tgindex

ግጥም እና ወግ ( ረሂማ ሁሴን)

Статистика

ጥበብ የሙስሊም ሀብት ናት! ካገኘባት ቦታ ይውሰዳት ረሱል(ሰ.ዐ.ወ) ጥበበኛው ጌታ የሰጠኝን ሂክማ ተጠቅሜ እይታወቼን እና ሀሳቦቼን በግጥም እና በወግ አዚህ ቻናል ላይ አጋራችኋለሁ። . .ተቀላቀሉን ለአስተያየትዎ @rehimahubot

Последний пост
5 авг.
Последнее чтение
13 авг.
Постов за неделю
0
Всего постов
20
Тип
открытый
Язык
ti
В каталоге с
13 авг.
Подписчики
970
+1 за 2 дн.
Сутки
0
0,00%
Неделя
 
Месяц
 
Просмотров на пост
752
20 постов
Вовлечённость
77,5%
к подписчикам
Постов в день
0,0
всего 20
Упоминаний
1
каналов
Охват размещения
оценка
1/24сутки в ленте
215
1/48двое суток
246
1/72трое суток
265

Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.

Посты

  • "አልሀምዱ ሊላህ እማ በትዳርሽ ደስተኛ መሆንሽን ስለሰማሁ፣ የደበቅሽኝ ሀዘንሽን ሳይሆን ደስታሽን ስለሆነ፣ አልሀምዱሊላህ ለአመታት የተብሰለሰልኩት እና የተጨነቅኩት በባዶ ስለሆነ፣ልቧ ተሰብሮ ይሆን ብዬ ያሰብኩት አንቺ ልብሽ በተጠገነበት እና በደስታ ጌታሽን በምታመሰግኚበት ሂወት ስለሆነ... አልሀምዱሊላህ ስለ ሁሉም ብዬ... ተንሰቀሰቅኩ በአንድ በኩል ደስተኛ መሆኗን ስለሰማሁ እና ከፈራሁት ነገር ስለተረፈችልኝ እፎይታ በሌላ በኩል ግን ለአመታት የተጨነቅኩት ጭንቀት እንዲሰማኝ ስላደረገችን በመከፋት በሁለት የተለያዩ ስሜቶች ክብደት ግራ በመጋባት ሰውነቴ እስኪንዘፈዘፍ አለቀስኩ ።በሁኔታዬ ደንግጣ ይህን ያደረገችበትን ምክንያት እስካሁን ስታስረዳኝ የነበረውን እንደገና መድገም እና ማብራራት ጀመረች። ለኔ አስባ እንጂ ድብቅ ለመሆን ፈልጋ እንዳልነበረ በተደጋጋሚ ልታስረዳኝ ሞከረች እኔ ግን ሀሳቧ ቢገባኝም መቀበል ከበደኝ። ገና ለገና እኔ የወደፊት ትዳሬ እንደሷ አይነት ይሆናል ብዬ አስቤ ባይሆን እንዳልጎዳ በማሰብ ቀድማ ድብቅ በመሆን እኔን በጭንቀት መጉዳት ምን የሚሉት ነው አልኩ፣ደሞስ ለሷ እንደዚህ አይነቱን ሰው የሰጠ ጌታ ለኔስ ሊሰጠኝ እንደማይችል ለምን አሰበች? ስለኔ ትዳር አላህን ለምን በመልካም ብቻ አልጠረጠረችውም? አልኩ እሷ ስለምታምነው የአላህ ፈተና ጥልቅ ግንዛቤ ስለለኝ ይሁን ስሜታዊ ሁኜ ብቻ በጣም ከፋኝ ልታባብለኝ እና ልታስረዳኝ ብዙ ብትሞክርም ለረጅም ደቂቃወች እናቱ እንደሞተበት ልጅ እንስቅስቅ ብዬ ካለቀስኩ በኋላ ስረጋጋ ወደ ቤቴ መሄድ ፈለኩ። ትንሽ እንድቆይ እና እንድናወራ ብትለምነኝም ብቻዬን መሆን ስለፈለኩ ስረጋጋ እንደምናወራ ነግሪያት ወደቤቴ ተመለስኩ። እናንተ ብትሆኑ ምን ይሰማችሁ ነበር? ምክንያቷስ አሳማኝ ነው? @rehimahu @rehimahu ለአስተያየትዎ @rehimahubot

  • ስለምፈራ ነው! (ክፍል 3) (ረሂማ ሁሴን) "ግን ደግሞ ይህን የጌታዬን ፀጋ አውጥቼ ለሰው ማሳየት እፈራለሁ!" ለምን? አልኳት በመገረም "ምክንያቱም ይህ ብዙወች የዱንያ ስኬት ብለው የሚመኙት ሂወት ነው። ብዙ ሰወች የሚመኙት አይነት ሰው ነው የተሰጠኝ እናም ይህን በመናገር ውስጥ ሁለት ፍርሀት አለኝ አንድ የሚጠሉኝን ወይም በኔ ወሬ ሳያውቁ ልባቸው ውስጥ ሀዘን፣ የበታችነት ፣ቅናት እና ምቀኝነት የሚፈጠርባቸውን ሰወች ስሜት። ሁለት ይህን ኒዕማ ያልታደሉ ሰወችን ልብ ሀዘን ወይም እንዳንቺ ገና ያላገቡ ወጣቶችን expectation እፈረዋለሁ" አለችኝ "አልገባኝም?" አልኳት ስላልገባኝ ሳይሆን እንዴት በዚህ ልክ አስባ ሂወቷን እንደምትመራ ገርሞኝ ማብራሪያ ፍለጋ። እየውልሽ አንዳንዴ በዝርዝር ማውራት የሌሉብሽ ነገሮች አሉ ለሰወች አሳይተሽ ከምታገኝው ደስታ ይልቅ በዝምታ እያጣጣምሽ የምትኖሪያቸው ኒዕማወች፣ አልሀምዱሊላህ ማለት በቂ የሆነባቸው፣ሰወች ከተረዱ አይተው የሚረዷቸው ካልተረዱ ድብቅ ሁነው መቆየታቸው የተሻለ የሆኑ ቢወጡ እና ቢያንፀባርቁ በአጭር ሊቀጩ፣ ብርሀናቸው ሊደበዝዝ የሚችሉ ሀብቶች አሉ ።ከነዛ ሀብቶች መሀል አንዱ ጥሩ ትዳር ነው ብዬ አምናለሁ! ጥሩ ትዳር የገጠመው ሰው እዩልኝ በሎ ከሚያወጣ ይልቅ በዝምታ አላህን እያመሰገነ ቢኖር ጥሩ ነው ብዬ አምናለሁ እንደው ለሰወች አርአያ እሆናለሁ ብሎ በማሰብ ስለትዳሩ ማጋራት ካሰበም እጅግ ቁጥብ በሆነ መልኩ ቢሆን ብዬ አስባለሁ ።ምክንያቱም አንዳንዴ ለሰወች ይጠቅማል ብለሽ ያለሽን ፀጋ ስታወሪ ምን አልባት እነዛ ሰወች ከራሳቸው ሂወት ጋር እያነፃፀሩ ሊከፉ፣ሊያዝኑ ፣ የነሱ ሂወት ጌታቸው ፈተና መሆኑን አውቀው ከመታገስ ይልቅ አላህዬ እኔ ምንበድዬ ነው ለሰው ይህን እየሰጠህ ለኔ መከራን ብለው ሊያማርሩ እና ሂወታቸውን ሊጠሉ ይችላሉ። አለፍ ሲልም እነሱ የሚሰማቸው የዝቅተኝነት እና ያለመታደል ስሜት የሚድነው በዛ ሰው ውድቀት ይመስላቸው እና የዛን ሰው ደስታ ለማሳጣት በዙ መጥፎ እርቀቶችን ሊሄዱ ይችላሉ። በዚህ ውስጥ ምንም እንኳን ግልፅ የሆነ ያንቺ ጥፋት ባይታይም ግን ለነዚህ ሰወች ሀዘን፣ማማረር፣ክፋት ማሰብ አልፎም ያለሽን ፀጋ ለማጣትሽ ምክንያት እራስሽ ያወራሽው እና እዩልኝ ያልሽው ሰው ትሆኛለሽ። ሁለተኛው እንዳንቺ ላሉ ላላገቡ ወጣቶች እንደዚህ አይነት ፀጋ ውስጥ ያለን ሰወች የትዳራችንን መልካም ጎን እጅግ አግዝፈን የምናወራላችሁ ከሆነ ትዳር ስትመሰርቱ ይህን አይነት አጋር እና የትዳር ሂወት ጠብቃችሁ ይሆናል የምትገቡት። ይህ ደግሞ ለሁሉም አይገጥምም እንዳልኩሽ አላህ ሰወችን በሁለት መንገድ ነው የሚፈትነው አንድ በምትጠይው አንድ በምትወጂው(ኒዕማ)ብለሽ በምጠሪው መንገድ። እናም የኔ ፈተና እስካሁን በፀጋ እንደሆነው ሁሉ አይበለውና ያንቺ ፈተና ደግሞ በተቃራኒ ሊሆን ይችላል። ታድያ ያኔ ከፈተናው በላይ የጠበቅሽው ነገር ይሰባብርሻል ጭራሽኑ ለፈተና ተዘጋጅተሽ ስለማትገቢ ፈተናው በጣም ጥቃቅን እና በቀላሉ የሚፈታ አልያም ተቀብለሽው መኖር የምትችይው ቢሆን እንኳን አንቺ ግን ቀድሞ አይምሮሽ የተዘጋጀው ፍፁም ለሚመስል አጋር እና ትዳር ስለሆነ በቀላሉ ትዳርሽን ትበትኛለሽ አልያም አማራሪ፣ ብስጩ አና ተካዥ ሰው ትሆኛለሽ። ሌላው ቀርቶ በገጠመሽ ጉዳይ እንደኔ አይነት ሰው ሊመክርሽ ቢሞክር እራሱ አንቺ ስላልተፈተንሽ ነው የኔ ሂወት ቢገጥምሽ ኑሮ... ብለሽ ችግርሽ እጅግ ግዙፍ መሆኑን እና አንቺ ፈተና ውስጥ እኔ ግን ስኬት ላይ እንደሆንኩ እስኪሰማኝ ታሳምኚኛለሽ። እውነታው ግን ሁለታችንም ፈተና ውስጥ ነን !! እኔ አላህ ለሰጠኝ መልካም ሰው መልካም ለመሆን፣ሀቁን ለመጠበቅ፣በትዛዙ ስር ለመኖር፣ያለውን መልካም ነገር እያገዘፍኩ የማልወዳቸውን እንከኖቹን ጭምር ተቀብዬ ለመኖር እየጣርኩ ያለሁ ሰው ነኝ። ሰው የፈለገ ጥሩ ቢሆን ሰው ነውና እንከን አይጠፋውም አንዳንዴ ካለው ግዙፍ መልካምነት ይልክ እንከኑ ሊረብሽሽ እና መልካምነቱን ሊያጠፋብሽ ይችላል ያኔ በንቁ አዕምሮ የተሰጠሽን ኒዕማ መጠበቅ እንዳለብሽ ካላወቅሽ ፈተናሽን ትወድቂያለሽ። ለዛ ነው ላንቺም ሆነ ለሌላ ሰው ምንም የማልለው አላህ ከኔ የተሻለ አጋር እና ያማረ ትዳር እንዲሰጥሽ ሁሌ ነው ዱዐ የማደርግልሽ።እናም ስለኔ ትዳር ለመንገር የሚገጥምሽን የትዳር ፈተና አይነት ማወቅ ስለነበረብኝ ነው ሳታገቢ በፊት ስለትዳሬ ምንም ማለት የማልፈልገው። ሁሌም "አላህዬ ስለሰጠኸኝ ፀጋ አውርተን በጋራ አንተን እናመሰግንህ ዘንድ መልካም ሰው ስጣት የምትሰጣትን ፀጋም የምትጠቀምበት እና አኼራዋን የምትገዛበት አርጋት በኒዕማህ ፈትናት ፈተናዋን የምታልፍበት ልብም ስጣት" ብዬ ዱዐ የማደርግልሽ አለችኝ ዐይኗ በእምባ ተሞልቶ ። ምንም ሳልመልስላት ለረጅም ደቂቃ ፈዝዤ ካየኋት በኋላ በተራዬ "አልሀምዱሊላህ!" አልኩ። "ለምኑ?" አለችኝ .... ይቀጥላል... @rehimahu @rehimahu ለአስተያየትዎ @rehimahubot

  • ስለምፈራ ነው ! (ክፍል 2) (ረሂማ ሁሴን) "እውነት ለመናገር አንድም ቀን በዚህ ልክ ይህ ነገር ያሳስብሻል ብዬ አስቤ አላውቅም ነበር። እርግጥ ነው አንድ ቀን ስለትዳሬ ለምን እንደማላወራሽ ልትጠይቂኝ ትችያለሽ ብዬ አስብ ነበር። ምክንያቱም ላንቺ የማላወራሽ ብቸኛው የሂወት ክፍሌ በመሆኑ ልብ ልትዪው እንደምትችይ እገምት ነበር። ነገር ግን በዚህ ልክ አብሰልስሎሽ ትዳርን እንድትፈሪ እና እንድትጠራጠሪ ያደርግሻል ብዬ አስቤ አላውቅም። ለምን እንደዚህ አሰብሽ ብዬ አልወቅስሽም እኔም ብሆን ማሰቤ አይቀርም ነበር ግን ደግሞ ጠበቅ አድርገሽ ብትጠይቂኝ በቀላሉ ልመልስልሽ የምችለውን ነገር ነው አውሰብስበሽ የተረበሽበት" አለችኝ። ትዝብት በሚመስል አይን እያየችኝ።" አየሽ አንቺ ራሱ እንደዚህ ላስብ እንደምችል እስክታስቢ ድረስ ነው ድብቅ የሆንሽብኝ ቆይ ለምን?" አልኳት በመገረም እያየኋት። "እንደዚህ ልታስቢ እንደምትችይ የገመትኩት አስቤበት ነገሩን አደርግ ስለነበር ነው። ዛሬ ግን በዚህ ልክ አንቺን እየጎዳሽ ከሆነ እውነቱን እና ያደረኩበትን ምክንያት አስረዳሻለሁ ግን ይሄ በኔ እና ባንቺ መሀል የሚቀር ሚስጥር ነው። ከዚህ በኋላ ስለትዳሬ ግልፅ ከሆንኩ የምሆነው ላንቺ ብቻ ነው። እስከዛሬ የመጣሁበትን መንገድ ልቀይረው አልፈልግም በዚህ እንስማማ! " አለችኝ። "እሺ " አልኳት ትካሻዬን ምንቸገረኝ በሚል እየሰበቅኩ እውነቷን እና ምክንያቷን እኔ ካወቅኩ በቂዬ ነው ማንም እንዲያውቅ የምፈልግበት ምክንያት የለኝም። "እየውልሽ አላህ ባሪያውን በሁለት መንገድ ይፈትናል አንደኛውን የሚፈልገውን በመንጠቅ እና እሱ የመረጠለትን በመስጠት ምርጫዬን ወዶ በመቀበል ፈተናዬን ይታገሳል? ወይስ በኔ ይክዳል? ብሎ ሲሆን ሌላኛውን ደግሞ አጥብቆ የሚመኘውን እና በሰወች አይን ምቹ የሚባለውን ነገር በመስጠት በኒዕማ ይፈትነዋል። ይህኛው ሰው ያለበትን ኒዕማ እሱም ሆነ ሰወች ሲያዩ አላህ ስለወደደው ስላከበረው ሊመስላቸው ይችላል። አላህ ግን ባሪያዬ የሰጠሁትን ኒዕማ በአግባቡ ይጠቀማል ወይስ ያባክነዋል? የኔን ቻይነት እና ታላቅነት መስክሮ በተደረገለት ፀጋ ለኔ እጅግ ተናናሽ እና አመስጋኝ ይሆናል ወይስ ደካማነቱን እና የተደረገለትን ረስቶ ይኩራራል፣ ያምፃል? ብሎ ሊፈትነው ነው ይህን ኒዕማ የሚሰጠው።ምክንያቱም ዱንያ የፈተና ሀገር ናት ሁሉም ሰው ፈተና ላይ ነው ፈተናውን ያለፈ ውቧ ጀነት የወደቀም አስከፊው ጀሀነም ማረፊያው ይሆናል። ትዳርም የዚህ አለም የፈተና አንዱ አካል ነው ጥሩ ባል እና ሚስት ያላቸው ሰወችም ሆኑ መጥፎ ባል እና ሚስት ያላቸው ሰወች እየተፈተኑ ነው ።በእርግጥ እኛ እየተፈተኑ የሚመስለን መጥፎ ትዳር ላይ ያሉት ብቻ ሊሆን ይችላል ይህ ግን ፈፅሞ የተሳሳተ ነው አንዳንዴ እንደውም ጥሩ የትዳር አጋር ያላቸው ሰወች መጥፎ የትዳር አጋር ካላቸው የበለጠ እየተፈተኑ ያሉ ይመስለኛል። ምክንያቱም የተሰጣቸውን ኒዕማ በአግባቡ ላይጠቀሙበት እና ላይጠብቁት ይችላሉ። እንደኔ በዳይ ከመሆን ተበዳይ መሆን ይሻላል። ነገ አኼራ ላይ ተበዳይ ሁኖ መቅረብ መታደል ነው በዳይ ሁኖ መቅረብ ግን ከባድ ጭንቅ ነው። ምክንያቱም ዱንያ ላይ የተሰጠሽን ኒዕማ በአግባቡ አለመጠቀምሽ እና አለመጠበቅሽ በዳይ አድርጎ ሊያቆምሽ ይችላል። እና ወደኔ ስመጣልሽ ገና ታዳጊ እያለሁ ዱንያ ላይ ሳይፈተኑ ማለፍ እንደማይቻል፣ሁሉም ነገር የፈተና አካል እንደሆነ እና አላህ ሰወችን በመስጠትም በመንፈግም ውስጥ እንደሚፈትን፣ አላህን ፈተናህን የማልፍ አድርገኝ እንጂ አትፈትነኝ ማለት እንደማይቻል ሳወቅ ከዛ ጊዜ ጀምሮ አላህዬን "ጌታዬዋ እኔ ደካማ ነኝ መከራን እና በደልን አልችልልህም እና ስትፈትነኝ በኒዕማህ ፈትነኝ ያን የኒዕማህን ፈተና ደግሞ የማልፍ አድርገኝ "ብዬ ዱአ አደርግ ነበር ። እና አላህም ለምኑኝ እሺ እላችኋለሁ ያለ ጌታ ነውና እስካሁን በሂወቴ ውስጥ የተለየ የምለው ከባድ መከራ ገጥሞኝ አያውቅም። የሚገጥመኝ ሁሉ ኸይር ነው ጥሩ ቤተሰቦች፣ጥሩ ጓደኞች ፣ ጥሩ የትምህርት ውጤት እና ደረጃ ፣አሁን ደግሞ ጥሩ ትዳር ሰጥቶኛል። ሁሉም የተሰጡኝ መልካም ነገሮች ፈተናዬ ናቸው ትዳሬን ጨምሮ አየሽ እኔ ትዳሬ ፈተናዬ ነው ብዬ አምናለሁ ብዙወች ለራሳቸው እራሱ ያለ ባይመስላቸውም እና የሚያስቡት ሰው ህልም ቢመስላቸውም ለምዶባቸው የሚመኙትን አይነት ሰው አላህ ሰጥቶኛል። አንዳንዴ ሳስበው እውነት እኔ ይሄን ደስተኛ ሂወት እየኖርኩ ነው ?ብዬ እስክገረም ሙሉ ሰው በለለበት አለም ሙሉ እስኪመስለኝ መልካም ጎኑ ገዝፎ የሚታይበትን ሰው አላህ ሰጠኝ አልሀምዱሊላህ ግን......ብላ ዝም አለች። ግን ምን ?"አልኳት ለረጅም ደቂቃ በተመስጦ ስሰማት ከቆየሁ በኋላ ይቀጥላል.... @rehimahu @rehimahu ለአስተያየትዎ @rehimahubot

  • ስለምፈራ ነው! (ረሂማ ሁሴን) "እና ትዳርስ እንዴት ነው ? "አልኳት ካገባች ሶስት አመት ያለፋት ጓደኛዬ ጋር በስልክ ረዘም ላለ ሰአት ስለሌሎች ጉዳዮች ስናወራ ከቆየን በኋላ። "አልሀምዱ ሊላህ ትዳር ቆንጆ ነው" አለችኝ እንደተለመደው።ሶስት አመት ሙሉ ስለትዳሯ ስጠይቃት ከዚህ የዘለለ መልካምም መጥፎም ነገር ጨምራ አታውቅም። እንደዚህ እየተደዋወልን ስናወራ ከአንዳንድ ወሬወቻችን አንፃር ባሏ መልካም ሰው እንደሆነ እና ጥሩ ትዳር እንዳላት ባስብም ጠለቅ ያለ ነገር ግን አታወራም። እርግጥ ነው ሁሌ በተደዋወልን እና በተገናኘን ቁጥር እንዳገባ ትወተውተኛለች ፣ስለትዳር መልካምነት፣ስለ ባል ጥቅም ብዙ ትመክረኛለች ያም ሁኖ ግን የራሷን ትዳር እንደ መልካም ተምሳሌት አንስታልኝ አታውቅም። አንዳንዴ ትንሽ እንኳን ብታወራኝ እልና "አንቺ እኮ አላህ ጥሩ ባል ስለሰጠሽ ነው ስንት ትዳርን የሚያስጠላ ባል እያየን አይደል ?" ስላት ..." አልሀምዱሊላህ ግን ደግሞ ለኔ የሰጠ ጌታ ላንቺ የማይሰጥበት ምንም ምክንያት የለውም! ደግሞ ጥሩወች ለጥሩወች ናቸው አይደል አላህ ያለው? አንቺ ደግሞ በጥሩነት ከኔ ብትበልጪ እንጂ አታንሺም ስለዚህ አላህ ጥሩ ሰው ይሰጥሻል" ብላ ስለትዳሯ ብዙ ለመስማት የጓጓ ልቤን ታኮላሻዋለች። ከዚህ በላይ ምን ብዬ እንደምጠይቃት ግራ ይገባኝና ዝም እላለሁ። እስኪ ፍረዱኝ ከዚህ በላይ ስለባልሽ፣ስለትዳርሽ ንገሪኝ ተብሎ እንዴት ይጠየቃል? በጣም ስለብዙ ነገር በግልፅ የምናወራ የረጅም አመት ጓደኛሞች ስለሆንን አንዳንዴ ለምን ይሄን እንደምትደብቀኝ ሳስብ እጨነቃለሁ ምን አልባት ህመሟን ችላ እየኖረች ስለሆነ ይሆን ?እላለሁ። የሷን ትዳር አይቼ ጎጉቼ ወደ ትዳር እንዳልገባ ያገባውም ያላገባውም ሰው ከሚመክረኝ የትዳር ጥቅም የተለየ የምትነግረኝ ነገር የለም! ያ ደግሞ ትዳር የሚባለውን አለም እንዳልደፍር አድርጎኛል። ምንም ያየሁት አጠራጣሪ ነገር ባይኖርም እየደበቀችኝ ያለ ነገር አለ ብዬ ማሰብ ከጀመርኩ ቆየሁ። ምክንያቱም እሷ ለኔ የማታብራራው ብቸኛው ጉዳይ የትዳሯ ጉዳይ ብቻ ነው። ከትዳሯ ውጭ ስለሁሉም የሂወቷ መንገድ ከሷ እኩል አውቃለሁ እሷም ስለኔ የማታውቀው አንድም ዝርዝር ጉዳይ የለም። ታድያ ስለትዳሯ አንድም ነገር አለመተንፈሷ የሰላም ነው? ብዙ ሰው እንደሚያረገው በጣም ጥሩ ባል ከሆነ ማሞገስ እና ስለሱ ሁሌም ማውራት የለባትም? መጥፎ ሁኖባት ከሆነስ ባትነግረኝ እንኳን ድምፆን ሰምቼ፣አይኖን አይቼ ማወቅ አልነበረብኝም? እርግጥ ነው ሁሌ ስለትዳር ጥሩነት ትናገራለች ግን ስለባሏ ጥሩነት ስለትዳር በምታወራው ልክ አውርታ አታውቅም! ትዳር ማለትባል ነው? ከሆነ ለምን ስለባሏ አትናገርም? በዚህ ሁኔታ ለሶስት አመት እኔም ትዳርን ሳልደፍር ሰበብ እየደረደርኩ እሷንም በግልፅ ስለባሏ እና ስለትዳሯ መጠየቅ ፈርቼ ጊዜ ይፍታው ብዬ እንደተብሰለሰልኩ እዚህ ደረስኩ። ከትዳር የምሸሽበት ዋነኛው ምክንያቴ የሷ ሁኔታ ነበር ከልቧ እየተደሰተች ይሁን በውስጧ ህመም ደብቃ ይሁን አለማወቄ ትዳርን እንድፈራው አድርጎኛል።ወደ ሂወቴ የሚመጡ ወንዶችን እውነተኛ ማንነት አላውቅምና እሷ መልካም ባል ካላገባች እኔማ በምን እድሌ እና መልካም ስራዬ መልካም ሰው ይገጥመኛል?እላለሁ። ምንአልባት እሷ ኢማኗ ጥሩ ስለሆነ የዱንያ ፈተና መሆኑን ተቀብላ ችላው ይሆናል መጥፎም ደግም የማታወራው እኔ ግን የሷ አይነት ኢማን የለኝም!ደስታዬንም ህመሜንም መደበቅ የማልችል ደካማ ነኝ! ስለዚህ ይሄ ከማያቁት፣ አብረውት ካልኖሩት ሰው ጋር አንድ ላይ ሂወት መመስረት የሚባለው ከባድ የሂወት ውሳኔ ይቅርብኝ እላለሁ ። አንድ ቀን ግን ቤቷ ጠርታ ከትዳር መሸሼ በጣም እያበሳጫት እንደሆነ እና ምክንያቴን በግልፅ ካልነገርኳት እንደምትጣለኝ አምርራ ስትቆጣኝ በሷ ምክንያት መሆኑን አለማወቋ አበሳጭቶኝ መሰለኝ በንዴት አይኗን እያየሁ "ምክንያቴ ብዙ ቢሆንም አንዷ አንቺ ነሽ አንቺ የደበቅሽው የትዳር ሂወትሽ ለኔ ያስፈራኛል፣ ስለባልሽም ሆነ አጠቃላይ ስለትዳርሽ አልሀምዱ ሊላህ ከማለት ያለፈ ባልሽን ስታሞግሽም ሆነ ስታማርሪ ሰምቼሽ አላውቅም ያ ያስፈራኛል። እየተጎዳች ችላው ቢሆንስ እያልኩ እጨነቃለሁ"አልኳት። በመገረም ውስጥ ሁና እውነትሽን ነው የምታወሪው? ቆይ አልሀምዱሊላህ የሚለው ቃል ደስተኛ መሆኔ አያረጋግጥም እንዴ? አለችኝ። ኮስተር ብዬ "አያረጋግጥም ! አላህ ጋር ያለሽን ነገር አውቃለሁ ቢከፋሽም አልሀምዱሊላ ትያለሽ እንጂ አታማርሪም አልሀምዱሊላህ የሚለው ቃል ያንቺ አይነት ሰወች የጌታችሁን ውሳኔ ወዳችሁ ስለምትቀበሉ የምታመሰግኑበት ቃል እንጂ እንደኛ የደስታ መግለጫ ብቻ አይደለም !" አልኳት። ለትንሽ ደቂቃ ዝም ካለች በኋላ ትንፋሽ ሰብስባ በትኩረት እያየችኝ ከሷ እሰማዋለሁ ብዬ ያልጠበኩትን የሚገርም ረዥም ንግግር መናገር ጀመረች ይቀጥላል... @rehimahu @rehimahu ለአስተያየትዎ @rehimahubot

  • Make it a habit to talk more about your blessing than your burdens ❤

  • #የኔእይታ 72 (ረሂማ ሁሴን) አንድ ቀን ህልሜ ይሳካና ደስተኛ እሆናለሁ፣አንድ ቀን ከልቤ አላህን አመሰግነዋለሁ ፣አንድ ቀን አላህ የጠየቅኩትን ሁሉ ይሰጠኝ እና እደሰታለሁ እውነተኛ አመስጋኝ ሁኜም እኖራለሁ ፣ለሰወች ችግርም እደርሳለሁ አትበሉ! አላህን ዛሬ አመስግኑት፣በፈተናወቹ ውሰጥ ደስተኛ ሁኑ ፣ወደ ፊት ብር ሲሰጣችሁ ስለምትረዱት ደሀ አታልሙ ዛሬ አንዱን ፌርማታ ወክ አድርጉና የታክሲ ብራችሁን መፅውቱ፣ አላህ ሀብታም ሲያረጋችሁ አዲስ ልብስ ገዝታችሁ ለየቲሞች ለማልበስ አትመኙ ዛሬ ከልብሳችሁ መሀል አንዱን የአላህን ውዴታ ሽታችሁ መፅውቱ፣ ምኞታችሁ ሁሉ ሰምሮ አላህዬ እውን ይሄ ለኔ ተደረገልኝ ብላችሁ በምስጋና ስለማልቀስ ማሰብ አቁሙና ዛሬ ስላላችሁ የብናኝ ያክል ፀጋ እንኳን አላህን በእምባ ተሞልታችሁ አመስግኑ ፣ዛሬ ለበላችሁት ሽሮ እና ደረቅ ዳቦ አመስግኑ፣ የታክሲ አጥታችሁ በፀሀይ ተንከራታችሁ ይሆናል ስለእግሮቻችሁ ግን አመስግኑ፣ ለአይን የሚማርክ ሰፊና ውብ ቤት አትኖሩ ይሆናል ለደሳሳ ጎጇችሁ አመስግኑ ፣ለተሰተረላችሁ አይብ አመስግኑ። ዛሬ ካላመሰገናችሁ መቸም አታመሰግኑም! የምታመሰግኑት ከናንተ በታች ያነሰ ሂወት የሚኖር ስላለ አልያም እናንተ ያላችሁን ነገር የሚመኝ ሚስኪን ሰው ስላለ ከእሱ እሻለለሁ በሚል ሊሆን አይገባም ! ይህ በጣም ደባሪው አላህን የማመስገን መንገድ ነው። ይህ አይነቱ ማመስገን የመጨረሻ ውድቀት ላይ ያለ ሰው ብትሆን እንደማታመሰግን በግልፅ አረጋጋጭ ነው። ስለእግሮችህ የምታመሰግነው እግር የሌለው ስታይ፣ሰለ ደሳሳ ጎጆህ የምታመሰግነው ጎዳና የሚያድርን ስታይ፣ስለ ኑሮ ሁኔታህ የምታመሰግነው ምግብ አጥቶ የሚለምን ስታይ ብቻ ከሆነ አንተ ደካማው አመስጋኝ እና አማኝ ነህ። እግርህ ቢቆረጥ፣ጎዳና ብትወድቅ፣ ቢርብህ እንኳን አመስጋኝ መሆን እችላለሁ ወይ ብለህ እራስህን ጠይቅ። የአማኞች እና የአመስጋኞች እውነተኝነት ማረጋገጫ በሁሉም ፈተናወች ውስጥ ማመስገናቸው ነው። አንድ ነገር እርግጠኛ ሁኜ ልንገርህ በችግር ውስጥ ያላመሰገነ በማግኘት ውስጥም አያመሰግንም! ምስጋና ከማግኘት እና ከማጣት ጋር የተያያዘ አይደለም!! ምስጋና አላህን እጅጉን በመውደድ እና በማመን ውስጥ የሚገኝ ፀጋ ነው። ዛሬ ያላመሰገንከውን ጌታ ነገ የእውነት ማመስገንን ልታመሰግነው ከቶ አይቻልህም !ብታመሰግነው እንኳን ከምላስ የማያልፍ ምስጋና ነው ፀጋው በጠፋ ቅፅበት የሚበን ምስጋና። አመስጋኝነትን መለማመድ እና ከልብ መተግበር የተረጋጋ ሂወት ባለቤት እና ደስተኛ ማንነትን ይገነባልሀል። እውን አላህን የምትወድ፣በእርሱ የምትተማመን እና የምትመካ ከሆንክ አመስጋኝ ሁን። በሁሉም የሂወት ከፍታህና ዝቅታህ ውስጥ ከልብ የመነጨ ምስጋና እና ሪዷ ይኑርህ። ያኔ አለም ላይ ሁሉም የሚያሳድደው እውነተኛ ደስታ ባለቤት ትሆናለህ ። በጣም በደስታ አመስግን! @rehimahu @rehimahu

  • 19 апр.1 1061810

    #የኔ እይታ 71 (ረሂማ ሁሴን) ጎበዝ ተማሪ ነበር።ከትምህርት ሌላ የማይታየው፣በትምህርቱ ትልቅ ቦታ የመድረስ ህልም የነበረው እና የሚጥር ከማትሪክ ፈተና በኋላ ጥሩ የዩኒቨርስቲ ውጤት ከማምጣት አልፎም የሚመኘው ዲፓርትመንት ውስጥ ገባ።ያኔ ብዙ ጎደኞቹ ውጤት ስላልመጣላቸው ሀሉም በተለያየ የሂወት አቅጣጫ ተበትነው ሪዝቃቸውን ፍለጋ ሲኳትኑ እርሱም ቀን ከለሊት በማጥናት የግቢው ሰቃይ ሁኖ ተመረቀ። በዚህ ብቻ አላበቃም ስንት ወጣት ተመርቆ በስራ ማጣት በሚንከራተትበት በሀገራችን ሁኔታ ከተመረቀ አንድ ወር እንኳን ሳይቆይ ጥሩ የሚባል ስራ ተቀጠረ። ሂወት ለሱ በልጅነት እንደሚመኘው እና አላህን እንደለመነው በጥሩ ሁኔታ ነበር እየሄደለት የነበረው።አንዳንዴ "እኔ ግን የአላህ ምርጥ ባሪያ ነኝ እንዴ?"ብሎ እስኪያስብ አላህ ሂወቱን ሙሉ የሚመኘውን ሲያመቻችለት ነው የኖረው። ከአምስት አመት የዩኒቨርስቲ ቆይታ በኋላ ወዳደገበት ሰፈሩ ተመልሶ በሚወደው ሙያ ላይ ተቀጥሮ መስራት ሲጀምር ከአብሮ አደግ ጎደኞቹ ጋር መገናኘት ጀመረ። አብዘሀኞቹ በቤተሰቦቻቸውም በግላቸውም የሚንቀሳቀሱ ነጋዴወች ሁነዋል። ግማሾቹ ጥሩ በሚባል የዱንያ ሂወት ላይ ያሉ ናቸው መኪና ያላቸው እና ቤት ሰርቶ ትዳር መስርቶ ለመኖር መንገድ የጀመሩ ፣ሌሎቹ ደግሞ በተለያየ መንገድ ከሀገር ወጥተው ለቤተሰቦቻቸው ዶላር ይልካሉ የሚባልላቸው። ይህን ሲያይ ሙሉ የነበረው ደስታው እና ምኞቴን እየኖርኩ ነው የሚለው ልቡ ቀስ በቀስ ያለው ነገር አንሶ ይታየው እና ይቆዝም ጀመር። እነሱ ስራቸው ውስጥ የሚያወሩትን የብር መጠን ሲሰማ የሱ ደመወዝ ለነሱ ከኪስ ገንዘብ ያነሰች እንደሆነች ተሰማው ይባስ ብሎ በራስ መተማመኑእና የአመታት ልፋቱ ከንቱ ሁኖ ታየው። ያን ሁሉ አመት እንቅልፍ አጥቼ ሳነብ ያደርኩት ቀልደው ከተማሩት እና ተኝተው ካደሩት በታች የሆነ ሂወት ለመኖር ነበር? በሚል ሀሳብ ድብርት ውስጥ መግባት ጀመረ ይባስ ብሎ የሱን እውቀት ሲያደንቁለት እና በግብዣቸው መሀል ለሱ በማሰብ"ኧረ አንተ አትከፍልም ደመወዝተኛ አይደለህ እንዴ?" ምንበወጣህ ሲሉት ስድብ መስሎ ታየው። በትምህርት ባሳለፈው ጊዜ መቆጨት እና አሁን ባለበት ሂወት መደበር ጀመረ ።ከወራት በፊት ይህን ስራ ሲያገኝ እና ደመወዙን ሲሰማ የተደሰተውን ደስታ ሁሉ ረሳው ለሱ በዛ ሰአት ብዙ ብር ነበር ዛሬም ቢሆን የጎደኞቹ ገቢ የሱን አሳንሶ አሳየው እንጂ ለሱ ብዙ ነው። ትናንት እንደሱ ሳይማሩም እንደሀብታም ጎደኞቹም ሂወት ሳይቀናቸው ሰፈር ተቀምጠው የሚዉሉ ጎደኞቹን እና ሱሰኛ ሁነው ለቤተሰብ ያስቸገሩትን ሲያይ በራሱ እንዳልተደሰተ እና አላህን እንዳላመሰገነ ዛሬ አጊንቷቸው" አንተማ ተምረህ እዚህ ደረስክ እኛ ነንእንጂ..."ብለው ብሶታቸውን ሲጀምሩ ባካችሁ እኔም ተምሬ ምንም አላመጣሁ ደግሞ የኛ ሀገር ትምህርት በቅጡ ሆድ እንኳን የማይሞላ ያኔ ግቢ ከምሄድ እንደጎደኞቼ ሰርቼ በነበር እያለ ማማረር እና መሰላቸት ጀመረ።በዚህ ሁሉ ውስጥ ግን ባልማር ካልተሳካላቸው ውስጥ ልሆን እችል ልነበር፣አልያም በሱስ ተዘፍቄ ባክኜ እቀር ነበር ወይም ተሳክቶላቸው ከሀገር ከወጡት ሳይሆን በስደት መሀል በረሀላይ ያለቀባሪ ከቀሩት ልሆን እችል ነበር አላህ የፈለግኩትን የልጅነት ህልሜን አሳክቶ ከማንም ሳልከጅል ለኔ በቂ በሆነ ሪዝቅ እያጣቀመኝ ነው ብሎ ማሰብ ከበደው ሸይጣን ጌታውን እንዳያመሰግን ልቡን ተቆጣጠረው። ጌታውን አመስጋኝ በነበረበት ወቅት የነበረው የልብ ሰላም እና መረጋጋት ጠፋ፣የአመታት ልፋቱ ባዶ ሁኖ ታየው የሚወደውን ሙያውን መስራት እስኪያስጠላው ድብርት ውስጥ ገባ። ያኔ ተማሪ እያለ እነሱ በትምህርታቸው ደካማ ስለነበሩ ወደፊት ከነሱ የተሻለ ሂወት እንደሚኖር ማሰቡ እና ዛሬላይ ተቃራኒውን ማየቱ ቅናት ይሁን ምቀኝነት አልያም የሰውን አጥብቆ መመኘት እና የራስን ስኬት አሳንሶ ማየት ባይገባውም እየተሰማው ባለው ስሜት ግን ደስተኛ አይደለም። ብዙ ወጣቶች በዚህ ሁኔታ ላይ እንዳሉ ይሰማኛል። ለሁላችንም የምለው ነገር አላህን ማመስገን ያለብን ከሰው ከፍ ሲያረገን ወይም ያልጠበቅነውን ሲሰጠን እና ፀጋውን ያንቧቧብን ሲመስለን ብቻ አለመሆኑን ነው። አላህ አላህ ነው በየትኛውም ሁኔታ ሊመሰገን የሚገባው ጌታ !አይደለም ስኬት ካልነው ቦታ ደርሰን እንዳሰብነው ባይሆን እና ብንከስር፣ባይሳካልን እና ነገሮች ቢበላሹብን፣ትዳራችን፣ስራችን እንዳሰብነው ባይሆን እንኳን አላህን መለመን ያለብን ከማመስገን ጋር ነው።እውነተኛ ምስጋና፣እውነተኛ የአላህን ፀጋ ተመልካች መሆን ይገባናል ደስታ እና መረጋጋት ልባችን ውስጥ እንጂ አይናችን ላይ መሆን የለበትም አይን ላይ ያለ አመስጋኝነት እና መብቃቃት የበላዮቻችንን ባየን ሰአት ይበናል መብቃቃት እና መርካት ልባችን ውስጥ ሲሆን የትኛውም ከፍታ እና ዝቅታ አያጠፋውም። ልባችን ውስጥ የዱንያ ጌጣጌጥ፣እና የሰው ፍቅር ካለ እናፅዳው አላህ እነዚህ ነገሮች ያሉበት ሰው ልብ ላይ አይኖርም የአላህ ቦታ አማኝ ልብ ውስጥ ነው አላህ ልቡውስጥ እንዲነግስ እና ልቡን እንዲያበራለት የሚመኝ ሰው ልቡላይ ያለውን ኮተት ያፅዳ።አላህ ንፁህ ልብ ላይ ነው የሚነግሰው።አላህ የነገሰበት ልብ በዝቅታም ሆነ በከፍታ ውስጥ ሰላም እና ደስተኛ ነው። የምንኳትነው ደስታን ፍለጋም አይደል? መልካም ምሽት💚 @rehimahu @rehimahu ለአስተያየትዎ @rehimahubot

  • 7 апр.1 026123

    #የኔ እይታ 70 (ረሂማ ሁሴን) ወደ 30 ወቹ እድሜ ተጠግታለች።ቆንጆ፣ አስተዋይ እና የተማረች ሴት ናት። ብዙወች በሚመኙት ከፍተኛ ውጤት ተመርቃ ከልጅነቷ ጀምሮ ትመኘው የነበረውን ስራ ይዛለች።እሷ ዩኒቨርስቲ ስትገባ ያገቡ ጎደኞቿ በሷ ይቀናሉ። እኛም ተምረን በነበር ይሄኔ እንደሷ የራሳችን ገቢ ኑሮን ደስተኛ ሁነን እንኖር ነበር ይላሉ(በባላቸው ገንዘብ መኖር የሰለቻቸው ጓደኞቿ) ጓደኞቿ ጋር ስትገናኝ ሂሳብ የምትከፍለውም ሆነ ከሁሉም የተሻለ አለባበስ ለብሳ የምትገኘው እሷ ናት። ከሁሉም በላይ የምታወራው ወሬ ከቤት ውስጥ ወሬ እና ከልጆች ጣጣ መለየቱ ይስባቸዋል። በተገናኙ እና በተደዋወሉ ቁጥር ስለሷ ሂወት እያወሩ በቁጭት መብሰልሰል ሁኗል የሰሞኑ ሁኔታቸው። አንዳንዶቹ ባሏቻቸው ጋር መጋጨት እና በትዳራቸው መበሳካትም ጀምረው ነበር። አንድ ቀን ብቻችንን ተገናኝተን ስለሂወት ማውራት ስንጀምር የማልጠብቀውን ነገር ከሷ አንደበት ሰማሁ። ባለችበት ሁኔታ ደስተኛ እንዳልሆነች እና በጓደኞቿ ሂወት ምንያህል እንደምትቀና አጫወተችኝ። የተመረቀችበት ከፍተኛ ውጤቷም ሆነ በራሷ ሁሉንም ማድረጎ ብቻውን ለሷ ደስታ እንዳልሆነ እና ትልቁ ምኞቷ እንደነሱ አግብታ ልጆች መውለድ እና መሰተር እንደሆነ አይኗ እምባ አቅርሮ ስትነግረኝ የሰውልጅ ባህሪ እጅጉን እየገረመኝ "ግን እኮ ድግሪሽን ይዘሻል በዛላይ የራስሽ ገቢ አለሽ ከነሱ ውስጥ ይሄ ያለው የለም እነሱ ባንቺ ሂወት በጣም እኮ ነው የሚቀኑት"አልኳት ለማፅናናት ሳይሆን እውነታውን እንድትረዳ እና ያለችበት ሂወት የሌሎች ምኞት እንደሆነ እንዲገባት አስቤ። የውሸት ፈገግታ አሳይታኝ ይሄ ከልብስ የማያልፍ ደመወዝ ነው ያስቀናቸው ?ወይስ ኧረ እድሜሽ ሄደ እየተባልኩ በቤተሰብ መነዝነዜ፣ወይስ እድሜዬ በጨመረ ቁጥር ብዙ ልጅ የመውለድ ህልሜ አደጋ ላይ እንደሆነ እያሰብኩ መጨነቄ? አለችኝ። በንግግሯ ደነገጥኩ ከልጅነቷ ጀምሮ የምትመኘውን ትምህርት ተምራ ለስራ በመብቃቷ አላህን ማመስገን አልነበረባትም? የዩኒበርስቲ መግቢያ ውጤት ለማግኘት አላህን ብዙ ከለመነችው እና ህልሟን እንዲያኖራት ከጠየቀችው በኋላ ህልሟን ስትኖር እንዲዘገይ የፈቀደችለት ትዳር ስለዘገየ ስኬቷን በ 0 ማባዛት አግባብ ነው? እነሱስ ቢሆኑ ከትምህርት ይልቅ ትዳር ያስደስተናል ብለው ጌታቸው ጥሩትዳር እና ልጅ እንዲሰጣቸው ለምነው ካገኙት በኋላ ሲሳካላቸው ትዳራቸውን ማጣጣል ነበረባቸው?ቆይ የሰው ልጅ ምን ቢደረግለት ነው አመስጋኝ የሚሆነው? ለምንድነው አይናችን እስኪያብጥ አልቅሰን የለመንነው ዱአ ሲሳካ የሚረክስብን እና ከምስጋና ይልቅ ሌላው ጉድለታችን የሚታየን? ለምን ያለንን እያመሰገንን ሌላ የምንፈልገውን ሰጥቶ ከማያልቅበት ጌታ መጠየቅ ከበደን?ለምን ከምላስ ያለፈ ምስጋና እራቀን?ለምን ባለን ነገር መደሰት አልቻልንም?የኢማን ጉዳይ ወይስ የሰውን አጥብቆ የመመኘት አባዜ? ምንድነው ችግሩ? @rehimahu @rehimahu ለአስተያየትዎ @rehimahubot

  • #የኔ እይታ 69 (ረሂማ ሁሴን) ከአድካሚ ውሎዬ በኋላ ወደ ቤት ስመጣ አይኖቿ በእምባ ተሞልተው የበረንዳው ጫፍ ላይ ትክዝ ብላ ተቀምጣለች። "አሰላሙ አለይኩም " ስላት ወአለይኩም.. ብላ ሳትጨርስ እምባዋ በጉንጯ ላይ መፍሰስ ጀመረ። ድንግጥ ብዬ "ደግሞ ምን ሆንሽ?" አልኳት። አክስቴ ናት ሰሞኑን ከፍተኛ ደስታ ላይ ነበረች ከ10 አመት በላይ በሲህር በሽታ ስትሰቃይ የነበረችው ልጇ ትድናለች የተባለችበት ቦታ ሁሉ አብራት ስትንከራተት ኑራ ከቅርብ ወራት ጀምሮ በጣም ጥሩ ለውጥ እየታየባት እና ወደ ጤናዋ ሙሉ ለሙሉ እንደተመለሰች የሚያረጋግጥ ሁኔታ ላይ ነች። እንደድሮው ከሰው አትሸሽም፣አትከፋም፣ አታለቅስም.....ደስተኛ እና የተረጋጋች ሁናለች። ታድያ በዚህ ሁኔታ ውስጥ ይቺ እናት ለአመታት በልጆ ህመም የጠፋው ደስታዋ እና ተስፋዋ ተመልሶ አይቻት ነበር። የዛሬው ፊቷ ግን ትድንልኛለች በሚል ተስፋ ጌታዋን ስትለምን ከኖረችባቸው የፈተና አመታት በላይ ጨፍግጎ ነበር። "አመማት?"አልኳት ለመጀመሪያው ጥያቄዬ መልስ ሳጣ።" አሁን እድሜዋ ካለፈ በኋላ አፊያዋ ቢመለስ ምት ትርጉም አለው አንድ ልጄ ያለዘር ያለትዳር እንዲሁ ቀርታ"አለችኝ ተስፋ በመቁረጥ ስሜት ውስጥ ሁና። በንግግሯ ማዘን ወይስ መናደድ እንዳለብኝ ግራ ገባኝ። ወደኋላ መለስ ብዬ ከልጇ ጋር ያሳለፈችውን ስቃይ ሳስብ አላህን ከሱጁድ ቀና ሳትል እሰክትሞት ስታመሰግነው ለመኖር የልጇ ጤና መስተካከል ብቻ በቂ እንደነበር ነው የሚሰማኝ። እርግጥ ነው በሰው ህመም መፍረድ አይቻልም ነገርግን የአመታት ልመናዋ የልጇ ጤና፣የረሳችውን ፈገግታዋን እና ተጫዋችነቷን ማየት እና ከእኩዮቿ ጋር ስትቀላቀል ማየት ነበር ።ጌታዋ ዱአዋን ሰምቶ ዛሬ ለአይኗ እንኳን ጠልታቸው ከነበረቻቸው እኩዮቿ ጋር መገናኘት፣ያ ሁሉ ድምፅ መጥላት ጠፍቶ ሰርግ ሳይቀር መሄድ፣መሳቅ መጫወት ጀምራለች። ታድያ እንደእናት ልጇ እንድታገባላት መጓጓቷ ነውር ባይሆንም አሁንላይ የጎደለ ከመሰላት በላይ አላህ የሰጣት፣ያስደሰታት እና ዱአዋ ስቲጃባ የሆነበት አላህን የምታመሰግንበት ነገር መብዛቱን አለማስተዋሏ እና ያጣችው እንደጎላባት ሳይ ተገረምኩ። በእርግጥም የሰው ልጅ በዳይ እና ከሀዲ ነው። ጤናዋን በሰጠልኝ እንጅ ሌላ ምንም አልጠይቀውም ነበር ባለችበት አንደበቷ ጌታዋን ስታማርር ሳያት ጨነቀኝ። ለ10 አመታት ጌታዋን የለመነችው ነገር ሲሳካ ለ1 አመት እንኳን ያለማማረር ማመስገን እንዴት ተሳናት? ደግሞስ ባለማግባቷ ከከፋፍ ከዚህ ቀደም ዱአዋን መርሀባ ያለው ጌታ አሁንስ በመተናነስ ብትለምነው የፈለገችውን ሂወት ለልጇ አይሰጥላትም ነበር?ማማረርን ለምን መረጠች ?ለምን ማመስገን እራቃት? አልኩ በመገረም ። ከዛ ግን እሷ ልክ ባትሆንም እሷን በዚህ ልክ ስታዘብ እኔስ ግን እንዴት ነኝ?ብዬ ወደራሴ ተመለከትኩ። እኔስ የጌታዬን ውለታ ወይስ የጎደለኝን ነው ሂወቴ ውስጥ አጉልቼ የማየው? እኔም ጌታዬ ፊት እንደሷ ብስኩ እና ከምስጋና ይልቅ ምሬት የሚቀናኝ ነኝ ወይስ አመስጋኝ እና የጎደለኝን ለጌታዬ በመተናነስ የምለምን ? ውይ አላህን ስናማርር ስናስጠላ...... @rehimahu @rehimahu ለአስተያየትዎ @rehimahubot

  • የቱ ነው ጎልቶ የሚታይህ? ያጣኸው ወይስ ያገኘኸው? እስቲጃባ ያገኘው ዱአህ ወይስ የዘገየው ልመናህ? በዙሪያህ ያሉት መልካም ሰወች ወይስ የጎዱህ እና ያስከፉህ? ያገኘህባቸው ጊዜያት ወይስ የተቸገርክባቸው? ሰሞኑን በነዚህ ጉዳዮች ላይ ተከታታይ ሀሳቦች ይኖሩናል ነቃ ነቃ እያላችሁ የጠፋችውን እህታችሁን ተከታተሏት ። መልካም ምሽት💚

  • 26 мар.1 03461

    እንደዚያች ፈትሏ ከጠነከረ በሆላ ተርትራ እንዳፈረሰችው ሴት አትሁኑ (ሱረቱ አል-ነሕል:- 92) ረመዳን ላይ የተውነውን ወንጀል ረመዳን ሲወጣ ተመልሰን ከሰራነው ፣ የጠነከርንበትን ሰላት ፣ፆም ፣ቁርአን ፣ዚክር እና ሰደቃ ቀስበቀስ እርግፍ አድርገን ከተውነው በእርግጥም አላህ በቁርአን ውስጥ የነገረንን ያዛችን የሞኝ ሴት ባህሪ እንላበሳለን። ⚡️ረመዳንን ይገዛ የነበረ ሰው ካለ ረመዳን አልቆል! ህያው እና ዘላለማዊ የሆነውን ጌታ የሚገዛ ካለ ግን የሞት  መለይካ መጥቶ እስትንፋሱን እስኪያቆርጠው ድረስ ጌታውን መታዘዝ አያቆምም!!!! አላህ የረመዳን ባሮች አያድርገን! @rehimahu @rehimhu ለአስተያየትዎ @rehimahubot

  • 21 февр.1 200245

    አንድ እህታችን ይህን ፅሁፍ face book ላይ አጋርታ አየሁት እና ተዝኪያ ይሆነን ዘንድ አጋራኋችሁ ተጋበዙልኝ። (Meliha Mahi) ወላሂ ሁሌም ይቆጨኛል! ያኔ ተራዊህ መስገድ እየቻልኩ መስጂድ ሄጄ ልጅነት አሸንፎኝ ከጓደኞቼ ጋር ወሬ በማውራት ያቃጠልኩት ጊዜ ዛሬም ድረስ እንደ እሳት ይፋጀኛል። ያኔ እንደ ቀልድ ያሳለፍኳቸው ቀናት ነጉደው ተራዊህ ከሰገድኩ ዛሬ 11 ዓመታት አለፉኝ። አሁን ቁርዓን ለማክተም የምታገለው ትግል ከባድ ነው። በታክሲ ውስጥ በሥራ መሃል ወይም የልጆቼን ሰርቪስ እየጠበቅኩ በስልኬ ለጥቂት ደቂቃዎች እቀራለሁ። ነገር ግን ማስተንተንና ረጋ ብሎ መቅራት የሚታሰብም አይደለም። ምንም ዓይነት ኃላፊነት ሳይኖርብኝ የተዘናጋሁባቸውን ጊዚያት ሳስብ፣ 'ኢስላሚክ ፊልሞች' እንደ ኢባዳ መስለውኝ ቁጭ ብዬ ያሳለፍኳቸውን የረመዳን ወሮች ከአላህ ጋር ምን ብዬ ልተሳሰባቸው? እላለሁ። ከሰላት በኋላ ከሚባሉ አዝካሮች ውጭ፣ እንደ ድሮው በቤተሰብ ጥላ ስር ሳለሁ እንደነበረኝ የትርፍ ጊዜ በአግባቡ ቁጭ ብዬ የምዘክርበት ሰዓት እንደሌለኝ ሳስተውል ያኔ በደንብ አለመጠቀሜ ያቃጥለኛል። የመጨረሻዎቹን አሥር የረመዳን ቀናት ተሃጁድ ለመስገድ ብሞክር እንኳ ድሮ የነበረኝ አቅም አሁን የለኝም። 🥺 ቀኑን ሙሉ በሥራ ደክሜ ስለምውል ሰውነቴ ይዝላል። ያኔ ግን እየቻልኩ 'ዛሬ ልረፍና ነገ እሰግዳለሁ' እያልኩ ያሾፍኩባቸው ወርቃማ ቀናት ዛሬ ይናፍቁኛል። ኪታብ ቀርተን ተፍሲር ሊጀመር ሲል ክላስ እንዳይረፍድብን ለመውጣት ስንነሳ፣ ኡስታዛችን 'ቁጭ በሉ' ብለው በግድ ያስቀምጡን ነበር። እኛ ግን እየተነጫነጭን ብንቀመጥም ልባችን ሌላ ቦታ ነበር። 'ጊዜያችሁ ነውና ተጠቀሙበት' ይሉን ነበር ሁሌም። ዛሬ ላይ ሆነን ስናየው በጣም ልክ እንደነበሩ ይገባኛል። ሕይወት ምን እንደሚገጥምሽ፣ ወዴት እንደምትመራሽና ምን እንደተጻፈልሽ ከአላህ በቀር ማንም አያውቅም። ምናልባት ዛሬ ያለሽ ጊዜ የዛሬ ዓመት ላይኖርሽ ይችላል። ዛሬ ያለሽ አፊያ ጤናየዛሬ ወር ላይኖርሽ ይችላል። ስለዚህ ዛሬን በአግባቡ እንጠቀምበት። አላህ ፆመው ከተጠቀሙት እና ፆማቸው ተቀባይነት ካገኘው ባሮቹ ያድርገን። አሚን።

  • 15 февр.1 340137

    ድሮ ድሮ በሰፊው የነበረ አሁን ላይ እየቀዘቀዘ ካለ የረመዳን ድባብ አንዱ አውፉታ መጠያየቅ ይመስለኛል። አውፍታ መጠየቃችን አመቱን ሙሉ ሁኖ ከሆነ መልካም ግን እንደዛ አልመሰለኝም። እስካሁን ረመዳን መድረሱን አስመልክቶ አውፍታ የሚጠይቅ የፅሁፍ መልዕክትም ሆነ የስልክ ጥሪ አልደረሰኝም! እኔም ብሆን እስካሁን ማንንም አውፉታ አልጠየቅኩም! እውነት የኔ ሀቅ ያለባቸው ሰወች ሳይኖሩ ቀርተው ከሆነ መልካም! ካለም ሁላችሁንም ለአላህ ብዬ አውፍ ብያለሁ ።እኔም የብዙ ሰወች ሀቅ እንዳለብኝ ይሰማኛል እናም ሆን ብዬም ሆነ በስህተት ልባችሁን የሰበርኳቸሁ፣ስማችሁን በመጥፎ ያነሳኋችሁ ፣በኔ ያልተገባ ባህሪ ቅር እንድትሰኙ የሆናችሁ እህት ወንድሞች በሙሉ ለአላህ ብለው አውፍ የሚሉ ባሮች ከጌታቸው ዘንድ የሚያገኙትን ትልቅ ደረጃ እና ስጦታ አስባችሁ አውፍ እንድትሉኝ እና ከፊታችን የሚመጣውን የተከበረ ወር ከጥላቻ፣ከቂም እና ከቅሬታ የፀዳ ልብ ይዘን እንድንቀበለው እጠይቃችኋለሁ። የቆሸሸ ልብስ ላይ ሽቶ ከመቀባት በፊት ልብሱን ማጠብ ይቀድማል እና   ረመዳንን አጊንተን ነፍሳችንን በኢባዳ ለማስዋብ ከመጣራችን በፊት ላለፉ ወንጀሎቻችን ተውበት በማድረግ ፣ የምንሰራቸውን ሀራም ነገሮች በማቆም እና ሀቃቸውን የነካንባቸውን ሰወች አውፉታ በመጠየቅ ልባችንን ቀድመን አፅድተን እንግዳችንን እንጠብቀው! እወዳችኋለሁ💚 አላህ ረመዳንን አጊንተው ከሚጠቀሙ ባሮች ያድርገን! @rehimahu @rehimahu ለአስተያየትዎ @rehimahubot

  • 12 февр.1 03541

    የሚተገበር ኒያ + ስቲቃማ (ረሂማ ሁሴን) ረመዳን ላይ የብዙወቻችን ስህተት ከአቅማችን በላይ ማቀድ ይመስለኛል። ይህን ሀሳብ ከረመዳን ቀደም ብለን ብናነሳው ጥሩ የነበረ ቢሆንም አሁንም ገና ጅማሮው ላይ እንደመሆናችን አጠር አርገን እናውጋበት። መጀመሪያ ላይ የሚኖረን ነሻጣ ሳይቀዘቅዝ ወሩን እንድንጨርስ እና ረመዳን ካለቀም በኋላ ቀጣይነት ያለው ኢባዳ ይዘን እንድንቀጥል ረመዳን ላይ የምናወጣቸው የኢባዳ እቅዶች አቅማችንን፣ልምዳችንን እና ውሏችንን ያማከሉ መሆን ይኖርባቸዋል። በስራ ቢዚ ሁኖ የሚውል ሰው ቀን ላይ ብዙ የቁርአን ገጾችን ማንበብ እንደማይችል እያወቀ በቀን 5 ጁዝ እቀራለሁ ብሎ ማቀድ እውነታ ጋር መጋጨት እና ሳይሰራው ሲቀር እራስን ማዳከም ነው። ስለሆነም ቀን ላይ ቢዚ የምትሆኑ ሰወች ለቁርአን የሚሆን ምቹ ሰአት በመሀል ካላችሁ እዚያ ሰአት ላይ ብቻ በትክክል መቅራት የምትችሉትን ያክል አስባችሁ አቅዱ እና ለመተግበርም ጣሩ። ስራ ላይ የምትሆኑባቸው ሰአታት ላይ የተለያዩ ዚክሮችን፣ እንዲሁም አንዴ ስትሉ 10 ወንጀል አሳባሹን፣ 10 ሀሰናት አስመዝጋቢውን፣10 ደረጃ ከፍ አስደራጊውን እና ከጭንቅ ፈራጂውን ሰለዋት በተወዳጁ ነብይ ላይ  አብዙ። ዚክር የውጭ ስራም ሆነ የቤት ስራ ላይ ቢዚ የሚሆን ሰው እራሱን ወደጌታው የሚያስጠጋበት፣ልቡን የሚያነፃበት እና ረመዳንን በተጣበበ ጊዜው ውስጥ እንኳን እንዲጠቀምበት የሚያደርግ ሲሰራ ቀላል ትሩፋቱ ግን ትልቅ ኢባዳ ነው። ከዚህ ሳንወጣ ቀን ላይ የሚሰራው ስራ የማያደክመው የሆነ ሰው ለይሉን ለመጠቀም መነየት እና መትጋት ይጠበቅበታል። ቀን ላይ መቅራት ያልቻለውን ቁርአን እና መስገድ ያልቻለውን ሰላት ከለይሉ ክፍል ላይ ለመጠቀም መስራት ነው። ይህ ሲሆን እቅዱ ከሱ ሁኔታ ጋር የተጣጣመ ስለሆነ ወሩን ሙሉ ሳይጨነቅ የመተግበር እድል ያገኛል። ከዛም አልፎ ለሂወት ዘይቤው ምቹ የኢባዳ ሁኔታ ስለመረጠ ከረመዳን በኋላም ቀጣይነት የሚኖረው ኢባዳ ይመሰርታል። አስታውሱ:- ጌታችን የሆነ ጊዜ ላይ በብዛት ተሰርቶ ከጊዜ በኋላ ከሚተው ኢባዳ ይልቅ ዘውታሪነት ያለው ትንሽ ኢባዳን ይወዳል። ስለዚህ ዘንድሮ ስነይቱ ለረመዳን ብቻ ሳይሆን ከረመዳን በኋላም የምትቀጥሉትን ኢባዳ ነይታችሁ ትጉ። ይህ ኒያ  ረመዳን ላይ ይበልጥ መትጋት እንዳለባችሁ ሳይዘነጋ ነው። @rehimahu @rehimahu ለአስተያየትዎ @rehimahubot

  • ፌስታል መመረት እና አገልግሎት ላይ መዋል መታገዱን ተከትሎ እነዚህን ጠንካራ እና የሚያምሩ የጨርቅ መያዣወች በብዛት እኛ ጋር ያገኛሉ። ዋጋ -ትንሽ (ለሞባይል ፣ለኮስሞቲክስ እና ለተለያዩ አነስ ያሉ እቃወች የሚሆን) 17cm*21.....8 ብር -መካከለኛ .....32cm*35.......18 ብር -ትልቅ ........40cm*40cm .....25 ብር ከነዚህ ውጭ የምትፈልጉት ሌላ መጠን ካለም በትዛዝ እንሰራለን ለማዘዝ @rehimaye ላይ ያነጋግሩን ወይም በ 0980175239 ይደውሉ

  • አሰላሙ አለይኩም ወራህመቱላህ እዚህ ቻናል ላይ ምንም አይነት የቢዝነስ ማስታወቂያ ለቅቄ እንደማላውቅ ታውቃላችሁ። ከዚህ በታች የምለቅላችሁ የኔ የእህታችሁ ቢዝነስ ነው እቃውን የምትፈልጉ በማዘዝ እና ለሚፈልጉ ሸር በማድረግ የተለመደ ፍቅራችሁን አሳዩኝ መልካም ቀን💚

  • #ረመዳን መጣላችሁ (ረሂማ ሁሴን) ካሁኑ ኒያችንን አናስተካክል !የረመዳን ፆም ፈርድ ከተደረገብን(ቡሉግ ከደረስን) ጀምሮ የፆምናቸውን ረመዳኖች እናስባቸው እስኪ..... ብዙ ጊዜ አኽትመን፣ ብዙ ለሊቶችን ሰግደን፣ ብዙ በእምባ የተሞሉ ዱአወችን አድርገን ነበር አይደል? ግን ዛሬ ላይ የትኛውን ተግባር አስቀጥለነዋል? ብዙወቻችን ረመዳንን የምንገዛ እንጂ አላህን የምንገዛ አንመስልም አይደል? ሰላት የማይሰግድ ሰው ረመዳን ላይ ይሰግዳል፣ ቁርአን ያልቀራ ሰው ከአሊፍ ይጀምራል፣ በሳምንት አንድ ቀን ጁመአ ሱረቱል-ካህፍን መቅራት የሚከብደው ሰው በአንድ ሳምንት ያኸትማል፣ ሱና ሰላት የሚከብደው ሰው ይጠነክራል፣ ለወራት የተሸከመውን የወንጀል ብዛት ሊያራግፍ በተውበት እምባ ይርሳል፣ የሀራም ፍቅር ውስጥ የሚባክኑ ወጣቶች ረመዳን ሲመጣ ያቆማሉ፤..... ከዛ ግን ረመዳን ሲያልቅ መስጂዶች ባዶ ከሆኑ፣ ሰላት የጀመረው ሰው ካቆመ፣ ቁርአን መቅራት የጀመሩ ምላሶች ከዘነጉ ፣ልባችን በወንጀል እየጠቆረ ተውበት ከማድረግ ከተቆጠበ፣ የሀራም ግንኙነቶች ከቀጠሉ... የረመዳን ትርፉ ምንድን ነው? በአላህ ይሁንብን የዘንድሮው ረመዳን ቢያንስ ፈርድ ነገርን ጀምረን የምንተውበት፣ ሀራም ነገርን ካቆምን በኋላ የምንቀጥልበት አይሁን! ለመስገድ፣ ቁርአን ለመቅራት፣ ሀራም ነገርን ለመተው ስንነይት ለረመዳን ብቻ አይሁን! በስልካችን ሀራም ነገርን በመመልከት በሽታ የወድቅን ሰወች፣ የሀራም ግንኙነት ውስጥ ያለን ወጣቶች፣ ሰላትን የተውን ሰወች፣ ቁርአንን የረሳን ሰወች ረመዳን ላይ ብቻ ሳይሆን ከዛ በኋላም ላንመለስበት ረመዳንን የመልካም ተግባሮች ልምድ ማስጀመሪያ እንጂ መጨረሻ አናድርገው! ረሱል (ሰ ዐ ወ)አንድ ግዜ እንዲህ አሉ"አንተ አብደላህ እንደ እከሌ አትሁን ለይል ሰላት ይሰግድ ነበር ተወው!"በሚያሳዝን ሁኔታ ይህ የኛ ተጨባጭ ነው። በሌላ ሀዲስ መልዕክተኛው(ሰ ዐ ወ)" አላህ ዘንድ በጣም ተወዳጅ ስራ ትንሽም ብትሆን ሰውየው ጀምሮ የፀናባት ናት"ማለታቸውን እናስታውስ! በእርግጥ ሁሉም ኢባዳወቻችን ረመዳን ላይ ከሌላው ቀን የተለዩ ሊሆኑ ይገባል! ወሩ ሸይጣን የሚታሰርበት በመሆኑ ከኢባዳ ከሚያሳንፈን ትልቅ ጠላት አላህ ጠብቆናል ፣ በተጨማሪ ሱና ኢባዳወች በፈርድ ደረጃ የምንመነዳበት በመሆናቸው እና ከእሳት ነፃ የምንባልበት ልዩ VVIP ወር በመሆኑ ከማንኛውም ግዜ የተሻለ አቢድ መሆን ይገባናል! በዛው ልክ የምንሰራው ሀራም ነገርም ከሌላው ጊዜ በበለጠ ስለሚያስቀጣ ልንጠነቀቅ ይገባናል! ይህ ግን ሂወታችን ላይ ለውጥ የሚፈጥረው ከረመዳን በኋላም ማስቀጠል ስንችል ነው ብዬ አምናለው! እንደዛች ፈትሏ ከጠነከረ በኋላ  እንዳፈረሰችው ሴት እንዳንሆን ኒያችንን በማሳመር ብንጀምር አትራፊወች እንሆናለን ኢንሻ አላህ! አላህ ሂወታቸውን ሙሉ የሚቀይር ረመዳን ከሚፆሙ ባሮቹ ያድርገን! ረመዳን ከሪም @rehimahu @rehimahu ለአስተያየትዎ @rehimahubot

  • Channel photo removed

  • 2 февр.1 070101из rehimahu

    አሰላሙ አለይኩም ውድ እና የተከበራችሁ የቻናሌ ቤተሰቦች እንዴት ናችሁ? ስለጠፋሁ አውፍ በሉኝ😊እንደሚታወቀው የናፈቅነውን እና በጉጉት የጠበቅነውን የረመዳን ወር ልንገናኝ ቀናቶች ነው የቀሩን አላህ ፈቅዶ ከሚያገኙት ካደረገን የአሁኑን ረመዳን እንዴት ውብ አድርገን ማሳለፍ(መጠቀም) እንዳለብን ሳስብ ነው የሰነበትኩት፤ እስኪ አስራ አንድ ወራትን ወደኋላ መለስ ብለን ያለፈውን ረመዳን እናስታውስ 🤔 ሰላት ላይ ምን ያክል ጠንክረን ነበር?፣ ስንት ግዜስ አኽትመን ነበር?፣ ዱአ ላይስ? ያለፈውን ረመዳን በተገቢው ሁኔታ ተጠቅሜበታለሁ ብላችሁስ ታስባላችሁ? ከአምናው ረመዳን በሆላ በጣም ብዙ የቅርብ ወዳጆቻችንን ፣ትላልቅ ኡለማወቻችንን አጥተናል። እኛ እድለኞች ነን ረመዳንን በቅርብ እያየነው ነው አላህ ከሚያገኙትም ያድርገን 🤲 ታድያ ብዙወች እንደጎጉ ሳያገኙት የሄዱትን ወር አላህ የማግኘት እድል ከሰጠህ እንዴት ለመጠቀም እያሰብክ ነው? እንዳለፈው ረመዳን የመጨረሻወቹን አስር ቀናት ብቻ ነው ለይል ለመስገድ ያሰብከው? ወይስ ሁሉንም ቀን? እንዳለፈው ብዙወችን አውፍ ብለህ የተወሰኑት ላይ ግን ቂም እንደያዝክ ነው መቀበል ያሰብከው? ወይስ ሁሉንም ከልብ አውፍ ብለህ ለመቀበል? አምና ከቀራኽው ምን ያህልስ ለማሻሻል አስበሀል? አመድ አፋሽ ወይስ አጅር አፋሽ ነው መሆን ያሰብከው? መልስህ ግልፅ ነው በረመዳን መጠቀም ትፈልጋለህ። ስለዚህ ከአሁኑ እንቅስቃሴ ጀምር ሱና እና የለሊት ሰላቶችን ተለማመድ ፣ቁርአንን ከእስከዛሬው በተሻለ በቀን ውስጥ አንብብ፣ ከማይጠቅሙ ነገሮች እራስህን ማራቅ ተለማመድ፣ ሰወችን ይቅርታ መጠየቅ እና ይቅርታ ማድረግም ጀምር፣ ምላስህንም ዚክር አስለምደው ይህ ረመዳን ላይ ለምታደርገው የለውጥ መንገድ ይረዳሀል/ሽ ብዬ አስባለሁ። ✍ rehima hussen @rehimahu @rehimahu

  • 28 янв.1 09082

    ሸዕባን (ረሂማ ሁሴን) የረመዳንን ውብ መአዛ ቀድሞ የሚያሳውደን ፣የረመዳንን መድረስ አብስሮ በደስታ ጮቤ የሚያስረግጠን፣የረመዳንን ሀቅ እወጣ ይሆን? ከረመዳን ከስረው ከሚወጡት ወይስ አትርፈው ከሚወጡት እሆን ይሆን በሚል ፍርሀት የምንዋጥበት ፣ረመዳንን ለመቀበል በሁሉ ነገር የምንዘጋጅበት፣ የምንጎጎበት፣ እድሜ ሰጥቶ ሌላ እድል አላህ ስለሰጠን የምናመሰግንበት ፣ ሸዕባን ብዙ አይነት ስሜቶችን የምናስተናግድበት ውብ ወር ነው። የሸዕባን ወር ረሱል ﷺ ከረመዳን ቀጥሎ አብዝተው የሚፆሙበት ተወዳጅ ወራቸው እንደሆነ ብዙ ሐዲሶች ላይ ተጠቅሷል። ሻዕባን በውስጡ የያዛቸው ፀጋዎች ብዙ ናቸው።የሻዕባን ወር መላይካዎች ስራችንን ወደ አላህ የሚያቀርቡበት ወር ነው። ዑሳማ ኢቢን ዘይድ ረዲየላሁ አንህ ባንድ ወቅት ረሱልን እንዲህ ብሎ ጠየቃቸው:- «يا رسول الله! لم ارك تصوم شهرا من الشهور ما تصوم من شعبان؟! «ያ ረሱለላህ ሌሎች ወሮች ላይ እንደ ሻዕባን ስትፆሙ አላየሁህም?» አላቸው قال: ذلك شهر يغفل الناس عنه، بين رجب ورمضان، وهو شهر ترفع فيه الأعمال إلى رب العالمين، فأحب أن يرفع عمل، وأنا صائم» ረሱልም ﷺ: «ይህ ወር በረጀብና በረመዳን መካከል የሚገኝ፤ ሰዎችም የዘነጉት ወር ነው። በዚህ ወር የሰዎች ስራ ወደ ዓለማቱ ጌታ ከፍ የሚልበት ነው! ስለዚህ ስራዎቼ ከፍ እያሉ ባለበት መፆምን እወዳለሁ።» ብለው መለሱለት። ለታላቁ ወር መንፈሳዊ እና አካላዊና ዝግጅት የምናደርግበት ወር ነው የብዙ ደጋግ ባሮችን ታሪክ ስንሰማ በዚህ ወር ልክ እንደ ረመዳኑ በየቀኑ አልያም በየሳምንቱ ቁርዓንን ማኽተምን ይለማመዱ እንደነበር ፤ ዝምታን ያዘወትሩ እንደነበር እና ሰደቃን በእጅጉ ያበዙ እንደነበር ተዝግቧል።ሻዕባንን መጠቀም ለራሳችን ነው በዚህ ወር ላይ የተለማመድነው ቁርዓን ፤ ዚክር ፤ የለይል ሰላት ፤ መልካም ንግግርና ይቅር ባይነት ረመዳን ሲገባ እንዲቀለን ያደርግልናል። ኢስቲቃማ ያለው መልካም ስራ እንዲኖረንም ቀድመን መለማመዳችን ይጠቅመናል። መፆም የምንችል ሰኞና ሀሙስን በመፆም፣ ቁርአን ሳንቀራ እንውል ከነበርን በቀን ከአንድ ገፅ ጀምረን ግማሽ፣አንድ ጁዝ እያልን በማሳደግ ረመዳን ላይ ቁርአን ይገራልን ዘንድ ከወዲሁ መለማመድ፣ትርፍ ወሬን ቀንሰን ምላሳችንን ዚክር ማለማመድ፣ሱና ሰላቶችን ከትንሽ ጀምረን መጀመር፣ጥሩ ግዜ ወስደን ዱአ ማድረግ....እነዚህና የመሳሰሉ ኢባዳወችን በቀሩን 21 ቀናት ውስጥ ያለማቋረጥ በሚገራልን መንገድ በመስራት ረመዳን ማረሻ ሳይሆን ፍሬ መዝሪያ እና ማፍሪያ ይሆን ዘንድ ለነፍሳችን ጠቃሚ ነገር እናድርግ። ሳይንቲስቶች እንደሚናገሩት የሰው ልጅ የሚፈልገውን ተግባር የሂወት ዘመን ልምዱ ለማረግ ተከታታይ 21 ቀናት ያለማቋረጥ መተግበር በቂ ነው ይላሉ። ታድያ እነዚህ የሻዕባን 21 ቀናት ረመዳን ላይ የምንፈልገውን ኢባዳ በቀላሉ ለመተግበር ስለሚረዱን እንጠቀምባቸው። መልካም የኢባዳ ወራት💚 @rehimahu @rehimahu ለአስተያየትዎ @rehimahubot

ግጥም እና ወግ ( ረሂማ ሁሴን) — tgindex