 👉ዛሬውኑ ተነሳ! በውስጥህ ያለውን ፍርሃት በጽናትህ ተካው፤ ምክንያቱም ዓለም የምትጠብቀው የእንቅስቃሴህን ውጤት ሳይሆን የውስጥህን ጀግንነት ነው።
#መልእክተ_ቅዱስ_ፓትርያርክ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሓዱ አምላክ፤ ኣሜን ! በሃገር ውስጥና በመላው ዓለም የምትገኙ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን እምነት ተከታዮች በሙሉ! የሰውን ወገን ለማዳን የልጁ ማደሪያ ትሆን ዘንድ ድንግል ማርያምን የመረጠ መፍቀሬ ሰብእ እግዚአብሔር ኣምላካችን እንኳን ለሁለት ሺሕ ዓሥራ ስምንት ዓመተ ምሕረት ጾመ ማርያም ኣደረሰን ኣደረሳችሁ! “ወእመሰ ታፈቅሩኒ ዕቀቡ ትእዛዝየ፡- ከወደዳችሁኝስ ትእዛዜን ጠብቁ” (ዮሓ14÷15)፤ ፍቅር የሕያዋን ኣካላት ረቂቅ መገናኛ ነው፤ ሕያዋን ኣካላት በውጫዊው ግዙፍ ኣካላቸው በተወሰኑ ጊዜያትና ቦታ ይገናኛሉ፤ ስለ ጋራ ጉዳያቸውም በጋራ ይመክራሉ፤ ይበልጥም ይቀራረባሉ፡፡ ይሁንና የሕያዋን ኣካላት ግንኙነት በኣካል በጊዜና በቦታ ብቻ የተወሰነ ኣይደለም፤ በፍቅረ መንፈስ ተገናኝተውም ይግባባሉ፤ ከኣካላዊ ግንኙነት በላይ የበለጠም ይኸው ፍቅረ መንፈስ ነው፤ ከዚህ ኣንጻር እግዚአብሔርንም ማግኘት የምንችለው በዚሁ ፍቅረ መንፈስ ሆነን በእምነት ዓይን ነው፤ ይህም በመሆኑ ሓዋርያው ቅዱስ ዮሓንስ በመልእክቱ “በፍቅር የሚኖር በእግዚአብሔር ይኖራል፤ እግዚአብሔርም በእርሱ ይኖራል” በማለት ያስተምረናል፤ (1ዮሓ.4÷16) ይህም ማለት ከሱ ጋር በፍቅር ስንገናኝ፣ እሱም በኛ፣ እኛም በእሱ የመኖሩ ኩነት ይፈጠራል ማለት ነው፡፡ የተወደዳችሁ የመንፈስ ቅዱስ ልጆቻችን ምእመናንና ምእመናት! ጌታችን “አፍቅሮ ለእግዚአብሔር ኣምላክከ፤- አምላክህን እግዚአብሔርን ውደደው” በማለት በፍጹም ልባችን እንድንወደው፣ እንደዚሁም ራሳችንን በምንወድበት መጠን እርስ በእርሳችን እንድንዋደድ ማዘዙን እናውቃለን፤ የመውደዳችን መለኪያ ሚዛንና መገለጫ ምልክትም ትእዛዙን ማክበርና መጠበቅ እንደሆነ “ብትወዱኝስ ትእዛዜን ጠብቁ” በማለት ኣስተምሮናል፤ ከዚህ ኣኳያ ጌታን መውደድ ማለት ትእዛዙን በመጠበቅ የሚገለጽ ግዙፍ ነገር እንጂ ምናባዊና የማይታይ ድብብቆሽ ነገር ኣይደለም ማለት ነው፤ ጌታችንን የመውደድ ነገር ትእዛዙን በመጠበቅ የሚገለጽ ከሆነ ትእዛዙ ምንድን ነው? የሚለውን ማየት ኣስፈላጊ ይሆናል፤ ትእዛዙን በጥቅል ስናይ እግዚአብሔርንና ባልንጀራን በመውደድ እንደሚጠቃለል ራሱ ጌታችን ኣስገንዝቦናል፤ በተለይም በባልንጀራችን ላይ የምንከተለው መውደድ ከላይ እንደተገለጸው “እንደራስህ ኣድርገህ ውደድ” ተብሎ በግልጽ ተቀምጦኣል፤ የሰው ባልንጀራ እነማን ናቸው? በሕይወት ያሉት ናቸው? ወይስ የሞቱት? ወገን ዘመድ? ወይስ የሰው ወገን በሙሉ የሚለውንም ማወቅ ኣስፈላጊ ነው፡፡ ጌታችን ነገሩን በዚህ ደረጃ ለያይቶ ኣላስቀመጠም፤ ለምን? ቢባል ባልንጀራ ማለት የተወሰነን የማኅበረ ሰብ ወገን የሚያሳይ ሳይሆን መላውን የሰው ወገን የሚገልጽ በመሆኑ፣ እንደዚሁም የሞቱም ሆኑ ያለነው ሁላችን በእሱ ፊት ሕያዋንና እርስ በእርሳችን ባልንጀሮች በመሆናችን ነው፤ በመሆኑም መዋደዳችንም ሆነ መከባበራችን በሕይወተ ሥጋ ሳለን ብቻ ሳይሆን ከዚያም በኋላ እስከ በሌለው ዕድሜ በመሆኑ ጌታችን በጊዜ በቦታና በከፊል ለይቶ ኣላስቀመጠም፡፡ የተወደዳችሁ የመንፈስ ቅዱስ ልጆቻችን ምእመናንና ምእመናት ! ከነሓሴ ፩ ቀን ጀምሮ ለ፲፭ ቀናት የምንጾመው የጾመ ማርያም መነሻ ምክንያቱ የእግዚአብሔር ትእዛዝና ፍቅር ነው፤ እግዚአብሔር ሰውን በኣጠቃላይ በተለይም ደግሞ እንደፈቃዱ የኖሩ ቅዱሳንን እንድናከብር ኣዞናል፤ከቅዱሳን ፍጥረታት መካከል ደግሞ ቅድስት ድንግል ማርያም የመጀመሪያውን ደረጃ ትይዛለች፤ ይህም በመሆኑ ከፍጥረት ወገን ከሷ ክብር የሚደርስ ባለመኖሩ ከሁሉም ኣብልጠን እናከብራታለን፤ ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በዚህ ደረጃ የድንግል ማርያምን ክብር ስትገልጽ ከእግዚአብሔርና ለባስያነ እግዚአብሔር ከሆኑ ቀደምት ኣበው ተምራ ነው፤ በኣራተኛው መቶ ክፍለ ዘመን የነበረው ዕውቁ ቅዱስና ዓለም ዓቀፋዊው ኣባት ቅዱስ ኤፍሬም የድንግል ማርያምን ክብር፣ ቅድስና እና ልዕልና ሲናገር “ይእቲ ተዓቢ እምኪሩቤል፤ ወትፈደፍድ እምሱራፌል፤ እስመ ኮነት ታቦተ ለአሓዱ ዘእምቅድስት ሥላሴ፡- እሷ ከኪሩቤል ትበልጣለች፤ ከሱራፌልም ትልቃለች፤ ከቅድስት ሥላሴ ኣንዱ ለሆነው ታቦት ወይም ማደሪያ ሆናለችና” በማለት ኣስተምሮናል፡፡ በመሆኑም ለስሟ መታሰቢያ በሆነው በዚህ ጾም ድንግል ማርያምን በዚህ ደረጃ ስናከብር ትእዛዙን እንጠብቃለን፤ ትእዛዙን በመጠበቃችን ደግሞ እሱን መውደዳችንን እናረጋግጣለን፤ እኛ ድንግል ማርያምን እንድንወዳት “እናታችሁ” ብሎ እንዳዘዘ፣ እሷም ልትወደን “ልጆችሽ” ተብላ ታዛለችና ስለኛ ትጸልያለች፤ በጸሎቷም ከመከራ ትታደገናለች፤ በኣጠቃላይ በእግዚአብሔር፣ በቅዱሳንና በእኛ መካከል ያለው ግንኙነት በዚህ ትእዛዝና ፍቅር በትዕይንተ ዓለም ባለች ቤተ ክርስቲያን ዘንድ የተሳሰረ ነው፤ ስለሆነም በዚህ የጾመ ፍልሰታ ለማርያም ሱባዔ የተራቡትን በመመገብ፣ የታረዙትን በማልበስ፣ የተጣሉትን በማስታረቅ፣ የታመሙትንና የታሰሩትን በመጠየቅ፣ ቅዱስ ቊርባንን በመቀበልና ለኃጢኣታችን የንሥሐ ሥርየትን በመለመን ሱባዔውን ልናሳልፍ ይገባል፡፡ በመጨረሻም፡- በሀገራችንም ሆነ በዓለም ዙሪያ ከባድ ስጋት የሆነው የፍጥረት ኣውዳሚ ጦርነትን በመለኮታዊ ጥበቡና ሥልጣኑ እንዲያስቆምልን በቅን ልቡና፣ በትሑት ሰብእና ሆነን እግዚአብሔርን በዚህ ሱባዔ እንድንጠይቀው ኣደራ ጭምር ኣባታዊ መልክታችንን በእግዚአብሔር ስም እናስተላልፋለን፤ የተባረከና የተቀደሰ ጾም ያድርግልን፤ እግዚአብሔር ኢትዮጵያንና ሕዝቦችዋን ይባርክ፤ ወስብሐት ለእግዚአብሔር፤ ኣሜን! ኣባ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጰሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘኣኲስም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት፤ ነሐሴ 1 ቀን 2018 ዓ.ም አዲስ አበባ ኢትዮጵያ © የቅዱስ ፓትርያርኩ ልዩ ጽ/ቤት
የማያቋርጥ እድገት ልምምዶች! (ክፍል አምስት) ዓላማ እና ራእይ (Purpose and Vision) – በዓላማ መኖር እስካሁን የሚከተሉትን ልምምዶች ተመልክተናል፡ “ራስን ማወቅ”፣ “የግል ሃላፊነት”፣ “ቀጣይነት ያለው ትምህርት” እና “ዲሲፕሊን እና ወጥነት”፡፡ ዛሬ ደግሞ፣ “ዓላማ እና ራእይ” የተሰኘውን የመጨረሻ ክፍል አጋራለሁ፡፡ በዓላማ የሚያድጉ ሰዎች ወዴት አእጣጫ እንደሚሄዱ እና ለምን እንደሚሄዱ ጥርት አድርገው ያውቃሉ። ስለሆነም፣ ከመወላወል እና ተስፋ ከመቁረጥ አጉል ልምምዶች ራሳቸው ያላቀቁ ሰዎች ናቸው፡፡ የዓላማ ሰው የመሆንን ወሳኝ ልምምድ ለማዳበር ደግሞ የሚከተሉት መርሆች አስፈላጊ ናቸው፡፡ 1. ለሕይወት ግልጽ የሆነ ራእይ መያዝ 2. ትርጉም ያላቸው ግቦችን ማውጣት 3. ድርጊቶችን ከእሴቶቻችን እና ከመርሆቻችን ጋር ማጣጣም ዛሬን እና ላለፉት አራት ቀናት፣ “የማያቋርጥ እድገት ልምምዶች” በሚል ርእስ ስር እንደተመለከትነው፣ የጀመርነው የእድገት ሂደት ቀጣይነት እንዲኖረው መለማመድ ከሚገቡን ልምምዶች አንጋፋውና የመጨረሻው፣ “ዓላማን እና ራእይን” የማወቅና የመከተል ጉዳይ ነው፡፡ ይህንን ተከታታይ ሃሳብ ስቋጭ፣ ዓላማን እና ራእይን አስመልክቶ የሚከተሉትን ጥያቄዎች ራሳችሁን በመጠየቅ ወደ ፊት እንድትገሰግሱ አበረታታችኋለሁ፡፡ · ለሕይወቴ ማስረዳት የምችላው ግልጽ የሆነ ራእይ አለኝ? · ዕለታዊ ተግባሮቼ እና ውሳኔዎቼ ከእሴቶቼ፣ ከመርሆቼ እና ከረጅም ጊዜ ዓላማዬ ጋር የተጣጣሙ ናቸው? · ዓላማዬን ለመፈጸም በዚህ የሕይወት ምዕራፍ ውስጥ የትኞቹን ትርጉም ያላቸው ግቦች መከታተል አለብኝ? ተጠናቀቀ Dr. Eyob Mamo
የማያቋርጥ እድገት ልምምዶች! (ክፍል አራት) ዲሲፕሊን እና ወጥነት (Discipline and Consistency) – ዕለታዊ ልማዶችን መለማመድ በሕይወታችን የማያቋርጥ እድገት ውስጥ ለመግባት ከፈለግን ልናዳብር ከሚገቡን ልምምዶች አምስቶቹን ላጋራችሁ ብዬ፣ ባለፉት ሶስት ቀናት “ራስን ማወቅ”፣ “የግል ሃላፊነት” እና “ቀጣይነት ያለው ትምህርት” የተሰኙ ሃሳቦች አጋርቻለሁ፡፡ ዛሬ ደግሞ፣ “ዲሲፕሊን እና ወጥነት” የተሰኘውን አጋራለሁ፡፡ ሕይወታችን በቀጣይነት እንዲያድግ ከፈለግን ዲሲፕሊን እና ወጥነት ችላ ሊባሉ የማገባቸው ልምምዶች ናቸው፡፡ ዲሲፕሊን ከሌለን የተለያዩ ነገሮችን እንጀምራለን፣ ነገር ግን አንቀጥላቸውም፡፡ ይህንን ወሳኝ ልምምድ ለማዳበር ደግሞ የሚከተሉት መርሆች አስፈላጊ ናቸው፡፡ 1. ከዓላማችን አንጻር ጠቃሚ የሆኑ ልማዶችን ማዳበር 2. ጊዜያችንን በጥበብ መጠቀም 3. በትናንሽ ነገሮች ላይ ታማኝ መሆን የጀመርነው የእድገት ከአንዱ ደረጃ ወደ ሌላኛው ደረጃ እደገ እንዲሄድ ከፈለግን የጸና ዲሲፕሊን እና ወጥነት ያለው ልምምድ ያስፈልገናል፡፡ ነገሮችን እየጀመርን የምናቆምና በምኞት ብቻ የምንኖር ከሆነ እድገታችን ይገታል፡፡ በነገው ፖስቴ ክፍል አምስትን ይዤ እመለሳለሁ፡፡ እሰከዚያው ድረስ የሚከተሉትን ጥያቄዎች ራሳችሁን በመጠየቅ ሃላፊነትን የመውሰድ ልምምድን ለማዳበር ሞክሩ፡፡ · እያደግኩ እንድሄድ የሚረዱኝና አድገቴን የሚከለክሉ ዕለታዊ ልማዶቼ ምንድን ናቸው? · ጊዜዬን በታቀደ መንገድ እየተጠቀምኩ ነው ወይስ ትኩረትን በሚከፋፍሉ ነገሮች እየተወሰድኩኝ ነው? · ጀመርኳቸው እንጂ መጨረስ ያልቻልኳቸው አስፈላጊ ነገሮች ምንድን ናቸው? ይቀጥላል . . . Dr. Eyob Mamo
የማያቋርጥ እድገት ልምምዶች! (ክፍል ሶስት) ቀጣይነት ያለው ትምህርት (Continuous Learning) – ለማደግ መወሰን በሕይወታችን የማያቋርጥ እድገት ውስጥ ለመግባት ከፈለግን ልናዳብር ከሚገቡን ልምምዶች አምስቶቹን ላጋራችሁ ብዬ፣ ባለፉት ሁለት ቀናት “ራስን ማወቅ” እና “የግል ሃላፊነት” የተሰኙ ሃሳቦችን አጋርቻለሁ፡፡ ዛሬ ደግሞ፣ “ቀጣይነት ያለው ትምህርት” የተሰኘውን አጋራለሁ፡፡ ሕወታችን በቀጣይነት እንዲያድግ የግድ ቀጣይ የሆነ ትምህርት የምንማር ሰዎች መሆን አስፈላጊ ነው፡፡ ትምህርት ደግሞ እድሜ ልካችንን የሚቀጥል ሊሆን ይገባዋል፡፡ ይህንን ወሳኝ ልምምድ ለማዳበር ደግሞ የሚከተሉት መርሆች አስፈላጊ ናቸው፡፡ 1. ያለማቋረጥ ማንበብ፣ መማር እና መሰልጠን 2. አማካሪዎችን መፈለግ እና የእነሱን ግብረ-መልስ (feedback) መስማት 3. በየጊዜው የሚገጥሙንን ውድቀቶች ወደ ትምህርት መቀየር የጀመርነው የእድገት ጉዞ እስከመጨረሻው እንዲዘልቅ ከፈለግን በየእለቱ የምንማር ሰዎች መሆን አስፈላጊ ነው፡፡ መማር ያቆመ ሰው ማደግ ያቆመ ሰው እንደሆነ በማስታወስ ከሁሉም ነገር፣ ሁል ጊዜ እንማር፡፡ በነገው ፖስቴ ክፍል አራትን ይዤ እመለሳለሁ፡፡ እሰከዚያው ድረስ የሚከተሉትን ጥያቄዎች ራሳችሁን በመጠየቅ ሃላፊነትን የመውሰድ ልምምድን ለማዳበር ሞክሩ፡፡ · የተሻለ ሰው እንድሆን የሚረዱኝ ነገሮች ምንድን ናቸው? · በሽንፈት ጊዜ ተስፋ እቆርጣለሁ ወይስ እንደ መማሪያ እና ማደጊያ እድል እጠቀመዋለሁ? · ሊያሳድጉኝ የሚችሉ አማካሪዎች፣ መምህራን ወይም ሰዎች እነማን ናቸው? ነገ ይቀጥላል . . . Dr. Eyob Mamo
የማያቋርጥ እድገት ልምምዶች! (ክፍል ሁለት) የግል ኃላፊነት (Personal Responsibility) – ኃላፊነትን መውሰድ በሕይወታችን የማያቋርጥ እድገት ውስጥ ለመግባት ከፈለግን ልናዳብር ከሚገቡን ልምምዶች አምስቶቹን ላጋራችሁ ብዬ፣ ባለፈው ፖስቴ “ራስን ማወቅ” የሚለውን ሃሳብ አጋርቻለሁ፡፡ ዛሬ ደግሞ፣ “የግል ኃላፊነት” የተሰኘውን አጋራለሁ፡፡ እድገታችን ቀጣይነት የሚኖረው በሁኔታዎች ላይ ማማረርን ስናቆም እና ለምርጫዎቻችን፣ ለስሜቶቻችን እና ለድርጊቶቻችን ሙሉ ኃላፊነት ስንወስድ ነው። ይህንን ወሳኝ ልምምድ ለማዳበር ደግሞ የሚከተሉት መርሆች አስፈላጊ ናቸው፡፡ 1. ለስህተቶቻችን ሙሉ ኃላፊነትን መውሰድና መቀበል 2. ለማንኛውም ተግባራችንም ሆነ ባህሪያችን ተጠያቂ መሆን 3. መቆጣጠር በማንችላቸው ነገሮች ላይ ሳይሆን መቆጣጠር በምንችላቸው ነገሮች ላይ ማተኮር የጀመርነው የእድገት ጉዞ ቀጣይነት እንዲኖረው ከፈለግን በሕወታችን ለሚከናወኑት ነገሮች በሙሉ የሚወቀስ ሰው ከመፈለግ ይልቅ ሙሉውን ሃላፊነት እኛው ስንወስድ ነው፡፡ በነገው ፖስቴ ክፍል ሶስትን ይዤ እመለሳለሁ፡፡ እሰከዚያው ድረስ የሚከተሉትን ጥያቄዎች ራሳችሁን በመጠየቅ ሃላፊነትን የመውሰድ ልምምድን ለማዳበር ሞክሩ፡፡ · በሕይወቴ በየትኞቹ ዘርፎች ነው ኃላፊነቱን እኔ ከመውሰድ ይልቅ ሁኔታዎችን ወይም ሌሎችን ሰዎችን የምወቅሰው? · ሊታወቁ እና ሆን ተብሎ ሊለወጡ የሚገባቸው ምን ዓይነት ስህተቶች ወይም ጤናማ ያልሆኑ ባህሪያት አሉብኝ? · እየተጠቀምኩ ያለሁት ጉልበት ልቆጣጠራቸው በማልችላቸው ነገሮች ላይ በመጨነቅ ነው፣ ወይስ ተጽዕኖ መፍጠር እና ማሻሻል በምችላቸው ነገሮች ላይ ነው? ነገ ይቀጥላል . . . Dr. Eyob Mamo
የማያቋርጥ እድገት ልምምዶች! (ክፍል አንድ) በሕይወታችን የማያቋርጥ እድገት ውስጥ ለመግባት ከፈለግን ልናዳብር ከሚገቡን ልምምዶች አምስቶቹን ላጋራችሁ፡፡ ራስን ማወቅ (Self-Awareness) – ራስን መረዳት የማያቋርት እድገት የሚጀምረው የራስን ጥንካሬዎች፣ ድክመቶች፣ እሴቶች፣ ስሜቶች እና መነሳሳቶች በመረዳት ነው። እነዚህን ነገሮች ለመረዳት ደግሞ የሚከተሉት ልምምዶች የግድ ናቸው፡፡ 1. የሕይወታችንን ዓላማ መለየት እና እሱ ላይ መቆየት 2. ሁል ጊዜ ራሳችንን መፈተሽ (Self-reflection) 3. መሻሻል ያለባቸውን ክፍተቶች በመለየት ማሻሻል እድገት የሚጀምረው በጽኑ ፍላጎትና በውሳኔ ቢሆንም፣ የሚቀጥለውና ዘላቂ የሚሆነው ግን በዓላማችን ላይ በመቆየት፣ ራስን በመፈተሽ እና የማያቋርጥ መሻሻል በማድረግ ነው፡፡ በነገው ፖስቴ ክፍል ሁለትን ይዤ እመለሳለሁ፡፡ እሰከዚያው ድረስ የሚከተሉትን ጥያቄዎች ራሳችሁን በመጠየቅ ራስን የማወቅ ልምምድን ለማዳበር ሞክሩ፡፡ · በዓላማ እየኖርኩ ነው ወይስ ሕይወት በሚያመጣው ሁኔታ እየተገፋሁ ብቻ ነው የምኖረው? · ቅን የሆነ ራስን መመርመር ስላስወገድኩ ብቻ ሳይለወጡ የቀሩ የሕይወቴ ክፍሎች የትኞቹ ናቸው? · ከሌሎች ሰዎች በተደጋጋሚ እንዳርም የምቀበለው አስተያየት ምንድን ነው? ነገ ይቀጥላል . . . Dr. Eyob Mamo
አታምታቱ! 1. ይቅርታ እና አብሮነት አንድ ሰው ሆን ብሎ እና ደጋግሞ የሚያጠፋችሁ ከሆነና ይቅርታ የሚጠይቃችሁ ከሆነ፣ ይቅርታውን ተቀበሉና ይቅር በሉት፡፡ ነገር ግን ይቅርታን እና አብሮነትን አታምታቱ፡፡ ሰዎችን ይቅር ብላችሁ በአብሮነት ግን ያለመቀጠልን ጥበብ ማዳበር ትችላላችሁ፡፡ ሁለቱ የተለያዩ ነገሮች ናቸው፡፡ ሰዎች ምንም ያህል ሆን ብለው ደጋግመው ቢያጠፉኝም ይቅር ብዬ አብሮነቴን መቀጠል እፈልጋለሁ ካላችሁ ደግሞ ደጋግማችሁ ለመጎዳት ራሳችሁን ማዘጋጀት የግድ ነው፡፡ 2. አጋርነት እና ወዳጅነት አጋርነትን እና ወዳጅነትን አታምታቱ፡፡ ከሰዎች ጋር በአጋርነት እየሰራችሁ የግድ ወዳጅ መሆን የለባችሁም፡፡ ሁለቱ የተለያዩ ነገሮች ናቸው፡፡ ከአንድ ሰው የስራ አጋር ሆናችሁ ጓደኛ ላትሆኑ ትችላላችሁ፡፡ በተመሳሳይ ሁኔታ ከአንድ ሰው ጋር የቅርብ ጓደኛ ሆናችሁ በምንም አይነት የስራ ዘርፍ አጋር ያለመሆንን ነጻነት ልትጠብቁ ትችላላችሁ፡፡ ያንንም በማድረጋችሁ ምንም ጥፋተኝነት ሊሰማችሁ አገባም፡፡ ከወዳጆቼ ሁሉ ጋር የስራ አጋር መሆን እፈልጋለሁ ካላችሁ ደግሞ በስራ አጋርነት ምክንያት ወዳጅነታችሁን የመሰዋት ሁኔታ ሲከሰት ለዚያ ሁኔታ ራሳችሁን አዘጋጁ፡፡ 3. መግባባትን እና የቀይ መስመር መግባባትን እና ቀይ መስመርን አታምታቱ፡፡ ከአንድ ሰው ጋር በጣም ተግባባችሁ ማለት መከበር ያለበት የቀይ መስመር የላችሁም ማለት አይደለም፡፡ ሁለቱ የተለያዩ ነገሮች ናቸው፡፡ ከሰዎች ጋር እጅግ ተግባብታችሁ ሳለ፣ እንዲከበርላችሁ የምትፈልጉት ወሰን ሊኖራችሁ ይችላል፡፡ መግባባት አንደኛችን ለሌላኛው ያለን አመለካከት ጉዳይ ነው፡፡ የቀይ መስመር ወሰን ግን የሚፈቀደውና የማይፈቀደው የሚለይበት ገደብ ነው። አንድ ሰው ከቀረበኝ ምንም አይነት የቀይ መስመር ማስመር አልፈልግም ካላችሁ ደግሞ፣ የስሜት፣ የጊዜ፣ የቁሳቁስና የመሳሰሉት ክስረቶችን ለማስተናግድ ተዘጋጁ፡፡ የመርህ ሰው መሆን ማለት ክፉ መሆን ማለት አይደለም! ይህንን እውነት ስትለማመዱ በማንም ሰው ሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ ሰላምና ውስጥ መረጋጋት ታገኛላችሁ፡፡ Dr. Eyob Mamo
#ነገ_ሐምሌ_19_ቅዱስ_ገብርኤል ሊቀ መላእክት ቅዱስ ገብርኤል 💞 “እኔ በእግዚአብሔር ፊት የምቆመው ገብርኤል ነኝ” (ሉቃ. ፩፥፲፱) የመላእክት አለቃ የቅዱስ ገብርኤል አማላጅነትና ጥበቃ በሁላችንም ላይ ይደር🤲 የእግዚአብሔር ቸርነት፣ የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም አማላጅነት፣ የቅዱሳን መላእክት ጥበቃ፣ የጻድቃን ምልጃ፣ የሰማዕታት በረከትና ረድኤት ከሁላችን ጋር ይሁን🙏 ሠለስቱ ደቂቅን ከእቶነ እሳት ያዳነ መልአክ እኛንም በመልአኩ ፈጣን አማላጅነት ከሚመጣው መከራ ሁሉ ይጠብቀን፤ በሃይማኖትና በምግባር አጽንቶ ለክብሩ መንግሥት ያብቃን። አሜን!!
በአንድ ዘመን፣ በውጫዊ አምልኮውና በፆም ጸሎቱ በሰዎች ዘንድ እጅግ የተከበረ አንድ አባት ነበረ። በአደባባይ ሲቆም አንገቱን ይደፋል፣ ሲጸልይ ድምፁን ከፍ አድርጎ ያለቅሳል፤ ሰዉ ሁሉ "ይህማ ጻድቅ ነው፣ የእግዚአብሔር ሰው ነው" እያለ ያደንቀው ነበር። ነገር ግን ማንም በማያየው የልቡ ጓዳ ውስጥ ትዕቢት፣ በሰዎች ላይ መፍረድ እና ራስ ወዳድነት ነግሦበት ነበር። አንድ ቀን በኃጢአት ብዛት የተሰበረ አንድ ምስኪን ሰው ወደ ቤተ መቅደስ መጥቶ መሬት ላይ ተደፍቶ በዕንባ ንስሐ ሲገባ፣ ይህ አስመሳይ አባት በልቡ "እግዚአብሔር ሆይ፣ እንደዚህ ኃጢአተኛ ስላልሆንኩ አመሰግንሃለሁ" ብሎ ናቀው። በዚያች ሌሊት የእግዚአብሔር መልአክ በራእይ ተገለጠለትና እንዲህ አለው፡- "በሰዎች ፊት የለበስከው የቅድስና ካባ በሰማይ ፊት ዕራቁትህን አስቀርቶሃል። ከንፈርህ እግዚአብሔርን ሲጠራ ልብህ ግን ከእርሱ ርቋልና ጸሎትህ ከጣሪያህ አላለፈም። አስመሳይነትህ የሰዎችን ዓይን እንጂ ልብን የሚመረምረውን አምላክ አላታለለም።" አባቱ ከእንቅልፉ ሲነቃ በከባድ ድንጋጤ ውስጥ ነበር። የውሸት ማንነቱ በእግዚአብሔር ፊት ምን ያህል አስጸያፊ እንደሆነ ተረዳ። ከዚያች ዕለት ጀምሮ በሰዎች ፊት መታየቱን ትቶ፣ በስውር የልቡን ጓዳ በማንጻት እውነተኛ የንስሐ ሕይወትን ጀመረ። እግዚአብሔር የሚፈልገው የውጭውን ማሸብረቅ ሳይሆን፣ በውስጥ ያለውን እውነተኛና ንጹሕ ልብ መሆኑን አውቆ እስከ ዕለተ ሞቱ በቅንነት ኖረ።
ስልታዊ ማፈግፈግ (Strategic Retreat) ስልታዊ ማፈግፈግ (Strategic Retreat) ማለት አንድን የጀመርነውን ነገር ርግፍ አድርጎ መተው ማለት አይደለም። ለወደፊት በብቃት ለመንቀሳቀስ ሲባል ለተወሰነ ጊዜ በብልሃት ወደ ኋላ ማፈግፈግ ማለት ነው። በህይወት ውስጥ አንዳንዴ ለማሸነፍ ምርጡ መንገድ ወደ ፊት መግፋቱን መቀጠል ሳይሆን፤ ቆም ብሎ ማሰብ፣ ሁኔታዎችን መገምገም፣ ከተጎዳንበት ነገር ማገገም እና እራስን እንደገና ማዘጋጀት ነው። ስልታዊ ማፈግፈግ ማለት ጥንካሬን ለመጠበቅ፣ ግልጽነት ለማግኘት እና ለወደፊት ለተሻለ ውጤታማነት ለመዘጋጀት ሆን ተብሎ የሚወሰን ጊዜያዊ ዝምታ፣ ከነገሮች ዘወር የማለት፣ የመውጣት፣ የመቆም ወይም አቅጣጫን የመቀየር ውሳኔ ነው። ይህ ማለት፦ ☑️ ማቋረጥ ሳይሆን፣ መስተካከል (recalibrating) ነው። ☑️ ፍርሃት ሳይሆን፣ ጥበብ ነው። ☑️ መሸነፍ ሳይሆን፣ ለተሻለ የላቀ ግስጋሴ መዘጋጀት ነው። "አንዳንዴ ትልቁን ስእል ለማየት ወደ ኋላ ማፈግፈግ ያስፈልጋል" እንደሚባለው ማለት ነው፡፡ መቼ ነው ስልታዊ ማፈግፈግን ማሰብ ያለብን? 1. ወደ ፊት መቀጠል አላስፈላጊ ጉዳት ሲያስከትል አንዳንድ ጊዜ ሁኔታው ውስጥ መቆየት የስሜትን ወይም የአካልን ጥንካሬን ሲያሟጥጥ መለስ ማለት ጥሩ ነው። 2. ግልጽነት እና አቅጣጫ ሲፈልጉ አንዳንድ ጊዜ ህይወት ግራ ሲያጋባን፣ “ትክክለኛ አቅጣጫ ላይ ነኝ? ብሎ ለመጠየቅ ማፈግፈግ አስፈላጊ ነው፡፡ 3. ዝለት (Burnout) ሲሰማን አንዳንድ ጊዜ ብዙ ለፍተን ጥቂት ስናገኝ፣ ከመሯሯጣችን የተነሳ ውስታችን ሲደክም መረጋጋት ያስፈልጋል፡፡ 4. መርዛማ (Toxic) ሰዎች ሲበዙብን አንዳንድ ጊዜ በዙሪያችን ያሉ ሰዎች ከትቅማቸው ጉዳታቸው ሲበዛና ጤና-ቢስ የሆነ ሃሳብና ተግባራቸው ሲበዛ ዘወር ማለት የግድ ነው፡፡ 5. ለታላቅ እድል ለመዘጋጀት አንዳንድ ጊዜ እስካሁን በሰራነው ስራ፣ በሄድንበት መንገድና በድግግሞሹ የሕወት ለውጥና እድገት ካላገኘት ራሳችን ለማሻሻል የትኩረት ለውጥ ማድረግ ወሳኝ ነው፡፡ በስልታዊ ማፈግፈግ ወቅት ምን ማድረግ አለብን? ስልታዊ ማፈግፈግ ስናደርግ ከከባድ ሁኔታዎች በማምለጥ ዝም ብለን ገለል ማለት ሳይሆን የሚከተሉትን ልምምዶች ማዳበር ማለት ነው፡፡ ማሰላሰል (Reflect): ምን ትምህርት ተምሬያለሁ? ማገገም (Recover): አካላዊ፣ ስሜታዊ እና መንፈሳዊ ጥንካሬን መመለስ። እንደገና መገምገም (Reevaluate): ምን መቀጠል አለበት? ምን ማቆም አለበት? ቦታ መቀየር (Reposition): ቀጣዩ ስራዬ ወይም እድሌ የት ነው? እንደገና መገንባት (Rebuild): አዳዲስ ልማዶችን፣ ስርዓቶችን እና አመለካከቶችን ማዳበር። አንዳንዴ ጥንካሬ የሚገኘው ዝም ብሎ ወደ ፊት በመገስገስ ሳይሆን መቼ ወደ ኋላ ማፈግፈግ እንዳለብን በማወቅ፣ መረጋጋት፣ ጸሎት ማድረግ፣ አመለካከትን በማስተካከል እና ለቀጣዩ የህይወት ምዕራፍ በመዘጋጀት ነው። Dr. Eyob Mamo
ምክንያታዊነት...! ( የጠራ የህይወት ኮምፓስ) በዘመናችን ትልቁ ፈተና መረጃ ማጣት ሳይሆን፣ በስሜት ማዕበል ውስጥ ጠልቆ እውነትን መለየት ማቃቱ ነው። የዓለምን ውጣ ውረድ በብዕሬ ስቃኝ የምረዳው አንድ ትልቅ ሀቅ አለ፤ እሱም«ምክንያታዊነት» (Rationality) የሰው ልጅ የጠራ የህይወት ኮምፓስ መሆኑን ነው። ምክንያታዊነት ማለት ስሜትን መካድ ወይም እንደ ማሽን መሆን ማለት አይደለም። ይልቁንም የስሜት ሞገዶችን ተረድቶ፣ በመዘውሩ ላይ አእምሮን ማስቀመጥ ማለት ነው። በአመራር ጥበብም ሆነ በግል ዕድገት ጉዞ ውስጥ፣ ምክንያታዊነት ጥልቅ እይታን ይሰጠናል። ጊዜያዊ ከሆኑ ስሜቶች ባሻገር ተሻግረን እንድናይ እና በፅናት ላይ የተመሰረተ ውሳኔ እንድናሳልፍ ያደርገናል። 👉 ምክንያታዊነትን በሶስት መሠረታዊ ምሰሶዎች እገልጸዋለሁ፦ 1. ማቆም እና ማሰብ (Pause and Reflect)፦ ከማንኛውም ትልቅ እርምጃ ወይም ውሳኔ በፊት፣ ለጥቂት ጊዜ ቆም ብሎ "ለምን?" ብሎ ራስን መጠየቅ የብስለት መጀመሪያ ነው። 2. በእውነታ ላይ መገንባት (Seek Evidence)፦ ውሳኔዎቻችንን እና የህይወት ፍልስፍናችንን በጭፍን እምነት ሳይሆን፣ በተጨባጭ መረጃ እና በተግባራዊ እውቀት ላይ መገንባት። 3. ለለውጥ ክፍት መሆን (Flexibility)፦ እውነተኛ ምክንያታዊ ሰው የተሻለ እውቀት እና አዲስ መረጃ ሲያገኝ፣ የቆየ አመለካከቱን ለመቀየር ወደኋላ አይልም። ✍️በመጨረሻም፣ ምክንያታዊነት የነጻነት መንገድ ነው። ከፍርሃት፣ ከጭፍን ጥላቻ እና ከስሜታዊነት እስር ነጻ አውጥቶ የራስዎን ታሪክ በእራስዎ እውነት እንዲጽፉ ያደርግዎታል። 👉በዕለት ተዕለት ውሳኔዎችዎ ውስጥ፣ ስሜትዎን እና ምክንያታዊነትዎን ሚዛን ለመጠበቅ የሚጠቀሙበት የራስዎ የተለየ ዘዴ አለዎት?
የዕድገት አስተሳሰብ ያላቸው ሰዎች 3 ትልልቅ ሚስጥሮች "የዕድገት አስተሳሰብ ባለቤት መሆን ማለት ፍፁም መሆን ማለት አይደለም፤ ትናንት ካልነበረህ አቅም ዛሬ የተሻለ አቅም መገንባት እንደምትችል ማመን እንጂ።" 👉 "ገና" (Not Yet) የሚለውን የኃይል ቃል ይጠቀማሉ፦ አንድን ነገር ዛሬ አለማወቃቸው ወደፊትም አያውቁትም ማለት እንዳልሆነ ይረዳሉ። "ይህንን የአስተዳደር ወይም የዲጂታል ክህሎት አላውቀውም" ከማለት ይልቅ "ገና አላወቅኩትም" ይላሉ። ይህች ቃል አእምሮአቸው መፍትሄና ትምህርት እንዲፈልግ በር ትከፍታለች። 👉የሂደቱ (Process) ፍቅረኛ ናቸው፦ ውጤቱ ላይ ብቻ ከማተኮር ይልቅ ውጤቱን ለማምጣት በሚደረገው ጥረት፣ ልምምድና እውቀትን የማዳበር ሂደት ላይ ትኩረት ያደርጋሉ። 👉በሌሎች ስኬት አይቀኑም፣ ይማሩበታል፦ ሌላ ስኬታማ ሰው ሲያዩ "እሱ ተፈጥሮ አድልታው ነው" አይሉም፤ ይልቁንም "እሱ የተጠቀመበትን ስልትና ያሳየውን ዲሲፕሊን እኔ እንዴት ልማረው እችላለሁ?" ብለው ይጠይቃሉ። ✍️ በአጭሩ፣ የዕድገት አስተሳሰብ ማለት የህይወትህን መሪነት በቁጥጥርህ ስር ማድረግ ማለት ነው። እድሜህ፣ ያለህበት ደረጃ ወይም ያለፈው ታሪክህ ምንም ይሁን ምን—አእምሮህ አዳዲስ ነገሮችን ለመቅሰምና የትኛውንም ከፍታ ለመድረስ ሁልጊዜም ዝግጁ እንደሆነ ማወቅ ነው።
እውነተኛ አሸናፊነት ከሌሎች መበለጥ ሳይሆን፣ ከትናንት ማንነትህ መሻሻል ነው!!! 👉እውነተኛ አሸናፊ ለመሆን እነዚህን ሶስት ወርቃማ ህጎች በዕለት ተዕለት ህይወትህ ተግብራቸው፦ 1. ውድቀትን እንደ ግብዓት እየው፡ መውደቅ የጉዞው ማብቂያ ሳይሆን፣ የተሻለ መንገድ እንድትፈልግ የሚገፋፋህ የልምድ መምህርህ ነው። እያንዳንዱ ፈተና ስብዕናህን የሚቀርጽ መዶሻ ነው። 2. የውስጥ ድምፅህን አበርታ፡ አለም "አትችልም" ስትልህ፣ ውስጣዊ ማንነትህ "ይቻላል፣ አንድ ጊዜ ደግሜ እሞክራለሁ" እንዲል አሰልጥነው። የአስተሳሰብህ ጥራት የህይወትህን ጥራት ይወስናል። 3. በሂደቱ ተደሰት፡ ግቡ ላይ ብቻ አትኩረህ መንገዱን አትጥላው። በየቀኑ የምታደርጋት ትንሿ እርምጃ፣ ነገ ለምትቆናጠጠው ትልቅ ድል መሰረት ናት። 💡 ያስታውሱ፦ አንተ የመጣኸው ዝም ብለህ አለምን ለማየት ሳይሆን፣ በችሎታህና በጽናትህ አለም ላይ አሻራህን ለማሳረፍ ነው። ዛሬውኑ ተነሳ፣ በራስህ እመን፣ መስራት የምትፈልገውን ነገር በሙሉ ልብህ ጀምር። ድል ሁልጊዜም ለሚጸኑት ናት! #አሸናፊነት #የስነልቦናጥንካሬ #ተነሳሽነት #ስኬት #የእኔቀን
የህሊና ሚዛን በአንድ ወቅት በነበረ ታላቅ ግዛት ውስጥ የሚኖር ዳኛ በየነ የሚባል በፍትሃዊነቱ የታወቀ ሰው ነበር። በአካባቢው የሚነሱትን ማናቸውንም ክርክሮች በእውነትና በቅንነት በመዳኘት ይታወቃል። አንድ ቀን ግን ከንጉሱ ቤተሰቦች ጋር የጠበቀ ቁርኝት ያለው አንድ ባለሀብትና አንድ ምስኪን ገበሬ ፍርድ ፍለጋ ወደ እርሱ መጡ። ባለሀብቱ የገበሬውን ለም መሬት በሃይል ለመውሰድ ፈልጎ በሀሰት መስክሮበት ነበር። ፍርዱ ከመሰጠቱ በፊት ባለው ምሽት፥ ባለሀብቱ ወደ ዳኛ በየነ ቤት በምስጢር በመምጣት የወርቅ ከረጢት አስቀመጠለት። "ይህንን ውሰድና ለእኔ ፍረድልኝ፤ ንጉሱም ቢሆኑ ደስ ይላቸዋል፤ የወደፊት የስልጣን እጣ ፈንታህም ያምራል" አለው። ዳኛ በየነ በዚያች ምሽት እንቅልፍ አጣ። በአንድ በኩል ስልጣንና ሀብት፥ በሌላ በኩል ደግሞ የገበሬው እውነትና የገዛ ንፁህ ህሊናው ተፋጠጡ። በማግስቱ ፍርድ አደባባይ ላይ ህዝቡ ተሰብስቧል። ዳኛ በየነ በግርማ ሞገስ ወንበሩ ላይ ተቀመጠ። ሁሉም ባለሀብቱ እንደሚያሸንፍ ጠብቆ ነበር። ዳኛ በየነ ግን የወርቅ ከረጢቱን አውጥቶ በሰው ሁሉ ፊት አስቀመጠውና እንዲህ አለ፦ "ሰው ሰውን ሊያታልል ይችላል፤ ንጉስንም በሃሰት ማስደሰት ይቻላል። ነገር ግን ማንም ሰው ሊያመልጠው የማይችል አንድ ትልቅ ዳኛ አለ— እርሱም ንፁህ ህሊና ነው። ይህ ወርቅ እጆቼን ሊያበለጽግ ይችላል፥ ህሊናዬን ግን ያቆሽሸዋል። ህሊናው የቆሸሸ ሰው ደግሞ በየትኛውም የክብር ወንበር ላይ ቢቀመጥ እስረኛ ነው።" በማስከተልም ፍርዱን ለምስኪኑ ገበሬ ሰጠ። ባለሀብቱም በዕብሪቱና በጉቦኝነቱ ተቀጣ። ዳኛ በየነ ምንም እንኳን የወርቅ ክምችትና የባለስልጣናትን ሙገሳ ባያገኝም፥ በዚያች ምሽት ግን እንደ ህጻን ልጅ በሰላም ተኛ። ምክንያቱም ትልቁን የህሊና ፍርድ አሸንፎ ነበርና። የህይወት ትምህርት የሰው ልጅ ትልቁ ዳኛና መሪው ንፁህ ህሊናው ነው። ከሰው ብንሸሽ ከራሳችን መሸሽ አንችልም። እውነትና ቅንነት ሁልጊዜም ያሸንፋሉ።
የመላቀቅ መርሆች ("Principles of detachment") (ክፍል አራት) ይህንን ትምህርት ስንጀምር እንዲህ ብለን ነበር፡- ጤናማ ካልሆኑ ተጽዕኖዎች ለመላቀቅ በጣም ውጤታማ ከሆኑ መንገዶች አንዱ አንድን ነገር ማቆም ብቻ ሳይሆን፣ በምትኩ የተሻለ ነገር መተካት ነው። ዘላቂ ለውጥ የሚመጣው ዝም ብለን አሮጌ ልማዶችን ለማስወገድ ከመሞከር ይልቅ፣ ሆን ብለን አዳዲስ የአኗኗር ዘይቤዎችን ስንፈጥር ነው። ባለፈው የተመለከትናቸው፣ 1) “መርዛማ (Toxic) ከሆነ ወዳጅነት ወይም ግንኙነት መላቀቅ”፣ 2) ”ቁጥጥር ከሌለው 3) የማህበራዊ ሚዲያ አጠቃቀም መላቀቅ” የሚሉትን ነው፡፡ ዛሬ የምንመለከተው፣ “ጤናማ ካልሆኑ ልማዶች መላቀቅ” የሚለውን ነው ተግባራዊ ሐሳቦች ✅ ለልማዱ መንስኤ የሆነውን ነገር መለየት (ጭንቀት፣ መሰልቸት፣ ብቸኝነት፣ ፍርሃት)። ✅ ልማዱን ለማቆም ከመታገል በተጨማሪ በሌላ መልካም ልማድ ቀስ በቀስ መተካት። ✅ጤናማ ላልሆነውን ልማድ ተጋላጭ የሚያደርጉ ሰዎችን በመለየት ቀስ በቀስ መለየት። ✅ ጤናማ ላልሆነውን ልማድ ተጋላጭ የሚያደርጉ ቦታዎች በመለየት ቀስ በቀስ መቅረት። ✅ ፍጽምናን ከመጠበቅ ይልቅ በትንንሽ ድሎች መደሰትና ራስን ማበረታታት። ✅ ሲሳሳቱና ልማዱን ሲያደርጉ እንደገና መነሳትና መስተካከል፡፡ የራስ-በራስ ጥያቄ ❓ ጭንቀትና ፍርሃት ሲሰማኝ ወደ አጉል ልማድ ከመሄድ ይልቅ ስሜቱን በምን ማረጋጋት እችላለሁ? ❓ መሰልቸት ሲሰማኝ ወደ አጉል ልማድ ከመሄድ ይልቅ ምን ማድረግና የት መሄድ እችላለሁ? ❓ ብቸኝነት ሲሰማኝ ወደ አጉል ልማድ ከመሄድ ይልቅ ማን ጋር መደወል ወይም ማንን መግኘት እችላለሁ? Dr. Eyob Mamo
ሰው ላይ አትፍረድ... ምክንያቱም እያንዳንዱ ሰው በውስጡ አንተ ከማታየው እና ከማታውቀው ትልቅ የህይወት ውጊያ ጋር እየተጋደለ ሊሆን ይችላል:: ህይወት እንደዚህ እሽክርክሪት ናት፤ ዛሬ ላይ ታች ብትሆንም ነገ ደግሞ ወደ ላይ መውጣትህ አይቀሬ ነው። ዋናው ነገር በውስጥህ ያለውን እውነተኛነት እና ንጽህና ሳታጣ በፈገግታ መጓዝ ነው! መልካም እለተ ሰንበት❤️❤️
የመላቀቅ መርሆች ("Principles of detachment") (ክፍል ሶስት) ይህንን ትምህርት ስንጀምር እንዲህ ብለን ነበር፡- ጤናማ ካልሆኑ ተጽዕኖዎች ለመላቀቅ በጣም ውጤታማ ከሆኑ መንገዶች አንዱ አንድን ነገር ማቆም ብቻ ሳይሆን፣ በምትኩ የተሻለ ነገር መተካት ነው። ዘላቂ ለውጥ የሚመጣው ዝም ብለን አሮጌ ልማዶችን ለማስወገድ ከመሞከር ይልቅ፣ ሆን ብለን አዳዲስ የአኗኗር ዘይቤዎችን ስንፈጥር ነው። ባለፈው የተመለከትናቸው፣ 1) “መርዛማ (Toxic) ከሆነ ወዳጅነት ወይም ግንኙነት መላቀቅ” እና 2) ”ቁጥጥር ከሌለው የማህበራዊ ሚዲያ አጠቃቀም መላቀቅ” የሚሉትን ነው፡፡ ዛሬ የምንመለከተው፣ “አሉታዊ ተጽዕኖ ከሚያሳድሩ ቦታዎች መላቀቅ” የሚለውን ነው፡፡ አሉታዊ ተጽዕኖ ከሚያሳድሩ ቦታዎች መላቀቅ ተግባራዊ ሐሳቦች ✅ ሁልጊዜ ለመጥፎ ውሳኔዎችና ተግባሮች የሚያጋልጠንን ቦታዎች መለየት። ✅ አስፈላጊና ጠቃሚ ካልሆነ በስተቀር ወደዚያ አካባቢ ከመሄድ መቆጠብ። ✅ ጊዜን በጤናማ እንቅስቃሴዎችና ተግባሮች እንዲሞሉ ፕሮግራም ማውጣት። ✅ ለዕድገት በሚረዱ ቦታዎች ብዙ ጊዜ ማሳለፍ (መንፈሳዊ ቦታ፣ ቤተ መጻሕፍት፣ የአካል ብቃት ማዘውተሪያ ቦታዎች፣ ፓርኮች፣ በጎ ፈቃድ ሥራዎች) ✅ ጥበብ የተሞላበት ምርጫ ለማድረግ የሚያበረታቱ ሰዎችን (ተጠያቂነትን የሚሰጠን አጋር) ማዘጋጀት። ✅ ወደዚያ ስፍራ የመሄድ ስሜት ሲመጣ በቁርጠኝነት መቋቋም፡፡ የራስ-በራስ ጥያቄ ❓ መሄድ የማይገባኝ ተገቢ ያልሆነ ቦታ እንድሄድ ተጽእኖ ያደረገብኝ የስነ-ልቦና ፍላጎት ምንድን ነው? ❓ ወደዚያ ስፍራ ለመሄድ የምነሳሳው የትኛው ቀንና ሰዓት ነው? ❓በዚህ ቀንና ሰዓት ምን አይነት ነገር ላይ ማተኮር እችላለሁ? Dr. Eyob Mamo
የመላቀቅ መርሆች ("Principles of detachment") (ክፍል ሁለት) ይህንን ትምህርት ስንጀምር እንዲህ ብለን ነበር፡- ጤናማ ካልሆኑ ተጽዕኖዎች ለመላቀቅ በጣም ውጤታማ ከሆኑ መንገዶች አንዱ አንድን ነገር ማቆም ብቻ ሳይሆን፣ በምትኩ የተሻለ ነገር መተካት ነው። ዘላቂ ለውጥ የሚመጣው ዝም ብለን አሮጌ ልማዶችን ለማስወገድ ከመሞከር ይልቅ፣ ሆን ብለን አዳዲስ የአኗኗር ዘይቤዎችን ስንፈጥር ነው። ባለፈው የተመለከትነው፣ “መርዛማ (Toxic) ከሆነ ወዳጅነት ወይም ግንኙነት መላቀቅ” የሚለውን ነው፡፡ ዛሬ የምንመለከተው ”ቁጥጥር ከሌለው የማህበራዊ ሚዲያ አጠቃቀም መላቀቅ” የሚለውን ነው፡፡ ቁጥጥር ከሌለው የማህበራዊ ሚዲያ አጠቃቀም መላቀቅ ተግባራዊ ሐሳቦች ✅ አላስፈላጊ መተግበሪያዎችን (apps) ከስልክ መነሻ ገጽ ማስወገድ። ✅ አስፈላጊ ያልሆኑ ማሳወቂያዎችን (notifications) ማጥፋት። ✅ ዕለታዊ የስክሪን ጊዜ ገደብ ማውታትና በዚያ መመራት። ✅ በምግብ ሰዓት፣ በሥራ፣ በጸሎት እና ከቤተሰብ ጋር በሚሆኑበት ጊዜ ስልክን ማራቅ። ✅ ስልክ ከመነካካት ይልቅ በማንበብ፣ በአካል ብቃት እንቅስቃሴ ወይም ትርጉም ባለው ውይይት ጊዜ ማሳለፍ። ✅ማታ ከመኝታ በፊት እና ጠዋት ከተነሳን በኋላ የአንድ ሰዓት "ከማህበራዊ ሚዲያ ነፃ" ጊዜ ማበጀት። የራስ-በራስ ጥያቄ ❓ ማህበራዊ ሚዲያን የምጠቀምበት ሆን ብዬና አስቤበት ነው ወይስ በልምድ? ❓ ስልክ በመነካካት ሰበብ ከየትኛው ስሜት ለማምለጥ እየሞከርኩ ነው? ❓ይህ የማሕበራዊ ሚዲያ ድርጊት እረፍት ይሰጠኛል ወይስ ያደክመኛል?
የመላቀቅ መርሆች ("Principles of detachment") (ክፍል አንድ) ጤናማ ካልሆኑ ተጽዕኖዎች ለመላቀቅ በጣም ውጤታማ ከሆኑ መንገዶች አንዱ አንድን ነገር ማቆም ብቻ ሳይሆን፣ በምትኩ የተሻለ ነገር መተካት ነው። ዘላቂ ለውጥ የሚመጣው ዝም ብለን አሮጌ ልማዶችን ለማስወገድ ከመሞከር ይልቅ፣ ሆን ብለን አዳዲስ የአኗኗር ዘይቤዎችን ስንፈጥር ነው። ዛሬንና የሚቀጥሉትን ሶስት ቀናት የመላቀቅ መርሆችን ከአራት ዘርፍ ዙሪያ እንመለከታለን፡፡ መርዛማ (Toxic) ከሆነ ወዳጅነት ወይም ግንኙነት መላቀቅ መርዛማ ባህሪያ ካላቸው ሰዎች ጋር መቅረብና መቆየት ለሁለንተናዊ ጤንነታችን ጠንቅ ነው፡፡ ብዙ ሰዎች ግን ከመርዛማ ግንኙነት መላቀቅ ያስቸግራቸዋል፡፡ ተግባራዊ መመሪያዎች ✅ ሁሉም ግንኙነት ለዘላለም የሚቀጥል እንዳልሆነ መቀበልና ራስን ማዘጋጀት። ✅ ግልጽ የሆነን የቀይ መስመር (personal boundary) ማበጀትና ክልከላን ማድረግ መልመድ፡፡ ✅ ለመለየት ተገቢ በሚሆንበት ጊዜ ድንገት ከመጥፋት ይልቅ ግንኙነቱን ቀስ በቀስ መቀነስ። ✅ ጤናማ እና አበረታች ከሆኑ ሰዎች ጋር ብዙ ጊዜ ማሳለፍ። ✅ ራሱን መቀየር የማይፈልግን ሰው ለመቀየር በመሞከር ጊዜንና ስሜንት ከማባከን መቆጠብ። ✅ ከሁሉም በፊት የእኛ ሰላምና ጤንነት እንደሚበልጥ በማወቅ ያንን መጠበቅና ያንንም ማድረግ ራስ ወዳድነት አለመሆኑን ማስታወስ። የራስ-በራስ ጥያቄ ❓ ይህ ግንኙነት የምፈልገውን ሰው እንድሆን ያቀርበኛል? ❓ ክብር እና ዋጋ እንደተሰጠኝ ይሰማኛል? ❓ ከዚህ ሰው ጋር ጊዜ ካሳለፍኩ በኋላ ሁልጊዜ እጨነቃለሁ፣ እጸጸታለሁ ወይም በስሜት እደክማለሁ? Dr. Eyob Mamo