ጎህ የልዩ-ፍላጎት ማዕከል
Статистикаይህ ቻናል ብቁ የሆኑ የልዩ-ፍላጎት፣የስነ- ልቦና፣ እና ሌሎች ባለሙያዎች የሚገኙበት ሲሆን የተለያዩ ትምህርታዊ፣ ስነ ልቦናዊ፣ የባህሪ እና ሌሎች ድጋፎችን በሰለጠኑ ባለሙያዎች እንሰጣለን። 📲 0954842701 (ትዛዙ አበበ) በውስጥ ለማግኘት @Tizaabebe
- Последний пост
- 12 авг.
- Последнее чтение
- 13 авг.
- Постов за неделю
- 3
- Всего постов
- 33
- Тип
- открытый
- Язык
- ti
- В каталоге с
- 13 авг.
- 1/24сутки в ленте
- 439
- 1/48двое суток
- 503
- 1/72трое суток
- 542
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
ለልዩ ፍላጎት ልጆች የተሻለ ድጋፍ ይፈልጋሉ? 👩🏫 Shadow Teacher ነዎት? 👨👩👧 ወላጅ ነዎት? ወይስ በልዩ ፍላጎት ልጆች የሚሰሩ ባለሙያ? በBloom Psychological Services የተዘጋጀውን የABA ስልጠና ይሳተፉ! 🧠 በሳይንስ የተደገፉ የABA ዘዴዎች 📚 የባህሪ፣ የመግባባት እና የመማር ክህሎት ድጋፍ 📝 IEP እና የእድገት ክትትል 🎓 4 ቀናት ስልጠና + 1 ቀን ተግባራዊ ወርክሾፕ 📅 ነሐሴ 9፣ 10፣ 16 እና 17 📍 Bloom Psychological Services 📞 0986-777-555 ቦታ ከመሙላቱ በፊት አሁኑኑ ይመዝገቡ!
🌟 የPACA 2027 ምዝገባ ተጀምሯል።🌟 🎯 በአዲስ አበባ ለሚዘጋጀው የPACA 2027 ለመቀላቀል ካሰቡ ፣ አሁኑኑ ቦታዎን ይያዙ ፤ ይመዝገቡ። 🎯 📆 ቀን - መጋቢት 29 - ሚያዝያ 2, 2019 📍 ቦታ - ስካይላይት ሆቴል፣ አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ የቅድመ ምዝገባ፡ ወላጆች እና የአካል ጉዳተኞች፡ 150 ዶላር ባለሙያዎች፡ 200 ዶላር እዚህ ይመዝገቡ፡ https://lnkd.in/eSwzyX83 የቅድመ ምዝገባ በጥቅምት 1 ቀን 2026 ይዘጋል። ኑ በአፍሪካ የኦቲዝም ድጋፍን ያጋሩ፣ ይማሩ እና የወደፊት እጣ ፈንታን ይምሩ። 🌟 PACA 2027 registration is now open. 🌟 🎯 If you are planning to join us in Addis Ababa, this is the time to secure your place. 🎯 📆 7-10 April 2027 📍 Skylight Hotel, Addis Ababa, Ethiopia Early Bird Registration: Parents and individuals with disabilities: USD 150 Professionals: USD 200 Register here: https://lnkd.in/eSwzyX83 Early bird registration closes on 1 October 2026. Come share, learn and lead the future of autism support in Africa. #PACA2027 #NehemiahAutismCenter #AutismInAfrica #AutismInclusion #AddisAbaba
የልዩ-ፍላጎት ረዳት መምህር ረዳት መምህር / ቴራፒስት (4 ቦታዎች) የስራ መደብ፦ ረዳት መምህር / ቴራፒስት (Assistance) የቅጥር ሁኔታ፦ በቋሚነት (Full-Time) ደመወዝ፦ በስምምነት የትምህርት ደረጃ፦ 10/12 ክፍል ወይም በተዛማጅ መስክ የተሰጠ የምስክር ወረቀት (Certification) ያለው/ላት። የስራ ልምድ፦ ከተለያዩ ህጻናት ጋር አብሮ በመስራት፣ በመንከባከብ ወይም በማገዝ ዙሪያ የስራ ልምድ ያለው/ላት። በቴሌግራም ለማመልከት: @Tizaabebe በአካል መጥቶ ለማስገባት፦ ጦር-ሃይሎች ከሙሉ ወንጌል ቸርች ጀርባ https://t.me/gohcenters
ሶስት አባቶች ወግ እነዚህ ሶስት አባቶች ስለ አባትነት ልምዳተቸው ቢወያዩ፣ ውይይታቸው ምን ይመስል ይሆን ከሶስት በጣም የተለያዩ ዓለማት የመጡ ቢሆኑም፣ አንድ የሚያመሳስላቸው ነገር አለ፣ ልጆቻቸውን መጠበቅ፣ ለእነሱ መስዋዕት የመክፈል እና የመንከባከብ ተፈጥሯዊ ስሜት። የመጀመሪያው- የሳንድግሩዝ ወፍ ይባላል፡ የሳንድግሩዝ ወፍ አባት ውሃ ለማግኘት በረሃውን በረጅም ርቀት በመብረር ሕይወቱን አደጋ ላይ ይጥላል። ልዩ የሆኑትን የሆድ ላባዎቹን በውሃ ያርሳል፤ ከዚያም ያንን ውድ ውሃ ወደ ጫጩቶቹ ይዞ ይመለሳል። ጫጩቶቹም ውሃውን በቀጥታ ከራሰው የአባታቸው ላባ ይጠጣሉ። እነዚህ ወፎች በሚኖሩበት ከባድና በደረቅ በረሃ፣ የጫጩቶቹ ህይወት በአባትየው የዕለት ተዕለት ውሃ የማመላለስ ተግባር ላይ የተመሰረተ ነው፡፡ ሁለተኛው- የባንጋይ ካርዲናል አሳ አባት የባንጋይ ካርዲናል አሳ አባት እንቁላሎቹን ከአዳኞች ለመጠበቅ በአፉ ውስጥ ተሸክሞ ይይዛቸዋል። አንድ ወር ለሚጠጋ ጊዜ ምግብ ሳይበላ እንቁላሎቹን በአፉ ይሆ ይቆያል። የሚያድጉትን ፅንሶች በትዕግስት ይጠብቃል፣ ኦክስጅን እንዲያገኙም ያደርጋል፤ በመጨረሻም በራሳቸው ለመኖር ዝግጁ እስኪሆኑ ድረስ ይንከባከባቸዋል። ሶስተኛው- የሰው ልጅ አባት ሶስተኛው አባት ናራያን ይባላል። ልጁ ኒምራን እ.ኤ.አ. በ2015 ኔፓልን በአስከፊ ሁኔታ በመታው የመሬት መንቀጥቀጥ ወቅት ተወለደ። ሁለተኛው የመሬት መንቀጥቀጥ ሲከሰትና በዙሪያቸው ያሉ ሕንፃዎች ሲወድቁ፣ ናራያን ሳያመነታ ልጁን በልብሱ ስር ሸሽጎ በመሮጥ ህይወቱን አተረፈ። ሶስት አባቶች። ሶስት ዝርያዎች። ሶስት በጣም የተለያዩ ታሪኮች። ይሁን እንጂ በአንድ ነገር ላይ ይስማሙ ይሆናል፦ አባትነት በመልካም ጊዜ ብቻ ከልጅ ጋር አብሮ መሆን አይደለም። አባትነት ልጅዎ በጣም በሚፈልግዎት ጊዜ ከጎኑ መቆም፣ መጠበቅ፣ መስዋዕት መክፈል እና የሚያስፈልገውን ሁሉ ለማድረግ ዝግጁ መሆን ነው። እና ምናልባትም ታሪኮቻቸውን ከተካፈሉ በኋላ አንድ ነገር ይገነዘቡ ነበር፦ ምንም እንኳን የተለያዩ ቋንቋዎችን ቢናገሩም፣ የአባታዊ ፍቅር ቋንቋ ዓለም አቀፋዊ መሆኑን Fiseha Teklu https://t.me/gohcenters
видео или голосовое, без подписи
BLOOM PSYCHOLOGICAL SERVICES ABA TRAINING FOR SCHOOL IMPLEMENTERS Comprehensive Weekend Workshop • In-Person Program What We Will Cover Introduction to ABA & Historical Foundations Behavioral Assessment Methods Evidence-Based ABA Interventions & Techniques Data Collection & Measurement Strategies Understanding Neurodevelopmental Conditions Individualized Education Program (IEP) Preparation Practical Classroom & Home Implementation And more…. Who Should Attend? Schools supporting students with special needs School psychologists & counsellors Special education teachers Practitioners & shadow teachers working with children with Special Needs Parents seeking to improve 1-on-1 implementation skills with their child Event & Contact Details Schedule & Format: Weekends (In-Person) | Interactive Workshop Series Location: At Bloom Psychological Service Registration: Phone: +251986-777-555 | Email: mynewbloom@gmail.com Starting Date: August 15, 2026
видео или голосовое, без подписи
በኢትዮጵያ ጡት የሚያጠቡ እናቶች 57 በመቶ መሆናቸው ተገለፀ 👉 ጡት ማጥባት ለልጆች በሽታን ለመከላከል አስተዋፆ እንዳለው ተገልጿል ሐምሌ 28 ቀን 18ተኛው የጡት ማጥባት ቀን እንደሚከበር ጤና ሚኒስቴር ዛሬ ለመገናኛ ብዙሀን በሰጠው ስልጠና አስታውቋል። በአለም አቀፍ ደረጃ ለ 33 ተኛ ጊዜ በኢትዮጵያ 18ኛ ጊዜ ከ ሐምሌ 25 እስከ ነሐሴ 2 ቀን እንደሚገበር የገለጹት በጤና ሚኒስቴር የስርዓተ ምግብ መሪ ስራ አስፈፃሚ ወ/ሮ ህይወት ዳልሰኔ ናቸው። በኢትዮጵያ ጡት የሚያጠቡ እናቶች 57 በመቶ መሆኑን አንስተው በተለይ በከተሞች አካባቢ የጡት ማጥባት ባህል መቀነሱን ተናግረዋል። እናቶች ጉዳዩን በትኩረት ሊያዩት እንደሚገባ አንስተው በሀገሪቱ ከተሞች አካባቢ የሚገኙ እናቶች ለእናት ጡት ወተት ያላቸው ግንዛቤ አነስተኛ መሆኑን ገልፀዋል። የወሊድ ፍቃድ 4 ወር እንደሆነና በቀጣይ ወደ 6 ወር ከፍ እንዲል የፖሊሲ አቅጣጫ ያስፈልጋል ብለዋል። አክለውም ጡት ማጥባት ልጆችን ከበሽታ ከመከላከል ጋር የሚኖረው ጠቀሜታ ከፍተኛ መሆኑን ተናግረዋል ። ጡት ማጥባት እናትን ከማህፀን ካንሰር እንደሚከላከል እና አምራች ዜጋን ለማፍራት አስተዋፆ እንዳለው አንስተዋል። በህይወቴ ጌትነት #አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ #አሐዱ_ሬዲዮ_94.3
Training 🔴 LIVE 👤 Guest Speaker: Mr. Tizazu Abebe (Special needs and inclusive education expert | Founder of Addis Ababa Training and Special needs Center | Trainer | Publicly Known by Goh Special needs Center) 📆 Date: 31/07/2026 G.C | Friday ⏰ Time: 20:30 - 22:30 📌 Venue: https://t.me/MelaSpecialNeedsService 👨💼 Moderator: Woynshet Wendimu We invite all Parents and families to join us in this Live webinar to share their experiences and knowledge. #Parents_Webinar 🤳 +251952118642 @MelaSpecialNeedsService
የልዩ-ፍላጎት ረዳት መምህር ረዳት መምህር / ቴራፒስት (4 ቦታዎች) የስራ መደብ፦ ረዳት መምህር / ቴራፒስት (Assistance) የቅጥር ሁኔታ፦ በቋሚነት (Full-Time) ደመወዝ፦ በስምምነት የትምህርት ደረጃ፦ 10/12 ክፍል ወይም በተዛማጅ መስክ የተሰጠ የምስክር ወረቀት (Certification) ያለው/ላት። የስራ ልምድ፦ ከተለያዩ ህጻናት ጋር አብሮ በመስራት፣ በመንከባከብ ወይም በማገዝ ዙሪያ የስራ ልምድ ያለው/ላት። በቴሌግራም ለማመልከት: @Tizaabebe በአካል መጥቶ ለማስገባት፦ ጦር-ሃይሎች ከሙሉ ወንጌል ቸርች ጀርባ https://t.me/gohcenters
ዶክተሮችም ጭምር የሚሳሳቱበት የ'ቨርቹዋል ኦቲዝም' (Virtual Autism) እውነታ! ከማክዳ ገፅ የተወሰደ ብዙ ወላጆች "ልጄ ስልክ አብዝቶ ኦቲዝም ሆነብኝ" ብለው ይጨነቃሉ፤ አንዳንድ ዶክተሮችም ሁኔታውን ለይተው ባለመረዳት የተሳሳተ ፍረጃ ይሰጣሉ። ነገር ግን በሳይንሱ "ቨርቹዋል ኦቲዝም" የሚባል በሽታ የለም! ስልክ እና ቲቪ ማየት የልጆችን ንግግር እና ማህበራዊ ግንኙነት ያዘገያል እንጂ እውነተኛ ኦቲዝምን ሊያመጣ አይችልም። ትልቁ ልዩነት ምንድነው? በስክሪን የመጣ መዘግየት፦ ስልክ እና ቲቪ ሙሉ በሙሉ ሲቆም እና ህጻኑ ከሰዎች ጋር መጫወት ሲጀምር በጥቂት ወራት ውስጥ በፍጥነት ይሻሻላል። እውነተኛ ኦቲዝም፦ ከጽንስ ጀምሮ ከአንጎል አወቃቀር ጋር የተያያዘ የተፈጥሮ ሁኔታ ስለሆነ ስክሪን ቢጠፋም የዕድሜ ልክ ልዩ ድጋፍ ይፈልጋል። ልጃችሁ የንግግር መዘግየት ካሳየ ወዲያውኑ ተስፋ አትቁረጡ። በመጀመሪያ ስልኩን ዜሮ በማድረግ ከልጁ ጋር ፊት ለፊት መጫወት እና ማውራት ይጀምሩ! ቨርቹዋል ኦቲዝም" (Virtual autism) የሚባል እውነተኛ የህክምና ምርመራ ወይም በሽታ የለም። የህክምና እና የስነ-ልቦና ባለሙያዎች ይህንን አገላለጽ ፍጹም የተሳሳተ እንደሆነ ይገልጻሉ፤ ምክንያቱም የስክሪን እይታ እውነተኛውን የኦቲዝም መታወክ (ASD) ሊያስከትል አይችልም። እውነተኛ ኦቲዝም ከስነ-ተዋልዶ እና ከአንጎል እድገት ጋር የተያያዘ ነው። በሰዎች ዘንድ "ቨርቹዋል ኦቲዝም" ተብሎ የሚጠራው ግን ከከፍተኛ የስክሪን አጠቃቀም የመጣ የዕድገት መዘግየት ነው። የሳይንሱ ማህበረሰብ ይህንን ቃል እንዳንጠቀም በጥብቅ ያስጠነቅቃል። ምክንያቱም ህዝቡን ስለሚያደናግር እና የወላጆች ስህተት ኦቲዝምን እንደሚያመጣ አድርጎ የተሳሳተ ግንዛቤ ስለሚፈጥር ነው። ዋና ዋና ልዩነቶች እውነተኛው የኦቲዝም ባህሪ እና በስክሪን ምክንያት የሚመጣው የባህሪ መዘግየት ለምን እንደሚለያዩ መረዳት "ቨርቹዋል ኦቲዝም" የተሳሳተ አስተሳሰብ መሆኑን ያረጋግጣል፡- መነሻ ምክንያቱ፦ እውነተኛ ኦቲዝም ከተወለዱ ጀምሮ አብሮ የሚኖር የተፈጥሮ ሁኔታ ነው። "ቨርቹዋል ኦቲዝም" ግን አንድ ህጻን ከሰዎች ጋር ከመጫወት ይልቅ ቀኑን ሙሉ በዲጂታል መሳሪያዎች ላይ ሲያሳልፍ የሚመጣ የባህሪ ለውጥ ነው። ዋናው ችግር፦ ስክሪኖች ህጻናትን ከአንጎል እድገት፣ ከአይን ለአይን እይታ፣ ከሰዎች ጋር ከመነጋገር እና ከፍቅር ግንኙነት ያርቋቸዋል። ይህ መረጃ ለብዙ የኢትዮጵያ ወላጆች ስለሚጠቅም እባክዎ ሼር (Share) በማድረግ ያዳርሱት! 🙏 https://t.me/gohcenters
ክፍት የስራ ማስታወቂያ የአዲስአበባ የትምህርት እና ስልጠና ማዕከል (Addis Ababa Education and Training Center) ማዕከላችን ልዩ-ፍላጎት ላላቸው ህጻናት ሁለንተናዊ ድጋፍ የሚሰጥ ተቋም ሲሆን ጥራቱን የጠበቀ አገልግሎት ይበልጥ ለማስፋፋት ብቁ የሆኑ ባለሙያዎችን አወዳድሮ መቅጠር ይፈልጋል። በዚሁ መሠረት ከዚህ በታች በተዘረዘሩት ክፍት የስራ መደቦች ላይ መስፈርቱን የምታሟሉ አመልካቾች ብቻ እንድትወዳደሩ እንጋብዛለን። 💼 መደብ 1፦ የልዩ-ፍላጎት አስተባባሪ (Special Needs Coordinator) የቅጥር ሁኔታ፦ በቋሚነት (Full-Time) ደመወዝ፦ በስምምነት (በችሎታ እና ልምድ ላይ የተመሰረተ) 🎓 የትምህርት ደረጃ እና የስራ ልምድ የትምህርት ደረጃ፦ በመጀመሪያ/በሁለተኛ ዲግሪ (BA/MA Degree) በልዩ ፍላጎት ትምህርት (Special Needs Education)፣ በአካቶ ትምህርት (Inclusive Education)፣ በስነ-ልቦና (Psychology) ወይም በተዛማጅ የትምህርት መስክ የተመረቀ/ች። የስራ ልምድ፦ በልዩ ፍላጎት ትምህርት መስክ 3 ዓመት እና ከዚያ በላይ የሰራ/ች፤ ከዚህም ውስጥ በትምህርት ቤት ወይም በስልጠና ማዕከል ውስጥ የአስተባባሪነት/የአመራርነት (Coordinating/Supervisory) የስራ ልምድ ያለው/ላት። የባህሪ ድጋፍ እና ማሻሻያ ማዕቀፎችንና ዘዴዎችን የሚያውቅ/ የምታውቅ ተመራጭ ነው። 📋 ዋና ዋና የስራ ድርሻዎች 👉 የማዕከሉን የትምህርት፣ የቴራፒ እና የክትትል ፕሮግራሞች በበላይነት ማቀድ፣ ማስተባበር እና መምራት። 👉 በመምህራን እና በቴራፒስቶች የሚዘጋጁ የግል የትምህርት እና የቴራፒ እቅዶችን (IEP) መገምገም፣ ማጽደቅ እና አተገባበራቸውን መከታተል። 👉 የመምህራንን እና የረዳቶችን ስራ መከታተል፣ ሙያዊ ድጋፍና ስልጠና መስጠት (Mentorship)። 👉 ከወላጆች ጋር መደበኛ ስብሰባዎችን በማድረግ የልጆችን የዕድገት ሁኔታ መገምገም እና የቴክኒክ ማብራሪያዎችን መስጠት። 👉 የማዕከሉን አገልግሎቶች ጥራትና ደረጃ መጠበቁን ማረጋገጥ። መደብ 2፦ የልዩ-ፍላጎት ትምህርት መምህር (Special Needs Education Teacher) የቅጥር ሁኔታ፦ በቋሚነት (Full-Time) ደመወዝ፦ በስምምነት (በችሎታ ላይ የተመሰረተ) 🎓 የትምህርት ደረጃ እና የስራ ልምድ የትምህርት ደረጃ፦ በመጀመሪያ ዲግሪ (BA Degree) በልዩ ፍላጎት ትምህርት (Special Needs Education)፣ በአካቶ ትምህርት (Inclusive Education)፣ በስነ-ልቦና (Psychology) ወይም በተዛማጅ መስክ የተመረቀ/ች። የስራ ልምድ፦ ኦቲዝም፣ የአእምሮ እድገት ውስንነት፣ ዳውን ሲንድረም ወይም ሌሎች ልዩ-ፍላጎት ካላቸው ህጻናት ጋር በልዩ ማዕከል ወይም በትምህርት ቤት ውስጥ 2 ዓመት እና ከዚያ በላይ ቀጥተኛ የስራ ልምድ ያለው/ላት። 📋 ዋና ዋና የስራ ድርሻዎች 👉 የእያንዳንዱን ልጅ የክህሎት ደረጃ መነሻ በማድረግ የግል የትምህርት እና የቴራፒ እቅድ (IEP) ማዘጋጀት እና መተግበር። 👉 በግል (አንድ ለአንድ) የቴራፒ እና የትምህርት ድጋፍ መስጠት። 👉 በአነስተኛ ቡድን (ከ2-3 ህጻናት) እና በሙሉ ቡድን ውስጥ ተግባራዊ ትምህርት፣ ንግግር እና ማህበራዊ ክህሎቶችን ማስተማር። 👉 የልጆችን እለታዊ እድገት በትክክል መመዝገብ እና በየጊዜው በግልጽ የተዋቀረ የሂደት ሪፖርት ማዘጋጀት። 🎯 ለሁለቱም መደቦች የሚፈለጉ አጠቃላይ ክህሎቶች የቋንቋ ችሎታ፦ በአማርኛ እና በእንግሊዝኛ ቋንቋ በጣም ጥሩ የሆነ የንግግር እና የጽሁፍ ችሎታ ያለው/ላት (የቴክኒክ ፅንሰ-ሃሳቦችን ለወላጆች በአማርኛ ማብራራት የሚችል/ምትችል)። ከፍተኛ ትዕግስት፣ ፍቅር፣ እና ልዩ ፍላጎት ያላቸውን ህጻናት ለመርዳት የዳበረ ሰብአዊ ስብዕና። ከባለሙያዎች፣ ከቡድን አባላት እና ከወላጆች ጋር በቅንጅት የመስራት ችሎታ። የማመልከቻ ሂደት የሚፈለገውን መስፈርት የምታሟሉ አመልካቾች የትምህርት ማስረጃችሁን እና የስራ ልምዳችሁን ከማመልከቻ ደብዳቤ ጋር በማያያዝ እስከ ሀምሌ 22 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ ማመልከት ትችላላችሁ። በኢሜል ለማመልከት፦ tizazuab1988@gmail.com (የስራ መደቡን ስም በSubject መስመር ላይ መጥቀስ አይርሱ) በቴሌግራም ለማመልከት፦ @Tizaabebe በአካል መጥቶ ለማስገባት፦ ጦር-ሃይሎች ከሙሉ ወንጌል ቸርች ጀርባ ማሳሰቢያ፦የአዲስአበባ የትምህርት እና ስልጠና ማዕከል ለማንኛውም አመልካች እኩል የስራ ዕድል የሚሰጥ ሲሆን፣ ሴት አመልካቾች ይበረታታሉ። ስልክ መደወል ፈፅሞ የተከለከለ ነው!! 🔗 https://t.me/gohcenters
видео или голосовое, без подписи
1 ቢሊዮን የሚጠጉ ሰዎች የአዕምሮ ጤና ችግር አለባቸው #Ethiopia | በዓለም አቀፍ ደረጃ በአዕምሮ ጤና ችግር የሚሰቃዩ ሰዎች ቁጥር እያሻቀበ ይገኛል ተብሏል። በዓለም ዙሪያ ወደ 1ቢሊዮን የሚጠጉ ሰዎች የተለያየ ዓይነት የአዕምሮ ጤና ችግር እንዳለባቸው ነው የአለም ጤና ድርጅት የገለጸው። ከእነዚህ የአዕምሮ ጤና ችግሮች ውስጥ በጣም የተለመዱት ጭንቀትና ድብርት ናቸው። ጭንቀት በዓለም ላይ በብዛት የሚስተዋለው ዋነኛው የአዕምሮ ጤና ችግር ሲሆን በመቶ ሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ሰዎችን በዚህ የተጠቁ ናቸው ብሏል። ችግሩን ከሚያብሱት ነገሮች መካከል ድህነት፣ ሥራ አጥነት፣ እና የማህበራዊ መገለል ለአዕምሮ ጤና እክል ትልቅ አስተዋፅኦ እንዳላቸው ነው የተገለፀው። በጦርነት እና በተፈጥሮ አደጋዎች ውስጥ የሚያልፉ ሰዎችም ለአዕምሮ ህመም ተጋላጭ እንደሆኑም ተጠቁሟል። በአብዛኛው ዓለም በተለይም በታዳጊ ሀገራት ስለ አዕምሮ ጤና ያለው የግንዛቤ ማነስ ሰዎች ተገቢውን የህክምና እርዳታ እንዳያገኙ እንቅፋት ሆኗል። በመሆኑም በቂ እንቅልፍ ማግኘት የተመጣጠነ ምግብ መመገብ እና አዘውትሮ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማድረግ የአዕምሮ ጤናን በከፍተኛ ሁኔታ እንዲሻሻል ማድረግ ይቻላል። የአዕምሮ ጤና ህክምናን ተመጣጣኝ እና ተደራሽ ማድረግ በተለይም በታዳጊ አገራት የመጀመሪያ ደረጃ ጤና ጣቢያዎች ውስጥ የአዕምሮ ጤና አገልግሎት እንዲኖር ማድረግ የግድ ነው ሲል ድርጅቱ አሳስቧል። መንግስታት ለጤና በጀት በሚመድቡበት ጊዜ ለአዕምሮ ጤና ተገቢውን ትኩረት መስጠት ይኖርባቸዋል ብሏል። እንደዚሁም በቂ የአዕምሮ ጤና ባለሙያዎችን ማሰልጠን እና በየአካባቢው ማሰማራት ይገባል ሲል ገልጿል። ሔኖክ ወ/ገብርኤል #Ethiopia #GetuTemesgen #GetuNews #Worldhealthorganization #Depression #AnxietyDisorders #Schizophrenia
Interview 🔴 LIVE 👤 Guest Speaker: Meseret Kinfe Haile (Parent | Autism Advocate | Author of Yetikur enat negn and Yemaynagerew lioul | Founder of Lioul Foundation ) 📆 Date: 10/07/2026 G.C | Friday ⏰ Time: 20:30 - 22:30 📌 Venue: https://t.me/MelaSpecialNeedsService?livestream=186b447a393de0c09f 👨💼 Moderator: Haleluya Ayele We invite all Parents and families to join us in this Live webinar to share their experiences and knowledge. #Parents_Webinar 🤳 +251952118642 @MelaSpecialNeedsService
ዕድሜያቸው ከሁለት ዓመት በታች የሆኑ ሕፃናት ስማርትፎን በፍጹም እንዳይጠቀሙ አዲስ ጥናት አስጠነቀቀ በዩናይትድ ኪንግደም አራት ታዋቂ ዩኒቨርሲቲዎች በጋራ ያካሄዱት ጥናት እንደሚያመለክተው፣ ታዳጊዎችን ለዲጂታል ስክሪኖች አዘውትሮ ማጋለጥ በአካላዊ፣ አእምሯዊና ስሜታዊ እድገታቸው ላይ ከፍተኛ ጉዳት ያደርሳል። ዋና ዋና የግኝቱ ነጥቦች የሚከተሉትን ያካትታሉ፦ የቋንቋና የማኅበራዊ ግንኙነት መዳከም፦ ስክሪን ማየት የሕፃናትን የቋንቋ የመማር ፍጥነት የሚገታ ሲሆን፣ ከወላጆቻቸው ጋር ያላቸውን ስሜታዊ ትስስር ያላላል። የጤና እክሎች፦ የአካል ብቃት እንቅስቃሴን በመቀነስ ለእንቅልፍ እክል፣ ለውፍረት እና ለተለያዩ የጤና ችግሮች የመጋለጥ እድልን ይጨምራል። የስሜት መቃወስ፦ ሕፃናት ሲያለቅሱ ወይም ሲበሳጩ ስልኮችን መስጠት፣ ወደፊት ስሜታቸውን በራሳቸው የመቆጣጠር ብቃታቸውን ያሳጣቸዋል። የጥናቱ መሪ ሬፍ ክሌይተን እንደገለጹት፣ ወላጆች ግልጽ መመሪያ ስላላገኙ ሳያውቁት ልጆቻቸውን ለጉዳት እየዳረጉ ነው። በመሆኑም መንግስት ከጥንቃቄ መመሪያዎቹን እንዲከልስና ቴክኖሎጂ ኩባንያዎች አሳሳች ማስታወቂያዎችን እንዲያቆሙ ጥሪ ቀርቧል። ባለሙያዎች ወላጆች ከዲጂታል ስክሪን ይልቅ ከልጆቻቸው ጋር በመጫወት፣ በማውራትና ጥራት ያለው ጊዜ በማሳለፍ ላይ እንዲያተኩሩ መክረዋል። አዩዘሀበሻ ===================== 💎⬇👇👇👇👇👇👇👇👇👇 የቴሌግራም ቻናላችንን join በማድረግ ወቅታዊ መረጃዎችን በቀላሉ ይከታተሉ፣ሊንክ👇 https://t.me/+Vl6V8k9V3YNEOp2s https://t.me/+Vl6V8k9V3YNEOp2s
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
ውድ ቤተሰቦቻችን "የማይናገረው ልዑል" መጽሃፍ ምረቃ ቀን -፣ ቅዳሜ ሰኔ 27 ቀን 2018 ዓ.ም ቦታ-፣ ሃይሌ ግራንድ ሆቴል ጭላሎ ቦልሩም (ላምበረት ወደመናኸሪያ መሄጃው መንገድ ላይ) ሰዓት-፣ ከሰዓት በኋላ 9 ሰዓት መግቢያ - ፣ ነጻ
ክፍት የስራ ማስታወቂያ የአዲስአበባ የትምህርት እና ስልጠና ማዕከል(Addis Ababa Education and Training Center) ማዕከላችን ልዩ-ፍላጎት ላላቸው ህጻናት ሁለንተናዊ ድጋፍ የሚሰጥ ተቋም ሲሆን ጥራቱን የጠበቀ አገልግሎት ይበልጥ ለማስፋፋት ብቁ የሆኑ ባለሙያዎችን አወዳድሮ መቅጠር ይፈልጋል። በዚሁ መሠረት ከዚህ በታች በተዘረዘሩት ክፍት የስራ መደቦች ላይ መስፈርቱን የምታሟሉ አመልካቾች ብቻ እንድትወዳደሩ እንጋብዛለን። መደብ 1፦ የልዩ-ፍላጎት ትምህርት መምህር (3 ቦታዎች) የስራ መደብ፦ የልዩ-ፍላጎት ትምህርት መምህር (Special Needs Education Teacher) የቅጥር ሁኔታ፦ በቋሚነት (Full-Time) ደመወዝ፦ በስምምነት (በችሎታ ላይ የተመሰረተ) የትምህርት ደረጃ እና የስራ ልምድ የትምህርት ደረጃ፦ በመጀመሪያ ዲግሪ (BA Degree) በልዩ ፍላጎት ትምህርት (Special Needs Education)፣ በኢንክሉሲቭ ትምህርት (Inclusive Education)፣ በስነ-ልቦና (Psychology) ወይም በተዛማጅ መስክ የተመረቀ/ች። የስራ ልምድ፦ ኦቲዝም ፣ የአእምሮ እድገት ውስንነት፣ ዳውን ሲንድረም ወይም ሌሎች ልዩ-ፍላጎት ካላቸው ህጻናት ጋር በልዩ ማዕከል ወይም በትምህርት ቤት ውስጥ 2 ዓመት እና ከዚያ በላይ ቀጥተኛ የስራ ልምድ ያለው/ላት። 📋 ዋና ዋና የስራ ድርሻዎች 👉የእያንዳንዱን ልጅ የክህሎት ደረጃ መነሻ በማድረግ የግል የትምህርት እና የቴራፒ እቅድ (IEP) ማዘጋጀት እና መተግበር። 👉በግል (አንድ ለአንድ) የቴራፒ ድጋፍ መስጠት። 👉በአነስተኛ ቡድን (ከ2-3 ህጻናት) እና በሙሉ ቡድን ውስጥ ተግባራዊ ትምህርት፣ ንግግር እና ማህበራዊ ክህሎቶችን ማስተማር። 👉የልጆችን እለታዊ እድገት በትክክል መመዝገብ እና በየጊዜው በግልጽ የተዋቀረ የሂደት ሪፖርት ማዘጋጀት። 💼 መደብ 2፦ ረዳት መምህር / ቴራፒስት (4 ቦታዎች) የስራ መደብ፦ ረዳት መምህር / ቴራፒስት (Assistance) የቅጥር ሁኔታ፦ በቋሚነት (Full-Time) ደመወዝ፦ በስምምነት 🎓 የትምህርት ደረጃ እና የስራ ልምድ የትምህርት ደረጃ፦ በተዛማጅ መስክ የተሰጠ የምስክር ወረቀት (Certification) ያለው/ላት (ለምሳሌ፦ በልዩ ፍላጎት ረዳትነት፣ በቅድመ-መደበኛ መምህርነት፣ በነርሲንግ፣ በስነ-ልቦና ወይም ተያያዥ የክህሎት ስልጠናዎች)። የስራ ልምድ፦ ከተለያዩ ህጻናት ጋር አብሮ በመስራት፣ በመንከባከብ ወይም በማገዝ ረገድ ተመራጭነት ያለው የስራ ልምድ ያለው/ላት። 📋 ዋና ዋና የስራ ድርሻዎች 👉ዋናው መምህር/ቴራፒስት የሚያዘጋጃቸውን እለታዊ ስራዎች በተግባር ላይ እንዲውሉ ማገዝ። 👉ልጆቹ የምግብ ሰዓት (ቁርስ እና ምሳ) ስነ-ስርዓትን፣ እጅ መታጠብን እና የግል ንጽህናቸውን (ሽንት ቤት አጠቃቀምን) ራሳቸውን ችለው እንዲለማመዱ በቅርብ መርዳት። 👉ከተለያዩ ተግባራት እና ክፍሎች በሚደረጉ ሽግግሮች ወቅት ልጆቹ በተረጋጋ ሁኔታ እንዲንቀሳቀሱ መደገፍ። 👉የመማሪያ ቁሳቁሶችን እና የእይታ መርሃግብር ፕሮግራሞችን (Visual Schedules) በየቀኑ ማደራጀት። 🎯 ለሁለቱም መደቦች የሚፈለጉ አጠቃላይ ክህሎቶች የቋንቋ ችሎታ፦ በአማርኛ እና በእንግሊዝኛ ቋንቋ በጣም ጥሩ የሆነ የንግግር እና የጽሁፍ ችሎታ ያለው/ላት (የቴክኒክ ፅንሰ-ሃሳቦችን ለወላጆች በአማርኛ ማብራራት የሚችል/ምትችል)። ከፍተኛ ትዕግስት፣ ፍቅር፣ እና ልዩ ፍላጎት ያላቸውን ህጻናት ለመርዳት የዳበረ ሰብአዊ ስብዕና። ከባለሙያዎች እና ከወላጆች ጋር በቅንጅት የመስራት ችሎታ። 📬 የማመልከቻ ሂደት የሚፈለገውን መስፈርት የምታሟሉ አመልካቾች የትምህርት ማስረጃችሁን እና የስራ ልምዳችሁን ከማመልከቻ ደብዳቤ ጋር በማያያዝ እስከ ሰኔ 30 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ ማመልከት ትችላላችሁ። በኢሜል ለማመልከት፦ tizazuab1988@gmail.com (የስራ መደቡን ስም በSubject መስመር ላይ መጥቀስ አይርሱ) በቴሌግራም ለማመልከት፦ @Tizaabebe በአካል መጥቶ ለማስገባት፦ ጦር-ሃይሎች ከሙሉ ወንጌል ቸርች ጀርባ ማሳሰቢያ፦ የአዲስአበባ የትምህርት እና ስልጠና ማዕከል ለማንኛውም አመልካች እኩል የስራ ዕድል የሚሰጥ ሲሆን፣ ሴት አመልካቾች ይበረታታሉ። ስልክ መደወል ፈፅሞ የተከለከለ ነው!! https://t.me/gohcenters