ETHIO FACTS- እውነታዎች
Статистикаወቅታዊና ትክክለኛ መረጃዎችን ያገኛሉ።Join ያድርጉ ፣ ለጓደኛዎ ያጋሩ።ቤተሰብ ስለሆኑ ከልብ እናመሰግናለን።ሊንኩን ይጫኑ https://t.me/ethiofacts27
- Последний пост
- 18 нояб.
- Последнее чтение
- 13 авг.
- Постов за неделю
- 0
- Всего постов
- 30
- Тип
- открытый
- Язык
- ti
- В каталоге с
- 13 авг.
- 1/24сутки в ленте
- —
- 1/48двое суток
- —
- 1/72трое суток
- —
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
የኪራይ ግብር‼️ ከኪራይ በሚገኝ ገቢ ላይ ተፈጻሚ የሚሆኑ ምጣኔዎች‼️ የፌዴራል የገቢ ግብር አዋጅን ለማሻሻል በወጣ አዋጅ ቁጥር 1395/2017 ላይ በግለሰቦች ኪራይ ገቢ ላይ ተፈፃሚ የሚሆኑ የግብር ምጣኔዎች ከላይ ተቀምጠዋል፡፡
без подписи
አሳሳቢ መረጃ‼️ በጂንካ ከተማ 2 የጤና ባለሙያዎችን ጨምሮ 5 ሰዎች ምንነቱ በውል ባልታወቀ በሽታ በሳምንት ውስጥ መሞታቸው እያነጋገረ ይገኛል። ሟቾቹ ተመሳሳይ ምልክት እንደነበራቸው ተነግሯል። ጤና ሚኒስቴር በበኩሉ በደቡብ ኢትዮጵያ Hemorrhagic fever እንደተከሰተ መረጃ ሰጥቷል። ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ሌላ ተጨማሪ መግለጫ እስከሚሰጥ ድረስ፤ ለመከላከል የሚከተሉትን ምክረ-ሃሳቦች እና ጥንቃቄዎች ተግባራዊ እንዲያደርጉ አሳስቧል፡፡ • በአፍ፣አፍንጫ እና ሌሎች የሰውነት ክፍሎች የመድማት፣ትኩሳት፣ማስቀመጥ እና ማስመለስ ምልክት ሲኖር ወደ ህክምና ተቋማት መሄድና በወቅቱ የላቦራቶሪ ምርመራ ማድረግ፣ • ምልክት ከታየበት ማንኛዉም ሰዉ ጋር ንክኪ በሚኖርበት ጊዜ ራስን የመከላከያ ዘዴዎችን መጠቀም፣ • ሁልጊዜ እጅን በሳኒታይዘር ወይም በውሃና በሳሙና በመታጠብ ማጽዳት፣ • ማንኛውም ጤና ተቋም በታካሚዎች ልየታ አካባቢ ልዩ ትኩረት በመስጠት የቫይራል ሄሞሬጅክ ፊቨር (Viral Hemmoragic fever) መሰል በሸታ መለየት፣ መመርመር፣ ማከም እና ሪፖርት ማድረግ ያስፈልጋል።
እነዚህ ስደተኞች በህገወጥ መንገድ ወደ ሳውዲ አረቢያ ለመግባት በየመን እና በሳውዲ ድንበር ላይ የሚገኙ ስደተኞች ሲሆኑ ቁጥሩ እጅግ አስደንጋጭ ነው። የየመን ዜጎች የስደተኞቹን ብዛት አስመልክቶ ምስሉን እየተቀባበሉት ይገኛሉ።
без подписи
የታሸጉ ምግቦች አያዘውትሩ‼️ " በአሁኑ ሰአት ከወጣቶች በዘለለ እድሜያቸው 12 እና 13 የሆኑ ህፃናት በስኳር በሽታ ኩላሊታቸው እንዳይሰራ እየሆነ ነው። ለዚህም ዋነኛ ምክንያቱ የስኳር እና የጨው ይዘት ያላቸው የታሸጉ ምግቦች ናቸው " - የኢትዮጵያ የኩላሊት ንቅለ ተከላ ማህበር ተላላፊ ላልሆኑ በሽታዎች የሚያጋልጡ የታሸጉ ምግቦችን ለመቆጣጠር የሚያስችል አዋጅ ተዘጋጅቷል። አዋጁ መዘጋጀቱን ተከትሎ ፦ - የተዋልዶ ጤና አገልግሎት ሰጭ ማህበራት ህብረት (CORHA)፣ - የኢትዮጵያ የልብ ማህበር፣ - የኢትዮጵያ የስኳር በሽታ ማህበር እና የኢትዮጵያ የኩላሊት ንቅለ ተከላ ማህበር በጋራ በመሆን ከቀናት በፊት ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተው ነበር። የኢትዮጵያ የኩላሊት ንቅለ ተከላ ማህበር ሰብሳቢ አቶ ቢኒያም አበራ " በአሁኑ ሰአት ከወጣቶች በዘለለ እድሜያቸው 12 እና 13 የሆኑ ህፃናት በስኳር በሽታ ኩላሊታቸው እንዳይሰራ እየሆነ ነው " ብለዋል። " ለኩላሊት በሽታዎች ዋነኛ ምክንያቱ የስኳር እና የጨው ይዘት ያላቸው የታሸጉ ምግቦች ናቸው " ሲሉም ገልፀዋል። አቶ ቢኒያም አበራ በዝርዝር ምን አሉ ? " በማህበራችን ውስጥ አብዛኛው ኩላሊታቸው የተጎዱ ሰዎች ለኩላሊታቸው መጎዳት ዋነኛ ምክንያት የሆነው ደም ግፊት እና የስኳር በሽታዎች ናቸው። እነዚህ በሽታዎች ደግሞ ሙሉ በሙሉ በሚባል ደረጃ ከአመጋገብ ስርአት ጋር የተገናኙ ናቸው። ምክንያቱም የታሸጉ ምግቦች በአብዛኛው የስኳር እና የጨው ይዘት አላቸው። በተለይ ደግሞ በፋብሪካ የሚቀነባበሩ ምግቦች በውስጣቸው በምግብ ማቀነባበር ስርአት ውስጥ የተጠራቀመ የስብ ክምችት አለ። ይህ የሚጨመር ስኳር ሰዎች በሚመገቡበት ጊዜ በከፍተኛ ፍጥነት ወደ ሰውነት ውስጥ ከፍተኛ የስኳር መጠን እንዲገባ ያደርጋል። ይህ በሰውነታችን ውስጥ ያለውን የስኳር መጠን ያዛባዋል፤ በዚህም የስኳር በሽታ እንዲከሰት ያደርጋል። በምግብ ውስጥ የሚጨመር ንጥረ ነገር ደግሞ የደም ግፊትን ያመጣል። በመሆኑም ኩላሊት ስራውን በአግባቡ እንዳይሰራ ያዳክሙታል። በመጨረሻም ሙሉ በሙሉ በሚባል ደረጃ ኩላሊት ስራውን እንዳይሰራ ያደርጋል። እነዚህ ነገሮች በተናጠልም ሆነ በድምር በርካታ ቁጥር ያላቸውን ዜጎች እያጠቁ ያሉ ንጥረ ነገሮች ናቸው። ስለዚህ እነዚህን ንጥረ ነገሮች ወደ ዜጎች በሚመጡበት ጊዜ ቁጥጥር ሊደረግባቸው ይገባል። በታሸጉ ምግቦች ሽፋን ላይ በውስጣቸው የያዙት ንጥረ ነገር በአይነት እና በመጠን ሊገለጽ እንዲሁም ሰዎች እነዚህን ሲመገቡ ሊደርስባቸው የሚችሉ ጉዳቶች በመሸፈኛቸው ላይ በጉልህ መቀመጥ አለባቸው። በታሸጉ ምግቦች ላይ በቂ ቁጥጥርና ጥበቃ ሊደረግ ይገባል። እነዚህ ምግቦች በማህበረሰባችን ላይ እያደረሱት ያለው ጉዳት እና ቀውስ ለመቀነስ ማህበራችን ይህ አዋጅ ቶሎ ተፈጻሚ እንዲሆን ይሰራል " ብለዋል። የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የስነ ምግብ ህክምና ባለሙያ እና የኢትዮጵያ ስነ ምግብ ህክምና ባለሙያዎች ማህበር ተወካይ የሆኑት ዶ/ር ዘላለም ከበደ " ኢትዮጵያ በፋብሪካ በተቀነባበሩ እና ጤናማ ባልሆኑ ምግቦች ምክንያት ለሚደርሱ የጤና ጉዳቶች በየዓመቱ ከ31 ቢሊየን ብር በላይ ታወጣለች " ሲሉ ተናግረዋል። አያይዘውም " በየስአቱ 25 ሰው ተላላፊ ባልሆኑ በሽታዎች ማለትም በስኳር፣ በኩላሊት፣ በጉበት እና በልብ እንዲሁም በደም ቧንቧ በሽታዎች ይሞታሉ፣ በአሁኑ ስአት የህመሙ ጫና ከ52 በመቶ በላይ ሆኗል " ነው ያሉት። " የምግብ ጥራትን ማረጋገጥ ያስፈልጋል። ምክንያቱም በርካታ ሰዎች የታሸጉ ምግቦች ጥሩ እየመሰሏቸው ሲገዙ ይታያል። ይህ በጥናት መረጋገጥ አለበት። ማህበረሰቡ ባለው የግንዛቤ ክፍተት ምክንያት እየተጠቀመ እየተጎዳ ነው " ብለዋል። " ማህበረሰቡ በአዋጁ መሰረት ክልከላ የሚደረግባቸው የስብ፣ የስኳር እና የጨው መጠናቸውን ያልጻፉ የታሸጉ ምግቦችን ሲያዩ ለሚመለከተው አካል ማሳወቅ አለባቸው። አዋጁ ቶሎ ወደ ተግባር ገብቶ ክፍተቶቹ እየታዩ መስተካከያ ሊደረግበት ይገባል " ሲሉ ገልጸዋል። ቲክቫህ
без подписи
без подписи
ሰራተኞች የሚቀነሱት አግባብ‼️ የመንግስት ሰራተኞች የተሻሻለው አዋጅ 1353/2017 ስለ መንግስት ሰራተኞች ቅነሳ ምን ይላል። ክፍል አስራ አራት አንቀፅ 139 የሠራተኛ ቅነሳ: 1. ማንኛውም የመንግስት ሠራተኛ (ሀ). የሥራ መደቡ ሲሰረዝ፣ (ለ). መሥሪያ ቤቱ ሲዘጋ፣ (ሐ). ትርፍ የሰው ኃይል ሲኖር፤ እና (ሠ). ያለ በቂ ምክንያት ዝውውርን ካልተቀበለ፡፡ በዚህ አዋጅ አንቀፅ 55/1 መሠረት ለመደልደል ካልተቻለ ወይም የመንግስት ሠራተኛው ዝቅ ባለ የሥራ ደረጃ ላይ ለመሥራት ፍቃደኛ ካልሆነ ይቀነሳል፡፡ 2. በዚህ አንቀፅ ንዑሰ አንቀፅ 1 (ሐ)መሠረት ቅነሳ የሚደረገው የመንግስት ሠራተኛው በመሥሪያ ቤቱ ውስጥ በተመሳሳይ የሥራ መደብ ላይ ካሉ ሌሎች የመንግሰት ሠረተኞች ጋር ሲወዳደር በሥራ ውጤቱና ባለው ችሎታ ዝቅተኛ መሆኑ ሲረጋገጥ ነው።
ከባድ የመሬት መንቀጥቀጥ‼️ ዛሬ ጥቅምት 16/2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 2:24 ደቂቃ ላይ በአፋር፣በሸዋሮቢት፣በደብረሲና በደብረብርሃን፣በአዲስ አበባ፣በኮምቦልቻ፣በምንጃር እና በአዳማ ከበድ ያለ የመሬት መንቀጥቀጥ ተከስቷል። መነሻው(epicenter) በአፋር ክልል አዋሽ ፈንታሌ ሲሆን በሬክተር ስኬል 4.8 ተለክቷል።
без подписи
без подписи
አዲሱ አዋጅ‼️ሼር❗ የመንግስት ሰራተኞች አዲሱ አዋጅ ቁጥር 1353/2017 ምን ይላል? For your understanding. ከባድ የዲሲፕሊን ቅጣት የሚያስከትሉ ጥፋቶች አንቀፅ 69/5 አዋጁ እንዲህ አስቀምጦታል። +++++++++++++++++++++++++ 1.ሕጋዊ_ትእዛዝን ባለማክበር፣ በቸልተኝነት፣ በመልገም፣ ወይም ሆነ ብሎ የአሠራር ሥነ-ሥርዓት ወይም የመንግስትን ፖሊሲ ባለመከተል በሥራ ላይ በደል ማድረስ፤ 2. ጉዳዮችን ሆን ብሎ ማዘግየት ወይም ባለጉዳዮችን ማጉላላት፤ 3. ሥራ እንዳይሠራ ሆን ብሎ ማወክ ወይም ከሚያውኩት ጋር መተባበር፤ 4. በቀላል የዲስፕሊን ቅጣት እርምጃዎች ባለመታረም ያለበቂ ምክንያት በተደጋጋሚ ከሥራ መቅረት ወይም የሥራ ሰዓት አለማክበር፤ 5. በሥራ ቦታ በጠብ አጫሪነትን መደባደብ፤ 6. በልማዳዊ ስካር ወይም በአደንዛዥ ዕፅ ሱስ በመመረዝ ሥራን መበደል፤ 7. ጉቦ መቀበል ወይም እንዲሰጠው መጠየቅ፤ 8. በሥራ ቦታ ለሕዝብ ሞራል ተቃራኒ የሆነ ድርጊት መፈጸም፤ 9. የሌብነት ወይም የእምነት ማጉደል ድርጊት መፈጸም፤ 10.የማታለል ወይም የማጭበርበር ድርጊት መፈጸም፤ 11. በመሥሪያ ቤቱ ንብረት ላይ ሆን ብሎ ወይም በቸልተኝነት ጉዳት ማድረስ፤ 12. በሥልጣን አለአግባብ መጠቀም፤ 13. በሥራ ቦታ ላይ ፆታዊ ትንኮሳ ወይም ጥቃት መፈፀም እና 14.በዚህ አንቀፅ ከተዘረዘሩት ጋር ተመሳሳይ ክብደት ያለው ሌላ የዲሲፕሊን ጉድለት መፈፀም ። ++++++++++++++++++++++++++ አንቀፅ 72/1 እና 2 ሠራተኛን ከሥራ አግዶ ስለማቆየት 1.ማንኛውም የመንግስት ሠራተኛ ከሥራ አግዶ ማቆየት የሚቻለው (ሀ)ከተጠረጠረበት ጉዳይ ጋር አግባብነት ያላቸውን ማስረጃዎች በማበላሸት:በመደበቅ ወይም በማጥፋት ምርመራውን ያሰናክላል (ለ)በመንግስት ንብረት ላይ ተጨማሪ ጉዳት ያደርሳል (ሐ)ከተከሰሰበት ጥፋት ክብደት አንፃር የሌሎችን ሰራተኞች ሞራል የሚነካ ወይም የተገልጋዩን ሕዝብ በመሥሪያ ቤቱ ላይ ሊኖረው የሚገባውን እምነት ያዛባል (መ)ተፈፀመ የሚባለው ጥፋት ከሥራ ያስወጣል ተብሎ ሲገመት ነው 2.በዚህ አንቀፅ ንዑስ አንቀፅ (1) መሰረት አንድ ሠራተኛ ከሥራና ከደሞዝ ታግዶ ሊቆይ የሚችለው ከሁለት ወር ለማይበልጥ ጊዜ ይሆናል። ሰቭል ሰርቭስ ኮሚሽን
ምርጫው ይራዘማል❓👇👇 የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ስባተኛውን ሀገራዊ የምርጫ ሰሌዳ በሚመለከት የፖለቲካ ፓርቲዎችን ለማወያየት ለጋዜጠኞች ዝግ የሆነ ስብሰባ ትናንት አድርጎ ነበር፣ ይሁንና ፓርቲዎቹ በጊዜ ሰሌዳው ላይ ከመወያየታችን በፊት የሀገሪቱ ሰላምና ፀጥታ ነፃ ምርጫ ለማድረግ አስቻይ አይደለም የሚል መከራከሪያ አቅርበዋል። የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ሰባተኛው አገር ዓቀፍ ምርጫ የሚካሄድበትን ረቂቅ የጊዜ ሰሌዳ ለፖለቲካ ፓርቲዎች ለውይይት ባቀረበበት ወቅት ተቃውሞ እንደገጠመውም ተሰምቷል። ለጋዜጠኞች ዝግ የነበረው የቦርዱ እና የፖለቲካ ፓርቲዎች ተወካዮች ወይይት ዋና አጀንዳ የምርጫው ማካሄጃ ረቂቅ የጊዜ ሰሌዳ ቢሆንም፣ የውይይቱ ተሳታፊ የፖለቲካ ፓርቲዎች ተወካዮች ግን በአገሪቱ ምርጫ ለማካሄድ ከሰላምና ጸጥታ እንዲሁም ከፖለቲካ ምኅዳር ጋር የተያያዙ አስቻይ ሁኔታዎች በመኖር አለመኖራቸው ላይ ቦርዱ እና ፓርቲዎች ከስምምነት ላይ ባልደረሱበት ሁኔታ በምርጫ ማካሄጃ የጊዜ ሰሌዳ ላይ መነጋገር አንችልም በሚል ተቃውሞ አሰምተዋል። የፖለቲካ ፓርቲዎቹ ተወካዮች ግን ኢትዮጵያ ከሰላምና ጸጥታ አንጻር አሁን ባለችበት ነባራዊ ሁኔታ ነጻ እና ፍትሃዊ አገር ዓቀፍ ምርጫ ማካሄድ የሚያስችላት ቁመና ላይ አይደለችም በማለት የምርጫ ቦርድ አመራሮችን እንደሞገቱ ከምንጮች ተረድተናል። አብዛኞቹ ፓርቲዎች በተለይ በአማራ፣ ኦሮሚያና ትግራይ ክልሎች ያሉት የጸጥታ ሁኔታዎች ነጻ እና አሳታፊ ምርጫ ለማካሄድ አስቻይ አይደሉም የሚል አቋም ይዘው ከስብሰባው ተበትነዋል ተብሏል ። ዋዜማ
በደመወዝ ብድር‼️ መንግስት ሰራተኞች ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የገንዘብ ብድር አወሳሰድ እና አመላለስ ሂደት‼️ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ለመንግስት ሰራተኞች ያለ ምንም መነሻ ዋስትና በደመወዙ ልክ እስከ 150,000 ብር የዲጅታል ብድር አገልግሎት እንዲያገኙ ለማድረግ መመሪያ ማዘጋጀቱን ይታወሳል። ይህንን ገንዘብ ለመበደር የCEB Birr ተጠቃሚ መሆን የሚያስፈልግ ሲሆን፣ባንኩ ከደመወዝ ከፋይ ፋይናንስ ጋር በሚኖረውን ስምምነት መሠረት፣ ተበዳሪ አካል ባለበት ሆኖ፣በCEB Birr አማካይነት አገልግሎቱን የሚያገኝ ይሆናል። ለዚህም የብድር አወሳሰድ እና አመላለስ ሂደት እንደሚከተለው ቀርቧል ። 👉 የግማሽ ወር ደመወዝ የሚበደር ሰው፣በአንድ ወር ውስጥ ተመላሽ የሚደረግ ሲሆን ፣ ወለድ 3% ይሰላል። 👉 የአንድ ወር ደመወዝ ሲበደሩ.. ወለድ 8% የመመለሻ ጊዜ 3 ወር፤ 👉የሁለት ወር ደመወዝ ሲበደሩ..ወለድ 14% የመመለሻ ጊዜ 6 ወር፤ 👉የሶስት ወር ደመወዝ ሲሆን፣ ወለድ 17% በዘጠኝ ወር፤ 👉የአራት ወር ደመወዝ ለሚበደር ወለድ 20% በአንድ አመት። ማነኛውም የመንግስት ሠራተኛ ያለምንም ማስያዣ፣በዲጂታል ሲስተም ብቻ ባለበት ሆኖ፣የብድር አገልግሎቱን ማግኘት የሚችል ሲሆን፣የደመወዝ መደበኛ ሂሳብ(account ) በስልክ ቁጥር (CEB Birr) የሚተካ ይሆናል። ማነኛውም ተጨማሪ መረጃ የሚፈልግ ሰው ይህንን አግልግሎት ወደ ጀመሩ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፍ በአካል በመገኘት በቂ መረጃ እና ማብራሪያ ማግኘት እንደሚቻል ይህንን የብድር አገልግሎት ከጀመሩ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፎች ያገኘነው መረጃ ይጠቁማል ።
👉#ለሊት_እንቅልፍ_የለኝም‼️ "አሁን ኢትዮጵያ ያለችበት ሁኔታ ያሳስበኛል፤ እኔ አሁን 86 ዓመት ሊሞላኝ ነው፤ ለሊት እንቅልፍ የለኝም ፥ ለ 2 ሠዓታት ብተኛ ነው ቀሪውን አለቅስበታለሁ። ለምንደነው ብዙ ለማንቆይበት የምንጋደለው!? ለምንስ ነው የምንጫረሰው!? በጣም ያሳስበኛል ያስለቅሰኛል!" ሰውነት ይቀድማል! ‹‹ሰው ሁኑ! ቅድሚያ ሰውነት ይቀድማል! ከሐይማኖት ሰውነት ይቀድማል! ከዘርም ሰውነት ይቅደም! አላህ ሰውን ከሁሉ በላይ አልቆታል:: ሰው ሊገፋ፣ ሊሰደድ፣ ሊገደል፣ ሊናቅ፣ ሊወገዝ በፍፁም አይገባም:: ልዩ ፍጥረቴን ክብሩን ጠብቁት በማለት አዟል›› የክብር ዶክተር፣ተቀዳሚ ሙፍቲ ሃጂ ዑመር እንድሪስ
ግሪሳ ወፍ‼️ በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋና ኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር ዞኖች የግሪሳ ወፍ መንጋ ተከስቷል❗ -የኬሚካል ርጭት በአፋጣኝ ይከናወናል ተብሏል የግብርና ሚኒስቴር በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ እና ኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር ዞኖች የተከሰተውን የግሪሳ ወፍ መንጋ ለመከላከል እየተሰራ መሆኑን ገለጸ።ዘንድሮ የተከሰተው የወፉ መንጋ ከተጠበቀው ጊዜ አስቀድሞ በመሆኑ በደረሰ የመኸር ሰብል ላይ የከፋ ጉዳት እንዳያስከትል ርብርብ እየተደረገ ነው ተብሏል፡፡ በዚህ መሰረትም የአካባቢው አርሶ አደሮች የወፍ መንጋውን በባህላዊ መንገድ በወንጭፍና ድምፅ በማሰማት ለመከላከል ጥረት እያደረጉ እንደሚገኙ የኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር ዞን ግብርና መምሪያ ም/ሃላፊ ሃሰን ሰይድ ለመንግስት መገናኛ ብዙኃን ተናግረዋል፡፡ በብሔረሰብ አስተዳደሩ ጂሌ ጥሙጋና ደዋ ጨፋ ወረዳዎች ላይ የወፉ መንጋ በስፋት መታየቱን አመልክተዋል። በአማራ ክልል የሰሜን ሸዋ ዞን ግብርና መምሪያ የሰብል ልማት ቡድን መሪ አበበ ጌታቸው ፥ የግሪሳ ወፍ መንጋ በተወሰኑ የዞኑ ወረዳዎች መከሰቱን ተናግረዋል። የሰብል ምርታማነት ላይ ተጽዕኖ የሚያስከትሉ ችግሮችን ለመቆጣጠር የሚያስችል ዝግጁነት እንዳለ የተገለጸ ሲሆን፤ የግሪሳ ወፍ መንጋው ጉዳት እንዳያስከትል የሎጂስቲክ ማጓጓዝ ሥራ እየተከናወነ ነው ብለዋል።የኬሚካል ርጭቱ በአፋጣኝ የሚከናወን መሆኑንም አቶ ከበደ አመልክተዋል።
без подписи
ይሄን መረጃ ሼር አድርጉት‼️ የአይን ስፔሻሊስት ሃኪሞች ሞባይል ስልክ የሚያመጣብን ጣጣ የአይን ማኩላር እርጅና እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ እድሜአቸው በገፋ ሰዎች ላይ ብቻ ነበር የሚታየው። ✅አሁን ግን ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ከ30 እስከ 40 አመት የሆኑ ወጣቶች ሁሉ ‘ማኩላር ዲጀኔሬሽን’ የተባለና ወደ አይነ ስውርነት የሚያደርስ ሕመም እየተጠናወታቸው መጥተዋል ይላሉ የሲንጋፖር የአይን ሕክምና ሆስፒታል ዋና ዳይሬክተር ፕሮፌሰር ሊሊ። ✅ይሄም የሆነበት ማክንያት ብዙ ሰዎች ማታ መብራት ካጠፉ በኋላ ተንቀሳቃሽ ስልክ እየከፈቱ ያያሉ። በጭለማ ውስጥ ወይም ጨለም ባለ አካባቢ የሞባይል ስልክን ለ30 ደቂቃ እንኳን መጠቀም መታረም የማይችል አደጋ ውስጥ የሚከት ነው። ሕመሙም ካታራክት አይነት ሕመም ማስከተል ብቻ ሳይሆን የአይን ካንሰርም ያስከትላል። ✅ይህ ደግሞ ደግሞ መድሃኒት የሌለው በመሆኑ አይን ሲጠፋ ብቻ ቁጭ ብሎ መመልከት ነው ይላሉ ሃኪሙ።ይህን መልዕክት ያስተላለፉት 254 የሚሆኑ የአይን ስፔሻሊት ሃኪሞች አንድ ላይ በመሆን ነው። ✅ብዙ ሰዎች ማታ አልጋቸው ላይ ሆነው መብራት አጥፍተው ወይም ፈዘዝ ባለ መብራት ተንቀሳቃሽ ስልካቸውን እንደሚጠቀሙ ስለሚታወቅ ራሳችሁን ከማይድን ሕመም ጠብቁ ብለዋል። 👉ለወዳጅም ሼር ማድረግዎን በፍፁም እንዳትረሱ።
በደመወዝ ጭማሪ ሰበብ ዋጋ ያናሩ ከ57 ሺህ በላይ ነጋዴዎች ላይ ርምጃ ተወሰደ * ለመንግሥት ሠራተኞች ደመወዝ ተጨምሯል በሚል ሰበብ ዋጋ ያናሩ 57 ሺህ 212 ነጋዴዎች ላይ ሕጋዊ ርምጃ መወሰዱን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር አስታወቀ። የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር እና የተጠሪ ተቋማት የ2018 በጀት ዓመት የ1ኛ ሩብ ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም ገምግመዋል። በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የንግድ ስርዓትና ላይሰንሲንግ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤት አብዱል ሃኪም ሙሉ (ዶ/ር) ባቀረቡት ሪፖርት በሩብ ዓመቱ ንግድን ሥርዓት ለማስያዝ የተለያዩ ሥራዎች ሲከናወኑ መቆየታቸውን አብራርተዋል። በዚህም ለመንግሥት ሠራተኞች ደመወዝ ተጨምሯል በሚል ሰበብ ዋጋ ያናሩ 57 ሺህ ሺህ 212 ህገ ወጥ ነጋዴዎች ላይ እርምጃ ተወስዷል ብለዋል።