- Последний пост
- 14 авг.
- Последнее чтение
- 15 авг.
- Постов за неделю
- 1
- Всего постов
- 38
- Тип
- открытый
- Язык
- ti
- В каталоге с
- 13 авг.
- 1/24сутки в ленте
- 53
- 1/48двое суток
- 60
- 1/72трое суток
- 65
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
ጉራጌ ውስጥ የተፈፀመ አሳዛኝ የታሪክ ጠባሳ. እነኝህ 3 ወጣቶች መኪና ላይ ተሳፍረው እየሄዱ እያለ: ወታደሮች ከመኪና አስወርደው ፋኖ ናችሁ በማለት ረሽነዋቸዋል. አስከሬንም ለቤተሰብ አንሰጥም በማለት ሲያጉላሉ ከቆዩ በሗላ በህዝቡ ተማፅኖ ቀብራቸው ተፈፅሟል. @tikus_tikusuan
የምክክር ኮሚሽን ምናልባት የኢትዮጵያን ግባተ መሬት የሚፈፅም ይመስላል!! @tikus_tikusuan
የህወሓት ቡድን ታንኮችን እና በተሽከርካሪዎች ላይ የተገጠሙ ZU-23 ፀረ አውሮፕላን መድፎችን ጨምሮ ከባድ የጦር መሣሪያዎችን ወደ ራያ ግንባር እያዘዋወረ መሆኑ ታውቋል። @tikus_tikusuan
በዚህ ዘመን የመከራንና የድህነትን አስከፊነት አብዛኛው ኢትዮጵያዊ የሚያቀውና የሚረዳው ቢሆንም: እንደትግራዋይ በከፋ ሁኔታ የሚገኝ አለ ብሎ ለመናገር ይከብዳል. ትግራይ አሁን አፉን ከፍቶ የሚጠባበቅ የሞት ዘንዶ በሏት. አምሀራም ጦርነቱ ባጠረ ጊዜ ፍፃሜ የማያገኝ ከሆነ እጣፈንታው ይኸው ነው. ይህ ወጣት: በባህር እንዳይሰደድ ባህር ላይ መቅረትን ፈርቶ; ትግራይ እንዳይቀመጥ አፈሳን ፈርቶ; ወደአዲስ አበባ ቢመጣ: ደንብ አስከባሪወች እቃውን ወስደው የመከራ እምባ እንዲያለቅስ አደረጉት. እባካችሁ ሰውነትን አስቀድመን እንተዛዘን. @tikus_tikusuan
#Amhara የ8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና ውጤት ይፋ ሆነ። በአማራ ክልል የ2018 የትምህርት ዘመን የ8ኛ ክፍል ክልል አቀፍ ፈተና ውጤት ይፋ ሆኗል። ከሰኔ 3-5/2018 ዓ.ም የተሰጠውን የ8ኛ ክፍል ክልል አቀፍ ፈተና 173,699 ተማሪዎች ውስደው ነበር። ፈተናውን ከወሰዱት ተማሪዎች መካከልም 135,003 (77.72%) ተማሪዎች 50% እና በላይ ውጤት አስመዝግበዋል። ተማሪዎችም ውጤታቸውን https://amhara.ministry.et/#/result የሚለውን አድራሻ በመፃፍ ፤ በሚመጣው ቅጽ ላይ የተማሪ መለያ ቁጥር (Registration Number) እና ስም በአማርኛ በማስገባት ፤ ዉጤት ይመልከቱ (Check your result) የሚለውን ቁልፍ በመጫን ማየት ይችላሉ፡፡ በተጨማሪም @emacs_ministry_result_qmt_bot ላይ መመልከት ይችላሉ። ተማሪዎች ማንኛውም ከውጤት ጋር የተያያዘ ቅሬታ ካላቸው https://amhara.ministry.et/#/complaint ላይ በመግባት ቅሬታቸው ማቅረብ እንደሚችሉ የክልሉ ትምህርት ቢሮ አሳውቋል። 2018 ዓ.ም የ6ኛ ክፍል ክልል አቀፍ ፈተና ውጤት ነገ ይፋ ይደረጋል ተብሏል።
ህውሀት ጦርነቱን ጀምራለች. ከዛሬ ቅዳሜ ሀምሌ 25 2018 ከጠዋቱ 12 ሰአት ጀምሮ ህውሀት በመድፍና በታንክ የታጀበ ተኩስ በሁመራ ሱዳን ድንበር አካባቢ ጦርነት ጀምራ የነበረ ቢሆንም: መከላከያ በወሰደው ርምጃ የመጣው የህውሀት ሀይል ወደሗላ እየተመለሰ ይገኛል. ህውሀትም በበኩሉ: የፌደራል መንግስት በድሮን የታገዘ የዘር ጭፍጨፋ በትግራይ ህዝብ ላይ እየፈፀመ ይገኛል. በመሆኑም ዛሬም እንደትናንቱ መላው ወገናችን ከጎናችን እንዲ መልክት እናስተላልፋለን በማለት መግለጫ አውጥቷል. @tikus_tikusuan
የጎንደር ዩንቨርሲቲን ላለፉት 7 አመታት በፕሬዘዳንትነት ሲያስተዳድሩ የነበሩት ዶ/ር አስራት አፀደወይን የአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩንቨርሲቲ ፕሬዘዳንት ተደረጉ. በርሳቸው ቦታ ደግሞ ዶ/ር የቻለ ከበደ የጎንደር ዩንቨርሲቲ ፕሬዘዳንት ተደርገዋል. @tikus_tikusuan
ከሰሞኑ ፈረስቤት ደጋዳሞት በፋኖና በመከላከያ መካከል በተደረገ ውጊያ መከላከያ ፈረስቤትን መቆጣጠሩ ይታወቃል. መከላከያ እንደመግቢያ ካርድ የተጠቀማቸውም: የ12ኛ ክፍል ተማሪወች የሀገር አቀፍ ፈተናቸውን ተፈትነው ወደየመጡበት ቀዬ በሚመለሱበት ስአት አጅባለሁ በሚል ሰበብ ነው. ሲጀመር ማን አጅብልኝ አለው? እነኝህን ተማሪወች ማን እንዳያግታቸው ተሰግቶ ነው? ፈረስቤት ብቻ አይደለም. ቢቡኝ ወረዳም ያደረጉት ይህንኑ ነው. ፈረስቤት ለመግባት የተመደበው ሀይል ኮረኔልና ሌላው ተዋጊ ሳይቆጠር: ጀነራል ብቻ 4 ነበር የተላከው. መድፍና BM አይነገርም. ፋኖም ተበላሽቶ የቆመና ከጀባ የቀረ መኪናላይ ተኩሶ 4 ተማሪወችን ማቁሰሉ ፍፁም ስህተት ነው. በተለይ አንደኛው ልጅ ደረቱጋ ስለሆነ የተመታው: የመትረፉ ነገር አጠያያቂ ነው. ተማሪ የጫነ መኪና መሆኑን እያወቁና መኪናው ተበላሽቶ ሲቆም መከላከያ ትቶት ሲሄድ በንፁሀን ላይ መተኮስ ፍፁም ጨካኝነት ነው. እነርሱ ፈልገው ላልታጀቡት ነገር የመከላከያን እልህ እነርሱላይ መወጣት አግባብ አይደለም. ለማንኛውም: ተማሪወች ሞተዋል; የሞቱት ቁጥርም 27 ነው. እየተባለ የሚዘዋወረው መረጃ ከእውነት የራቀ ነው. @tikus_tikusuan
ነገ ሀምሌ 11/11/2018 አ.ም ህውሀትን የሚያወግዝ ሰልፍ በአዲስ አበባ ይካሄዳል. @tikus_tikusuan
ህገመንግስቱ ሊሻሻል ነው ወገን! የምክክር ኮሚሽኑ ስራውን ዛሬ በአዲስ አበባ በይፋ ጀምሯል. አዲሱ ህገመንግስት ከመምጣቱ በፊት: ይህኛውን እየተሰናበታችሁ. @tikus_tikusuan
" የቤት ኪራይ ከአብዛኛው ዜጎቻችን ወርሃዊ ገቢ በላይ ሆኗል። በአሁኑ ወቅት በሀገራችን መካከለኛ የሚባል የህብረተሰብ መደብ ጠፍቶ ጥቂት እጅግ የበለፀጉ እና አብዛኛው በድህነት የሚማቅቅ ሁለት መደቦች ሆነዋል " - ደሳለኝ ጫኔ (ዶ/ር) የፓርላማ አባሉ ደሳለኝ ጫኔ(ዶ/ር) ሰላም እና ጸጥታ እንዲሁም የማክሮ ኢኮኖሚ ጉዳዮችን የተመለከቱ ጥያቄዎችን ለጠቅላይ ሚኒስትሩ አቅርበዋል። ደሳለኝ (ዶ/ር) "ላለፉት አምስት ዓመታት የኢትዮጵያ ህዝብ የከፈለው ዋጋ እጅግ የበዛ እና ከባድ ነው እርሶ ስልጣን ላይ ሲቀመጡ የገቡት የሰላም እና የብልጽግና ቃልኪዳን ነበር በተግባር ያየነው ተገላቢጦሹን ነው" በማለት ጠንከር ያለ ትችት ሰንዝረዋል። "የሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት ያስከተለው አስከፊ ሰብአዊ ውድመት እና ጠባሳ ሳይሽር ዛሬም በአማራ፣ በኦሮሚያ፣ በጋምቤላ፣ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ እና በሌሎችም አካባቢዎች የሚታዩት ቀጣይነት ያላቸው ግጭቶች እና ጦርነቶች፣ ብሄር እና ሀይማኖት ተኮር ጥቃቶች፣ እገታዎች እና አለመረጋጋቶች የዜጎችን የመኖር መብት ነፍገዋል" ሲሉም አክለዋል። በቅርቡም "ከትግራይ እና ከኤርትራ ሀይሎች ጋር የሌላ ጦርነት ስጋት አሳሳቢ ደረጃ ላይ ደርሷል" ሲሉም ጉዳዩ የደረሰበትን አሳሳቢነት ጠቁመዋል። በዝርዝር ባቀረቡት ጥያቄ ምን አሉ ? " በፖለቲካው መስክ የፖለቲካ ምህዳሩ መጥበብ፣ የሀገራዊ ተቃርኖዎች መስፋት ወይም Political Polarization፣ የሲቪክ ማህበራት መኮስመን፣ በጋዜጠኞች እና በሚዲያዎች ላይ እገዳዎች እና ክልከላዎች ዜጎች አማራጭ ድምፅ እንዳያሰሙ አፍነዋቸዋል። በርካታ የፖለቲካ እስረኞችም ህገ-መንግስታዊ የፍትህ ዋስትና ተነፍገው ይገኛሉ። ይህ አጠቃላይ የሰላም፣ የፀጥታ እና የፖለቲካ ውድቀት የፓርቲዎ የተሳሳተ ፖለቲካዊ ፍልስፍና ውጤት፣ አንድነትን በተግባር ማምጣት ያቃተው የመደመር ትረካ መዋቅራዊ ስብራት ውጤት ነው። መንግስት የችግሮቹን ስር መሰረት ትቶ ምልክቶቹን ብቻ የመቀጥቀጥና እና በቁጥር ጨዋታ ህዝብን የማደናገር አካሄድ እየተከተለ ነው። በተላከልን የመንግስት አፈፃፀም ሪፖርት ላይ የሀገሪቱ ኢኮኖሚ በ2018 በጀት አመት 10.2% እንደሚያድግ፣ የግብር ገቢ 1.5 ትሪሊዮን ብር መድረሱ፣ የሸቀጦች ወጪ ንግድ 11 ቢሊዮን ዶላር ማስገኘቱ እና የውጭ ቀጥታ ሃዋላ ፍሰት ኢንቨስትመንት 7.7 ቢሊዮን ዶላር መድረሱ ተገልጿል። ነገር ግን እነዚህ የቁጥር ስኬቶች የዜጎችን የመኖር እውነታ ፍፁም አይወክሉም፤ እንዲያውም መሬት ካለው እውነታ ጋር በፅኑ ይጋጫሉ። ምክንያቱም የኑሮ ውድነት እና የዋጋ ግሽበት ከገቢያችን ጋር አልተመጣጠነም። ሪፖርቱ እስከ ግንቦት 2018 ዓ.ም አጠቃላይ የዋጋ ግሽበት 13.4፣ የምግብ የዋጋ ግሽበት ደግሞ 15% ደርሷል ይላል። ይህን ግሽበት ለመደጎም መንግስት 379 ቢሊዮን ብር ማውጣቱ ቢገለፅም በተግባር ግን ባለፉት አመታት የተተገበረው የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ ዝቅተኛውን የማህበረሰብ ክፍል ለከፋ ድህነት በዳረገበት ሁኔታ ላይ እንገኛለን። ማሻሻያውን ተከትሎ የመጣው ሰማይ የነካ የዋጋ ግሽበት በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ዜጎችን የመግዛት አቅም ሙሉ በሙሉ አሳጥቷል። ይህንንም ተከትሎ ቋሚ ደሞዝ የሚከፈላቸው የመንግስት እና የግል ድርጅቶች ሰራተኞች፣ ዝቅተኛ ገቢ ያላቸው የከተማ ነዋሪዎች፣ አነስተኛ ነጋዴዎች፣ አነስተኛ ይዞታ ያላቸው አርሶ አደሮች እና አርብቶ አደሮች ወገኖቻችን በስውር ረሀብ ውስጥ ወድቀዋል። የቤት ኪራይ ከአብዛኛው ዜጎቻችን ወርሃዊ ገቢ በላይ ሆኗል። በአሁኑ ወቅት በሀገራችን መካከለኛ የሚባል የህብረተሰብ መደብ ጠፍቶ ጥቂት እጅግ የበለፀጉ እና አብዛኛው በድህነት የሚማቅቅ ሁለት መደቦች ሆነዋል። በሪፖርቱ መረጃ መንግስት በበጀት አመቱ 1.13 ትሪሊዮን ብር ብድር መልቀቁን እና 91% የሚሆነው ለግሉ ዘርፍ የተሰጠ ነው ይላል። ክቡር የብሄራዊ ባንክ ገዢ እና የፋይናንስ ሚኒስትርም በተደጋጋሚ ላለፉት አመታት መንግስት አንድም ሳንቲም የንግድ ብድር (Commercial Loan) አልተበደረም እያሉ ይናገራሉ። ይህ የውጭ ንግድ ብድርን ብቻ ነጥሎ በማየት እውነታውን የማደብዘዝ አካሄድ ነው። መንግስትዎ በግምጃ ቤት ሰነድ እና በሀገር ውስጥ እዳ ዋስትናዎች አማካኝነት ከሀገር ውስጥ ባንኮች እና ተቋማት በቢሊዮኖች የሚቆጠር ብር እየተበደረ መሆኑን እና ይህም የሀገር ውስጥ እዳ ሸክምን በከፍተኛ ደረጃ እንዳንናረው እና የግሉ ዘርፍ ብድር እንዳጠበበው ለምን ተደበቀ? በየጊዜው በዚህ ፓርላማ የምናፀድቃቸው በቢሊዮኖች ዶላሮች የሚቆጠሩ የእርዳታ ብድሮች (Concessional Loans) ለምን በሪፖርቱ አይካተቱም? የእዳ ምንጭ እና አይነት መለወጡ እዳ መኖሩን ያስቀራል ወይ? ሪፖርቱ አሁንም ድረስ ከዩሮ ቦንድ ባለቤቶች ጋር ያለው ድርድር ስላልተጠናቀቀ ሀገሪቱ በከፍተኛ የእዳ ቀውስ ውስጥ ያለች ወይም Debt Distress መሆኗን ይሸሽጋል። ሌላው የትምህርት እና የማህበራዊ ዘርፍ መውደቅ አለ በሪፖርቱ ላይ 26 ሚሊዮን ተማሪዎች በመመዝገባቸው በስፋት ቢወራም የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ፈተና ከወሰዱ ተማሪዎች መካከል 50% እና ከዚያ በላይ ማምጣት የቻሉት 8.7% ወይም 50 ሺህ ተማሪዎች ብቻ ናቸው። ይህም የመንግስትዎ የትምህርት ጥራት መዋቅራዊ ኪሳራ የሚያሳየን ነው ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ከ8.7% የማለፍ ምጣኔ በየትኛውም አለም ታይቶ የማይታወቅ ወይም 92% የመውደቅ ምጣኔ ከፍተኛ የትውልድ ብክነት ወይም Generational Catastrophe ነው። እኔ የህይወቴን ግማሽ ጊዜ በማስተማር ያሳለፍኩበት በተለያዩ ደረጃዎች እና ኮመን የሚባል አባባል አለ፤ 'መምህሩ ፈተና አውጥቶ ተማሪዎችን ማሳለፍ ካልቻለ እና ከወደቁ የወደቀው መምህሩ ነው' የሚል ኮመን አባባል አለ በእኛ በአስተማሪዎች ዘንድ። እና ይህን ያህል 92% የመውደቅ ምጣኔ ካለ እኔ ወደቋል ብዬ የማስበው ትምህርት ሚኒስቴር ነው። በዚህ ሁሉ ተስፋ አስቆራጭ ሂደት ውስጥ አልፈው ለምረቃ የበቁ ወጣቶችም የስራ እድል የላቸውም ይባስ ብሎም ወደ 7 ሚሊዮን የሚደርሱ ተማሪዎች አሁንም ድረስ ከትምህርት ገበታቸው ተገልለው ይገኛሉ። ይህ 7 ሚሊዮን አሃዝ ከ20 በላይ የአፍሪካ ሀገራት እያንዳንዳቸው ካላቸው አጠቃላይ የህዝብ ቁጥር በላይ መሆኑንም ልብ ይሏል። ሌላው የሰብአዊ ቀውሶች ትኩረት አለመስጠቱ ነው መንግስትዎ የመረጃ ማጥራት ስራ ሰርቻለሁ በሚል ሰበብ የሰብአዊ ድጋፍ ፈላጊዎች ቁጥር ከ27 ሚሊዮን ወደ 2.3 ሚሊዮን ወርዷል ይላል። ነገር ግን መሬት ላይ በጦርነት እና በድርቅ ምክንያት የተፈናቀሉ፣ የለጋሾች እርዳታ ያጡ፣ ለቤተሰቦቻቸው ፍጆታ በቂ ምርት የማይያመርቱ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ዜጎች እያሉ ይህንን ቁጥር ወደ 2.3 ሚሊዮን ዝቅ አድርጎ ማቅረብ ፖለቲካዊ የቁጥር ማሳመር እንጂ የዜጎችን ነባራዊ ህይወት በተጨባጭ የሚያሳይ አይመስለኝም። እነ WFP፣ FAO፣ Famine Early Warning Network የሚያስቀምጡት ዝቅተኛ ግምት ከ15.8 እስከ 21.4 ሚሊዮን ኢትዮጵያውያን ከፍተኛ የምግብ እጥረት ውስጥ እንደሚገኙ ነው " ብለዋል። ምን የመፍትሄ ሃሳብ አቀረቡ ? @tikus_tikusuan
ከሀይማኖት እስከአለማዊ እውቀት ጥንቅቅ አድርገው የሚያቁ: በአማረኛና በእንግሊዘኛ እንዲሁም በግእዝ የሚራቀቁ: ምመኑን አክብረውና ሀቅ ሀቁን እየሰበኩ የዘለቁ: ከሊቅ እስከደቂቅ አፋቸውን ከፍተው ይሰሟቸዋል እርሳቸው ሲናገሩ. እርሳቸው ከአምላካቸው በቀር የሚፈሩት የለም የሚያከብሩት እንጂ! የደሀ እንባና ለቅሶ ይሰማቸዋል: ሀቁን ተናግሮ በመሸበት ማደር የሚለው አባባል ይገዛቸዋል. አባ ገብረኪዳን. ሁልጊዜም ያስገርሙኛል; ያስደንቁኛል: ከርሳቸው ውጭ የሀይማኖት አባት የሌለ እስኪመስለኝ ድረስ: በህሌናዬ ነግሰዋል. በመልካም ስራቸው እኛን ማስገረም ለርሳቸው የተለመደ ቢሆንም: ለኔ ግን የአሁኑ ስራቸው ተለየብኝ. የመንግስትን ግንባር ተቋቁመው: በባህርዳር ከተማ ከአዲሱ ድልድይ አካባቢ ቦታ ተቀብለው: ሀይማኖቱ ሳይጠየቅ ታማሚ የሚታከምበት ሆስፒታል ሊያስገነቡ እነሆ የመሰረት ድንጋይ እያስቀመጡ ናቸው. እንዲህ ነው የሀይማኖት አባት ማለት! ፓትሪያርኩ ሳይቀር በሀገራችን ታሪክ አድርጎት የማያቀውን ተግባር እርሰዎ አድርገው ስላሳዩን በአምላካችን ስም እናመሰግነወታለን. ፈጣሪ እድሜና ጤና ያድልልን. ለቤተክርስቲያን ድጋፍ ማድረግስ እንዲህ ላለው ተግባር ነውና: ሁላችንም በምንችለው እንረዳ ዘንድ መልክታችን ነው. @tikus_tikusuan
без подписи
без подписи
без подписи
без подписи
#2 ከላይ የቀጠለ የፌዴራል ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ወደ 70 በሚጠጉ ክፍት የሥራ መደቦች ላይ ሠራተኞችን በኮንትራት እና በዝውውር አወዳድሮ መቅጠር ይፈልጋል። ለመመዝገብ ይህን ማስፈንጠሪያ ይንኩ https://forms.lmis.gov.et/federal_-civil_services_new/ ወይም ዋናውንና ኮፒ የትምህርትና የስራ ማስረጃችሁን ይዛችው ፍላሚንጎ በሚገኝው ዋና ማስሪያ ቤት መመዝገብ የምትችሉ መሆኑን ተገልጿል። @tikus_tikusuan
без подписи
без подписи
без подписи