ወራቤ[ ደርሶች እና ፈዋኢዶች ]
Статистикаበሰለፊይ ኡስታዞች በሀገራችኝ በተለያዩ አከባቢዎች በሚገኙ መስጂዶች፣መርከዞች የሚሰጡ ደርሶች፣ኮርሶች፣ሙሓዳራዎች፣ እና የቁርዓን ተፍሲሮች እና ሙስሊሞችን የሚመለከት ልዩ ልዩ ወቅታዊ ጉዳዮች የሚለቀቁበት ቻናል ነው ። { وَقُل رَّبِّ زِدْنِى عِلْمًا } سورة طه : ١١٤ [ " ጌታዬ ሆይ! እውቀትንም ጨምርልኝ" በል። ] ሱረቱ-ጧሃ: 114
- Последний пост
- 12 авг.
- Последнее чтение
- 13 авг.
- Постов за неделю
- 2
- Всего постов
- 21
- Тип
- открытый
- Язык
- und
- В каталоге с
- 13 авг.
- 1/24сутки в ленте
- 263
- 1/48двое суток
- 301
- 1/72трое суток
- 325
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
📣 የምስራች ለትምህርት ፈላጊዎች በሙሉ! የኡስታዝ ኢማዱዲን ጀውሀር የቁርኣን ተፍሲር እና የኪታብ ትምህርቶች በጥራት፣ በየቀኑ በድምፅ እዲሁም ጠቃሚ ጽሁፎች የሚለቀቅበት አዲስ ኦፊሻላዊ የቴሌግራም ቻናል ተዘጋጅቷል። 🎙 በቻናሉ የሚያገኙኣቸው👁🗨፦ • የቁርኣን ተፍሲር (ቃላት እና ሰፊ ማብራሪያ) • ልዩ ልዩ የኪታብ ትምህርቶች • አጫጭርና አስተማሪ የድምፅ እና የጽሁፍ መልእክቶች 🔗 ከላይ ያለው ድምፅ ተቀንጭቦ የቀረበ ነው ድምፁን እና ትምህርቱን ሙሉ ለማግኘት ከታች ያለውን ሊንክ በመጫን Join በማድረግ ይከታተሉ፦ 👇👇👇 https://t.me/AbuFaykEmadudin
የላቀ ሐዲስ! ረሱል ﷺ እንዲህ ብለዋል፦ ﴿اتَّقِ اللهَ حيثُ كنتَ وأتبِعِ السيئةَ الحسنةَ تَمْحُها وخالِقِ الناسَ بخُلُقٍ حسنٍ﴾ “የትም ብትሆኑ አላህን ፍራ፣ ከወንጀል በኋላ መልካም ስራን አስከትል ታጠፋዋለችና። ከሰዎች ጋር ደግሞ በመልካም ስነምግባር ተኗኗር።”
Live stream finished (55 days)
ቀጣይ የደዕዋ ፕሮግራም ኡስታዝ ሙከመል ከማል
መቃመዲን ዩሱፍ ከሰአድ መስጅድ ሙባረክ አ/ረሂም ከኢብኑ አባስ መስጅድ አ/ዋሂድ ሸምሰዲን ከአቡበክር መስጅድ ሀሲፍ ሳዲቅ ከሪያድ መስጅድ አቡበከር አ/አዚዝ ዛዱል ቁሉብ መድረሳ
አሁን የቁርኣን ጥያቄ እና መልስ ፕሮግራም ተጀምሯል።
ቀጥታ ስርጭት | LIVE የዳዕዋ ፕሮግራም በሚከተለው ሊንክ ይከታተሉ 👇 https://t.me/fewaidworabe?livestream 🕌በወራቤ ከተማ ኡመር መስጂድ
видео или голосовое, без подписи
“የተውሒድ በይድ” ቢብላን ሱም በስልጥኘ አፍ በደኑሪ ሙሰ የትስናጄይ ክታብ ያለሃነ ሀድነተ በሱትዋ በቀሊሎ ኡንገ ለቻሎትዋ ለትፈሀሞት ጥሽተ ያትኬሻነን ክታብ። የክታበይ ሱመ “የተውሒድ በይድ” የባሉዪ በስልጥኘ አፍ ትዮን “በይድ” በሎት ወሪ በጀመረ በ14ለኜይ አሮት ዮጫነይ ወሪ በሎትን። ክታበይ ቀራሞኔ የእልመ ኑረ ልታቆዱዋ ለገናም ሰብ ልታቤሩ ጀበ ባልነማን!
видео или голосовое, без подписи
ስለ አረንጓዴው አደንዛዥ ቅጠል በስልጥኛ ቋንቋ የተገጠመ ምርጥ ግጥም ስልጤ ኤጋሀ ብራግ ወልዳሀ ጫት አይቅማ!! ➖➖➖➖ ጫት ደመኛኔ ጫት ደመኛኔ፣ አረንጓዴት ቁጠል አኜተኝ ወመኔ፣ ኣዴሜየ ኢቲሽለኝ ቃነናን ዋመኔ፣ በሰሬየ ተፈጃን ቀጠናን ሰሀኔ። ዜግነተ አታሙሱ ቂባጬ አታሙሱ፣ የቀተለኝ ጫትን ደሜ ቡሀ ኪሱ። ኤሄ በከተማ የጫትንኩ አራሼ፣ አበሮሴ በጌዬ ይመስላን ጦቃሼ። ስልጤ ኤጋሀ ብራግ ወልዳሀ ጫት አይቅማ፣ ቀልብምከ ብርምከ ለዮንብሀ ዶማ። ጤሼየ ተመለጋን ኤሄን ሂንዞ ተቀጡ፣ ዜግነት ሳቅትብኛት ኤሄን ሂንዞ ተቀጡ፣ ኢስናሙ ተፈጃኔ በመቀጥ ተቶቅጡ። ወሲዬየ የጂጂ ለስልጤይ ሀልቡለ፣ ጫት ሀድክ ተይችልቢ ኣቦናሀ ቀተለ፣ አቦ ማል ፈተኛ አተን ለደበለ። ✍ ከኡስታዝ ኸይረዲን ሐሰን(ቶክቻው) ረሒመሁሏህ ረህመተን ዋሲዓ ➖➖➖➖➖➖➖➖➖
ስለ ቁርኣኒዮች በሸይኽ ኢልያስ አሕመድ የዛሬ የሮም መስጅድ ኹጥባህ
ወራቤ[ ደርሶች እና ፈዋኢዶች ] pinned a photo
🔺ታላቅ የዳእዋ ፕሮገራም ቁጥር 2 እነሆ ወርሃዊው የዳእዋ ዝግጅታችን ቀን ደረሰ ============//============= የፊታችን እሁድ ሃምሌ 5 ከጠዋቱ 3፡00 ጀምሮ ዝግጅቱን አጠናቆ እናንተን ይጠባበቃል 👉 በእለቱ 1) በታላቁ ኡስታዛችን ሸይክ ሙከሚል ከማል ስለ ሸዐ ምንነት ሰፊ ትምህርት ይሰጣል 2) ሌላኛው ከመዲና ለእረፍት በመጣው በኡስታዝ ሰይፈዲን ሙሀመድ ስለ ሰሃቦች ፈድል ይዳሰሳል 3) አጓጊው የጥያቄና መልስ ውድድር በ6 መድረሳ ተማሮዎች መሀከል ይደረጋል """"""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""" ⏰ቀን 05/11/2018 ከጠዋቱ 3፡00 ጀምሮ 🕌ቦታ ታላቁ ኡስማን መስጅድ @ https://t.me/fewaidworabe
Methodology (way of teaching for Qur'an )
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
بسم الله الرحمن الرحيم الحمد لله بنعمته تتم الصالحات، والحمد لله الذي وفقنا لإتمام هذا العمل، والصلاة والسلام على نبينا محمد ﷺ. የወራቤ ሙስሊም ሴቶች ጀምዓ ያዘጋጀው የሴቶች በሴቶች የሸርዓዊ ኮርስ በስኬት ተጠናቀቀ "አላህ ለአንድ ሰው ኸይርን ሲሻለት በዲኑ ያስገነዝበዋል።" የሚለውን የነቢያችን ﷺ ሐዲስ መሠረት በማድረግ፣ የወራቤ ሙስሊም ሴቶች ጀምዓ ለሙስሊም እህቶች ብቻ ያዘጋጀው የሶስት ቀን የሸርዓዊ እውቀት ኮርስ እሑድ 14/10/2018 ዓ.ም. በአላህ ፈቃድ በተሳካና በተዋበ ሁኔታ ተጠናቋል። ከሁሉ በፊት ይህንን መልካም ሥራ ለማስጀመር፣ ለማስኬድና በውብ ፍጻሜ ለማድረስ ለወፈቀን አላህ ﷻ ወደር የሌለውን ምስጋና እናቀርባለን። ከዚያም ለዚህ ኮርስ መሳካት በዱዓ፣ በጊዜ፣ በገንዘብ፣ በጉልበትና በሃሳብ ድጋፍ ያደረጋችሁ ወንድሞችና እህቶች በሙሉ جزاكم الله خيرًا። አላህ ከሁላችሁም ይቀበል፣ ያደረጋችሁትንም በሚዛናችሁ ላይ የሚመዘን ሰደቃ ጃሪያ ያድርግላችሁ። በኮርሱ የተዳሰሱ ዋና ዋና ርዕሶች 📖 1. አርካኑል ኢማን የመጀመሪያው ቀን በእምነት መሠረቶች ላይ ያተኮረ ነበር። በተለይም በአላህ ማመን፣ በተውሒድ፣ በአላህ ስሞችና ባህሪያት፣ እንዲሁም በቀደር ማመን ላይ በሰፊው ተብራርቷል። ትምህርቱ አንድ ሙስሊም ሁሉንም ሥራውን በትክክለኛ አቂዳ ላይ መመሥረት እንዳለበት አሳስቧል። 👩👧 2. ተምሳሌታዊ እናትነት ሁለተኛው ቀን መልካም እናት የመልካም ትውልድ መሠረት መሆኗ ተብራርቷል። ልጆችን በተውሒድ፣ በሶላት፣ በቁርኣንና በመልካም አኽላቅ ማሳደግ፣ ለእነርሱ መልካም አርአያ መሆንና በዱዓ አለመለየት የእያንዳንዷ ሙስሊም እናት ታላቅ ኃላፊነት መሆኑ ተወስቷል። 💰 3. آداب مع المال (ከገንዘብ ጋር ያሉ ኢስላማዊ ሥነ-ምግባሮች) በመጨረሻው ቀን እስልምና በግብይትና በገንዘብ አያያዝ ያስቀመጠው ታላቅ ሥርዓት ተብራርቷል። የግብይት አርካኖችና ሸርጦች፣ የተፈቀዱና የተከለከሉ የግብይት አይነቶች፣ እንዲሁም ወለድ (ሪባ) እና ጉዳቱ በሰፊው ተዳስሰዋል። ከትምህርቱ የተገኘው ትልቁ መልእክት፣ "የሚያስፈልገን ብዙ ገንዘብ ሳይሆን ሐላልና በረካ ያለው ገቢ ነው" የሚል ነበር። ስለዚህ ሙስሊም በግብይቱ ውስጥ እውነተኛ፣ አማኝ እና ፍትሐዊ መሆን ይገባዋል። መደምደሚያ ይህ ኮርስ በአቂዳ፣ በቤተሰብ ግንባታ እና በኢስላማዊ ግብይት ዙሪያ ጠቃሚ እውቀቶችን ያካተተ የኸይር መድረክ ነበር። እውቀት የሚጠቅመው ግን ሲማር ብቻ ሳይሆን ወደ ተግባር ሲቀየር ነው። ስለዚህ አላህ የተማርነውን በሕይወታችን የምንተገብር ያድርገን፣ የተሳተፉትን እህቶች በእውቀታቸው ይባርክ፣ ያልተሳተፉትንም በሚቀጥሉት መሰል የእውቀት መድረኮች ለመሳተፍ ይወፍቃቸው። በመጨረሻም ይህ ኮርስ እንዲሳካ ከጎናችን ለቆማችሁ፣ በማንኛውም መልኩ ላገዛችሁን ወንድሞችና እህቶች፣ ለኡስታዛችን፣ ለተሳታፊ እህቶች እና ለሁሉም ባለድርሻዎች ከልብ ምስጋናችንን እናቀርባለን። አላህ ከሁላችሁም ይቀበል፣ በዱንያም በአኺራም በኸይር ይመንዳችሁ። وصلى الله وسلم على نبينا محمد، وعلى آله وصحبه أجمعين. وآخر دعوانا أن الحمد لله رب العالمين.
﷽ السلام عليكم ورحمة الله وبركاته 🌹 ውድ እህቶቻችን! አልሐምዱ ሊላህ! በአላህ ፈቃድ የ"ሴቶች በሴቶች" የሦስት ቀን የእውቀት መርሃ ግብራችን ሁለተኛ ቀን በተሳካ ሁኔታ ተጠናቋል። 📖 በመጀመሪያው ቀን በ"አርካኑል ኢማን" ርዕስ የእምነታችንን መሠረቶች ተምረናል። ኢማናችን እንዴት እንደሚጠና፣ በአምልኮአችን፣ በሥነ ምግባራችን እና በዕለት ተዕለት ሕይወታችን እንዴት ሊንጸባረቅ እንደሚገባ ተገንዝበናል። 🌷 በሁለተኛው ቀን ደግሞ "ተምሳሌታዊ እናትነት" በሚለው ርዕስ፣ እናት የቤተሰብ ልብ፣ የትውልድ አንፃሪ እና የማኅበረሰብ ግንባታ መሠረት መሆኗን በሰፊው ተምረናል። መልካም እናት መልካም ትውልድን ታንጻለች፤ መልካም ትውልድ ደግሞ መልካም ኡማን ይገነባል። ✨ እነሆ! ነገ የመጨረሻው ቀን ነው። የመጨረሻው ቀን ብዙ ጊዜ ከሁሉም የበለጠ ልዩ ይሆናል፤ የቀደሙትን ትምህርቶች የሚያጠቃልል፣ የሚያነቃቃ እና በአላህ ፈቃድ በሕይወታችን ውስጥ የሚቆይ መልእክት የምንቋደስበት ቀን ነው። 🍃 ስለዚህ ውድ እህቶች! ይህን የበረከት ዕድል አታምልጡ። ነገ ቀድማችሁ ተገኙ፤ እህታችሁን፣ ጓደኛችሁን፣ ጎረቤታችሁንም ይዛችሁ ኑ። አንዲት ሰው ወደ ኸይር እንድትመጣ ምክንያት መሆን፣ በአላህ ዘንድ ታላቅ ምንዳ ያለው ተግባር ነው። قال رسول الله ﷺ: «مَنْ دَلَّ عَلَى خَيْرٍ فَلَهُ مِثْلُ أَجْرِ فَاعِلِهِ» "ወደ ኸይር የመራ ሰው፣ ያንን ኸይር እንደሠራው ሰው ምንዳ ያገኛል።" (ሙስሊም) 🌹 ነገ ኢንሻአላህ በፈገግታ፣ በጉጉት እና በእውቀት ፍቅር እንገናኝ። "የሚቀረው አንድ ቀን ብቻ ነው፤ ነገን አትናፍቁ!" بارك الله فيكن، ونفع بكن الإسلام والمسلمين ✍ የወራቤ ሙስሊም ሴቶች ጀምዓ