tgindex
DebreTabor Communication

DebreTabor Communication

Статистика

ይህ የደብረታቦር ኮሙኒኬሽን የቴሌግራም ቻናል ነው።ወቅታዊ፣ታሪካዊ እና ሌሎች አስተማሪ መረጃዎችን ያገኙበታል።

Последний пост
4 авг.
Последнее чтение
13 авг.
Постов за неделю
0
Всего постов
20
Тип
открытый
Язык
und
В каталоге с
13 авг.
Подписчики
799
0 за 2 дн.
Сутки
0
0,00%
Неделя
 
Месяц
 
Просмотров на пост
186
20 постов
Вовлечённость
23,3%
к подписчикам
Постов в день
0,0
всего 20
Упоминаний
0
каналов
Охват размещения
оценка
1/24сутки в ленте
171
1/48двое суток
195
1/72трое суток
211

Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.

Посты

  • без подписи

  • без подписи

  • без подписи

  • без подписи

  • በደብረታቦር ከተማ አስተዳደር ዘላቂ ሰላምን ለማረጋገጥና ለሀገዊ ተልዕኮ ዝግጁ ለመሆን ሲሰለጥኑ የቆዩ የደጀን ሀይል የፀጥታ አባላት ተመረቁ፤ ​ዘላቂ ሰላምና ደህንነት ለማረጋገጥ በሚደረገው ጥረት በደብረታቦር ከተማ አስተዳደር ለተከታታይ ቀናት ሲሰለጥኑ የቆዩ ጥምር የፀጥታ ኃይሎች ስልጠናቸውን አጠናቀው ተመርቀዋል። ተመራቂዎች ​የሀገርን ነፃነትና ሉዓላዊነት የማስጠበቅ ታሪካዊ አደራን የመጠበቅ ሃላፊነት እንዳለባቸው ተመላክቷል። የደብረታቦር ከተማ አስተዳደር ሰላምና ጸጥታ መምሪያ ኮማንደር አብራራው አበጀ እና የደብረታቦር ከተማ አስተዳደር ሚሊሻ መምሪያ ሃላፊ አቶ ብሩክ አለምነው በምረቃ ፕሮግራሙ ንግግር በማድረግ ተመራቂዎችን በጎዳና ላይ እንቅስቃሴም አበረታተዋል። ​ደብረታቦር ኮሙኒኬሽን ሀምሌ 28 ቀን 2018 ዓ/ም

  • без подписи

  • без подписи

  • без подписи

  • без подписи

  • "ጽዱ ኢትዮጵያ ለትውልድ" ሶስተኛ ዙር ሀገር አቀፍ የአካባቢ ብክለት መከላከል ንቅናቄ ማስጀመሪያ መርሃ ግብር በጽዳት ዘመቻ በደብረታቦር ከተማ አስተዳደር ተካሂዷል። ንቅናቄው ለተከታታይ ሶስት ወራት የሚቆይ ንቅናቄ መሆኑን እና ይህ ንቅናቄ ከተሞች የተሻለ ገጽታ እንዲኖራቸው ለማስቻል እንዲሁም ጤናማ ማህበረሰብ ለመፍጠር ታሳቢ ያደረገ እንደሆነ የደብረታቦር ከተማ አስተዳደር ጽዳትና ውበት ጽ/ቤት ሃላፊ አቶ መልሰው ዋለ ተናግረዋል።ሶስቱን የብክለት አይነቶች የሚባሉትን ማለትም ፕላስቲኮችን ማስወገድ፣ የኬሚካል አጠቃቀም ቁጥጥር እና የድምጽ ብክለት መከላከል ሥራ እንደሚሰራ የተናገሩት ሃላፊው በቀጣይም ተከታታይነት ባላቸው የግንዛቤ መፍጠሪያ መድረኮችና በጽዳት ዘመቻዎች ሞዴል ቀበሌና ክፍለ ከተሞችን ለመፍጠር ጭምር የተጀመሩ ስራዎች ውጤታማ እንዲሆኑ የሚሰራ ይሆናል ብለዋል። የደብረታቦር ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ አቶ ሀይለኢየሱስ ሰለሞን እንዳሉት ደብረታቦር ከተማ እንደ ታሪኳ ውብና ጽዱ ለማድረግ ከዘመቻ የጽዳትና የግንዛቤ ስራዎች ባሻገር ባህል አድርጎ መውሰድ እንደሚገባ ተናግረዋል።የፕላስቲክ ምርቶች በቀላሉ የማይበሰብሱና ለትውልድም ጭምር ስጋት ስለሆኑ ማስወገድና ሌሎች ምርቶችን መጠቀም እንደሚገባም አሳስበዋል። በጽዳት ዘመቻው የከተማ እና የክፍለ ከተማ አመራሮች፣የጽዳትና ውበት ሰራተኞች እንዲሁም የከተማ ሴፍቲኔት ተጠቃሚዎች ተገኝተዋል። ደብረታቦር ኮሙኒኬሽን ሀምሌ 28 ቀን 2018 ዓ/ም

  • без подписи

  • без подписи

  • без подписи

  • без подписи

  • የደብረታቦር ከተማ አስተዳደር ፖሊስ መምሪያ አዲሱን የደንብ ልብስ በየደረጃው ለሚገኙ የፖሊስ መዋቅርና አባላቶች አስተዋወቀ! በአማራ ክልል ፖሊስ ዋና ጠላቅላይ መምሪያ የደብረታቦር ከተማ አስተዳደር ፖሊስ መምሪያ ''በጀግነት መጠበቅ በሰብአዊነት ማገልገል'' በሚል መሪ ሀሳብ አዲሱን የደንብ ልብስ አስተዋውቋል። የኢትዮጵያን ብሄራዊ መዝሙር በመዘመርና ሰንደቅ አላማዋን በመስቀል የጀመረው ፕሮግራም የተለያዩ የጎዳና ላይ ትዕይቶችም ተከናውነዋል። የደብረታቦር ከተማ አስተዳደር ፖሊስ መምሪያ ሃላፊ ኮማንደር ያለው ዘለቀ ፖሊስ ከዘመኑ ጋር አሰራሩን እያዘመነ ወቅቱ የሚጠይቀውን ስራ ለመስራት ጥረት እያደረገ እንደሆነ በመግለጽ የደንብ ልብስ አንዱ የተቋሙ የክብር መገለጫ እንደሆነም አንስተዋል።ተቋማዊ ሪፎርሞች በቀጣይ የህዝብና የሀገርን አደራ ለመወጣት አስፈላጊ መሆናቸውን ያነሱት ኮማንደር ያለው ተቋሙ የህዝብ በህዝብና ለህዝብ የሚሰራ በመሆኑ ማህበረሰቡ የተለመደ አጋርነቱን እንዲያስቀጥል አሳስበዋል። የደብረታቦር ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ አቶ ሀይለኢየሱስ ሰለሞን የፖሊስ መዋቅር በየደረጃው ሪፎርሞችን እያከናወነ እንደሚገኝ አንስተዋል።በአለም አቀፍ ደረጃ ወንጀልን ለመከላከልና የዜጎችን ደህንነት በአስተማማኝ ሁኔታ ለመጠበቅ የላቀና የዘመነ የፖሊስ መዋቅርና አደረጃጀት አስፈላጊ መሆኑንም አንስተዋል።የፖሊስ መርህ ለገባው ቃልኪዳንና ለለበሰው ደንብ መሆኑን ያነሱት ምክትል ከንቲባው እንደ ከተማም ወንጀልን በመከላከልና በማክሸፍ ያሉ ጥንካሬዎችን ማስቀጠል ጎደሎዎችንም ተከታትሎ ማረም እንደሚያስፈልግ አሳስበዋል። እስካሁን የተሻለ አስተዋጽኦ ላበረከቱ የፖሊስ አባላት የማዕረግ እድገትና እውቅና ተሰጥቷቸዋል። ደብረታቦር ኮሙኒኬሽን ሀምሌ 28 ቀን 2018 ዓ/ም

  • без подписи

  • без подписи

  • без подписи

  • без подписи

  • በደብረታቦር ከተማ አስተዳደር “ተስፋን እንትከል” በሚል መሪ መልእክት የአንድ ጀምበር አረንጓዴ አሻራ መርሀ ግብር በንቅናቄ ተካሄደ፡፡ በከተማ አስተዳደሩ ወይብላ ሰላምኮ ቀበሌ አንጓ ተፋሰስ ላይ የተለያዩ የማህበረሰብ ክፍሎች የተሳተፉበት የአንድ ጀምበር አረንጓዴ አሻራ መርሀ ግብር በንቅናቄ ተካሂዷል፡፡ በመርሀ ግብሩ ላይ የመንግስት የስራ ሀላፊዎች፣ የሐይማኖት አባቶች፣ አርሶ አደሮች፣ የመንግስት ሰራተኞች፣ በጎ ፈቃደኛ ወጣቶች እና ሌሎችም የህብረተሰብ ክፍሎች ተሳታፊ ሁነዋል፡፡ በችግኝ ተከላው ላይ ከተሳተፉ የህብረተሰብ ክፍሎች መካከል ቄስ ሲሳይ ማሞ እና ወ/ሮ አዝመራ ጌቴ በሰጡት አስተያየት ደን የአየር ንብረት ለውጥን ለመከላከል፣ የአፈር መሸርሸርን ለማስቀረት እና ሌሎችም ጥቅሞች ያሉት በመሆኑ ችግኝ መትከላቸውን ገልፀው የተከልናቸውን ችግኞች ተንከባክበን በማሳደግ ለአገልግሎት እንዲውሉ እናደርጋለን ብለዋል፡፡ በባለፉት ዓመታት የተከሏቸው ችግኞች ዘርፈ ብዙ አገልግሎት እየሰጧቸው መሆኑንም አንስተው ዛሬ የተከሏቸው ችግኞች ነገ ለልጆቻቸው ትልቅ ፀጋ በመሆናቸው እንደ ልጆቻቸው ተንከባክበው እንደሚያሳድጓቸውም ተናግረው ሁላችንም በተከልነው አግባብ ችግኞችን ተንከባክበን ማሳደግ አለብን ብለዋል፡፡ የደብረታቦር ከተማ አስተዳደር ግብርና መምሪያ ሀላፊ አቶ ጌታቸው ይበልጣል እንደገለጹት እንደ ከተማ አስተዳደር በአንድ ጀምበር የአረንጓዴ አሻራ መርሀ ግብር በአራቱም የገጠር ቀበሌዎች በአምስት ተፋሰስ ላይ የችግኝ ተከላ እየተካሄ እንደሚገኝ ጠቅሰው 308 ሽህ ችግኞች እንደሚተከሉም አሳውቀዋል፡፡ በባለፉት ዓመታት በተካሄደው የአረንጓዴ አሻራ መርሀ ግብር የስነ ምህዳር ለውጥ መምጣቱን፣ ምርትና ምርታማነት መጨመሩን፣ ለአርሶ አደሮችና ለወጣቶች የስራ እድል መፈጠሩንም ገልፀው የተተከሉትን ችግኞች ህብረተሰቡ በባለቤትነት እንዲይዛቸው በመደረጉ በጥሩ ሁኔታ እንደሚገኙ ተናግረዋል፡፡ የደብረታቦር ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ አቶ ሀይለኢየሱስ ሰለሞን እንዳሉት እንደ አገር እና እንደ ከተማ አስተዳደር በባለፉት ተከታታይ ዓመታት የአረንጓዴ አሻራ መርሀ ግብር ሲካሄድ መቆየቱን አውስተው የተተከሉት ችግኞች የመጽደቅ ምጣኔ በጥሩ ደረጃ ላይ እንደሚገኝ ገልፀዋል፡፡ የአርንዴ አሻራ መርሀ ግብሩ ዘርፈ ብዙ ፋይዳ ያለው በመሆኑ እና ለመጭው ትውልድ የተሻለች አገር ለማስረክብ ምቹ ሁኔታ የሚፈጥር ስለሆነ በተጠናከረ መንገድ መቀጠሉን አንስተው ከደን ችግኝ ባለፈ የተለያዩ አትክልትና ፍራፍሬ ችግኞችን በመትከል ማህበረሰቡ ተጠቃሚ እንዲሆን እየተሰራ ይገኛል ብለዋል፡፡ በተያያዘም በደብረታቦር ከተማ አስተዳደር በዚህ ዓመት የአረንጓዴ አሻራ መርሀ ግብር ከ1 ነጥብ 5 ሚሊየን በላይ ችግኞችን ለመትከል በእቅድ ተይዞ እየተሰራ እንደሚገኝ ተገልጿል፡፡ ደብረታቦር ኮሙኒኬሽን ሐምሌ 27 ቀን 2018 ዓ/ም