Hilina Belete
СтатистикаDeacon Hilina Belete is a servant of the Ethiopian Orthodox Tewahido Church.
- Последний пост
- 6 авг.
- Последнее чтение
- 07:34
- Постов за неделю
- 0
- Всего постов
- 20
- Тип
- открытый
- Язык
- английский
- Категория
- Книги (по похожим)
- В каталоге с
- 13 авг.
- 1/24сутки в ленте
- 1 809
- 1/48двое суток
- 2 073
- 1/72трое суток
- 2 235
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
ምን ባደርግ እክስ ይሆን? ኆኅተ ብርሃንን እንዴት ብወዳት ብድር እመልስ ይሆን? ቤተ ክርስቲያናችንን እንዴት ባገለግላት ያሸከማችሁኝን ዕዳ አቀል ይሆን? እግዚኦ... ምንድን ነው ያደረጋችሁት? ግርግርን ስሸሽ እንደ ኖርሁ የሚያውቀኝ ሁሉ ይመሰክራል፤ ከዚህ ቀደም ሚዜ ያደረጋችሁኝ ኹሉ ሚዜነቱ ሰማዕትነት እንደ ሆነብኝ ታውቁታላችሁ። ሚዜ ሆኜአችሁ እንኳን ከሁነቱ ጋር ባለ መጣጣሜ "በማያውቀው ሰው ሰርግ የተገኘ ይመስላል" እያላችሁኝም አልነበር!? ... እኔና አጋሬ ዕቅዳችን ባሕር ዳርን አልፎ በሚገኝ አንድ የደቡብ ጎንደር ክፍል ውስጥ፣ ዘወትር በሕይወታችን ወስጥ ያሉ አባታችን በሚኖሩበት ቦታ ሥርዓተ ተክሊላችንን ፈጽመን ወደ ሱባኤ መግባት ነበር። በተለያየ ምክንያት አልሆነም። እዚያ ካልሆነ በኆኅተ ብርሃን መፈጸሙ ግድ ነበር። እናም ሰርግ ሳይኖር፣ ጥሪ ሳይኖር፣ ሚዜ ሳይኖር፣ አጀብ ሳይኖር፣... ሥርዓታችንን ፈጽመን እንመለሳለን ብለን ከቀናት በፊት ወሰንን። ከሳምንት በፊት ሙሽሪት አመለጣትና (ሆን ብላ ብዬ አዲሱን ትዳር ከምበጠብጥ ብዬ መሆኑ ይመዝገብልኝ😂) ...ብቻ "አመለጣትና" ለኆኅተ ብርሃን ወንድሞቼ ቀኑን ነገረቻቸው። ከዚያ በኋላ መጠነኛ መረጃ እንጂ የዛሬው ዝግጅት መኖሩን አልገመትሁም ነበር። የእኔ አሳብ ሰውን ሳናስቸግር የሌሊት ሥርዓቱን ፈጽመን፣ ቁርሳችንን ፍትፍት በልተን መለያየትና ለወዳጅ ዘመድ ማሳወቅ ነበር። ሚዜ ሆነው ከጎኔ የቆሙትን ወንድሞች እንኳን ሚዜነታቸውን ያወቅሁት ትናንት ማታ ለተክሊሉ ሥርዐት ስንዘጋጅ ነበር። ለካስ ከሙሽሪት ጋር ተናበው በሳምንት ውስጥ ራሳቸውን ሚዜዎቼ አድርገው አዘጋጅተው ኖሯል። የኔን ፍቃድ መጠየቅም አላሻቸው። ዲኮሩን፣ ኬተሪንጉን፣ የኬክ መርሐ ግብሩን፣ ሻምፓኙን ሁሉ ሲያዘጋጁ እኔ አላውቅም። መጠነኛ ቁርስ እንጂ ሰርግ ማድረጋቸውን በምን ጠርጥሬ? ደግሞም በሁሉም ነገር ላይ አያገባህም አሉኝ። "ዛሬ አንተ ያንተ አይደለህም፤ የሚስትህና የወዳጆችህ ነህ። ስለዚህ እንደ ታዘዝከው ሁን" አሉኝ። ሌላ ምርጫ አልነበረኝም። በሌሎች ሰርጎች ላይ የምተቻቸውን ነገሮች ሁሉ ላለመፈጸም የግል ፈቃዴን በፍቅር ፈቃዳቸው ገርተውታል። ካለ ምንም ሰርግና ግርግር አገባለሁ ያልኩት እኔ ድል ባለ ድግስ ተሞሸርሁ። ማንንም ያልጠራሁት እኔ ድንገት ሰምተው መምጣት በቻሉት ሰዎች ተከበብሁ። ባለ ደረቅ ዓይኑ እኔ ገና ዲኮሩን ሳይ ነበር የኆኅተ ብርሃን ወንድሞቼና እኅቶቼ ፍቅርና ልፋት አሳዝኖኝ የዕንባ ቋቴን ለመጭመቅ የታገለኝ። እንደ ምንም ታግዬ ዕንባዬን እየዋጥሁ ዝግጅቱ ተገፋ። ሙሽሪቴ እርሷም ከዕንባዋ እየታገለች እኔን አይዞህ በማለት ደከመች። ድል ካለው የኬተሪንግ ድግስ የተጨለፈውን ምግብ መብላት መረረኝ፣ ሳግ ተናነቀኝ። ጉሮሮዬ ምግቡን ባይውጥም ዕንባዬን ግን ዋጥ አደረግሁት። ... በረፈደ ምሽት ይህችን ስጽፍ ቀን የታገለኝ ዕንባዬ በእንቅልፌ ፈንታ ዐይኔን ወርሶት ነው። እግዚኦ... ኧረ ምንድን ነው ያደረጋችሁት? ኆኅተ ብርሃን በፍቅር አሳድጋኝ ነበር። አሁን ግን በፍቅር አፈነችኝ። እፍን አድርጋ አሸገችኝ። ለካስ ፍቅርም ያፍናል!? ይህን ጉድ በእናንተ አየሁ። መተንፈስ እስኪያቅተኝ ፍቅራችሁ ተጫነኝ። ይሄ ሁሉ አክብሮትና ድካም ለምን? እሺ እንዴትስ ተቋቁሜው ላገልግል? እንዲህ አልፈስፍሳችሁኝ እንዴት ልበርታ? ግን እንኳንም ሆነ። እንኳንም እኔ እንደምፈልገው ፀጥ ብሎ አላለፈ። እንኳንም እናንተ እንደምትሹት ግርግር ኖረው። እንኳንም ከምጠላው የትኩረት ማዕከልነት ጋር አጋፈጣችሁኝ። እንኳንም የሽብሸባ እንቅስቃሴዬን አረማችሁ። እንኳንም እናንተና ባለቤቴ ደስ አላችሁ። እንኳንም የሚመርቁኝ እናቶቼ ተደሰቱ። ድል የነሳኝ፣ ከደረቁ ዓይኔ ዕንባን ያበዛው፣ ያልፈሰፈሰኝ ድግሱና ዲኮሩ እንዳይመስላችሁ፤ የልፋታችሁ ጥግ እንጂ። ለእኔና ለአጋሬ የተጓዛችሁብት ጥግ እንጂ። ... ውድ ወዳጆቼ! ዛሬ የሆነውን ገና እያሰላሰልሁት ነው። ባለፉት 42 ሰዓታት ለ2:30 ሰዓት ያህል ብቻ ብተኛም ቅሉ እንቅልፌ አልመጣም። ከነገርኋችሁ ውጪ የሆነውን ለመረዳት እየሞከርሁ ነው። ያልጠራኋችሁ ቤተሰቦቼና ወዳጆቼ፣ አለመጠራታችሁ በመዘንጋት ሳይሆን ጥሪ ስላልነበር መሆኑን ተረዱልኝ። ሰርጉም (የካሜራ ዝግጅቱን ጨምሮ) የሰንበት ትምህርት ቤት እኅቶቼና ወንድሞቼ ሳይነግሩኝ የደገሱት መሆኑን እወቁልኝ! ደግሞም ሳንውል ሳናድር ሱባኤው ይገባልና/ገብቷልና በጸሎት አስቡን! የኃይለ ማርያምና የወለተ ማርያምን ትዳር ይባርክልን ዘንድ ጸልዩልን! መልካም ሱባኤ!
без подписи
без подписи
без подписи
без подписи
ታቦትን በተመለከተ ከቤተ ያሬድ ሚዲያ ጋር ይህን ቆይታ አድርገናል። ተጋበዙልኝ! https://youtu.be/OBIgPGnEgCs
ባለ ቅኔው እንዲህ አለ:- ጉይ አብ መንገለ ራማ ወኢታጎንዲ ህዳጠ፣ እስመ ከማሁ ለወልድ ፀጋ መንፈስ ቅዱስ ተሴጠ። ስተረጉመው:- ልክ ወልድ እንደ ተሸጠው - ተቸረቸረ ተሸጠ - የመንፈስ ቅዱስ ጸጋም። አብ ሆይ! ወደ ራማ ሽሽ - ጥቂትም ቢሆን አትዘግይ - ይሸጡሃል አንተንም። መቼስ ቅኔ ድንበር የለበት፤ የማይገልጸው የለ! ብሎ ብሎ ሽሽ አለው። Sometimes retreat is better than surrender ይላሉ መሰል ነጮቹም።
ፍቁረ እግዚእ - (ከድንግል ጋር) ከሁሉ ይልቅ ከጌታ ጋር በፍቅር እስከ መጨረሻ የጸና እርሱ ነው። - ከሁሉ ይልቅ ከእመቤታችን ጋር በፍቅር እስከ መጨረሻ የጸና እርሱ ነው። - ከሁሉ መጻሕፍት ይልቅ ክቡር የሆነው የእርሱ ወንጌል ነው። - ብርሃን፣ ፍቅር፣ እውነት፣ ሕይወት እና ሃይማኖት ከየትኛውም ወንጌል ይልቅ በእርሱ ወንጌል ተደጋግመው ተጠቅሰዋል። - ከሐዋርያት ሁሉ በዕድሜ ትንሹ እንደ ነበር ይታመናል። በብስለቱ ግን "አባ አረጋዊ" ነው። - በሰማዕትነት ከከበሩት ከወንድሞቹ ከሐዋርያት ይልቅ የምድር ሕይወቱ ፍጻሜ የተለየ ነው። - የነጎድጓድ ልጅ ሆኖ እያተኮሰ መጥቶ ፍቁረ እግዚእ እስኪሆን ቀዝቅዞ የፍቅር ሐዋርያ ተብሏል። - የአገልግሎቱም የጽሑፎቹም ዋነኛ ጭብጥ ፍቅር ነው። - በዕድሜ ሸምግሎ መራመድ እንኳን ተስኖት ሳለ የራሱ ደቀ መዛሙርት ተሸክመውት ይሰብክ ዘንድ ሕዝብ ወደ ተሰበሰበበት ይወስዱት ነበር። የመጨረሻ ዘመን ስብከቱ ግን ዘወትር አንድ ዓይነት ነበር - ፍቅር። "ልጆች ሆይ! እርስ በርሳችሁ ተዋደዱ!" - 'ለምን ሁሌ ይህን ትሰብካለህ?' ሲሉትም መልሱ ዘወትር ተመሳሳይ ነበር:- "ምክንያቱም የጌታ ትእዛዝ ነውና፤ ይህ ብቻውን ቢደረግ እንኳን በቂ ነው" ይል ነበር። ፍቁረ እግዚእ! በረከቱ ይደርብን! ዲያቆን ሕሊና በለጠ
የበአታ ሰንበት ተማሪዎች የዕለቱን (የመስከረም 25ን) መዝሙር "ትብሎ መርዓት"ን እንዴት እንዳዜሙት መጨረሻ ላይ ያለውን ማስፈንጠሪያ ተከትላችሁ ስሙልኝማ! ያሬዳዊስ ማለት እንዲህ ነው!!! ትብሎ መርዓት ለመርዓዊሃ ወልድ እኁየ ነዓ ኀቤየ ወሪደ ኢታጎንዲ ዬ መስቀል ጸገየ ዘጋዲ ምስለ ጴጥሮስ አዋዲ ወጳውሎስ ሰዳዲ /ዬ/ ማርያም መስቀሎ ለበዓል ኀበ ትወዲ /ዬ/ መስቀል ጸገየ ዘጋዲ /ዬ/ መስቀል ጸገየ ዘጋዲ። ... ሙሽሪት ቤተ ክርስቲያን ክርስቶስን ሙሽራዋን ውዴ ሆይ ከሰባኪው ከጴጥሮስ ከአሳዳጁ ጳውሎስ ጋር ማርያም መስቀሉን ከኪሩቤል ጋር አመሳስላ /አንድ አድርጋ/ በምታከብርበት /ቀራንዮ/ ወደ እኔ ና አትዘግይ ትለዋለች። የጋዲ እንጨት መስቀል እሰይ አበበ። (መስከረም 25 - የዘመነ መስቀል የመጨረሻዋ ቀን ስትሆን ጴጥሮስ ወጳውሎስ ይታሰቡባታል) https://youtu.be/Xk9xLF-8rP8?si=8yQ8ICaA2sSTEYBt
የዛሬ ስደስት ዓመት ስለ ኢሬቻ የተጻፈ! https://www.facebook.com/share/p/1AzFC3Jceg/
የጌታ ደም መፍሰስ ትርጉሙ ድኀነት ነው፡፡ ስለዚህ ደሙ በማንኛውም ጊዜ፣ ቦታና ቁስ ላይ የሚፈስ አልነበረም፡፡ ደሙ የሚፈስበት ጊዜ፣ ቦታና የሚፈስበት ቁስ ልዩና በመለኮታዊ ጥበብ የተመረጡ ናቸው፡፡ ብቻ ደሙ ዝም ብሎ የሚፈስ አልነበረም፤ አይደለምም፡፡ በተወለደ በ8ኛው ቀን ይገዘር ዘንድ ግዝረት ወደሚፈጸምበት ቤት ወሰዱት፤ ደሙ የሚፈስበት ጊዜም ሆነ ቦታ ገና ነበርና ቁሱም የስለት መሣሪያ አልነበረምና ያሃ ሳያርፍበት እንዲሁ በመንፈስ ቅዱስ ተገዝሮ ተገኘ፡፡ አይሁድ በተደጋጋሚ ሊወግሩት ቢነሡ፡ ለኃጢአት ይቅርታ ደሙ ይፈስበት ዘንድ የተመረጠው ነገር ድንጋይ አልነበረምና ይሠወርባቸው ነበር፡፡ የደሙ ምሳሌ፣ ኋላም በምሥጢረ ቁርባን ደሙ ይሆን ዘንድ የተመረጠው ወይን ነው፡፡ እመቤታቸን ውኃውን ወደ ወይን ይለውጥ ዘንድ ስትማጸነው "ጊዜዬ አልደረሰም" ያላት በመስቀሉ ላይ ደሙ የሚፈስበት ጊዜ ገና እንደ ሆነ ሲገልጽ ነው፡፡ ደሙ በጋን ውስጥ ሳይሆን በመስቀል ላይ፣ በቃና ዘገሊላ ሳይሆን በቀራንዮ የሚፈስ ስለ ነበር ነው፡፡ ነገር ግን ለእርሱ ለአማናዊው ሙሽራ፡ ሰርጉ ለሚባል ለስቅለቱ የቃናው ሰርግ፣ ከእመቤታችን ከነሣው ሥጋው በመስቀሉ ላይ ለሚፈስ ደሙም፡ በእመቤታችን ምልጃ ከውኃነት የተለወጠው ወይኑ ምሳሌ ነው፡፡ እንግዲህ ደሙ የትም ቦታ ላይ በምንም ዓይነት መንገድ ከመፍሰስ ተጠብቆ ቆይቶ የፈሰሰው በመስቀሉ ላይ ነው፡፡ ታዲያ ደሙ አዳነኝ ብሎ የሚያምን ሰው ደሙ የፈሰሰበትን መስቀሉን እንዴት ሊቃወም ይቻለዋል? ጌታ 33 ዓመት ከ3 ወር በምድር ላይ ሲኖር ደሙን ምንም ነገር ላይ ሳያፈስ ቆይቶ በመስቀሉ ላይ ማፍሰሱንና ድኅነትን በዚያ መፈጸሙን እያዩ መስቀሉን ችላ ማለትስ ለክርስቲያን እንዴት ይቻለው ይሆን? ለማንኛውም ይህችን ስለ መስቀሉ በቤተ ያሬድ የተደረገችን ውይይት ጋበዝኳችሁ! https://youtu.be/a-GLaWc4m70?si=aUYNuIVIqQZicrab
ኹላችንም የተወለድንበት የየራሳችን የልደት ቀን አለን። የአዲስ ዓመት ዕለት ግን የጋራ የልደት ቀናችን ይመስላል። አዲስ ዓመት ብሔራዊ የልደት ቀን ነው። በአዲስ ዓመት ያሳለፍነውን መከራም ሆነ ስኬት ለአሮጌው ዘመን ትተንለት÷ በመከራው መቆዘሙን በስኬቱም መፈንጠዙን ገትተን÷ እንደ አዲስ እንደ ተወለደ ሰው በተስፋ መነሣት ይገባል። አዲሱን ዓመት በግልም ሆነ በጋራ ልክ እንደ ቅዱስ ጳውሎስ "በኋላችን ያለውን እየረሳን በፊታችን ያለውን ለመያዝ የምንዘረጋበት" (ፊል.3÷13) የስኬትና የጽድቅ ዘመን ያድርግልን። መልካም አዲስ ዓመት! ደ/ን ሕሊና በለጠ ዘኆኅተብርሃን!
без подписи
ዝም ብዬ አይሻለሁ (ዲ/ን ሕሊና በለጠ) ያ'ይን ማረፊያዬ! ዝም ብዬ አይሻለሁ። ፊደል ነሽ ለቃሉ - ሰብእናሽ ትርጓሜ - ሃይማኖትሽ ፍቅር የተዋሕዶ ቅኔ - ትሕትናሽ ዜማ ነው - ውበትሽም ምሥጢር ቅኔ ዜማ ምሥጢር - እምነትና ምግባር - ፊደል ከትርጓሜ እንዲዋሐዱልኝ - ዝም ብዬ አይሻለሁ - ደግሜ ደግሜ። ድንግል የንታዬ ያይን ማረፍያዬ ከድምጻዊው በላይ - ትሕትናሽ ዜማ ነው - ጆሮን ይማርካል ከዘራፊው በላይ - ውበትሽ ቅኔ ነው - ወርቁ ይራቀቃል ከገጽሽ ላይ ምሥጢር - ከመልክሽ ትርጓሜ - ዝም ብሎ ይፈልቃል። ድንግል የኔታዬ ዝም ባለ ዜማ ባረመመ ምሥጢር ልብን ልብ ያስገዛል መቀመጥ ሥዕልሽ ሥር። ዝም ብዬ አይሻለሁ የአባ ጊዮርጊስ ፍቅር - የቅዱስ ያሬድ ግብር - የኤፍሬም ውዳሴ የሕርያቆስን ልብ - ብትስይብኝ ብዬ - ከልቤ ከነፍሴ ዝም ብዬ አይሻለሁ የሥዕልሽ ግርማ - አፌን ቃል ያሳጣል ልነግርሽ ያሰብኩት - ሥዕልሽ ሥር ስሆን - ብትንትኑ ይወጣል። ያልተሰማ ብሶት - ያላጽናኑት ኀዘን - ያረገዘው ልቤ ባልሰከነ መሻት - ባልረጋ ማንነት - የተናጠው ቀልቤ ካንቺ ጋራ ሲሆን - ምንም ሳይናገር - እንዲሁ ይጽናናል ከሺህ አጽናኝ በላይ - ከሥርሽ መቀመጥ - ልቡናን ያቀናል። ስለዚህ እናቴ - ምንም ባለም ብናጥ - ከሥርሽ ሆናለሁ ዐይኔ እንባ አቅርሮ - አንድ ቃል ሳይወጣኝ - ዝም ብዬ አይሻለሁ። ያ ጠቢቡ ሐኪም - እንዴት ቢቀልምሽ - እንዴት ቢሥልሽ ነው? ወንጌላዊው ሉቃስ - ምን ቀለም ቢጠቀም - ምን ብሩሽ ቢያገኝ ነው? ሥዕልሽ ለሰው ሁሉ - ምሥጢርን 'ሚያፈልቀው - ዕንባንም 'ሚያብሰው? እንዴት ቢሥልሽ ነው? በሰው አካል ላይ ነው - የሐኪም ሥራማ ነፍስ እንዳላት አካል - የሁሉ ወዳጅ አ'ርጎ - እንዴት ሣለሽ እማ? ብሩሽ ቀለም ነክሮ - ሸራ ላይ አይደለም - ሉቃስማ የሣለሽ ባይኔ ብሌን መሃል - ባቀረረ ዕንባ ውስጥ - ተቀልመሽ አለሽ። ዓይኔ ነሽ ብርሃኔ - ጨለማዬን ገልጠሽ - ጌታን ያየውብሽ መደነቃቀፌ - መታወር መውደቄ - መርገም የጠፋብሽ። ያይን ማርፍያዬ! ዝም ብዬ አይሻለሁ። ሥጋዌ ሲነሣ ቀድሜ አይሻለሁ ተዋሕዶ ሲረቅ ቀድሜ አይሻለሁ ድኅነትም ሲነገር ቀድሜ አይሻለሁ ምሥጢረ ጥምቀት ላይ ቀድሜ አይሻለሁ በቁርባኑ ላይም ቀድሜ አይሻለሁ በሃይማኖት መቆም መዳን የተቻለው ባንቺ ምክንያትነት አንቺ ስላለሽ ነው። ያልተሰማ ብሶት - ያላጽናኑት ኀዘን - ያረገዘው ልቤ ባልሰከነ መሻት - ባልረጋ ማንነት - የተናጠው ቀልቤ ካንቺ ጋራ ሲሆን - ምንም ሳይናገር - እንዲሁ ይጽናናል ከሺህ አጽናኝ በላይ - ከሥርሽ መቀመጥ - ልቡናን ያቀናል። ስለዚህ እናቴ - ምንም ባለም ብናጥ - ከሥርሽ ሆናለሁ ዐይኔ እንባ አቅርሮ - አንድ ቃል ሳይወጣኝ - ዝም ብዬ አይሻለሁ። ሐምሌ ማርያም፣ 2013 ዓ.ም.
без подписи
ዐረገች ከሰማዮች ይልቅ ውብ ሰማይ ነበረች፣ የጨለማውን ሊቅ ድቅድቅ የሰበረች፣ እውነተኛ ፀሐይ ከርሷ ቢፈነጥቅ ብርሃን ያበሰረች። እርሷ ያወጣችው አማናዊ ፀሐይ፣ እንዳገዘፈችው ኑሮ በምድር ላይ፣ ሞቶ ተነሣና ከፍ ብሎ ቢያርግ ቢሔድ ወደ ሰማይ፣ እርሷም ሞተችና ፀሐዩአን ልትፈልግ ተነሣች ወደ ላይ፣ ዐረገች ወደ ላይ ብርሃን ልጇን ልታይ። ©ዘሕሊና
እዚህ ላይ አንድ የጽሑፍ ዑደት በመጠኑ ግቡን ሳይመታ አይቀርም። (ፎቶውን ይመልከቱ!)። - ኦርቶዶክሳዊነት ምንድን ነው የሚሉ ሁሉ ይህን መጽሐፍ ቢያዩ መልካም ነው። የቅዱስ ኤፍሬምን ሕይወትና ግጥማዊ ሥራዎችን መሠረት በማድረግ ኦርቶዶክሳዊ አስተምህሮ በጥልቀት ተቃኝቶበታል። - ይህ መጽሐፍ የኦርቶዶክሳዊ መንፈሳዊነትን ዶግማዊና ነገረ ሰብአዊ መሠረትን ይዳስሳል። በጉዳዩ ላይ ከእኛ ጋር ተመሳሳይ አስተምህሮ ያላቸውን የምሥራቅ ኦርቶዶክሳውያንን ምልከታ በጥልቀት ያሳያል። - ይህ መጽሐፍ የአከራካሪውን ሊቅ የአውግስጢኖስ ሕይወትና አስተምህሮን መሠረት በማድረግ የምዕራቡን ዓለም ክርስትና: በተለይም የካቶሊካውያንን የእምነት መነሻዎችን ያሳያል፤ ኦርቶዶክሳዊ አተያዮችንና ምላሾችንም በየትምህርቶቹ ያቀርባል። አውግስጢኖስ መጽሐፍ እንደ ገና መታተሙንና ገበያ ላይ መዋሉን ቅዳሜ ዕለት ባኮስ መጻሕፍት መደብር ካበሰረን በኋላ አሁን ሦስቱም በገበያ ላይ ይገኛሉ። መልካም ንባብ!!! ዲ/ን ሕሊና በለጠ ዘኆኅተ ብርሃን
Assumption - Dormition - ፍልሠታ (ዲ/ን ሕሊና በለጠ) #Assumption የሚለው ቃል ወደ ላይ መነጠቅ፣ መወሰድ፣ መፍለስ ወይም ማረግ እንደ ማለት ሲሆን ይህን ቃል አጉልተው የሚጠቀሙት ካቶሊካውያን እመቤታችን በምድር ሕይወቷ ፍጻሜ ላይ ወደ ገነት እንደ ተወሰደች በግርድፉ ያስረዳሉ። (በግርድፉ ያልኩት በምክንያት ነው)። ዋናው ትኩረታቸው የእመቤታችን ወደ ሰማይ ማረጓና መክበሯ ላይ ነው። ሞቷ ላይ ግልጽ ሆኖ የሚነገር ነገር የለም። በዓሉንም "Assumption of the Blessed Virgin Mary" በማለት August 15 ያከብሩታል እንጂ ሞቷን አጉልተው አይናገሩም። በዓሉ ግን ደማቅ ነው። ካቶሊካውያን በበዙባቸው ሀገራትም ብሔራዊ በዓል ነው። አሁን ለሥራ ተልእኮ በምገኝባትና አብዛኛው ሕዝቧ የሮማ ካቶሊክ እምነት ተከታይ በሆኑባት በካሜሩን ውስጥ ዓርብ August 15 ብሔራዊ በዓል ነበር - Assumption of Mary. ምዕራባውያኑ ይህን በዓል ከምሥራቁ ዓለም በመቀበል ማክበር የጀመሩት በ7ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ቢሆንም፣ በእመቤታችን ዕረፍት ላይ ግን ግልጽ አስተምህሮ የላቸውም። ከፊሉ መሞቷን ሲያምኑ ሌሎቹ ግን "አልሞተችም እንዲሁ ነው ያረገችው" ይላሉ። ፖፕ ፒየስም በኖቬምበር 1፣ 1950 (እ.ኤ.አ.) አስተምህሮውን Munificentissimus Deus በተባለው ዶግማውን ባብራሩበት ሥራ ላይ ሲያብራሩት "The immaculate mother of God, the ever virgin Mary, having completed the course of her earthly life, was assumed body and soul into heavenly glory" ብለው ነው። ይህም ነፍስና ሥጋዋ ወደ ሰማይ የተወሰደው ሞታ ይሆን ወይስ ሳትሞት አልገለጸም። ስለዚህ ዛሬም ይከራከሩበታል። #Dormition የምሥራቁ የክርስትና ዓለም የበዓሉ መጠሪያ ደግሞ መነሻው የግሪኩ ቃል koímēsis ሲሆን ትርጉሙም "ማንቀላፋት" ነው። ሞት በቅዱሳት መጻሕፍት እንደ እንቅልፍ መገለጡ እጅግ የተለመደ በመሆኑ ይህ ቃል የእመቤታችንን ይህን በዓል ለመጥራት የተመቸ እንደ ሆነላቸው መገመት አያስቸግርም። በምሥራቁ ዓለም (እኔ ባየኋቸው ጽሑፎች ሁሉ) እመቤታችን ሞትን መሞቷ፣ ነፍሷንም ክርስቶስ በክብር መቀበሉን (ይህንን በሥዕላቸውም ላይ ነፍሷን በሕፃን ልጅ አምሳል ሲቀበል ያሳያሉ) ፣ በተቀበረች በሦስተኛው ቀን ሥጋዋ መፍለሱን እናም መነሣቷንና መክበሯን ይናገራሉ። ይህንንም በተመሳሳይ ቀን August 15 ላይ ሲያከብሩት "Dormition of the Theotokos" ይሉታል። ስለዚህ የምሥራቁ ቀደምት ትውፊት ሞቷን ትኩረት ሰጥቶ ይናገራል። #ፍልሠታ የሚለው የእኛ ቃል ከሥርወ ቃሉ ትርጉም ባሻገር ስፉሕና አካታች ነው። ሞቷ፣ መቃብሯ፣ ፍልሠቷ፣ ትንሣኤዋና ዕርገቷ ሁሉ ካለ ምንም አሻሚነት በግልፅ ይታሰቡበታል። "ሞት በጥር ነሐሴ መቃብር" ተብሎ ከሞቷ እስከ ዕርገቷ ይዘከራል። በጥር ሞተች፣ ሥጋዋ ከዮሐንስ ጋር ተነጥቆ በዕፀ ሕይወት ሥር ተቀመጠ፣ ሐዋርያት በሱባኤ ተሰጣቸው፤ ቀበሩት፤ ተነሣች፤ ዐረገች። ስታርግም ቶማስ ብቻ አያት፤ ሐዋርያት በዓመቱ ሱባኤ ገቡ፤ ትንሣኤዋን ዕርገቷን አዩ፤ ተሳተፉ። ምእመናን በየዓመቱ ሱባኤውን ይዘክራሉ፤ እንደ ሐዋርያቱ ሱታፌን ያገኛሉ። ይህ ፍልሠታ ተብሎ በአንድ ቃል ይነገራል። ለማንኛውም ፍልሠታ በእኛ ሀገር ብቻ ያለ ለሚመስላቸው ሙሉውንም ይሁን ከፊሉን ታሪክ ይዞ አብዛኛው ክርስቲያን ዓለም አብሮን በተመሳሳይ የዝክርና የሱባኤ ሱታፌ ላይ እንዳለ ለማሳየት የተጻፈች ናት። (ከሥር የሚታየው የመጀመሪያው ሥዕል ከምሥራቃውያን መካከል የራሺያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ሥዕል ሲሆን እመቤታችን ነፍሷ ከሥጋዋ ተለይቶ፣ ሐዋርያት ሥጋዋን ከበው፣ ክርስቶስ ደግሞ ነፍሷን በሕፃን አምሳል ተቀብሎ ይታያል። ሁለተኛው ሥዕል ደግሞ የካቶሊካውያን ሲሆን ነፍስ ወሥጋዋ ወደ ሰማይ መወሰዱን እንጂ ሞቷን አያሳይም። የእኛ ደግሞ ታሪኩን የሚያስረዱ ብዙ ሥዕላት ስላሉን እናንተ በአስተያየት መስጫው እንድታጋሩ ልጋብዝ!) ሱባኤያችንን ያስፈጽመን! ©ዘሕሊና
без подписи
без подписи