tgindex
የመዝሙርና ኪነ ጥበባት ሚዲያ ክፍል

የመዝሙርና ኪነ ጥበባት ሚዲያ ክፍል

Статистика

ይህ ቻናል የክፍሉ ስራዎች ለአባሉ የሚደርስበት ይሆናል

Последний пост
12 авг.
Последнее чтение
15 авг.
Постов за неделю
1
Всего постов
20
Тип
открытый
Язык
und
В каталоге с
15 авг.
Подписчики
1 555
0 за сутки
Сутки
0
0,00%
Неделя
 
Месяц
 
Просмотров на пост
682
19 постов
Вовлечённость
43,9%
к подписчикам
Постов в день
0,1
всего 20
Упоминаний
0
каналов
Охват размещения
оценка
1/24сутки в ленте
140
1/48двое суток
160
1/72трое суток
173

Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.

Посты

  • ለምን የአብነት ተማሪዎች የደብረታቦር ዕለት ይዘክራሉ ? 🤔 በማቴዎስ ወንጌል ምዕራፍ ፲፯ ከቁጥር ፩-፱ ያለው የእግዚአብሔር ቃል :-      ከስድስት ቀንም በኋላ ÷ ጌታችን ኢየሱስም ጴጥሮስን፣ ያዕቆብን እና ወንድሙንም ዮሐንስን ይዞ ወደ ረዥም ተራራ ብቻቸውን አወጣቸው። መልኩም በፊታቸው ተለወጠ፤ ፊቱም እንደ ፀሓይ በራ ልብሱም እንደ ብርሃን ነጭ ሆነ። እንሆም ሙሴና ኤልያስ ከርሱ ጋራ ሲነጋገሩ ታዩዋቸው። ጴጥሮስም መልሶ ጌታችን ኢየሱስን ጌታ ሆይ በዚህ መኾን ለእኛ መልካም ነው ብትወድስ በዚህ ሦስት ዳስ አንዱን ለአንተ አንዱንም ለሙሴ አንዱንም ለኤልያስ እንሥራ አለ። እርሱም ገና ይህን ሲናገር እንሆ ብሩህ ደመና ጋረዳቸው እንሆም ከደመናው ውስጥም ''በርሱ ደስ የሚለኝ የምወደው ልጄ ይህ ነው ርሱን ስሙት'' የሚል ድምፅ መጣ። ደቀ መዛሙርቱም ሰምተው በፊታቸው ወደቁ እጅግም ፈርተው ነበር። ጌታችን ኢየሱስም ቀርቦ ዳሰሳቸውና ተነሡ አትፍሩም አላቸው። ዐይናቸውንም አቅንተው ሲያዩ ከጌታችን ከኢየሱስ ብቻ በቀር ማንንም አላዩም። በማለት ይነግረናል። ይህ ዕለት ከተሰዓቱ ዐበይት በዓላት መካከል አንዱ ሲሆን በዚህ ወቅት ለሐዋርያት የክርስቶስ የባህርይ ልጅነት ከባህርይ አባቱ ተገልጧልና፣ እንዲሁም የባህርይ አምላክነቱን በመግለጥ በልባቸው የነበረውን ጥርጣሬ አስወግዶላቸዋልና፣ በተጨማሪም ነገረ ሥጋዌውን እንዲሁም ምስጢረ ሥላሴን ገልጦላቸዋልና። የአብነት ተማሪዎችም አቤቱ በዚህ ዘመን ላለን ሐዋርያትን በመምሰል አርድዕተ ሊቃውንት ለሆንን ለእኛም ትምህርታችንን ግለጥልን፣ የራቀውን አቅርብልን የቀረበውንም አራቅልን በማለት በየዓመቱ ነሐሴ ፲፫ የደብረታቦር ዕለት ዝክር ይዘክራሉ። ይህ ዕለትም በፖሊ ግቢ ጉባዔ አብነት ተማሪዎች በደመቀ እና በአማረ መልኩ ይከበራል ። ለበዓሉ ማዘጋጃ ድጋፍ ለምታደርጉ :- ንግድ ባንክ :-1000358173199 ተስፋሁን ገድፍ እሸቴ እመሰ ረሳይኩኪ ቤተ ጉባዔ ለትርስዓኒ የማንየ ወይጥጋዕ ልሳንየ በጉርዔየ   መዝ 136÷8 ትርጉም:-   የአብነት ቤተ ጉባዔ ሆይ ብረሳሽ ቀኘ ትርሳኝ፣ ባላስብሽም ጉረሮየ ከተናጋየ ትጣበቅ። እርስዎም ድጋፍ በማድረግ ፣ በዕለቱ በመገኘት የበረከቱ ተካፋይ ይሁኑ ❗️ ⏰ሰዓት:- ምሽት 11:00 📆ቀን:- ነሃሴ 13/12/2018 ዓ.ም 🏛ቦታ:- አቡዬ ግቢ ጉባዔ አዳራሽ አዘጋጅ :- ፖሊ ግቢ ጉባዔ አብነት ተማሪዎች ────────── ✦ ──────────                        ፖሊግቢ ጉባኤ 📩@polygbigubaecommentbox ለሃሳብ አስተያየትዎ 📚@polylibrary   መፅሐፍትን ለማንበብ 📖@polytmhirt   ለኮርስ 📷@mkpoly_gallery  የፎቶ እና ቪዲዮ ማኅደር ────────── ✦ ──────────               Telegram | Instagram

  • እንኳን ለጾመ ፍልሰታ ጾም በሰላም አደረሳችሁ❕ ​ጾመ ፍልሰታ የእናታችን የቅድስት ድንግል ማርያም ፍቅርና በረከት በሁላችንም ላይ የሚፈስስበት፤ በተለይም የሕጻናትን ልብ በቅዱስ ደስታና በየዋህነት የሚሞላ የተቀደሰ ወቅት ነው። ​ሕጻናት በነጭ ነጠላ ተሸፋፍነው በጠዋት ወደ ቤተክርስቲያን ሲገሰግሱ፣ ታቦት ሰርተው በደስታ ሲዘምሩና ምጽዋት ሲካፈሉ ማየት የፍልሰታን በረከት ልዩ ያደርገዋል። ​እግዚአብሔር አምላክ ጾሙን የሰላም፣ የፍቅርና የበረከት ያድርግልን፤ የእመቤታችን አማላጅነት አይለየን❕

  • ++ ኪነጥበብ - መንፈሳዊ መነባንብ !! (ርዕስ - ግቢ ጉባኤ ትዝ አለኝ) የፍረሽ ቅበላው ትምህርት መጀመሪያው፡ የከረመው ግቢ አየሩን ስንቀስመው፡ ዌል ካም ሩጫው መልካም ግርግሩ፡ የልዩ ጉባኤው እሑድ መርሃ ግብሩ፡ . . . . . . . ትዝ አለኝ. . . . . . . . . ነጭ ነጭ ለብሶ ማስታወሻ ይዞ ለጉባኤ መብረር፡ ቀኖናና ዶግማ ሥርዓት ለመማር፡ ደግሞ ተመልሰን ጭምጨማው ችከላው፡ አቤት ተማሪነት ስንቱን አሳለፍነው። . . . . . . . ትዝ አለኝ. . . . . . . . . የበዓል ዋዜማው ማኅሌት ቅዳሴው፡ በተማሪ ድባብ ተመስጠን ስንቆመው፡ መዝሙር ምስጋናውን በኅብረት ስናወርድ፡ የበዓል ድግሱን የፍቅሩን ማዕድ፡ ስንጎራረሰው ሁላችን አንድ በአንድ፡ . . . . . . . ትዝ አለኝ . . . . . . . . . መሮጥ ለአገልግሎት ማዘዝ መታዘዙ፡ ንስሐ አባትን ለማግኘት መፍጠኑ፡ ጭቅጭቅ ንትርክ ክርክሩ ቁጣው፡ ያ ሁሉ ለመልካም በኛ ዘንድ የሆነው፡ . . . . . . ትዝ አለኝ . . . . . . . ለንግስ ተያይዞ ከተማ ማቋረጥ፡ በማታም በሌሊት ዝማሬውን ማቅለጥ፡ ቅዱሳት መካናት አይቶ ለመባረክ፡ ተራራ ቁልቁለት መውጣትና መውረድ በጉልበት በእንብርክክ፡ መጓዝ በመኪና ወደ ፊት መገስገስ፡ የተቀደሰውን ነክቶ ለመቀደስ፡ . . . . . . . ትዝ አለኝ . . . . . . . . ሱባኤና የሰርክ ማኅበር ፀሎቱ፡ ደካማው በብርቱ ሲታገዝ ማየቱ፡ ኧረ እንዴት ደስ ይላል ያ ሁሉ ትጋቱ። . . . . . . . . ትዝ አለኝ . . . . . . . የህይወት ውይይት በክፍል በክፍል፡ ዛሬ ምን አደረግህ አንችስ ምን አገኘሽ ስንል ስንባባል፡ በጠዋት በማታ ተቀሳቅሶ መሄድ ለህይወት መታገል፡ አቤት መጣፈጡ እንዴት ነፍስ ይገዛል፡ የአንዱን ሸክም ሌላው ሲሸከም ደስ ይላል። . . . . . . . . ትዝ አለኝ. . . . . . . . ከምሥራቅ ከምዕራብ ከሰሜን ከደቡብ፡ የመጣነው ሁሉ ለየራሳችን ግብ፡ መስርተን ተገኝተን ጠንካራ ቤተሰብ፡ በማትናወጠው በስላሴ ወደብ፡ ስንሄድ ስንመጣ ሲያየን ጎረቤቱ ይሉ ነበር አጀብ። . . . . . . . . ትዝ አለኝ . . . . . . . . . ገናና ፋሲካ በዓሉ ሲመጣ፡ ሽር ጉድ ስንል ስንገባ ስንወጣ፡ አምናና ታች አምና እዚህ የነበረ ወንድማችን መጣ፡ ብለን በደስታ አቅላችን ስናጣ፡ ሲገኝ ፍሪዳውን ዳቦውን ሲታጣ፡ ለማቅረብ ስንኳትን በቀንና ሌሊት፡ ውሃውን ስንቀዳ ሊጡን ስናቦካ ሲያምርብን የዛንለት፡ እሳቱ ሲገርፈን ጭቃውም ሲነካን፡ ፍፁም ደስ ይለናል ከሌሎች ጋር ሆነን። . . . . . . . . . ትዝ አለኝ . . . . . . . የግንቦት ልደታ በእንግዶች ታጅበን፡ በጧፍ መብራት ደምቀን በዜማ ረስርሰን፡ ስናከብር ማርያምን እማሆይ ጋር ሆነን፡ . . . . . . . ትዝ አለኝ. . . . . . . . አብሮን የቆየውን ቅድመ አባታችን ቅድመ አያታችን፡ ሲሄድ ሸኝተነው ስትሄድ ሸኝተናት በእንባችን ተራጭተን፡ እኛም ተቀብለን አዲሱን ቤተሰብ በደንብ አቋቁመን፡ ደግሞ ደረሰና እኛም ተሸኝተን ቃል ኪዳኑን ይዘን መስቀሉን አጥልቀን፡ ኢየሩሳሌም ሆይ፡ ግቢ ጉባኤ ሆይ አልረሳሽም ብለን፡ ዘምረን ተጫውተን የልብ የልባችን፡ ምከረኝ ምከሪኝ ምን ላድርግ እንግዲህ እንዲያ ተባብለን፡ . . . . . . . ትዝ አለኝ. . . . . . . . . . ግቢውን አቋርጠን እስራኤልን መስለን፡ ከበሮ እየመታን ነጋሪት ጎስመን መለከቱን ነፍተን፡ ስንጓዝ በአንድ ላይ እግዚአብሔርን ይዘን ማደሪያውን ይዘን፡ ባህረ ጥምቀቱ እንዴት ይረሳኛል፡ ጉባኤው ዝማሬው ልቤን ይንጠኛል። . . . . . . . ትዝ አለኝ . . . . . . ብቻ ሁሉም ነገር እዛ የነበረው፡ ትዝ አለኝ በድንገት ልቤን በረበረው፡ እናቴ ግቢ ጉባኤ በዚሁ እንደምን ነሽ? ይችን ስዕለት ስሚኝ በለመደ ግብርሽ፡ ፍቅርሽ አነሳስቶ ያብረኝ ያክንፈኝ አንዴ ዳግም ልይሽ። ወስብሐት ለእግዚአብሔር ወለወላዲቱ ድንግል ወለመስቀሉ ክቡር ይቆየን !!

  • видео или голосовое, без подписи

  • ንዒ ሀቤነ ንዒ ሀቤነ ኦ ድንግል ምስለ ወልድኪ መድኃኒነ ከመ ትባርኪ ላዕሌነ ነይ ከአምላክሽ ጋር ከልጅሽ ይቅር እንዲለን በምልጃሽ ንዒ ድንግል(፪)ከልጅሽ ከአማኑኤል       አዝ = = = = = = የሐና የኢያቄም መልካም ተክል የሐዋርያት ስብከት የሰማዕታት አክሊል ነይ ድንግል(፪)ነይልን ፈጥነሽ ድንግል       አዝ = = = = = = አሕዛብ ነገሥታት ይገዙልሻል የናቁሽም ሁሉ ይሰግዱልሻል የእግዚአብሔር ከተማ (፪)ድንግል ሆይ ፅዮን ይሉሻል       አዝ = = = = = = በጥልቅ ማዕበል ሳለን በኃጢአት ወጥመድ ተይዘን ድረሽልን(፪)ከልጅሽ አንቺ አማልጅን

  • видео или голосовое, без подписи

  • 27 июн.1 01332

    💐🌹🌹🌹🌹ውድ የ2018 ዓ ም ተመራቂ እህት ወንድሞቼ እንኳን ለዚች በጉጉት ስትጠብቋትና ስትናፍቋት ለነበረችው ቀን በሰላም አደረሳችሁ አደረሰን 🌹🌹🌹🌹💐 🌹🌹🌹🌹🌹 🌹🌹🌹🌹🌹 🌹🌹 🌹🌹 🌹🌹 እንኳን ደስ አላችሁ 🌹🌹 🌹🌹 🌹🌹 🌹🌹🌹🌹 🌹🌹🌹🌹🌹🌹 “ሁሉ በእርሱ ሆነ፥ ከሆነውም አንዳች ስንኳ ያለ እርሱ አልሆነም።” — ዮሐንስ 1፥3 ✨ነገ እሁድ እንደሚታወቀው በቤተ ክርስቲያን ደግሞ ምርቃት ይኖረናል ፤ በዚህም ዕለት ስንዘጋጅ የነበረውን ወረብ ስለምናቀርብ መርሃ ግብሩ 2፡00 ስለሚጀመር እኛ ቀድመን አንድ ጊዜ ማየት ስላለብን በተባለው ሰዓት ወረቡን የምናውቅ በሙሉ እንድንገኝ ይሁን ።✨ ሰዓት፡ ጠዋት 1፡00 ቦታ፡ ፔዳ ቅድስት ሥላሴ አዳራሽ 👉ለበለጠ መረጃ በ0952757862 ይደውሉ ──────── ✦ ──────────                     ፖሊ ግቢ ጉባኤ

  • ተወዳጆች ሆይ እንዴት ናችሁ 👋 “ስለዚህ፥ ወንድሞች ሆይ፥ መጠራታችሁንና መመረጣችሁን ታጸኑ ዘንድ ከፊት ይልቅ ትጉ፤ እነዚህን ብታደርጉ ከቶ አትሰናከሉምና።” — 2ኛ ጴጥሮስ 1፥10 ከብዙ ተመራቂዎች መሀል የእግዚአብሔር ቃል ለመመስከር የተመረጣችሁ ሁሉ ነገ የመጨረሻ የወረብ ጥናት አዳር ስላለ በተባለው ሰዓት እና ቦታ ጠሪን አክብረን እንድንገኝ ይሁን ። 📅 ነገ ሐሙስ ምሽት 1፡00 ጀምሮ ⛪️ ግቢ ጉባኤ አዳራሽ ማሳሰቢያ፡ ክረምት እየገባ ስለሆነ ወፈር ያለ ልብስ ለብሰን እራት በጊዜ በልተን እንድንመጣ ይሁን።

  • የወረብ ጥናት ☺️ 🔶ውድ ተመራቂያን ትናንት ጥናት ተብሎ ተማሪ ባለመገኘቱ ምክንያት ጥናት አልነበረም ቀኑ እየደረሰ ስለሆነ ዛሬ ሁላችንም ሰዓት አክብረን በመገኘት የግል ሀላፊነታችንን እንወጣ ፤ ለጓደኞቻችንም ሼር እናድርግ። ዛሬ ረቡዕ ከቀኑ 9፡00 -11፡30 ጥናት ይኖራል ቦታ፡ ግቢ ጉባኤ አዳራሽ ሰላመ እግዚአብሔር አይለየን 🙏

  • ለተከታታይ ቀናት የወረብ ጥናት ☺️ 🔶ውድ ተመራቂያን እንደሚታወቀው እሁድ በ21/10/2018 ለሁሉም ኦርቶዶክስ የባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ተመራቂ ተማሪዎች ሰላም አርጊው ማርያም ምርቃት ይኖራል። 🔶 እዚህ መርሃ ግብር ላይ ደግሞ እንደ እኛ ግቢ ጉባኤ ወረብ በመዘጋጀት ላይ እንገኛለን ስለሆነም በፈተና ምክንያት በደንብ ስላልተዘጋጀን ከዚህ በኋላ ባሉት ቀናት ተከታታይ ጥናት ስለሚኖር ተቀሳቅሰን በሰዓት በመገኘት እንድናጠና ይሁን። ነገ ማክሰኞ ከቀኑ 9፡00 -11፡30 ጥናት ይኖራል ቦታ፡ ግቢ ጉባኤ አዳራሽ ሰላመ እግዚአብሔር አይለየን 🙏

  • ሰላም እንዴት ናችሁ ውድ ተመራቂያን የመውጫ ፈተና የተፈተናችሁ እንኳን በሰላም ጨረሳችሁ ፤ ገና ለምትፈተኑ ደግሞ መልካም ፈተና ይሁንላችሁ እያልኩኝ ቅዳሜ ለእሁድ አዳር የወረብ ልምምድ ስለሚኖር ሁላችንም ከአሁኑ አስበንበት ሌላ ፕሮግራም ሳንደርብ እንድንገኝ ይሁን ። ድምፁ መልካም በሆነ ጸናጽል አመስግኑት፤ እልልታ ባለው ጸናጽል አመስግኑት ፤ እስትንፋስ ያለው ሁሉ እግዚአብሔርን ያመስግን =>…

  • ሰላም እንዴት ናችሁ ውድ ተመራቂያን የመውጫ ፈተና የተፈተናችሁ እንኳን በሰላም ጨረሳችሁ ፤ ገና ለምትፈተኑ ደግሞ መልካም ፈተና ይሁንላችሁ እያልኩኝ ቅዳሜ ለእሁድ አዳር የወረብ ልምምድ ስለሚኖር ሁላችንም ከአሁኑ አስበንበት ሌላ ፕሮግራም ሳንደርብ እንድንገኝ ይሁን ። ድምፁ መልካም በሆነ ጸናጽል አመስግኑት፤ እልልታ ባለው ጸናጽል አመስግኑት ፤ እስትንፋስ ያለው ሁሉ እግዚአብሔርን ያመስግን => መዝ 150፥5-6 ⏰ ምሽት 2፡00 📅 ቅዳሜ በ13 - 2018 ዓ.ም ⛪️ ግቢ ጉባኤው አዳራሽ ────────── ✦ ──────────                     ፖሊ ግቢ ጉባኤ

  • የመዝሙርና ኪነ ጥበባት ሚዲያ ክፍል pinned «ታውቃላችሁ አይደል 🤔? የተመራቂ ተማሪዎች ወረብ ጥናት መጀመሩን ግን የምትቀሩበት ምክንያት የወረብ እንቅስቃሴ ስለማንችል ነው ብላችሁ እንደሆነ ሰምቻለሁ ፤ ይሁን እንጂ ፍላጎት ኖሮት አልችልም ብሎ ማንም ከምስጋናው እንዳይቀር ታስቦ የወረብ እንቅስቃሴ ልምምድ ስለተዘጋጀ መለማመድ የምትፈልጉ በሙሉ በሰዓት እንድትገኙ ይሁን። ድምፁ መልካም በሆነ ጸናጽል አመስግኑት፤ እልልታ ባለው ጸናጽል አመስግኑት ፤…»

  • 12 июн.1 14134

    ታውቃላችሁ አይደል 🤔? የተመራቂ ተማሪዎች ወረብ ጥናት መጀመሩን ግን የምትቀሩበት ምክንያት የወረብ እንቅስቃሴ ስለማንችል ነው ብላችሁ እንደሆነ ሰምቻለሁ ፤ ይሁን እንጂ ፍላጎት ኖሮት አልችልም ብሎ ማንም ከምስጋናው እንዳይቀር ታስቦ የወረብ እንቅስቃሴ ልምምድ ስለተዘጋጀ መለማመድ የምትፈልጉ በሙሉ በሰዓት እንድትገኙ ይሁን። ድምፁ መልካም በሆነ ጸናጽል አመስግኑት፤ እልልታ ባለው ጸናጽል አመስግኑት ፤ እስትንፋስ ያለው ሁሉ እግዚአብሔርን ያመስግን => መዝ 150፥5-6 ⏰ 11፡00 📅 እሁድ 7 - 2018 ዓ.ም ⛪️ ግቢ ጉባኤው አዳራሽ ────────── ✦ ──────────                     ፖሊ ግቢ ጉባኤ

  • 9 июн.1 38026

    ሰላም ለእናንተ ይሁን ውድ የ2018 ተመራቂ ተማሪዎቻችን! ከእግዚአብሔር ቤት መረቅናችኹ መዝ 117÷26 🔶የወረብ ዝማሬ ጥናታችን ሃሙስ ስለሚቀጥል የተለቀቁትን ዜማዎች አዳጠን ሁላችንም ተመራቂ ተማሪዎች ተቀሳቅሰን በሰአት እንድንገኝ ይሁን። ✨ኑ! አብረን አጥንተን በምርቃታችን ዕለት ለአምላካችን በዝማሬ ምስጋናን እናቅርብ🤲 ⏰ሰዓት: 10:30 📅ቀን: ሃሙስ 4 - 2018 ዓ.ም ⛪️ቦታ: ግቢ ጉባኤው አዳራሽ ────────── ✦ ──────────                     ፖሊ ግቢ ጉባኤ

  • 8 июн.1 0413

    видео или голосовое, без подписи

  • ወረብ

  • ሰላም

  • አቡን የቀጠለ...

  • አቡን

የመዝሙርና ኪነ ጥበባት ሚዲያ ክፍል — tgindex