የደሱ ግጥሞች
Статистика☞ የስብህና ልቀት ለማምጣት ከመፃህፍት ጋር እናዉጋ ☞ በዚህ ቻናል ተወዳጅ የሆኑ ግጥሞችንና አስተማሪ ታሪኮችን ይቀርቡበታል 👇👇👇👇👇👇👇 ለሃሳብ አስተያዬታች @Almnu6 @Almnu6
- Последний пост
- 12 авг.
- Последнее чтение
- 13 авг.
- Постов за неделю
- 1
- Всего постов
- 20
- Тип
- открытый
- Язык
- und
- В каталоге с
- 13 авг.
- 1/24сутки в ленте
- 54
- 1/48двое суток
- 61
- 1/72трое суток
- 66
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
ሺዎች የሚወዱትን የንባብ ማህበረሰብ ይቀላቀሉ! በየቀኑ ምርጥ ታሪኮችን እያነበቡ አእምሮዎን ያዝናኑ። የቻናላችን አባል ለመሆን ሊንኩን ይጫኑ 👇👇👇👇👇👇👇👇👇 https://t.me/Fiction_123
"አብ ሆይ! በዛለ ሰውነት፣በደከመ ገላ፣ ከቦን የሞት ጥላ .. አንጋጠን ወደ ላይ፦ ኤሎሄ ኤሎሄ፣ሰርክ ብንጣራ፣ እንባችንን ማታይ፣ሀዘን 'ማትጋራ፣ በዘመን ሽግግር፣ሌላ ዕዳ ሊከፈል፣ እኛም እንደ እየሱስ፣ተሰቅለናል መሰል🤔🙄
ልብ የሚነኩ፣ ሳቅ እና እንባ ያዘሉ ድንቅ ልቦለዶች ከገፀ-ባህሪያቱ ጋር አብረው የሚኖሩበት ልዩ የንባብ ቦታ። አሁኑኑ ይቀላቀሉን 👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇 https://t.me/Fiction_123
አለቀለት ያሉት (በእውቀቱ ስዩም) ከጅረት አጠገብ ፥ቆሞ የኖረ ዛፍ መብረቅ ገነደሰው አሁን ድልድይ ሁኖ፥ ያሸጋግራል ሰው :: “አለቀለት” ያሉት፤ ተልኮው መች አልቆ ቆሞ የጠቀመ፥ መላ አያጣም ወድቆ፤
ነ....ጠ...ብ..ጣ.ብ እድል ላልገጠመው፣አንድ ብላቴና፣ ጉድለት ላሰከረው፣ማን ቀርቦ ሊያፅናና፣ በፍርደ ገምድል ህግ፣ለከሰመ አምሮ፣ የትኛው አዛውንት፣ያፅናናዋል መክሮ። በግማሽ እንጀራ፣ባንድ ቁራሽ ዳቦ፣ ቀኑን ለሚገፋ አንጀቱን ጠፍንቆ፣ወስፋቱ ተርቦ፣ ጉልበት የት ይመጣል ዝሆን የሚያሸክም፣አንበሳ ደርቦ። ብቻ ምን አለፋን፦ ሕይወት ነ...ጠ...ብ..ጣ.ብ ነው፣ቀለም አልባ ምስል፣ ለአንዱ ደስታ ሲያለብስ፣ለሌላኛው ቁስል።
"ሰው ብልኃተኛው፣ ምንኛ ዘየደ፣ ለጨለማ ቀኑ፣ ብርሐን ወለደ! እያልኩኝ አባቱን፣ በቃል ሳሞግሰው፣ በልጁ ውስጥ አየሁ፣ ብርሃን እየሰጠ፣ ቀን የጨለመው ሰው! "የእድሜውን ማለዳ ዘንግ እንደጨበጠ፣ ሳያውቀው መምሸቱን፣ መንገድ እየመራ፦ ከሁዋላ የሚቀር፣ እያየ ፊት ፊቱን፣ ጸዓዳ ልጅነቱን፦ ሳቁን ቡረቃውን፣ በሆድ የተቀማ፣ ምስኪን ህፃን አየሁ ለአባቱ ብርሃን፣ ለራሱ ጨለማ፡፡
የሚማርኩ ታሪኮች፣ ልብ የሚነኩ ገፀ ባህሪያት እና ወደ ሌላ አለም የሚወስዱ አጫጭር ልብ ወለዶች። ቤተሰብ ይሁኑን! https://t.me/Fiction_123
"እየቻለው እንጂ በልቡ ሸሽጎ፣ በሆደ ሰፊነት ዘወትር ዋጥ! አድርጎ፣ አድማጭ ጀሮ ቢያገኝ ሁሉም በየተራ፣ ስንት አለ በውስጡ ሀዘን ወይ መከራ።
"ሌቱን ላያነጋው ቂሙን ላይዘነጋው ማረን ቢሉት ላይምር፥ እግዜር ላይማለድ፣ እንደ ትላንትናው ደሞ ዛሬ መሼ በጉድ ሌት ተረግዞ፥ የጉድ ቀን ሊወለድ። ተፃፈ✍️ደሱ
"ቀንም ለኛ ሲፈርድ፣ነገር ሲደላደል፣ ክፋት ደግ ይሆናል፣ልክነት ነው በደል፤ አሻጋሪን ጊዜ ምኞት ቢያስጠብቀን፣ ያለ ፈራጁ ግን ብዙ ነው ሚርቀን፣ ብንፈጥን አንደርስም ብንዘገይም እዛው፣ አምላኩን ለማያውቅ እድል ነው ሚገዛው፤ ስማኝ ጃል፦ ጊዜን መጠበቁ ያለ ዳኛ አይሆንም፣ ራሱም ባበጀው' ፈጣሪ አይኮነንም።
የዘመናችን ወጣቶች ታሪክ... የእኔ እና የእርስዎ! 🏙️🎧 በከተማዋ ግርግር ውስጥ የሚጠፉ ውበቶች፣ የጓደኝነት ፈተናዎች፣ የህልም ስኬቶች እና ውድቀቶች። ልክ እንደ እርስዎ የሚያስቡ እና የሚኖሩ ሰዎችን ታሪክ በየቀኑ ይከታተሉ። 👉 የዘመኑን ምት ይከተሉ፦ 🔗 https://t.me/Fiction_123
(በውቀቱ ስዩም) "አገር በሚያልፍበት፣በአዘቦት ጎዳና፣ በሁሉም ሰው ፊት ላይ ትካዜ ተስሎ፣ሲመስል ዳመና፣ ማን ከማን ተሽሎ፣ማን ማንን ሊያፅናና፣ በዕንባ ስፍር እንጂ የምንለያየው፣ ክንብንቡን ገልጦ፣ቀረብ ብሎ ላየው፣ ሁሉም ልቅሶ ላይ ነው። በየትኛው ዘመን፣ይፈርሳል ድንኳኑ፣ የምስራች መምጫው፣መቸ ይሆን ቀኑ፣ ብዬ ብጠይቅም መልሱን ግን አላውቅም።
ማንበብ ይወዳሉ?💝
አንደበቴ ላንቺ፣ቃላት መች ያገኛል፣ እግሬስ ወዳንቺ፣መች ይመጣልኛል፣ ጥርሴስ አንቺን ሳስብ፣መች ይስቅልኛል፣ ሚወሰድ ሳይጠፋ እንዴት ራሴውን ፍቅርሽ ይቀማኛል🤔
ፋሲካ ሆነ ❤
ባንድ ጭንቅላት በጠባብ ደረት ስንቱን ስሸከም ስንቱን ስደርት ለመሀላንኳ ምሳሌ ሚሆን ህያው ምልክት አንድም ሳላስቀር በሁሉም ሳጌጥ አጣሁኝ የክት እግሬ በመራው በነዳው ሲሄድ ጢሻ ለጢሻ ልቤም እንደ ዘር የትም ሲበተን ባገኘው እርሻ ለፈጠረኝም ለገደለኝም ስቆም ላምልኮ ስንት ብሆን ነው?.... አንድ ሰው ብቻ አልመስልምኮ!!🤔
#እንዳትመጪ ቅሪ ሰው ማሸብሸብ ትቷል ፖስት እያሳሰበው በካሜራ ሆኗል ታቦት የሚያጅበው፣ . እንዳትመጪ ቅሪ . የምን እልል ማለት መስገድ ተንበርክኮ፣ ልብሱ ከሚቆሽሽ ይቀራል አምልኮ፣ . እንዳትመጪ ቅሪ . ቀልዱ ሁሉ አሽሙር መስሎት ፖለቲካው፣ ዱርዬው ረስቷል ጭዌ በሀርሞኒካው፣ . እንዳትመጪ ቅሪ . ለሴቷ እኩልነት የሀበሻ ሱሪ እየተሸመነ፣ ተበጣጥሷል ቀሚስ ለጥምቀት ያልሆነ፣ . እንዳትመጪ ቅሪ . ጥምቀት እንዳይመስልሽ ያኔ እንደምታውቂው፣ ምእመኑ ሆኗል ካህኑን አጥማቂው፣ . ግን አንዴ ብቅ በይ . አይኔን እና ሎሚውን ከደርትሽ ልጣል፣ አንድም ናፍቀሽኛል አንድም አንቺ ካለሽ ድባቡ ይመጣል። #ደሱ
#የከሰመ ምኞት ከአመሻሽ ስኬት ላይ እንዳልሆን ሊሆኑ ተስፋ ሲያልቅ ተሟጦ ልፋት ከንቱ ሊቀር ውድቀትን ሲያሰማ የ"አልችል" ስሜት በልጦ ፡ እንደ ጊዜው ጥመት እንደየነገሩ ሲሰናዳ ክስመት ፡ ላልታደለ ኑሮ ለፍቶም የእጅ ሊታጣ እውኑን ለመናገር ከስኬት ጎዳና ምኞት የሚል ሀሳብ አያስመኝም ነበር ፡ ግና መለስ ይላል የጣለ ቀን ሲያልፍም ውስጥም ሲበረታ "አልችል" ባይ ማንነት በ"ይቻል" ሲረታ ከአቀረቀሩበት ዳግም ቀና ሲባል ከአመሻሹ ማልዶ ያልፍልኛል በሚል ብርሀን ሲያስፈነጥቅ ከጭልመት ተወልዶ ፡ እንደ ጥንካሬው አንደ ሕይወት ሚዛኑ እንደ ቀልቡ ምላሽ ስኬትን ማመኑ ይሁንለት ፅኑ ተፃፈ✍️ደሱ
እነሆ ድንግል ትፀንሳለች ወንድ ልጅም ትወልዳለች ስሙንም ዐማኑኤል ትለዋለች (ሉቃ ፩፡፳፯-፴)፡፡እንኳን ለብርሃነ ልደቱ በሰላም በጤና አደረሳችሁ!!!
መ'ከዳት ከወይዛዝርቶቹ ውበት ከታደሉት፣ አንድ ፉንጋ ነበረች ቀልቤ ያረፈባት፣ ላወጋት እንደሻትኩ ድፍረት ከኔ ሸሸ፣ ዕልፍ ቀናት ገፉ ሳይነጋ እየመሸ፣ ከእለታት አንድ ቀን እድል ለኔ ሁና፣ ድንገት ስንተያይ እኔም እኔ ሁኜ እሷም እሷ ሁና፣ ያ የናፍቆት ጉልበት ከፊቷ ስገተር ከዳኝ እንደገና። ተፃፈ✍️ደሱ