- Последний пост
- 14 авг.
- Последнее чтение
- 15 авг.
- Постов за неделю
- 13
- Всего постов
- 24
- Тип
- открытый
- Язык
- ti
- Категория
- Новости и СМИ (по похожим)
- В каталоге с
- 13 авг.
- 1/24сутки в ленте
- 358
- 1/48двое суток
- 410
- 1/72трое суток
- 442
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
እጃችንን ዘርግተን ልናየው በማንችለው ጨለማ ውስጥ ነን ። አላህ በከለከለን ጀልባ እየተሳፈርን ደስታችንና ሰላማችንን ጥለናል ። በኛው ስራ ጠንካራው እኛነታችን ፈራርሷል ። ታመናል ..ደስታ ርቆናል ..ልባችን ተሰብሯል ..በድባቴ ውስጥ ሰጥመናል ከዱንያ እስር ቤት ወደጨለማው ክፍል እግራችንን ጎትተን ገብተናል ። ወንጀሎችን ተላምደናል የአላህን ትዕዛዝ ችላ ማለትን ከቁብ አልቆጠርነውም ። ረሱልን ከምን ጊዜውም በላይ አውቀናል ባወቅነው ልክ ከነሱ ርቀናል ይህ አለም ትንፋሻችንን ቀይሮታል ። የሁላችንም አላማ ያሰጋል! ራሳችንን ለሌላ ብዙ ህመም እያጨን ነው በዚሁ ከቀጠልን ነጋችን ሲነድፈን ይኖራል እኛም ለመነደፍ ርቃናችንን አመቻችተን በመጓዝ ላይ ነን ። ሌላ ህመም ..ስቃይ ለመሸመት እየተጣደፍን ነው እንዴት ሁላችንም በዚህ መንገድ መጓዝ መረጥን ? ወየው ለሁላችን ። [ባለዕዳው]
ኹጥባ ላይ ኢማሙ " ከሞት ኋላ ጀነትና ጀሀነም እንጂ ሌላ የለም " አሉ ። ስራችሁን ታዘቡ ራሳችሁን ተሳሰቡ ጀነት የማያስገባ ከመሠላችሁ ጀሀነም እንጂ ሌላ መሄጃ የለም ማለታቸው ነበር ። አንዳንዴ ከሞት ኋላ ጀነት እንጂ የሌለ ይመስለናል ።
اللهم صل وسلم وبارك على سيدنا وحبيبنا محمد
"ስለምን ነው ሁሌ ሀቢብ ብቻ ሚወደሱት ? አላህስ ?" የሚል ጥያቄ ከአንድም ሶስት ሰው ሲያነሳው አይቼ ግራ ገባኝ .... ይህ የብዙ ሰው ጥያቄ ይሆን ? ረመዷን ላይ ነበር ስለዚህ ጉዳይ የሆነ ነገር ልል የነበረው ከዛ ያው እንደምታቁት ረሳሁት ¡ ድጋሚ ስሰማው ነው እስቲ የሆነ ነገር ልበል ብዬ የመጣሁት ። ይህን ጥያቄ ሲያነሱ " ብዙ ማወደስ ወደአምልኮ ይወስዳል ረሱልም ነሳራዎች ያደረጉትን እንዳታደርጉ…
እና ይህ ወር በመጣ ቁጥር ሁሉም ለመጨቃጨቅ ምላሱን በሚስልበት ወቅት ሁሉን ረስታችሁ በረሱል ስም ደም ለግሱ ... ኑ በነሱ ስም ደም ለግሳችሁ ብዙ ህይወቶች አድኑ እየተባላችሁ ነው ። እጃችሁን አዘጋጁ ።
"ስለምን ነው ሁሌ ሀቢብ ብቻ ሚወደሱት ? አላህስ ?" የሚል ጥያቄ ከአንድም ሶስት ሰው ሲያነሳው አይቼ ግራ ገባኝ .... ይህ የብዙ ሰው ጥያቄ ይሆን ? ረመዷን ላይ ነበር ስለዚህ ጉዳይ የሆነ ነገር ልል የነበረው ከዛ ያው እንደምታቁት ረሳሁት ¡ ድጋሚ ስሰማው ነው እስቲ የሆነ ነገር ልበል ብዬ የመጣሁት ። ይህን ጥያቄ ሲያነሱ " ብዙ ማወደስ ወደአምልኮ ይወስዳል ረሱልም ነሳራዎች ያደረጉትን እንዳታደርጉ ብለዋል " የሚል ንግግር ደገፍ አርገው ነበር ። እንዲ እንዲ ብሎ ከማስረዳት በፊት ይህን ጥያቄ እያነሳ ያለውን ትውልድ እስቲ በወፍ በረር እንቃኘው ። የአላህን ውብ ተፈጥሮዎች ሲያይ " ሴት " ትዝ የሚለው ትውልድ .... ጨረቃና ፀሀይ ብሎ መግጠም ከጀመረ መዝጊያ ቃሉ "ከአንቺ አይበልጡም" የሆነበት ትውልድ ... የአንቺን አይን ቢያይ አባጃህል በሰለመ ብሎ ድፍረቱን ሺ ሜትር የሚዘረጋ ትውልድ ረሱል ብዙ ተወደሱ የማለት ድፍረት ኬት ያመጣል ? ረሱል መች ተወለዱ መች ሞቱ ሲባል ፀጉሩን የሚያክ ትውልድ ... ስሞቻቸውን ጥቀስ ሲባል እእእ የሚል ትውልድ ... የረሱል ልጆች ማንናቸው ጥቀስ ቢባል ወደቻትጂቢቲ የሚከንፍ ትውልድ ረሱል ብዙ ተወደሱ የማለት ድፍረት ኬት ያመጣል ? ስለአንድ ተራጋጭ ውሎና አመሻሽ ... ባህሪና ፍላጎት ..እድሜን ከነቀኑ የሚያውቅ ትውልድ ስለረሱል ግን 5% የማያቅ ትውልድ ። ስለ አክተር ፀጉር አቆራረጥና አለባበስ ትኩረት ሰጥቶ ሰዎች ስለረሱል ቅንድብና ጥርስ ሲያወሱ ሲሰሙ "ኧረ ይሄ ነገር በዛ " የማለት ድፍረት ኬት አመጣ ? እንደው አላህ ሱ.ወ የላካቸውን መልዕክተኛ ማወደስ ቤት በኩል ሮጦ ነው አላህን መርሳት የሆነው ? በኛና በአላህ መካከል ድልድይ ሆነው አላህን ያሳወቁንን መልዕክተኛ ማወደስ ቤትኛው ተራራማ መንገድ ቢታሰብ ነው አላህን መርሳት የሆነው ? ያዕቁብ የልጃቸውን ልብስ እያሸተቱ ቢቆዩ ልብሱን ይዘው የሱፍን ረሱ የሚል ሎጂክ ? ኧረ ተውዋ ። ማወደስ ማምለክ ከሆነ አዋጅ የዚ ትውልድ አማልዕክት ሴት ነው !
ኧረ ግን ይብቃን ! በቃ ከየትም እንስማው ከየትም እናንብበው አሁን ይብቃን ። ካልጠቀሙኝ ጥንቅር ይበሉ .... ካልረዱኝ ገደ* ይግቡ .... ሲጨልም ጥላህ እንኳ ጥሎህ ይሄዳል ... ከሁሉም ነገር በፊት ገንዘብህን ያዝ ... እነዚህንና ተመሣሣይ መልዕክቶችን ተቀብለን ህይወትን አሰልቺና ትርጉም አልባ ማድረጉ ይብቃን ። ስሙኝ በነዚህ አባባል ህይወት ላይ ያከበብነው የጨለማ ግንብ ሊፈርስ ይገባዋል ! በዚህ የግፊት መኗኗር ስር ሺዎች እየሞቱ ... ሺዎች ተስፋ እየቆረጡ ነው ። በዚህ የቸልታ ዘመን ውስጥ ሺዎች እየሟሙ ... ሺዎች በብቸኝነት ምት እየሞቱ ነው ። በቃ አሪፍ ልትሆኑ ትችላላችሁ ግን ሰው ናችሁ ! የሰማቹትን ሁሉ የመተወን ግዴታ የለባችሁም ። ኧረ ስለአላህ ብለን መኖርን አናጠልሽ ... ህይወትን አናቁሽ ።
ነገ ኸሚስ ነው .... ከምግብ እንቆጠባለን 🫰
ርግት ... ሰከን በሉ የዚህ አለም ሰዎች ላይዙት በሚሯሯጡት ነገር ተጠልፋችሁ ከንቱ ልፋት አይያዛችሁ ... ፊጥራችሁ በማያስፍልገው ነገር አሰሳ ቦታችሁን አትሳቱ ... ቦታ መሳት ልብንም ሩህንም አያረጋጋም ። ተረጋጉ አለም ወዳዘነበለበት የምትዘነበሉ ሳይሆን መዘንበሉን ሚዛን የምታስጠብቁ ሁኑ ። መንገድ ስተው ደስታንና ሰላምን ፍለጋ ዱካው በሌለበት የባዶነት አለም ውስጥ ከሚውተረተሩት አትሁኑ ። ርግት ...ስክን በሉ ።
የስርዓት ለውጦች ሀይል ላይ ተመርኩዘው በሚመጡበት ሁነት ውስጥ ሆነን በምን መልኩ ነው መመሪያው የአላህ ህግ የሆነ አለም የምንፈጥረው ? ወራሪዋና አሜሪካ ኢራን ላይ የከፈቱት ጦርነት በስርዓት ለውጥ ላይ የተውጠነጠነ ነበር ። ህዝቡንም ሲገፋፉ የነበረው ስርዓቱን ጥለው ራሳቸውን ነፃ እንዲያወጡ በሚል የእሳቤ መንገድም ነበር ግን የኢራን ህዝብ ጠንካራ ነበርና ኢራን ይህን ትልቅ ፈተና አልፋለች ። ግን ይህ ኡማስ ? ዲሞክራሲን ብቸኛ መንገዱ አርጎ የሚያስብ ... ካፒታሊዝምን እንደጣዖት የሚያመልክ እና በዚ ርዕዮተአለም እሳቤው ተቀርፆ የተዋቀረ ኡማስ ? ለአላህ ህግጋት መስፈን የመጀመርያው ችግር የሚሆነው ራሱ ሙስሊሙ ነው የሚሆነው ። ስለዚህ ለተፈጠርንበት አላማ መኖር ካሻን እና በዚች ምድር ላይ የአላህን ምትክነት ከፈለግን የመጀመርያው እርምጃችን አላህ የሚፈልገውን ባርያ መሆን ነው ። የአላህን ስርዓት ተረድተን የሱን ስርዓት ወደፊት ለማምጣት በህይወታችን ቃል መግባት ነው ። ከዚያ ደግሞ በሰው ሰራሽ ርዕዮቶች ተጠልፎ የራቀውን ኡማ ወደኢማን መልሶ ከተተበተበው ሴራ አስመልጦ ለነገሮች ማዘጋጀት ነው ። ለዚህ ነው ኢማናችን ላይ ... ተቅዋችን ላይ መስራት የሚኖርብን ። ለዚህ ነው አንድ መሆን እና ተመሣሣይ ፍላጎት ሊኖረን የሚገባው ... እንበርታ ። ከዛ ይህን ካለፍን እና ዝግጁ ከሆንን በኋላ ስለቀጣይ እርምጃዎቻችን ማሰብ እንችላለን ።
እያንዳንዱ አካል የራሱ ግዛት አለው ... የሙስሊሙ ግዛት ግን አለም ነው ። ግዛትህን ትመራለህ አልያ በትግል መንገድ ትሞታለህ ።
ነገርን ቶሎ እንደመረዳት ሰቀቀን አለ ? ሰዎች ምን ለምን እንዳሉ በቅፅበት እንደመረዳት ... ሰዎች ስለአንድ ነገር ሲናገሩ ለምን እንደተናገሩና ከኛ ምን እንደጠበቁ በቅፅበት ተረድቶ መተወን ? የእያንዳንዱ ሀረካቸው ሰበብን እያወቁ ግን ሲያስመስሉ እንዳመነ ማስመሰልስ ? የሆነ የሚከብድ ነገር አለዋ😶🌫
መኖር ሲሸፈን አለም የሲቃ ድምፅ ያደነቁራታል ...የሰውን ልጅ ነፍስ በዝንባሌያቸው ቀጣጥለው የህይወት አንገት ላይ ጠምጥመው የሚንቀሳቀሱ ሲበዙ ምድር በተንቀሳቃሽ ሙታኖች ትሞላለች ። ምድር የሰውን ስሪት በከፊል ገልጠው በተረዱ ጭራቆች ሳቢያ ስትወካከብ አመታቶች እያለፉ ነው ። እየኖራቹ ነው ? ይሰማችኋል ግን ? ልባቹ አልሞተም አይደል ? እዝነት የሰው ልጅ ከጌታው የተቸረው ስጦታ ነው ...እዝነቱን ሲያጣ ክብሩን ያጣል ። ማሠብ የሰው ልጅ ማንነቱ ነው በሌሎች እሳቤ ተፅዕኖ ስር ወድቆ ሲቀር ማንነቱን ያጣል ። ስጦታችሁም ማንነታችሁም አለ ? መኖራችሁ ይሰማችኋል ግን ?
ከአንደኛው አለም ጦርነት በፊት ለዘመናት በተዋቀረ ስርዓት የአለምን ብዙ ክፍል የሚመራ ሀይል ነበር ... ያ ሀይል የመወለዱ ሰበብ ከሱ በፊት የነበረ ሀይል መዳከምና መሰነጣጠቅ ነበር ። ኦቶማን በሰላጂቃዎች ስር ነበር ተፈልፍሎ የወጣው ... ኦቶማኖች የሩቅ ሀሳባቸውን ይዘው ብቅ ሲሉ ለዛ የረጅም ጉዞ ዝግጁ ያልነበሩ ብዙ ግለሰቦች በተለመደው ህይወት ገብተው በክነዋል ... ብዙ የስልጣን ጥመኞች ለማክሰም…
ከአንደኛው አለም ጦርነት በፊት ለዘመናት በተዋቀረ ስርዓት የአለምን ብዙ ክፍል የሚመራ ሀይል ነበር ... ያ ሀይል የመወለዱ ሰበብ ከሱ በፊት የነበረ ሀይል መዳከምና መሰነጣጠቅ ነበር ። ኦቶማን በሰላጂቃዎች ስር ነበር ተፈልፍሎ የወጣው ... ኦቶማኖች የሩቅ ሀሳባቸውን ይዘው ብቅ ሲሉ ለዛ የረጅም ጉዞ ዝግጁ ያልነበሩ ብዙ ግለሰቦች በተለመደው ህይወት ገብተው በክነዋል ... ብዙ የስልጣን ጥመኞች ለማክሰም ታግለው ጠፍተዋል ። ያ በትንሽ ጎሳና በትልቅ ህልም የተነሳው ሀይል ለ 600 አመታት የአለም ሀያሉ ሀይል ሆኖ ስሙን በደማቁ አስፍሮ አልፏል ። ያ ሀይል በስኬቱ ላይ በሚሊየን የሚቆጠሩ እጆች አሻራቸውን አሳርፈዋል .... ለመንገዱ የኖሩና የሞቱ እልፍ ነፍሶች አልፈዋል ። የዘመኑ ፍሰት ስቧቸው ከትላልቅ ሀሳብ ርቀው ሆዳቸውን ያመለኩ ሽፍቶች ከነ ውርደታቸው ከታሪክ ገፅ ተፍቀዋል ። አሁን አለም ለየሆነ ነገር እየተዘጋጀች ያለ ይመስላል ... ሊመጣ ስለሚችለው ነገር ልተነብይ አልችልም ግና የተለመደ ያልሆነ ሽታ አለምን እያጠነ ያለ ይመስላል ። እየተፈረካከሰ ባለው ስርዓት ውስጥ ምን ፈልቅቆ ሊወጣ እንደሚችል ጥርት ያለ ምስል አላጋራችሁ ይሆናል ግን ራሳችሁን ማዘጋጀት እንዳለባችሁ እነግራችኋለው ። ከዘመናት በኋላ ተፈጥሮ ባለፈው ትልቅ ክስተት ላይ ለሆዱ የኖረና በታሪክ ገፅ የጠለሸ ሽፍታ ( ዱንያን በእውር ድንብር የሚያሳድድ) ሆናችሁ አትለፉ እላለሁኝ ። ኢማናችን ላይ ... እውቀታችን ላይ ለመስራት ቆርጠን እንነሳ ። በቃ ላሁኑ ይህን ብቻ እናድርግ ሌላው በጊዜ ንፋስ ታዝሎ ይመጣል ።
ዋሽንቱ በምግብ ሲሞላ ድፍን ነው ዜማም አይወጣው የፆም እሳት ነው ነዲዱ አቃጥሎ ውስጥን የሚያፀዳው ...... ሩሚ እንዳለው 🤍 ነገ ሰኞ ነው እንፆማለን ።
የት ውስጥ ለምን እንዳለ ለማወቅ የማይጥር ሰው የት እንዳለ ሳይገነዘብ ሀያቱ ይባክናል ..... ያለበት ቦታ ልክ ይሁን አይሁን ሳያረጋግጥ የተመቻቸ እና መመቻቸቱን ምክንያታዊ ለማስመሰል የሚጥር ደንቁሮ ይቀራል ። እያስተዋልን አህባብ🤍
ለሰዓት ረጅም ሰልፍ ላይ ተገትሬ ስልችት ብሎኝ መኪና መጣ ... አንድ ግብድዬ ሰውዬ አደብ ጥሶ ሊገባ ሲል ከፊት ያለው ገፍትሮ ያስወጣዋል.... ሰውዬው እንዴት ነካኝ ኡኡ ብሎ መሳሪያ አውጥቶ ይጮኻል .. ገፍታሪው ሸሸ ግን የሱ ሚስት መሳሪያውን ረስታ ካልገደልኩት ብላ ቅውጥ 😭 ሰው እንደመፍራት ብሎ ያገላግላል እሷ ሰውየውን ትገፈታትራለች ....እና ምን ልላቹ ነው አግቡ እናንተ ብትፈሩ እሷ ትጣላላችኋለች😂 አጅቦኝ ነው ብቻ🙌
"ድንግል ነው የምፈልገው " አለኝ ስለትዳር እያወራን በመሀል " ሁሉም ወንድ የሚፈልገው ነገር አይደል ?" ትዳር ላይ አቋሙ ሽሽት ስለሚበዛው እየገረመኝ ጠየኩት " ድንግል ስልህ የልብ ነው .... ልቧ ከዚያ የትግል ሜዳ ልምድ የሌለው ለነገሮች ንፃሬ የሚበቃ እውቀት የሌለው ... እንዲ ስትባል ያ እኮ ብላ ለማነፃፀር ልቧ ሰው ያልጎበኘው ። " የሆነ ተረት መፅሀፍ እያነበበ ይመስል ድምፁም አወራሩም ይስባል " ልቧ ውስጥ የምታገለው የኋላ ታሪክ የሌላት ... ትላንት ላይ እስከሞቷ አብራው ልትሆን ትመኝ የነበረ ሰው የሌላት ያን ሰው ከማግኘት አግዶ ያፈሳት ሰው መሆን አልሻም.... አዎ በዛኛው አለም ለድርሻዋ ታግላ የደከመች ሞክራ ያጣች ፈልጋ የባከነች ሴት እፈራለው" በዚህ ሰዓት እንዲ አይነት ሴት እንደማትኖር ራሱም ይጠፋዋል ብዬ አላስብም ... ብቻ መመለስ ስላለብኝ ብቻ " እኔም " አልኩት ።
ሰው ማለት ሌላ ነገር አይደለም ልክ እንደናንተው የሆነ ሌላ እናንተን ነው ! የሆነ ነገር ስታስቡ ለሀሳባችሁ መሳካት ውር ውር የሚል ሮቦት አይደለም ። በዚህ እሳቤ እየኖርን ነው የተቸገርነው ።