نَـحْـنُ أَبْـنَاءُ السَّلفِــيِّينْے
Статистикаفليس العلم بكثرة الرواية ولا بكثرة المقال. ولكنه نور يقذف فى القلب يفهم به العبد الحق ويميز به بينه وبين الباطل. /هـ አስታያየቶዎንና ምክሮዎን⇩ @Nehnu_abnau_aselefiyin_bot በዚህ ያድርሱን👆
- Последний пост
- 14 авг.
- Последнее чтение
- 15 авг.
- Постов за неделю
- 7
- Всего постов
- 22
- Тип
- открытый
- Язык
- арабский
- Категория
- Новости и СМИ (по похожим)
- В каталоге с
- 13 авг.
- 1/24сутки в ленте
- 1 264
- 1/48двое суток
- 1 448
- 1/72трое суток
- 1 562
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
ነጠላ ሰረዝ ታውቃለህ አይደል? ፅሁፍ ላይ አስፈላጊ ነው። ቃላትን ትለይበታለህ፣ ዝርዝር ሃሳብህን ትጠቅስበታለህ። ነገር ግን በድምፅ አታነበውም፣ ትፅፈዋለህጂ። እናልህ፤ ህይወትህ ላይ አንዳንድ ሰዎች አሉ፤ ክፉ ደጉን ትለይባቸዋለህ። ትምህርትህ ናቸው። ግን “ምን አሉ?” ብለህ አትጮህም። “በምን አሙኝ?” ብለህ ዋይታህን አታሰማም። ይፃፋሉ፤ ግን አይነበቡም !! t.me/abdu_rheman_aman t.me/abdu_rheman_aman
ሰዎች ሆይ ! 📀 ሸይኽ ሙሐመድ መህሩስ t.me/abdu_rheman_aman t.me/abdu_rheman_aman
በህይወትህ መንገድ ላይ ያለ ምንም ዝግጅት የምታቅፋቸው ስጦታዎች እንዳሉ ሁሉ፣ ጥርስህን ነክሰህ የምታልፋቸው የፈተና ዳገቶች ያጋጥሙኃል። አንዳንዴ ተስፋህ ጨልሞ ሂወትህ በእንባ የራሰ ይመስልኃል፤ ሌላ ጊዜ ደግሞ የደስታህ ብርኃን የጨለማውን በር ጥሶ ሲበራ ታየዋለህ… የሚሳኩ ህልሞችህ ይገርሙህና፣ ሳትይዛቸው የሚበኑ ተስፋዎችህ ያስደነግጡኃል። ግን ሁሌም ቢሆን በገዛ እጅህ ልትጽፈው የደከምክለት ሳይሆን፣ በአላህ ብዕር የተፃፈው ታሪክህ ይበልጥ ያምራል። ሁሌም ቢሆን የአላህን ውሳኔ ወደህ ተቀበል !! t.me/abdu_rheman_aman t.me/abdu_rheman_aman
ከፊሉ ልጅ የለኝም ብሎ ያለቅሳል። ሌላውን ልጁ ያስለቅሰዋል። ከፊሉ እህት ወንድም የለኝም ብሎ ይከፋዋል። ሌላው በእህት በወንድሞቹ ውስጡ ቆስሏል። ዱንያ አጃዒቧ አያልቅም። ግማሹ በመከራ፣ ሌላው በጥጋብ ያለቅሳል። "እናቱ የሞተችበትና፣ ገበያ የሄደችበት እኩል ያለቅሳል" በሚለው አገርኛ ብሂል ውስጥ ህመም አለ። መከራ ሁሉ አንድ አይደለም። ከባሰም በላይ ብዙ የባሰ እንዳለ በማስተዋል "አልሐምዱ ሊላህ" እንበል። = የቴሌግራም ቻናል፦ https://t.me/IbnuMunewor https://t.me/IbnuMunewor
በሲህር ምክንያት ሰዎች ቀብር ገብተዋል፤ ጤናቸውን ተነፍገዋል፤ ሰላማቸውን አጥተዋል፤ ፍቅር እና ደስታ እርቋቸዋል፤ የገንዘብ ህይወታቸው ተዘበራርቋል፤ ትዳራቸው ተበትኗል... ይህ ሁሉ እየሆነ ሳለ፣ አንድ ተጎጂ በሰው ዐይን ወይም በሲህር ምክንያት ችግር ገጠመኝ ሲል፣ "ቆንጆ ነኝ፣ ሀብታም ነኝ፣ ታዋቂ ነኝ" እያለ እንደሆነ አድርገን የምንተረጉመው ለምንድነው ?፤ አንዳንዶች ደግሞ የሰውየውን የእምነት እና የአስተሳሰብ ጥንካሬ ጥያቄ ውስጥ የሚከቱም አሉ። ነገር ግን ነብያችን ﷺ "የሰው ዐይን ሀቅ ነው" በማለት አስተምረውናል፤ የህይወት ተሞክሯችንም የሚያረጋግጠው ይህንኑ ነው። ካላወቅን መጠየቅ ደግ ነው፤ ችግሩን በሚያውቅ እና ገፈቱን እየቀመሰ ባለ አካል ላይ ለመሳለቅ መሞከር ግን አላዋቂነት ነው። በቁም በፈላ ዘይት ውስጥ እንዲነከሩ ከምመኛቸው ሰዎች መካከል ሳሂሮች እና አስደጋሚዎች ግንባር ቀደሞቹ ናቸው። አላህ ያዋርዳቸው !! t.me/abdu_rheman_aman t.me/abdu_rheman_aman
አንዳንድ ወንድሞች ለአጅነብይ ሴት ያላቹህን መልካምነት እና ትህትና .. ለኒካህ ሚስታቹህ ብታደርጉት አንድም ትዳር ባልፈረሰ ነበር !! t.me/abdu_rheman_aman t.me/abdu_rheman_aman
ጌታዬ! አንተን እንዳውቅ በማድረግ ለዋልክልኝ ውለታ በቂ የምስጋና ቃላት የለኝም። በፈጠርካቸው ፍጡራን እና መሬት ላይ በዘራኸው አፈር ልክ ምስጋና ይገባህ። ምስጋና የተባለ፣ መጀመርያውም መጨረሻውም ሁሉ ለአንተ ይሁን! ረቢ! ከዚህ በላይ ልወቅህ፤ ከዚህ በላይ ልውደድህ፤ ከዚህ በላይ ልጠንቀቅልህ፤ ከዚህ በላይ ልፍራህ። t.me/abdu_rheman_aman t.me/abdu_rheman_aman
በዚህ እድሜ ይሄን ማድረግ አለብህ፣ በዚህ እድሜ ደግሞ እዚህ መድረስ አለብህ የሚባል ቋሚ የህይወት ህግ የለም። እነ እከሌ በሆነ የእድሜያቸው ወሰን ላይ የሆነ ነገር ስላሳኩ ወይም ስላደረጉ፣ አንተም ማድረግ አለብህ ማለት አይደለም። ሁላችንም አንድ አይነት የህይወት መስመር የለንም፤ በተመሳሳይ እድሜ ላይም ብስለትና ክህሎት አይኖረንም። ዕጣ ፈንታችንም አንድ መልክ የለውም። ቁም ነገሩ ተጨባጭህ በፈቀደልህ የእድሜህ ወሰን ላይ ማድረግ ያለብህን ማድረግህ እንጂ ቁጥሩ አይደለም። لكل أوان قطاف، ولكل شيء إوان t.me/abdu_rheman_aman t.me/abdu_rheman_aman
ማፅናናት የአባት ነው !!
ግብፃዊው ፀኃፊ አህመድ ኻሊድ ተውፊቅ እንዲህ ይላል ፦ " እንደነዛ ሲናደዱ ምግብ እንደማይበሉት ጅሎች አይደለሁም ...በዙሪያዬ እየተከሰተ ባለው ጉዳይ የምበላው ምግብ ምን ያገባዋል ? " ይላል እና ዝም ብላቹህ ጨጓራችሁን አትላጡ ፤ እየበላቹህ ለማለት ነው !! t.me/abdu_rheman_aman t.me/abdu_rheman_aman
አበባም ይሁን ድንጋይ ፣ በግድ እስካሸከሙን ድረስ ያው ሸክም ነው። - ከመፀኃፍ ዓለም። t.me/abdu_rheman_aman t.me/abdu_rheman_aman
እኔም ተስፋን እወዳለሁ። እንደ ረሱል(ሰለዋቱ ረቢ ዓለይሂ)። ሁሉም ሰበቦች አልቀው እንኳን ቢሆን አሁንም ተስፋ ማድረግ። ምን መሰለህ? ነገ የሚባለው ቀን የራሱን ብርሃን ይዞ ነው የሚወለደው። አይደል? ሰማይ እንቅብ - ምድር የምታንቀረቅብ ጠባብ ሰፌድ በሚሆንብን ሰዓት እንኳን ተስፋ ማድረግ። ኢስላምም ይህን ነው የሚያስተምረው። t.me/abdu_rheman_aman t.me/abdu_rheman_aman
በውጭ ያለው ቅዝቃዜ በውስጣችን የሚነደውን እሳት ሊያጠፋው አይችልም። አንዳንዴ በጭንቅላታችን ውስጥ የሚንቀለቀለው ኃሳብ ... ሙሉ ዓለምን የሚያቃጥል ያህል ይሰማናል። ምን ተሰማቹህ ?
አንዳንዴ … መፃፍ የማይጨርሳቸው ዕውነቶች፣ ማንበብ የማይተረጉማቸው ታሪኮች፣ መስማት የማይለውጣቸው ንግግሮች አሉ። እንዲሁም ብቻ ለማወቅ የምናውቃቸው … እንደሚነጋ እንጂ፤ ለምን እና እንዴት እንደሚነጋ ማን ያውቃል ? t.me/abdu_rheman_aman t.me/abdu_rheman_aman
ቢረዝምም መንገዴ ግልፅ ይሆን ዘንድ፣ ቢዘገይም ምርጫዬ ሰላም ይኖረው ዘንድ እመኛለሁ። ህይወት መዕና ሲኖረው ደስ ይላል። በማያበስሉ የጊዜ ልምምዶች ውስጥ ቆይቶ አመድ አፋሽ መሆን እንዴት ያስጠላል?! … ትርጉም የሚኖረው ህይወት ግን ምንድን ነው? … አንድም ለአላህ የተሰጠ፣ ሁለትም ለቤተሰብና ለወዳጅ የተኖረ አይደል? … በእነዚህ ውስጥ ነው ሩህ የሚጠግበው። ከዚያ በኋላ ሩህ አካልን ቢለይም ግድ የለኝም። ለዚህ ሳንበቃ ወደ ቀብር አታስጠጋን፤ አላሁመ አሚን! t.me/abdu_rheman_aman t.me/abdu_rheman_aman
የህይወት እንቅፋቶችን አትጥላቸው። እነርሱ ላንተ ብለው የተፈጠሩ ናቸው። የህይወትን ጥፍጥና የምትገነዘበው በነርሱ ውስጥ ነው። እንቅፋቶች ባይኖሩ የህይወትን ምንነት መረዳት ይከብድህ ነበር። አስተውል! ጨለማ ሳይኖር የብርሃንን ጥቅም መረዳት ይርቅሃል። t.me/abdu_rheman_aman t.me/abdu_rheman_aman
ደግነትህ ወሰን ካጣ ጥቅምህ እንጂ ማንነትህ አይታይም፤ ልብህን ሳይሆን እጅህን ለሚወዱ ሰዎች ወሰን ይኑርህ !! t.me/abdu_rheman_aman t.me/abdu_rheman_aman
“መቼም ቢሆን ምሉዕ ነገር አታገኝም። ጎዶሎ የሆኑ ነገሮችን ታገኝና ወደህ በመቀበል ይሟላሉ።” لو كنت كاملا لما كنت بشرا، والنقص فيك هو جمالك t.me/abdu_rheman_aman t.me/abdu_rheman_aman
አፊያ ያጣ ሰው ዱዓው ሁሉ አፊያ ብቻ መሆኑን ስታይ ምን ያህል አላህ እንደታገሰን እና ኒዕማውን እንደለገሰን ይገባሀል!። አል-ሐምዱ ሊላህ t.me/abdu_rheman_aman t.me/abdu_rheman_aman
ከራሱ አልፎ መላ ቤተሰቡን በመኃላ እየረገመ የዑለማኦችን ስም በማጠልሸት የሚፈለግ ርካሽ ትኩረት፣ መጨረሻው የራስን አኺራ ማበላሸት እና በገዛ ድፍረት መዋረድ ብቻ ነው። የነቢያትን ወራሾች ክብር ማነወር በዒልም ስም የሚደረግ የሐዳዲዮች የጥፋት መርዝ ነው። ስንቱን ካፊር እና ሙብተዲዕ አለ በረቢ!