tgindex
ፈለገ አበው

ፈለገ አበው

Статистика

@TG,gebre tsadik

Последний пост
7 авг.
Последнее чтение
13 авг.
Постов за неделю
0
Всего постов
20
Тип
открытый
Язык
und
В каталоге с
13 авг.
Подписчики
547
+1 за 2 дн.
Сутки
0
0,00%
Неделя
 
Месяц
 
Просмотров на пост
231
20 постов
Вовлечённость
42,2%
к подписчикам
Постов в день
0,0
всего 20
Упоминаний
0
каналов
Охват размещения
оценка
1/24сутки в ленте
128
1/48двое суток
146
1/72трое суток
158

Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.

Посты

  • እንኳን ለጾመ ማርያም(ፍልሰታ-ለማርያም) በሰላም አደረሳችሁ 🙏 ጾሙን የሰላም የደስታ የፍስሃ እንዲሁም የሥጋን ፍላጎት ለነፍስ የምናስገዛበት ያድርግልን🙏 ከዚህ ጽሑፍ በኋላ ለትንሳዔዋ እንድንገናኝ አምላከ ቅዱሳን ይርዳን🙏 መልካም ሱባዔ @DnYW21

  • አንተን ተስፋ የሚያደርጉ አያፍሩም፤ በከንቱ የሚገበዙ ያፍራሉ። መዝሙረ ዳዊት 25:3

  • ሰላም ፡ ለኅድረትከ ፡ ውስተ ፡ ከርሠ ፡ ድንግል ፡ ቅድ ስት ። እምኵሎን ' ዓለማት፡ እንተ ፡ ይእቲ ' ንጽሕት ። ዐማኑኤል፡ ኄር፡ ገባሬ ፡ ኵሉ፡ፍጥረት ። እፎኑ ፡ ኅድረ ትከ ፡ ውስተ'ሥጋ፡ ወለት፡ ንእስት። እንዘ ፡ አንተ ፡ አምላኪየ ፡ ነዳዲ ፡እሳት።

  • የልመናዬን ቃል ሰምቶኛልና እግዚአብሔር ይመስገን። እግዚአብሔር ኃይሌና ጋሻዬ ነው፤ ልቤ በእርሱ ታመነ እኔም ተረዳሁ፤ ሥጋዬም ደስ ይለዋል፥ ፈቅጄም አመሰግነዋለሁ። መዝሙረ ዳዊት 28:6-7

  • https://youtu.be/VEP0MDVyyDo?si=WBvOsFmhonNyAQe8

  • https://youtu.be/VEP0MDVyyDo?si=WBvOsFmhonNyAQe8

  • የዘመን አቆጣጠራችን ይቀየር ተባለ‼️ በምክክሩ ላይ የኢትዮጵያን የዘመን አቆጣጠር በተመለከተ የተለያዩ አማራጮች ቀርበዋል። በኢትዮጵያ የዘመን አቆጣጠር ውስጥ የሂጅራ ወይም የእስላማዊ የዘመን አቆጣጠር ይካተት፣ «ዓመተ ምህረት» የሚለው ይቅርና አሁን ያለው የፈረንጆቹ አቆጣጠር ይቀጥል፣ እንዲሁም ከእስልምናም ሆነ ከክርስትና ሃይማኖቶች ነፃ የሆነ የዘመን አቆጣጠር እንከተል የሚሉ ምክረ ሃሳቦች መቀረባቸው ታውቋል። በተነሱት አጀንዳዎች ላይ እስካሁን ውሳኔ ደረጃ ላይ አልተደረሰም፣የውሳኔ ሂደቱ ገና መሆኑን ገልፀዋል። @Addis_News

  • ዓለምን በስድስት ቀን ሰርቶ የጨረሰ አምላክ የእኛን ህይወት ለማስተካከል ብዙ ቀን አይፈጅበትም!     እግዚአብሔር ቀን አለው አይዘገይም❤️‍🩹

  • 🌷ማርያም ድንግል🌷 •✨እኅቶሙ ለመላእክት፣ •✨ወለቶሙ ለነቢያት፣ •✨ሞገሶሙ ለሐዋርያት፣ •✨እሞሙ ለሰማዕት፣ •✨ተስፋ መነኮሳት፣ •✨ደብተራ ፍጽምት •✨አክሊል ንጹሕ ለካህናት፣ •✨ወላዲተ አምላክ ንጽሕት፣ °✨መጽደቂቶሙ ለኀጥአን፣ °✨ናዛዚቶሙ ለኅዙናን፣ °✨ፈዋሲቶሙ ለሕሙማን! 🌿ፍቅር ያጌብረኒ ከመ እንግር ዜናሆሙ ለቅዱሳን! (የቅዱሳንን ታሪክ እንድመሰክር ፍቅር ያስገድደኛል) አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ (መጽሐፈ ምሥጢር)

  • #ዓለም በእመቤታችን ድኅነት ተፈጽሞለታል# ➽ በዓለም ላይ ያሉ ፀረ ክርስቶስ ፀረ ሃይማኖቶች ሁሉ ቀድመው በጠላትነት የሚነሱ በእመቤታችን ላይ ነው ። 👉ዝሙተኞቹ የሚጠሉ እመቤታችንን ነው ። እርሷ ቅድመ ወሊድ ጊዜ ወሊድ ድኅረ ወሊድ ንጽህት ናትና። 👉ሐሰተኞቹ መጀመሪያ የሚጠሉ እመቤታችንን ነው። እርሷ ከእለተ ልደቷ እስከ እለተ እረፍቷ ከአንደበቷ ሐሰት አልተገኘባትምና ። ➽  ያለእመቤታችን የተፈጸመ ድኅነት የለም ። ክርስቶስ በእለተ ዓርብ የቆረሰው እኛ የዳንበት ሥጋ ያፈሰሰው ደም ከእመቤታችን የነሳው ሥጋ ነው። በዓርባ በሰማኒያ ቀን የምንጠመቅበት ከእግዚአብሔር የምንወለድበት ማየ ገቦ ከእርሷ በነሳው ሥጋ ከእርሱ ጎኖ የፈሰሰ ማየ ገቦ ነው ። ➽ለአዳም የካሰባቸው ሕዋሳቱ ማለት? አዳም በእግሮቹ ሂዶ በለስን ቆርጧል ለዚህ ካሳ ይሆን ዘንድ ክርስቶስ እግሮቹን ተቸንክሯል ተቸንክሮ አዳምን የካሰባቸው እግሮች ከእመቤታችን የነሳቸው ናቸው። ➽ አዳም በዓይኖቹ አይቶ ዕፀ በለስን ተመኝቶ በልቶ በድሏል ክርስቶስም በዓይኖቹ ግርማ አይሁድን ገፀ ሠራዊተ ሮማውያንን አይቶ ለአዳም ክሶለታል ይህንን ያደሰገባቸው ዓይኖቹም ከእመቤታችን የነሳቸው ናቸው። ➽አዳም በዓይኑ አይቶ በልቡናው ተመኝቶ በእግሩ ሄዶ በእጁ ቆርጧል ክርስቶስም ለዚህ ካሳ ይሆን ዘንድ እጆቹን በሰንሰለት ታስሯል በቅንዋት ተቸንክሯል እሊህም እጆች ከእመቤታችን የነሳቸው እጆች ናቸው ። ➽አዳም ዕፀ በለስን ቆርጦ ተመግቧል ክርስቶስም አዳም በለሱ እየጣፈጠው ለተመገበበት አፍ ካሳ ይሆነው ዘንድ ሆምጣጤና መራራ ሐሞት የተቀላቀለበት ብሂዕ ጠጥቷል ይህም አፍ ከእመቤታችን የነሳው ነው። ➽ሔዋን ምክረ ከይሲን በጆሮዋ ሰምታ ዕፀ በለስን ተመግባ ሞትን እዳን በደልን መርገመ ሥጋን መርገመ ነፍስን አምጥታብናለች ክርስቶስም የአይሁድን ስድብ ሰምቶ {አንተ ዕሩቅ ብእሲ እንጅ አምላክ አደለህም መጀመሪያ ራስህን አድን የዮሴፍ ልጅ ....} በትዕግሥት ሕይወትን አድሎናል መርገመ ሥጋ መርገመ ነፍስን አስወግዶልናል እኛንም ከስድብ ታድጎናል ይህንን ሁሉ የተቀበለበት ጆሮ ከእመቤታችን የነሳው ነው። ➽ዲያብሎስ ሥጋትን በመቃብር ነፍሳትን በሲኦል ተቆራኝቼ እኖራለሁ ብሎ አዳማውያንን በመላ የላሜ ልጅ የአውራዬ ውላጅ ብሎ ሲገዛ ይኖር ነበር በሥጋው ወደመቃብር ወርዶ ትንሳኤ ሥጋን አበሠረ በነፍስ ወደሲኦል ወርዶ ድኅነተ ነፍሳትን አበሠረ ነፍሳትን ነጻ አወጣ ይህንን ያደረጋባቸው ነፍስንም ሥጋንም የነሳ ከእመቤታችን ነው ።  ➽በእመቤታችን ብቻ የተከናወኑ ግብራት            ንጽሐ፥ሥጋ፥ንጽሐ፥ነፍስ፥ንጽሐ፥ልቡና ከዊነእም፦ ዘምስለ አመት {እናትነት ከአገልጋይነት} ጽበተ ከርሥ፦ ዘምስለ ርሒብ {ጠባብነት ከሰፊነት} ፅንስ እንበለ፦ ሩካቤ {ያለዘር መጽነስ}             ሐሊብ፦ ምስለ ድንግልና { ድንግል ሆኖ ወተት ማስገኘት} ➽ይህንንም አበው እንዲህ ይገልጡታል። ኅቡዓትየ ዘምስሌኪ ኢከሰትኩ ለሰብእ ቅ.ያሬ ከአንቺ ጋራ ብቻ ያደረግሁትን ምሥጢር ለሰው አልገለጥሁትም ። ብፅዕት አንቲ ኦ ማርያም እስመ ለብፅዓንኪ ዘአልቦ ትርጓሜ ። ማርያም!! ብፅዕት ነሽ ለብፅዕትነትሽም ትርጓሜ የለውም      አረ መን ድር ➽መኑ ይእቲ ዛቲ { እንደ ጎኅ ሰማዩን ሰንጥቃ የምታበራ ያቺ ማን ናት}  መኃ 6÷10 መሥዋዕተ ወቁርባነ ኢፈቀድኩ ሥጋከ አንጽሕ ሊተ { መሥዋዕቱንም ቁርባኑንም አልወደድኩም ማደሪያዬ ሥጋህ ማርያምን አንጻልኝ }መዝ 39÷6 ➽ወሶበ አኮ ኢያትረፈ ለነ እግዚአብሔር ዘርዐ {እግዚአብሔር አንዲት ዘርን ባያስቀርልን እንደሰዶም በሆን ገሞራንም በመሰልን ነበር} ኢሳ 1÷9 አልብኪነውር ወኢምንትኒ {ምንም ምን ነውር ነቀፋ የለብሽም} መኃ 4÷8 ➽ወይብልዋ ቅድስተ ቅዱሳን {ከተለዩ የተለየች ከነጹ የነጻች ናት ይሏታል} ዕብ 9÷4 ወትቀዉም ንግሥት በየማንከ በአልባሰ ወርቅ {ንግሥቲቱ የወርቅ ካባ ደርባ ደራርባ በቀኝህ ትቀመጣለች}     መዝ 44÷9 ➽መልክም ያደረጉ ብዙ ሴቶች አሉ አንቺ ግን ከነዚያ ሁሉ ትበልጫለሽ ምሳ 41÷28 ቀደሰ ማኅሮ ልዑል {ልዑል ማደሪያውን መረጠ}         መዝ 46÷5 መጽሐፍ ጽሕፍት በሰብዐቱ ማኅተም {በሰባት መቆለፊያ የተቀለፈች መጽሐፍ} ራእ 5÷1 ➽ወርኢኩ ባህረ እንተ ትመስል ከመ ማህው ወድምርት {ብርጭቆ የምትመስል ባህር አየሁ} ራእ 15÷2 ብእሲት እንተ ትለብስ ፀሐየ {ፀሐይን የተጎናጸፈች ሴትን አየሁ} ራእ 12÷1 ተፈስሒ ፍስሕት ኦ ምልእተ ጸጋ {ፀጋን የተመላሽ ሆይ ደስ ይበልሽ}ሉቃ 1÷29 #እመቤቴ ሆይ ለልጅሽ ከአንቺ የሚቀርብ የለውምና በቸርነቱ ይቅር እንዲለኝ አማልጅኝ# ከሌላ ቻናል የተገኘ

  • በፍጹም ልቤ ፈለግሁህ፥ ከትእዛዝህ አታርቀኝ። መዝሙረ ዳዊት 119:10 መልካም ዕለተ ሰንበት

  • "በምስጋና የተከፈተ ዘመን አስደሳች ነው፤ በፀሎት የተከፈተ ቀን መልካም ነው፤ በእምነት የሆነ ኑሮ ረፍት ነው፤ በይቅርታ የሆነ ጓደኝነት ዘላቂ ነው፤" አቡነ ሺኖዳ ሳልሳዊ

  • አጋዕዝተ ዓለም ቅድስት ሥላሴ

  • видео или голосовое, без подписи

  • መልክዐ ጴጥሮስ ወጳውሎስ ሰላም ለዘባናቲክሙ በምኲራባት እለ ተቀሥፋ: ወለእንግድዓክሙ ዘሰፍሐ መልዕልተ ጠበብት ወፈላስፋ: በእንተ ኢየሱስ ክርስቶስ ዘተጸፍአ ቅድመ ቀያፋ: ሀበኒ ጴጥሮስ መስቀለከ ይኲነኒ ተስፋ: ወጳውሎስ ዉቅየተከ እንተ ደም ለከፋ። ትርጓሜ በቀያፋ ፊት በጥፊ ስለተመታ ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ በየአደባባዩ ለተገረፉ ጀርባዎቻችሁ፤ በአዋቂዎች እና በፈላስፎች ላይ ለመመስከር ለተዘረጋ (ለሰፋ) ደረታችሁም ሰላምታ ይገባል። ጴጥሮስ ሆይ የተሰቀልክበት መስቀል፣ ጳውሎስም የአንገትህ መቆረጥ የነካት መጎናጸፍያህ ተስፋ ይሆነኝ ዘንድ ስጡኝ። እንኳን አደረሳችሁ🙏

  • "የምድር ኃጥአን ሁላችሁ ወደ ቅድስት ድንግል ኑ፡ በእርሷ ስጦታ ጻድቃን ትሆኑ ዘንድ፤ ልብሳችሁም ያደፈ ሁላችሁ ወደዚህች ቅድስት ምንጭ ኑ፡ የይቅርታ ዉሃ ወደ ምታፈስ፤ ልብሳችሁንም በልጇ ደም እጠቡ፡ ለሰማያዊ ሙሽርነት ዝግጁ ትሆኑ ዘንድ፡፡ ድውያነ ሥጋ  ሁላችሁ ወደ ድንግል ኑ፡ በጸሎቷ ኃይል እንድትፈወሱ፡፡ የእውቀት ድሆች ሁላችሁ ኑ፡ የእውቀት ምንጭን ከእሷ ትቀዱ ዘንድ፡ ያማረ የተወደደውን የጥበብ ምክር ታገኙ ዘንድ” (አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ - አርጋኖን)

  • እንኳን ለመጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ በዓለ ልደት በሰላም አደረሳቹ እረድኤት በረከቱ አይለየን መልካም በዓል🙏

  • ጸሎቴን ያልከለከለኝ ምሕረቱንም ከእኔ ያላራቀ እግዚአብሔር ይመስገን። መዝ 65፥20 ይሄ በእግዚአብሔር ካልሆነ በሰው እንዴት ሊሆን ይችላል? ራሴን ጠየኩ። ነገር ግን ጌታ በወንጌሉ "እውነት እውነት እላችኋለሁ በእኔ የሚያምን እኔ የማደርገውን ሥራ እርሱ ደግሞ ያደርጋል ከዚህም የሚበልጥ ያደርጋል" ዮሐ 14፥12 ይላል። በዚህ በእኛ ዘመን እንዲህ ያሉ አባቶችን ማየትኮ ቀጥታ ወደ ቀደመች ቤተ ክርስቲያን ነው የሚወስደን። አንድ ታሪክ ላውሳችሁ(በጣም በአጭሩ) ✍ ✍ ✍ በቤተ ክርስትያን ታሪክ የመጀመርያውን ሆስፒታል ያስገነቡት አባት ቅዱስ ባሲልዮስ ዘቂሳርያ (St. Basil the Great) ይባላሉ። የመጀመሪያው ግዙፍ ክርስቲያናዊ ሆስፒታል በ369 ዓ.ም በቂሳሪያ (በአሁኗ ቱርክ) ተገነባ። በዚህ በእኛ ዘመን ደሞ በኢትዮጵያ አምላክ ፍቃዱ ሁኑ ተጀምሩኣል። ይህ የሕክምና ማዕከል «ባሲሊያስ» (Basilias) በመባል ይታወቅ የነበረ ሲሆን፥ የሚከተሉትን አገልግሎቶች ይሰጥ ነበር፦ለሕሙማን ነፃ የሕክምና እንክብካቤ ማድረግ።ለድሆች፣ ለነጋዲያንና ለባዕዳን መጠለያ መስጠት። ለሐኪሞችና ለነርሶች የመኖሪያ ቦታ ማቅረብ።በተጨማሪም በምዕራብ ሮም ስርወ-መንግሥት (አውሮፓ) የመጀመሪያውን የቤተክርስቲያን ሆስፒታል በ400 ዓ.ም አካባቢ ሮም ውስጥ የቆረቆረችው ቅድስት ፋቢዮላ (St. Fabiola) ትባላለች። እንግዲ ምን እንላለን እግዚአብሔር ይመስገን ከማለት ውጭ🙏 ያለእኔ ምንም ልታደርጉ አትችሉምና በእኔ የሚኖር እኔም በርሱ እርሱ ብዙ ፍሬ ያፈራል። ዮሐ 15፥6

  • ሰው የሳቅኩበትን ቀን ያውቃል፤ አንተ ግን ያለቀስኩበትን ምሽት ታውቃለህ። ሰው የደረስኩበትን ያያል፤ አንተ ግን ያለፍኩበትን መሰናክል ታውቃለህ። ጌታ ሆይ ዙሪያዬ በጨለማ ሲከበብ ብርሃን የሆንከኝ፣ በምሕረትህ የምታኖረኝ፣ በቸርነትህ የጠበቅኸኝ አሁንም ወደፊትም አትተወኝ። ​ ​People know the days I laughed, but You know the nights I cried. People see where I have reached, but You know the obstacles I have overcome. Lord, You who were my light when darkness surrounded me, who sustains me by Your mercy, and protected me by Your kindness—do not forsake me now or in the future.

  • እርሱ አምላክ ነው፤ ሥራውም ፍጹም ነው፤ መንገዱም ሁሉ የቀና ነው፤ የታመነ አምላክ፥ ክፋትም የሌለበት፥ እርሱ እውነተኛና ቅን ነው። ኦሪት ዘዳግም 32:4

ፈለገ አበው — tgindex