MS SCHOOL GRADE 1--4
Статистикаይህ ቻናል የኤም ኤስ ት/ቤት ከ1--4 ክፍል ላሉ ተማሪዎች መረጃ መስጪያ ነው።
- Последний пост
- 14 нояб.
- Последнее чтение
- 15 авг.
- Постов за неделю
- 0
- Всего постов
- 20
- Тип
- открытый
- Язык
- und
- Категория
- Новости и СМИ (по похожим)
- В каталоге с
- 15 авг.
- 1/24сутки в ленте
- —
- 1/48двое суток
- —
- 1/72трое суток
- —
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
видео или голосовое, без подписи
#ትኩረት🚨 ሄሞራጂክ ፊቨር (Hemorrhagic Fever ) ምንድን ነው ? በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጂንካ ከተማ ምንነቱ በመረጋገጥ ላይ ያለ Hemorrhagic Fever (ሄሞራጂክ ፊቨር) መከሰቱን የጤና ሚኒስቴር በትላንትናው ዕለት በሰጠው መግለጫ ማሳወቁ ይታወቃል። ምንነቱ በመረጋገጥ ላይ ያለው በሽታ ምክንያት በጂንካ ከተማ ሁለት የጤና ባለሞያዎችን ጨምሮ በአጠቃላይ ስድስት ሰዎች ህይወት ማለፉን መዘገባችን ይታወሳል። እስካሁን ስለበሽታው በጤና ሚኒስቴር የተገለጹ መረጃዎች ምንድን ናቸው ? እንደ ጤና ሚኒስቴር መረጃ እስካሁን በበሽታው ስምንት ሰዎች ተጠርጥረዋል። ተጨማሪ ስርጭትን ለመግታት እና ለመከላከል እንዲሁም ምንነቱን ለማወቅ የላብራቶሪ ምርመራዎች እየተከናወኑ ነው። በላብራቶሪ ምርመራ ውጤቱ እና በምንነቱ ዙሪያ እስካሁኗ ሰአት ድረስ ከጤና ሚኒስቴርም ሆነ ከኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የተሰጠ መግለጫ የለም። ቲክቫህ ኢትዮጵያ ቫይራል ሄሞራጂክ ፊቨር ምንድነው ? ምልክቶቹ እና መከላከያ መንገዶቹስ ? በሚለው ዙሪያ የውስጥ ደዌ ስፔሻሊስት እና የተላላፊ በሽታዎች ፌሎ የሆኑትን ዶ/ር ሰላም ቦጋለን አነጋግሯል። ቫይራል ሄሞራጂክ ፊቨር (Viral Hemorrhagic Fever) ምንድን ነው ? " ቫይራል ሄሞራጂክ ፊቨር (Viral Hemorrhagic Fever) በተለያዩ ምድቦች ሚከፈሉ የቫይረስ አይነቶች ሚከሰት ከባድ ምልክቶችን ያከተተ የህመም አይነት ስብስብ ሲሆን ፦ - ትኩሳት፣ - ደም መድማት፣ - የሰውነት ክፍሎች (ኦርጋኖች) ስራ እክል የእነዚህ ህመሞች ምልክት ነው። በተለያዩ የቫይረስ አይነቶች ሲከሰት ሚያመሳስላቸው ምልክት እንዳለ ሆኖ የህመሙ መተላለፊያ፣ ክብደት እና መከላከያ እንደየ ቫይረሱ አይነት ይለያያል። " ለቫይራል ሄሞራጂክ ፊቨር መከሰት መንስኤዎች ምንድን ናቸው ? " ለቫይራል ሄሞራጂክ ፊቨር መከሰት :- ➡️ ኢቦላ (Ebola virus) ➡️ ማርበርግ (Marburg virus) ➡️ Lassa fever virus(ላሳ ፊቨር ቫይረስ) ➡️ ደንጉ (Sever Dengue virus) ➡️ የሎው ፊቨር (Yellow fever virus) ➡️ ሪፍት ቫሊ ፈቨር ቫይረስ (Rift Valley Fever virus) ➡️ ክሪሚየን ኮንጎ (Crimean-Congo haemorrhagic fever) እና ሌሎች ቫይረሶች መንስኤ ናቸው። " በበሽታው የተያዘ ሰው የህመሙን ምልክቶችስ በምን ያህል ቀናት ውስጥ ማሳየት ይጀምራል ? " እነዚህ ህመሞች አንድ ሰው ከተያዘ በአማካኝ ከ2 እስከ 21 ቀን ምልክት ማሳየት ይጀምራሉ። " በበሽታው የተያዘ ሰው የሚያሳያቸው ምልክቶች ምንድን ናቸው ? " ሲጀምሩ እንደሌሎች ትኩሳት አምጪ ተላላፊ ህመሞች ፦ • ራስ ምታት፣ • ትኩሳት፣ • ብርድ ብርድ ማለት፣ • ጡንቻ ህመም፣ • ድካም ፣ • ትውከት እና የምግብ ፍላጎት መቀነስ ያስከትላሉ። ቀስ በቀስ ከበድ በማለት ደም ከተለያዩ የሰውነት ክፍሎች መድማት ይጀምራል። እንዲሁም የሰውነት ክፍሎች (ኦርጋኖች) ለምሳሌ ሳንባ፣ ኩላሊት ፣ ጉበት ስራቸው ይዳከማል እንዲሁም ደም ግፊት መውረድና ሌሎችም የሰውነት አካሎች ጉዳትና ሞት ሊያስከትሉ ይችላሉ። " የበሽታው ክብደት እና የሞት ምጣኔ ምን ይመስላል ? " የሞት ምጣኔ እንደየ ቫይረሱና ክብደቱ ሲለያይ ደንጉ (Sever Dengue virus) ከባድ ህመም ሳያመጣ ከመዳን እስከ ተወሰነ ሞት ያስከትላል፣ ላሳ (Lassa fever virus) እስከ 20 በመቶ ሞት ሲያስከትል እንዲሁም እነ ማርበርግ ቫይረስ ደግሞ እስክ 80 በመቶ ሞት ሊያስከትሉ ይችላሉ። ከላይ የተጠቀሱት ምልክቶች በሂሞራጂክ ፊቨር ብቻ ሳይሆን በሌሎች ህመሞችም ምክንያትም ሊከሰቱ ይችላሉ ለምሳሌ ከባድ ወባ፣ በባክቴርያ የሚመጣ ሴፕሲስ (sepsis)፣ ሜኒንጆኮከስ ተብሎ ሚጠራው ማጅራት ገትር አምጪ ተህዋስ እነዚህን መሰል ምልክቶች ሊያስከትሉ ይችላሉ ስለዚህ የህመሙ ምንነት በምርመራ መረጋገጥ አለበት። " መተላለፊያ መንገዶቹ አስተላላፊዎቹስ ምን ምን ናቸው ? " የቫይራል ሄሞራጂክ ፊቨር (Viral Hemorrhagic Fever) መተላለፍያ መንገዶች እንደየ ቫይረሱ ይለያያል። ቢንቢ (Aedes aegypti ተብሎ ሚጠራው ትንኝ) ፡- ደንጉ (Sever Dengue virus) እና የሎው ፊቨር (Yellow fever virus) ያስተለልፋል። የለሊት ወፍ (bat) ፡ ኢቦላ (Ebola virus) እና ማርበርግ (Marburg virus) ያስተላልፋል። የአይጥ አይነቶች ( rodents) ፦ ላሳ የተሰኘውን ፊቨር ቫይረስ (Lassa) ያስተላልፋል። መዥገር (tick) :- ክሪሚየን ኮንጎ (Crimean-Congo haemorrhagic fever) የተሰኘውን ያስተላልፋል። ከላይ የተጠቀሱት የቫይረሱ አይነት እና አስተላላፊዎች ሲሆኑ በተለይ ኢቦላ (Ebola virus) እና ማርበርግ (Marburg virus) በበሽታው ከታመመ ሰው ጋር በሚኖር የቅርብ አካላዊ ንክኪ (ደም ወይም ፈሳሽ) ይተላለፋሉ። " በበሽታው መያዛችንን ከጠረጠርን ምን እናድርግ ? " ከላይ የተጠቀሱ ምልክቶች ሲከሰቱ በቶሎ ጤና ተቋም መሄድ ያስፈልጋል። እነኚህ ህመሞች ሰውነት ላይ ያስከተሉት ጉዳት በተለያዩ ምርመራዎች ይታያል እንዲሁም ትክክለኛ መንስኤው በደም ወይም ሰውነት ፈሳሽ ናሙና ምርመራ መረጋገጥ አለበት። የህክምና እርዳታ በቶሎ ማድረግ ለማገገም እንዲሁም መተለለፍን ለመቀነስ ይረዳል። " በበሽታው መያዛችን ከተረጋገጠ ምን አይነት ህክምናዎች ይሰጣሉ ? " ባለሞያዎች የተለያየ ለምሳሌ ግሉኮስ ወይም እንዳስፈላጊነቱ ደም መስጠት፣ ህመም ማስታገስ፣ ኦክስጅን እንዲሁም መተንፈሻና የኩላሊት ህክምና እንደየ ክብደቱና አይነቱ ያደርጋሉ። በስፋት ባይገኙም ለተወሰኑት አይነቶች የተዘጋጁ መድሃኒቶች አሉ። የቫይረሱን ስርጭት ለመግታት የታወቀን ህመምተኝ ለይቶ ማከም፣ ንክኪን ማስወገድ መሰረታዊ ነው ሌሎች መተላለፍያ ዘዴዎችን መቆጣጠርም ያሻል። የሎው ፊቨር እና ደንጉ ለረጅም ግዜ ሚታወቁ ክትባቶች አላቸው ኢቦላም ክትባት አለው። " ዶ/ር ሰላም ስለህመሙ የበለጠ ለማወቅ የህብረተሰብረተሰብ ጤና ኢንስቲቱት እና ጤና ሚኒስተር ስለመንስኤው የሚሰጡዋቸውን የክትትል ውጤቶችን እና መግለጫዎች መከታተል አስፈላጊ መሆኑን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት ቃል አሳስበዋል። ቲክቫህ ኢትዮጵያ አዲስ አበባ #TikvahEthiopiaFamilyAA @tikvahethiopia
🔖 ማስታወሻ 🔖 ✍ የክፍያ ማስታወቂያ✍ የጥቅምት ወር ክፍያ ከመስከረም 25 -ጥቅምት 5 ድረስ ብቻ ያለቅጣት በአዲስ ባንክ የኢ-ሰኩል በኩል የመስከረም ወር እንዲከፍሉ የተሰጥዎትን የልጅዋን መለያ ኮድ በመጠቀም መክፈል እንደሚችሉ ልናስታዉስዋ እንወዳለን። አብረን በመስራት ለውጥ እናመጣለን ኤምኤስ ት/ቤት
видео или голосовое, без подписи
ውድ የኤም ኤስ ት\ቤት ተማሪዎች፣ወላጆች እና ሰራተኞች እንኳን ደስ አላችሁ። በ2017ዓም የ8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና ከተፈተኑ የማዕከላዊ ክልል የ8ኛ ክፍል ተማሪዎች መካከከል ተማሪ ሀሴት ፀጋዬ አሩሲ 94.17 በማምጣት 3ኛ የወጣች ሲሆን ከምስራቅ ጉራጌ ዞን 1ኛ በመውጣት ውድ ተማሪያችን የክልላችን፣የዞናችን እና የከተማችን ኩራት በመሆንሽ ኮርተንብሻል። ይህ ውጤት እንዲመጣ አስተዋጽዎ ላረጋቹህ የትምህርት ቤታችን መምህራን፣ሰራተኞች፣የአስተዳደር ሰራተኞች እና ወላጆች ትምህርት ቤታችን እጅግ በጣም ያመሰግናል። ኤምኤስ ት\ቤት አብረን በመስራት ለውጥ እናመጣለን
ልዩ የክረምት ትምህርት በኤም ኤስ ት\ቤት የክረምት ትምህርቱ የሚሰጠው ከሐምሌ 08\2017 እስከ ነሀሴ 13\2017ዓም ለአምስት ሳምንት ሰዓት ከጠዋቱ 2፡30--6፡30---ከሰኞ እሰከ ዓርብ ለ6ኛ እና 8ኛ ክፍል ተማሪዎች ለክልላዊ ፈተና ዝግጅት የሚያግዛቸው ትምህርት ይሰጣል። ለ6ኛ ክፍል ለ8ኛ ክፍል እንግሊዘኛ እንግሊዘኛ ሒሳብ ሒሳብ አካባቢ ሳይንስ ጀነራል ሳይንስ o ሲትዝንሺፕ ሶሻል ሳይንስ ከ1ኛ እስከ 4ኛ ክፍል፣5ኛ እና 7ኛ--ሒሳብ፣እንግሊዘኛ፣የእንግሊዘኛ የማንበብ ክህሎት እና የሳይንስ ትምህርት በተጨማሪም ፕሮግራሙን ሳቢ ለማድረግ የስዕል፣የአባከስ፣ስፓርታዊ ጨዋታዎች እና የእጅ ስራ በሰፊው እንዲሰሩ ይደረጋል። የኤል ኬጂ እና ዩኬጂ ተማሪዎች በዘንድሮው የክረምት ፕሮግራም የተካተቱ ሲሆን የሚማሩት የትምህርት ዓይነት--አማርኛ ማንበብ፣እንግሊዘኛ ማንበብ እና በቁጥሮች መዝናናት እንዲሁም ስፓርታዊ ጨዋታዎች፣የእጅ ስራ እና ልዩ ልዩ ፕሮግራሞችን ያካትታል። የምዝገባ ጊዜ ከሐምሌ 01\2017---ሐምሌ 08\2017 የምዝገባ ቦታ፡-ኤምኤስ ት\ቤት የክረምት ትምህርት ክፍያ፡- 700ብር(ለአምስት ሳምንት) ኤምኤስ ት\ቤት አብረን በመስራት ለውጥ እናመጣለን
የክረምት ትምህርታችን ተጀምሯል። በተለይ 6ኛ እና 8ኛ ክፍሎች እንድትማሩ እንመክራለን።
ልዩ የክረምት ትምህርት በኤም ኤስ ት\ቤት የክረምት ትምህርቱ የሚሰጠው ከሐምሌ 08\2017 እስከ ነሀሴ 13\2017ዓም ለአምስት ሳምንት ሰዓት ከጠዋቱ 2፡30--6፡30---ከሰኞ እሰከ ዓርብ ለ6ኛ እና 8ኛ ክፍል ተማሪዎች ለክልላዊ ፈተና ዝግጅት የሚያግዛቸው ትምህርት ይሰጣል። ለ6ኛ ክፍል ለ8ኛ ክፍል እንግሊዘኛ እንግሊዘኛ ሒሳብ ሒሳብ አካባቢ ሳይንስ ጀነራል ሳይንስ o ሲትዝንሺፕ ሶሻል ሳይንስ ከ1ኛ እስከ 4ኛ ክፍል፣5ኛ እና 7ኛ--ሒሳብ፣እንግሊዘኛ፣የእንግሊዘኛ የማንበብ ክህሎት እና የሳይንስ ትምህርት በተጨማሪም ፕሮግራሙን ሳቢ ለማድረግ የስዕል፣የአባከስ፣ስፓርታዊ ጨዋታዎች እና የእጅ ስራ በሰፊው እንዲሰሩ ይደረጋል። የኤል ኬጂ እና ዩኬጂ ተማሪዎች በዘንድሮው የክረምት ፕሮግራም የተካተቱ ሲሆን የሚማሩት የትምህርት ዓይነት--አማርኛ ማንበብ፣እንግሊዘኛ ማንበብ እና በቁጥሮች መዝናናት እንዲሁም ስፓርታዊ ጨዋታዎች፣የእጅ ስራ እና ልዩ ልዩ ፕሮግራሞችን ያካትታል። የምዝገባ ጊዜ ከሐምሌ 01\2017---ሐምሌ 08\2017 የምዝገባ ቦታ፡-ኤምኤስ ት\ቤት የክረምት ትምህርት ክፍያ፡- 700ብር(ለአምስት ሳምንት) ኤምኤስ ት\ቤት አብረን በመስራት ለውጥ እናመጣለን
ውድ ወላጆች የ2017ዓም የዩኬጂ ተማሪዎች የምርቃት እና ከ1ኛ እስከ 8ኛ ክፍል የደረጃ ተማሪዎች የሽልማት ፕሮግራም የሚካሄደው ቅዳሜ ሰኔ 28/2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 2፡30 ጀምሮ በሴራና አዳራሽ ይካሄዳል በዚህ ፕሮግራም ላይ የሚገኙት የተመራቂ ተማሪ ወላጆች(አባት እና እናት) ብቻ ሲሆን የተሸላሚ ተማሪዎች ደግሞ አንድ ወላጅ (አባት ወይም እናት) ብቻ እንድትገኙ ተጋብዛቹሀል። ውድ ወላጆች አዳራሹ የመያዝ አቅሙ ውስን ስለሆነ ከተጠቀሱት የተመራቂ እና ተሸላሚ ቤተሰብ ውጪ ወደ አዳራሽ የማናስገባ መሆኑን አስቀድመን እናሳውቃለን። ውድ የተመራቂ ተማሪዎች ወላጆች የመመረቂያ ገዋን ለመውሰድ ስትመጡ ወደ አዳራሽ መግቢያ ካርድ እንድትወስዱ እናሳስባለን። የተሸላሚ ተማሪ ወላጆች የማሪዎች ወጤት ተሰርቶ እንዳለቀ በስልክ የምናሳውቅ ሲሆን ከተደወለላቹህ በኻላ ት\ቤት በመምጣት ወደ አዳራሽ መግቢያ ካርድ እንድትወስዱ እናሳስባለን። ማሳሰቢያ በዕለቱ ወደ አዳራሽ የምናስገባው የመግቢያ ካርድ የያዙ ወላጆችን ብቻ ነው። አብረን በመስራት ለውጥ እናመጣለን ኤምኤስ ትምህርት ቤት
ማስታወሻ ውድ ወላጆች እና ተማሪዎች የማጠቃለያ ፈተና ወረቀት ሰኞ በቀን 23/10/2017ዓ.ም ለተማሪዎች ይመለሳል ስለሆነም የድምርና የእርማት ስህትት ካለ ማክሰኞ በ24/10/2017 ዓ.ም እስከ 5፡00 ሰዓት የመጨረሻ የማስተካከያ ጊዜ መሆኑን እናሳውቃለን ። አብረን በመስራት ለውጥ እናመጣለን ኤምኤስ ትምህርት ቤት
ውድ የት/ቤታችን ወላጆች ጉዳዩ:- የት/ቤት ክፍያን ይመለከታል የሰኔ ወር እና ውዝፍ የት/ቤት ክፍያ ያለባችሁ ወላጆች ነገ ሰኞ አስከ 2:30 ድረስ ክፍያችሁን እንድትፈፅሙ እናሳስባለን። ክፍያ ባልከፈሉ ወላጆች ምክንያት ክፍያው አስኪከፈል እና ያልከፈሉ ተማሪዎችን ከፈተና ላለማስወጣት ስንል ፈተናው ለነገ ብቻ 3:00 የሚጀምር መሆኑን እናሳስባለን።
ከ4ኛ እስከ 5ኛ እና የ7ኛ ክፍል የ2ኛ ሴምስተር የማጠቃለያ ፈተና ፕሮግራም
ከነርሰሪ እስከ 3ኛ ክፍል የ2ኛ ሴምስተር የማጠቃለያ ፈተና ፕሮግራም
ውድ የት/ቤታችን ወላጆች ጉዳዩ:- የት/ቤት ክፍያን ይመለከታል የሰኔ ወር እና ውዝፍ የት/ቤት ክፍያ ያለባችሁ ወላጆች ነገ ሰኞ አስከ 2:30 ድረስ ክፍያችሁን እንድትፈፅሙ እናሳስባለን። ክፍያ ባልከፈሉ ወላጆች ምክንያት ክፍያው አስኪከፈል እና ያልከፈሉ ተማሪዎችን ከፈተና ላለማስወጣት ስንል ፈተናው ለነገ ብቻ 3:00 የሚጀምር መሆኑን እናሳስባለን።
ውድ የት/ቤታችን ወላጆች የ2018ዓም የተማሪዎች ምዝገባ ቅድመ ዝግጅት ስራዎች እያከናወንን እንገኛለን።በመሆኑ በ2018ዓም የጀማሪ ተማሪዎችን ምዝገባ ቅድሚ በት/ቤታችን ልጆቻቸውን እያስተማሩ ላሉ ወላጆች ቅድሚያ ለመስጠት በተማሪዎቻችን በኩል የሚሞላ ፎርም የላክን ሲሆን ፎርሙን በተማሪዎቻችን በኩል ለአፀደ ህፃናት ት/ቤት ርዕሰ መምህርት እንድትሰጡ እናሳስባለን። ፎርሙ ያልደረሳችሁ ወላጆች ፎርም ከት/ቤት መውሰድ ይቻላል። አዲስ የጀማሪ ተማሪ ለማስመዝገብ የምትፈልጉ ወላጆች በት/ቤታችን ልጆቻቸውን የሚያስተምሩ ወላጆች ካስመዘገቡ በዃላ ባለን ክፍት ቦታ የምንመዘግብ ይሆናል። ለዚህም ልጆቻችሁን ከሀምሌ 1--15 ባሉት ቀናት በተጠባባቂ ዝርዝር ላይ እንድታስመዘግቡ እናሳስባለን። ማሳሰቢያ ጀማሪ ተማሪ ለማስመዝገብ የልደት ሰርተፌኬት ግዴታ ስለሆነ ከወዲሁ ዝግጅት እንድታረጉ እናሳውቃለን። ኤምኤስ ት/ቤት አብረን በመስራት ለውጥ እናመጣለን
ውድ የት/ቤታችን ወላጆች ጉዳዩ:- የት/ቤት ክፍያን ይመለከታል የሰኔ ወር እና ውዝፍ የት/ቤት ክፍያ ያለባችሁ ወላጆች ነገ ሰኞ አስከ 2:30 ድረስ ክፍያችሁን እንድትፈፅሙ እናሳስባለን። ክፍያ ባልከፈሉ ወላጆች ምክንያት ክፍያው አስኪከፈል እና ያልከፈሉ ተማሪዎችን ከፈተና ላለማስወጣት ስንል ፈተናው ለነገ ብቻ 3:00 የሚጀምር መሆኑን እናሳስባለን።
ውድ የ6ኛ እና የ8ኛ ክፍል ተማሪዎቻችን ሰኞ ለኦረንቴሽን እና ለአድሚሽን ካርድ ለመውሰድ ስትመጡ የሰኔ ወር ክፍያ ደረሰኝ ይዛችሁ እንድትመጡ እናሳስባለን።
ውድ የ6ኛ እና የ8ኛ ክፍል ተማሪዎቻችን ሰኞ ለኦረንቴሽን እና ለአድሚሽን ካርድ ለመውሰድ ስትመጡ የሰኔ ወር ክፍያ ደረሰኝ ይዛችሁ እንድትመጡ እናሳስባለን።
ለመላው የእስልምና እምነት ተከታይ ለሆናችሁ የትምህርት ቤታችን መምህራን፣ሰራተኞች፣ተማሪዎች እና ወላጆች በሙሉ እንኳን ለ1446ኛው የዒድ አል-አድሃ (አረፋ) በዓል በሰላም አደረሳችሁ!! ዒድ ሙባረክ ! ኤም ኤስ ት/ቤት አብረን በመስራት ለውጥ እናመጣለን
ውድ የኤም ኤስ ትምህርት ቤት ወላጆች የሰኔ ወር የት\ቤት ክፍያ ከግንቦት 25--ሰኔ 5\2017 ድረስ እንድትከፍሉ እናስታውሳለን:: ኤም ኤስ ት\ቤት አብረን በመስራት ለውጥ እናመጣለን